"እናንተ በብዙ ፈተና፣ ተግዳሮቶች እና ችግሮች ያለፋችሁ ፤ ችግርን መቋቋም የምትችሉ፣ አይበገሬና የአይበገሬ ትውልድ ማሳያ ተምሳሌት ናችሁ"

  Рет қаралды 135

Amhara Education Bureau

Amhara Education Bureau

7 ай бұрын

"እናንተ በብዙ ፈተና፣ ተግዳሮቶች እና ችግሮች ያለፋችሁ ፤ ችግርን መቋቋም የምትችሉ፣ አይበገሬና የአይበገሬ ትውልድ ማሳያ ተምሳሌት ናችሁ"
ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዕውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር በባህርዳር ከተማ አካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን ዛሬ የተሸለሙ ተማሪዎች በብዙ ፈተና፣ ተግዳሮቶች እና ችግሮች ያለፉ፤ ችግርን መቋቋም የሚችሉ፣አይበገሬና የአይበገሬ ትውልድ ማሳያ ተምሳሌት ናቸዉ ሲሉ ገልጸዋል ፡፡ ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ አክለዉም ሰዎችን ለማለፍ በሚከብዱ በርካታ ችግሮች ውስጥ ያለፋችሁ ጀግኖች ናችሁና እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ሀገር በተለያዩ የፈጠራ ሰዎችን እና ዉጤትን ትፈልጋለች ፤ እነዚያ ከሚፈለጉ ሰዎች መካከል ደግሞ እናንተ ቀዳሚዎቹ ናችሁ ያሉት አቶ አብዱ ነገን ጤናማ በሆነ መንገድ ተረክባችሁን የትውልድ አደራችሁን እንድትወጡ ሲሉ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
ትምህርት ጤናማ የሀገር ግንባታ እና የብሔራዊነት ትርክትን ለማምጣት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለዉ የተናገሩት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ‹‹ሀገር ፣ ህዝብ እና መንግስት ችግር በገጠማቸው ጊዜ ተመልሰው የትምህርት ስርአታቸውን ይፈትሹ " እንደሚባል በማስታወስ የዛሬው ክልላዊም ሆነ ሀገራዊ ችግሮቻችን መነሻ በትምህርት ስርአቱ ውስጥ የሚታዩ ጉድለቶች ነጸብራቅ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡ በመሆኑም የገጠሙንን ችግሮች ለመፍታት በትምህርት ስርአታችን ውስጥ ያሉትን ጉድለቶች መፈተሽ ለነገ የማይባል ተግባር ነው ብለዋል ፡፡
በቀጣዮቹ አመታት በምትመደቡባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚኖራችሁ ቆይታ የተበተነ እና የተበታተነ ነጠላ ትርክትን በመተው የወል እውነትና የብሄራዊነት ትርክትን በመገንባት እና የተለወጠ አአምሮን በማምጣት በኩል ተማሪዎቹ ታሪካዊ ሃላፊነት እንዳለባቸዉም ገልጸዋል፡፡
ሐቀኛ ትውልድ ለመፍጠር በሚደረገዉ ረጅም ጉዞ ዉስጥ እናንተ ቀዳሚዎቹ ናችሁ ያሉት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ተማሪዎች ከተቋማት ይዘውት ከሚወጡት ጥሩ ውጤት በተጨማሪ መልካም ሥነ ምግባር፣ የሚሠራ እጅ እና ሕዝብን የሚያገለግል አስተሳሰብ ይዞ መውጣትም ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ሰላምን ይፈልጋል፤ በክልሉ ዘላቂ ሰላም ሰፍኖ ተማሪዎች ጊዜያቸውን እና ዕድሜያቸውን በትምህርት ላይ እንዲያውሉ ማድረግ ይገባል ያሉ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ሁሉም ማኅበረሰብ ለሰላም የሚሆን ሀቀኛ እና ከልብ የመነጨ የሰላም አማራጭን እየተከተለ ለሰላም መሥራት አለበት ብለዋል።
ጤናማ ሀገር እና ሥርዓት የመገንባት ሂደት ጠንካራ የትምህርት ሥርዓት ያሥፈልጋል፤ ይህንን ለማምጣት ደግሞ የትምህርት ሥርዓትን እና ተደራሽነቱን በየጊዜው መፈተሽ እና እያስተካከሉ መጓዝ ለነገ የማይባል ሥራ ነው ፤ ትምህርት ከየትኛውም ሴክተር በላይ ሰላም ይፈልጋል፤ የትኛውንም አይነት የስነ ልቦናም ሆነ የአካላዊ ተጽእኖ ሊኖር አይገባም ያሉት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ በሂደታችሁ እና ባስመዘገባችሁት ዉጤት ክልሉን እና የአማራን ህዝብ ከፍ ያደረጋችሁ ናችሁ፤ ከዚህ በኋላም ለምታደርጉት እና ለስኬታችሁ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸዉ አረጋግጠዋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን / @amharaeducationbureau...
3. በፌስ ቡክ ገጻችን / amhara-education-bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን

Пікірлер
Who has won ?? 😀 #shortvideo #lizzyisaeva
00:24
Lizzy Isaeva
Рет қаралды 65 МЛН
КАК ДУМАЕТЕ КТО ВЫЙГРАЕТ😂
00:29
МЯТНАЯ ФАНТА
Рет қаралды 9 МЛН
Sigma girl and soap bubbles by Secret Vlog
00:37
Secret Vlog
Рет қаралды 12 МЛН
How to win a argument
9:28
ajaxkmr
Рет қаралды 405 М.
Who has won ?? 😀 #shortvideo #lizzyisaeva
00:24
Lizzy Isaeva
Рет қаралды 65 МЛН