በ2015 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ብሔራዊ ክፍል ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት፡፡

  Рет қаралды 207

Amhara Education Bureau

Amhara Education Bureau

7 ай бұрын

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2015 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሸለመ፡፡
በ2015 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ዛሬ በባህርዳር ከተማ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የሀይማኖት አባቶች፣የተማሪ ወላጆችና ተሸላሚ ተማሪዎች በተገኙበት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በሽልማት መርሃግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ርዕሰመስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶክተር) ተሸላሚ ተማሪዎች ክልላችን የገጠመውን የፀጥታ ችግር ተቋቁመው ያስመዘገቡት ውጤት በመሆኑ ክብር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
ሀገር የምትመስለው ዜጎቿን ነው፤ ዜጎችም የሚመስሉት የትምህርት ሥርዓቱን ነው" ሲሉም ኃላፊዋ ተናግረዋል። ብቁ፣ ንቁ እና ብርቱ ትውልድ ለመፍጠር ጥራት ያለው እና አካታች የትምህርት ሥርዓት መተግበር እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። ይህንን ለማድረግም እየተሠራ ስለመኾኑ ጠቁመዋል።
በ2015 የትምህርት ዘመን በክልሉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 44 ወንድ እና 11 ሴት በድምሩ 54 ተማሪዎች 600 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። በማኅበራዊ ሳይንስ ደግሞ አምስት ወንድ እና አንድ ሴት በድምሩ ስድስት ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። በተመሳሳይ ሶስት የልዩ ፍላጎት ተማረዎች ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በክልል ደረጃ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 646 በተፈጥሮ ሳይንስ ከደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲኾን፣ በማኅበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ደግሞ 533 ከክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተመዝግቧል።
ተሸላሚ ተማሪዎች የአይነትና የገንዘብ ሽልማት ከክልሉ መንግስትና ከአጋር ድርጅቶች ተበርክቶላቸዋል፡፡
ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት፣ ክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ትምህርት ቤት ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡

Пікірлер: 1
@user-wn8hu2zv2t
@user-wn8hu2zv2t 6 ай бұрын
very nice program
路飞太过分了,自己游泳。#海贼王#路飞
00:28
路飞与唐舞桐
Рет қаралды 13 МЛН
Задержи дыхание дольше всех!
00:42
Аришнев
Рет қаралды 3,2 МЛН
路飞太过分了,自己游泳。#海贼王#路飞
00:28
路飞与唐舞桐
Рет қаралды 13 МЛН