🔐ከፈተና በፊት የሚወሰዱ ጠቃሚ ነጥቦች| Exam tips for all studentsጎ🔐ጎበዝ ተማሪዎች የደበቁን የአጠናን ዘዴዎች

  Рет қаралды 18,441

Zetsion-ዘጽዮን

Zetsion-ዘጽዮን

Жыл бұрын

#ጎበዝተ_ማሪዎች_የደበቁንየ_አጠናን ዘዴዎች | Students have hidden from us Methods| ምርጥ የኖት አየያዝ ዘዴ
#ለፈተና ዝግጅት
#ፈተና ከመግባታችሁ በፊት
12 ለፈተና የሚጠቅሙ ነጥቦች
• 'ዕውቀት ሳያገኙ ትምህርት ቤት መመላለስ
በእነዚህ ምክሮች መሠረት የማስታወስ ችሎታችሁንና የትኩረት አቅማችሁን ታዳብራላችሁ።
1. ቁርስና ጠቃሚ ምግቦች
ሰውነታችን በአግባቡ ሥራውን እንዲሰራ ኃይል ያስፈልገዋል፤ አንጎላችን ደግሞ ትኩረት እንዲኖረውና የማስተዋል አቅማችን እንዲጨምር በቂ የሆነና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት ይፈልጋል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቁርሳቸውን ተመግበው ወደፈተና የሚገቡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ። የተመጣጠነ ምግብ ተመግበው ለፈተና የሚቀርቡት ደግሞ የበለጠ የማስታወስና የማስተዋል አቅም ይኖራቸዋል።
ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ፈተና ያለባቸው ተማሪዎች እንደ የገብስ ገንፎ፣ ዳቦ፣ ሩዝና ድንች ያሉ በካርቦሃይድሬት የበለጸጉ ምግቦችን በቁርስ ሰዓት ተመግበው ቢወጡ ይመከራል።
እርጎ፣ እንቁላል፣ አሳ፣ ጎመን፣ ቲማቲምና አቮካዶ ዓይነት ምግቦችም እጅጉን ጠቃሚ ናቸው።
2. በጠዋት ወደ ጥናት መግባት
ሁሌም ቢሆን ነገሮችን አስቀድሞ መጀመርን የመሰለ ነገር የለም። ለፈተናም ቢሆን ጥናት በጠዋት ተነስቶ መጀመር በፈተና ወቅት የተረጋጋ መንፈስ እንዲኖረን ይረዳል።
ጠዋት ላይ ጭንቅላታችን እረፍት አድርጎ በአዲስ መንፈስ ሁሉንም ነገር ስለሚጀምር፤ በዚህ ሰዓት ማጥናት ውጤታማ ያደርጋል። በተለይ ደግሞ የክለሳ ጥናቶችን ለከሰዓት ማሸጋገር ተገቢ አይደለም።
ጠዋት ጥናት የምንጀምርበትና የምናበቃበት ሰዓት ከፈተናው በፊት ባሉት ሁለት ወይም ሦስት ሳምንታት ውስጥ ተመሳሳይ ለማድረግ መሞከርም ውጤታማ ያደርጋል።
• ሶሻል ሚድያ በተጠቃሚዎች ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ?
3. ምን ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባችሁ ወስኑ
በመጀመሪያ ፈተናው የጽሁፍ ነው ወይስ የተግባር? ወይስ ቃለመጠይቅ ነው የሚለውን መለየት ወሳኝ ነው።
ሁሉም ዓይነት ፈተናዎች የራሳቸው የሆነ የተለያየ አይነት አቀራረብ አላቸው። በምሳሌ አስደግፎ ማብራሪያ መስጠት የሚጠይቅ ዓይነት ፈተና ከሆነ ከዚህ በፊት የተሠሩ ፈተናዎችን እያመሳከሩ ጥቂት ቦታዎች ላይ በትኩረት መዘጋጀት።
ምናልባት ፈተናው ምርጫ አልያም አጭር መልስ የሚፈልግ ዓይነት ከሆነ ቀለል ያለና አጠቃላይ መረጃዎችን ለመያዝ መሞከር።
4. እቅድ ማዘጋጀት
ምናልባት ነገሮችን ቦታ ቦታ ለማስያዝና እቅድ ለማውጣት የምናጠፋው ጊዜ የባከነ መስሎ ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን እውነታው በተቃራኒው ነው። ምክንያቱም ምን ማጥናት እንዳለባችሁና መቼ ማጥናት እንዳለባችሁ እቅዳችሁ ይነግራችኋል።
ከዚህ በተጨማሪም ምን ያክል እንደተጓዛችሁ ለመመዝገብና ለመከታተል ይረዳል።
የትኞቹን ማስታወሻ ደብተሮች መቼ መመልከት እንዳለባችሁ፣ የትኞቹን መጻህፍት ለተጨማሪ ማብራሪያ እንደምትጠቀሙ እንዲሁም የፈተና ጥያቄዎችን መቼ መለማመድ እንዳለባችሁ በእቅድ ውስጥ ማስገባት ውጤታማ ያደርጋል።
