Рет қаралды 15,482
👉እኛስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ ፤ እግዚአብሔርን እናውቅ ዘንድም ልብ እንደሰጠን አናውቃለን።
👉ጊዮርጊስ በመንኮራኩር ሲፈጭ ባይሆን እኔ ቆሞ ማስቀደስ ያቅተኛል እንዴ ?
ፋሲለደስ በገመድ ተለጎመ ሲባል ባይሆን እኔ ማለዳ ሂጄ ኪዳን ማስደረስ ያቅተኛል እንዴ ?
መርቆሬዎስ በእሳት ተጠበሰ ሲባል ባይሆን እኔ ብርድ ችየ ፆም መቻል ያቅተኛል እንዴ ? መስገድ ያቅተኛል እንዴ ?
👉አንድ ክርስቲያን በሰይፍ ተቆራርጦ ቢሞት ፤ እሱ ነው የተቆራረጠ ወይስ እሱ ነው የቆራረጠ ?
👉#የአይሁድን መስዋዕታቸውን እንቆራርጠዋለን ፤ ከእኛ ላይም የአሕዛብን ቀንበር እናስወግዳለን ፤ የአሕዛብ ቀንበራቸው 'ደም አፍስሱ ፣እንደኛ እመኑ እና እንደኛ እየገደላችሁ ኑሩ' ሲሉን " የለም የለም ጌታችን ሙቶ ነው ያሸነፈ ብለን እንደናንተ ግደሉ የሚለውን ሕግ እንቆራርጠውና ሙተን የነሱን ሕግ እናፈርሳለን ይላል። በሞታችን የአሕዛብን ሕግ እንድናፈርስ እግዚአብሔር ይርዳን
👉ወልደ እግዚአብሔርንም በማመን እስከዛሬ ድረስ አለን። እርሱም እውነተኛ የባህርይ አምላክ ነው።
👉ወልድ አብ ይበልጠኛል በማለቱ ከአብ ያንሳል የምትል ከሆነ ፤ አብ በማንም አይፈርድም ብሏልና እንግዲያውስ አብንም ከወልድ ያንሳል ማለትህ ነው !