እዚህ ጋር መርሳት የሌለብን ለእረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴም ቦታ መስጠት እንዳለብን ነው።
• “መሸ መከራዬ”፡ የታዳጊዎች ስቃይ
5. ከፋፍሎ ማጥናት
የክለሳ ጥናትን ከፋፍሎ ማካሄድን የመሰለ ነገር የለም። አንድ የትምህርት ዓይነት ላይ 10 ሰዓት ሙሉ ከማሳለፍ በየቀኑ አንድ ሰዓት በማጥናት በ10 ቀን መጨረስ ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል።
ያጠናነውን ነገር ለማስታወስና በቀላሉ ለመሸምደድ ጭንቅላታችን ጊዜ ይፈልጋል። ከፋፍሎ ማጥናት ደግሞ ለዚህ ፍቱን መድሃኒት ነው። ከፋፍሎ ማጥናት እጅግ ውጤታማው መንገድ እንደሆነም በመላው ዓለም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች ያለመክታሉ።
6. ራሳችሁን ቶሎ ቶሎ ፈትኑ
የሥነ አዕምሮ ጥናት ባለሙያዎች እንደሚሉት የማስታወስ ችሎታን ለማዳበርና በራስ መተማመናችንን ለመጨመር ራስን መፈተን ውጤታማ ያደርጋል።
ከዚህ በተጨማሪ እየተዘጋጀንበት ያለነውን ጉዳይ በደንብ እንድናውቀው ከማድረጉ በተጨማሪ የረሳናቸው አልያም የዘለልናቸው ርዕሶችን ለመለየት ይረዳናል።
7. መምህር መሆን
ከባዱን የክለሳና ራሳችሁን የመፈተን ሥራውን ካከናወናችሁ በኋላ ጓደኞቻችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ በጭንቅላታችሁ የሚመጣውን ነገር በሙሉ ንገሯቸው። ራሳችሁን በመምህር ቦታ አድርጋችሁ እውቀታችሁን ለማካፈል ሞክሩ።
ምን ያህል እንደምታስታውሱ ለማወቅ ከመርዳቱ በተጨማሪ ጓደኞቻችሁንም ትጠቅሟቸዋላችሁ።
8. ከተንቀሳቃሽ ስልካችሁ ራቅ በሉ
ስልኮች በጣም ብዙ ጥቅም አላቸው። ነገር ግን በጥናት ወቅት ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ነው የሚያመዝነው። በተለይ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ።
ብዙ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ብዙ ጊዜያቸውን ስልካቸው ላይ የሚያሳልፉ ተማሪዎች የትምህርት ውጤታቸው ሁሌም ቢሆን ዝቅ ያለ ነው።
ብትችሉ ስልካችሁን አጠገባችሁ እንኳን አታድርጉት።
9. ሙዚቃ መቀነስና በጸጥታ ማንበብ
በጸጥታ ውስጥ ሆነው ጥናታቸውን የሚያከናወኑ ተማሪዎች ሙዚቃ እየሰሙ ከሚያጠኑት ጋር ሲወዳደሩ በእጅጉ የተሻለ የማስታወስና የትኩረት አቅም እንዳለቸው ማረጋገጥ ተችሏል።
10. ቋሚ እረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴ
ውጤታማ የክለሳ ጥናት ማለት እረፍት አልባ ጥናት ማለት አይደለም። በጥናታችን መሀል መሀል ላይ ጥሩ አየር ለማግኘትና ሰውነታችንን ለማፍታታት ወጣ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ የማስታወስ ችሎታችንን በደንብ ከፍ ያደርገዋል።
• አስገራሚው የደቡብ ኮሪያ ፈተና
ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን እና ጭንቅላታችን በእጅጉ የተሳሰሩ በመሆናቸው እንቅስቃሴ ስናደርግ የደም ዝውውራችን ይስተካከላል፤ ይህ ደግሞ በቂ ኦክስጅን ወደ ጭንቅላታችን እንዲሄድ ይረዳል።
አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ጭንቀትን መከላከልና በራስ መተማመንን መጨመር ከነዚህ መካከል ይጠቀሳሉ።
11. እንቅልፍ
ከፈተና በፊት ያለችውን ምሽት ጥሩ እንቅልፍ አግኝቶ ማሳለፍ ተገቢ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ነገር ግን ጥሩ እንቅልፍ ፈተናው ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን ከሳምንታት በፊት ገና ዋናው ጥናት ሲደረግና ክለሳ በሚደረግበት ወቅትም እጅግ ወሳኝ ነው።
በጠዋት ተነስቶ ውጤታማ የክለሳ ጥናት ካደረጉ በኋላ በጊዜ ተኝቶ ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ሰውነታችንና ጭንቅላታችን በደንብ ተግባብተው እንዲሰሩ ይረዳቸዋል። ሌሊቱን በሙሉ ለማጥናት ሙከራ አታድርጉ ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። ምክንያቱም ራሳችን ላይ ጫና እያሳደርን ስለሆነ።
12. መረጋጋትና በጎ በጎውን ማሰብ
እስካሁን የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ተግባራዊ ካደረጋችሁ ምንም የሚያሳስባችሁ ነገር ሊኖር አይገባም። ዘና ብላችሁ ወደ ፈተና መግባት ብቻ ነው የሚቀራችሁ። ምናልባት ጥሩ ያልሆነ አጋጣሚ ቢገጥማችሁ እንኳን እሱን ረስታችሁ ለቀጣዩ በጥሩ መንፈስ ለመዘጋጀት ሞክሩ።
በመጨረሻም በእያንዳንዱ ጥሩ የፈተና ጊዜ ለራሳችሁ ሽልማት መስጠት አትርሱ።
በፈተና ጊዜ መደረግ ያለባቸው እና መዘንጋት የሌለብን ጠቃሚ ነጥቦች
የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያግዙ ነጥቦች
ፈተና ለመድፈን
ትምህርት ሚንስተር
Exam tips for Ethiopian students,
tips to perform well while taking your exam at any level
ስለ #ኢትዮጵያ #ማትሪክ #ፈተና #ውጤት #ለማየት #ተበላን #ለማለፍ #ጥያቄ #2014 #2015 #2016 #2022 #2023 #ተማሪ#markonmusic#markon_music#ላላተርፍ#እምዬሀገሬ#አንቺንብየ#ጎዳናው#ማር_ማር#ውሰጃት#ሞኙ_ልቤ#አትክልት #ምግብ #doctor #health #hakim #food #ethiopianfood #ethiopianfoodrecipe #ምግብ #ምልክቶች #ምክር #ምክንያቶች#መፍትሄ #hakim #hakimpage#haikmmeme#healthinfo#shegerinfo@shegerinfo
#ethiopian #matric #exam #result 2015 2022 2023 #highest #score #ከፍተኛ መፍትሄዎቹ#kedmialetenawo#university#college#grade 9 10 11 12
#የጤና#ጥቅሞች #መፍትሄዎች #መፍትሔዎች#ጉዳቶች#መድኃኒቱ#ምልክቶች#ህክምና#ዶክተር #ዶክተርሀበሻ #ዶክተርሀበሻኢንፎ #ዶክተርዳኒ #health #አትክልት #ምግብ #doctor #hakim #vegetables
#health_media # #ጤናሚድያ #ጤና_ሚድያ #የኔ_ጤና #yene_tena #ጤናሚዲያ#አትክልት #doctor

Пікірлер: 34
@user-ui3yj8tr1o
@user-ui3yj8tr1o 6 ай бұрын
በጣም ልክ ነው።ይበርቱ እናመሰግናለን!
@user-rq5qc8tr6k
@user-rq5qc8tr6k 7 ай бұрын
This is good advice grate
@MarthaTsehay
@MarthaTsehay Жыл бұрын
ሰላም ላንተ ይሁን በጣም ቆንጆ እና ጠቃሚ የሆነ ፊዶ ነው ሼር ያረከን እናመሰግናለን ተባረክ 👌👍💖#
@Zetsion
@Zetsion Жыл бұрын
ማርታ አመሰግናለሁ! ቻናልሽንም እያየሁት ነበር ጠቃሚ እውቀት ነው የምታጋሪው ፣ description እንደገለጽኩት share አደርግልሻለሁ
@user-is1zx3bs9f
@user-is1zx3bs9f 11 ай бұрын
Thank you 😊😊😊 brother
@Zetsion
@Zetsion 10 ай бұрын
Thank you too
@GebeyawChekol-ti5wi
@GebeyawChekol-ti5wi Жыл бұрын
ወንድሜ እኔ የብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ነኝ።ምን ባደርግ ይሻላል ?
@Zetsion
@Zetsion 9 ай бұрын
ጠቀመህ?
@kelemtube
@kelemtube Жыл бұрын
ሰላምጤናይሰጥልኝ እንኳን በሰላም መጣህ አሪፍመረጃወችን ሰለምታቀርብልን እናመሰግናለን
@Zetsion
@Zetsion Жыл бұрын
አመስግናለሁ ቀለም!❤❤
@user-to6bu7et1z
@user-to6bu7et1z Ай бұрын
እጅግ በጣም እናመሰግናለን
@ayalwello_
@ayalwello_ Жыл бұрын
ሰላም ጤና ይስጥልን ጥሩ ትምህርት ነው በርታ
@Zetsion
@Zetsion Жыл бұрын
አጅግ አመሰግናለሁ አያልየ♥️
@mekditube7654
@mekditube7654 Жыл бұрын
ሰላም ጤና ይስጥልኝ እናመሰግናለን #like #Share
@Zetsion
@Zetsion Жыл бұрын
ተባረኪ መቅዲ🙏 ሼር በማድረግ ለቤተሰቦችሽ ጋብዢልኝ። የወደደ እንዲያየው♥️❤🙏
@tekleharegot3506
@tekleharegot3506 Жыл бұрын
ወንድሜ ማስቲካ ኣይፈቀድልም ወንድሜ በጣም ኣመሰግናለን ሚኒስትሪይ ተፈታኝ ነኝ
@Zetsion
@Zetsion 10 ай бұрын
Good luck
@Zetsion
@Zetsion 9 ай бұрын
አመሰግናለሁ!
@KidistEthiopiankitchen
@KidistEthiopiankitchen Жыл бұрын
ግእዝ ጤና ሰላም ወንድማችን በርታ
@Zetsion
@Zetsion Жыл бұрын
I saw your contents, they r really impressive. I will the to my community እሺ። በርቺልኝ❤
@Betlemalm
@Betlemalm 6 ай бұрын
Ï Love YOU
@Zetsion
@Zetsion 5 ай бұрын
Thanks dear
@user-tk1oz7fx5v
@user-tk1oz7fx5v Жыл бұрын
ወንድሜ ክላስ ዉስጥ ማስቲካ ማኘክ አይቻልም😊😊🎉🎉❤
@Zetsion
@Zetsion 10 ай бұрын
Esh
@almazyimam3102
@almazyimam3102 Жыл бұрын
ምግብ አለመብላት ይቻላል
@Zetsion
@Zetsion 10 ай бұрын
አዎ። ነገር ግን ሊደክምሽ ይችላል
@Zetsion
@Zetsion 9 ай бұрын
አዎ. ድካም ግን አለው
@nebilabeauty
@nebilabeauty Жыл бұрын
በቅንኔት Subscribd አሬኩ አንተም ብቅበል
@Zetsion
@Zetsion Жыл бұрын
እሺ ነቢላ። እጅግ እጅግ አመሰግናለሁ
@user-rq5qc8tr6k
@user-rq5qc8tr6k 7 ай бұрын
This is good advice grate
@user-tk1oz7fx5v
@user-tk1oz7fx5v Жыл бұрын
ወንድሜ ክላስ ዉስጥ ማስቲካ ማኘክ አይቻልም😊😊🎉🎉❤
@hewanalemye-op3wu
@hewanalemye-op3wu Жыл бұрын
😂
@Zetsion
@Zetsion 9 ай бұрын
እሺ
@Zetsion
@Zetsion 9 ай бұрын
አመሰግናለሁ!
በ 1 ሳምንት ውስጥ ለፈተና መዘጋጀት
9:10
Yab Question
Рет қаралды 13 М.
Double Stacked Pizza @Lionfield @ChefRush
00:33
albert_cancook
Рет қаралды 84 МЛН
НЫСАНА КОНЦЕРТ 2024
2:26:34
Нысана театры
Рет қаралды 756 М.
A little girl was shy at her first ballet lesson #shorts
00:35
Fabiosa Animated
Рет қаралды 10 МЛН
Самый Молодой Актёр Без Оскара 😂
00:13
Глеб Рандалайнен
Рет қаралды 11 МЛН
የ' ወ' አገባብ/ሰዋስው
20:03
Zetsion-ዘጽዮን
Рет қаралды 5 М.
የጥናት ፕሮግራም እንዴት ማዘጋጀት እችላለሁ?
2:36
Gobez Temari - ጎበዝ ተማሪ
Рет қаралды 51 М.
Double Stacked Pizza @Lionfield @ChefRush
00:33
albert_cancook
Рет қаралды 84 МЛН