No video

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ - ክፍል 1 / St. Ephrem Syrian part-1

  Рет қаралды 357,359

የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik

የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik

9 жыл бұрын

††† እንኳን ለታላቁ ሊቅና አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ †††
††† እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው ንጽቢን በምትባል የሶርያ ግዛት ውስጥ በ298 / 306 ዓ/ም ነው:: ወላጆቹ በክርስቶስ የማያምኑ አላውያን ነበሩ:: (ምንም አንዳንድ ምንጮች ክርስቲያኖች ነበሩ ቢሉም)
ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ንጽቢን ጵጵስናን የተሾመ ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር:: የሰማዕትነት: የሐዋርያነት: የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት ነው:: ታዲያ ቅዱስ ኤፍሬም ይሔ አባት ሁሌ ሲያስተምር ይሰማው ነበርና በስብከቱ ተማርኮ ደቀ መዝሙሩ ለመሆን በቃ::
ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱስ ያዕቆብ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ሙሉ የወጣትነት ጊዜውን ያሳለፈው በትምሕርት ነው:: የሚገርመው መምሕሩ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡ የሚወድና ጠርቷት የማይጠግብ አባት ነውና ለልጁ ለቅዱስ ኤፍሬም ይሕንኑ አጥብቆ አስተምሮታል::
ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን ሲመረምር የእመቤታችን ፍቅር ይበዛለት ጀመር:: ምክንያቱም እመ ብርሃንን ሳይወዱ ክርስትና የለምና:: እንደ እርሱ የሚወዳት የለም እስኪባል ድረስ ያገለግላት: ይገዛላትም ገባ::
እንዲህ እንደ ዛሬ የድንግል ማርያም ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበር:: እርሱ ግን ከወንጌለ ሉቃስ በስድስተኛው ወርን (ይዌድስዋን) እና ጸሎተ ማርያምን(ታዐብዮን) አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ ስልሳ አራት ስልሳ አራት ጊዜ ያመሰግናት ነበር::
በእንዲህ ያለ ግብር እያለ አርዮስ በመካዱ እርሱን ለማውገዝና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማጽናት በ317 (325) ዓ.ም ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቃውንት በኒቅያ ሲሰበሰቡ አንዱ መምሕረ ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ኤፍሬም ከሊቃውንቱ ትምሕርትና በረከትን አግኝቷል::
ከጉባዔ መልስ መንገድ ላይ በራዕይ የብርሃን ምሰሶ አይቶ "ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ "ይሕማ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ነው::" አለው:: እርሱም መምሕሩን ቅዱስ ያዕቆብን ተሰናብቶ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ (ቂሣርያ) ወረደ:: ተገናኝተውም በአንድ ሌሊት ቋንቋ ተገልጦላቸው ሲጨዋወቱ አድረዋል::
በቦታው ብዙ ተአምራት ተደርጓል:: ቅዱስ ኤፍሬም ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በኋላ ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ያስተምር ጀመር:: ሁል ጊዜ ታዲያ ጸሎቱ ይሔው ነበር:: "እመቤቴ ሆይ! ምስጋናሽ እንደ ሰማይ ከዋክብት: እንደ ባሕር አሽዋ በዝቶልኝ: እንደ እንጀራ ተመግቤው: እንደ ውኃ ጠጥቼው: እንደ ልብስም ተጐናጽፌው" እያለ ይመኝ ነበር::
አፍጣኒተ ረድኤት: ፈጻሚተ ፈቃድ እመ ብርሃንም በገሃድ ተገልጻ የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት:: ዛሬ ጸጋ በረከት የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት:: ሲደርስላትም እርሷ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ ወርዳ: በፊቱም ተቀምጣ ሲሆን እርሱ ደግሞ ባጭር ታጥቆ: በፊቷ ቆሞ: በመንፈስ ቅዱስም ተቃኝቶ ነው::
ውዳሴዋን በሰባት ቀናት ከደረሰላት በኋላ በብርሃን መስቀል ባርካው: ሊቀ ሊቃውንትም እንዲሆን ምሥጢር ገልጣለት ዐረገች:: ከዚህ በኋላ በምሥጢር ባሕር ውስጥ ዋኝቶ አሥራ አራት ሺህ ድርሰቶችንም ደርሷል:: ዛሬ ሶርያ ውስጥ የምንሰማውን ዜማም የደረሰው ይህ ቅዱስ ነው::
እንዲያውም አንድ ቀን የምሥጢር ማዕበል ቢያማታው "አሃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" ብሎ ጸልዩዋል:: (የጸጋህን ማዕበል ያዝልኝ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በመጨረሻ ሕይወቱ ተክሪት በምትባል ሃገር ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ተሹሟል::
በጣፋጭ ስብከቱ ብዙዎችን ካለማመን መልሷል:: የምዕመናንንም ሕይወት አጣፍጧል:: ለመናፍቃንና ለአርዮሳውያን ግን የማይጋፉት ግድግዳ ሆኖባቸው ኑሯል:: በዘመኑም ብዙ ተጋድሎ አፍርቷል:: ተአምራትንም ሠርቷል:: በተወለደ በስልሳ ሰባት ዓመቱ ሐምሌ 15 በ365 (373) ዓ.ም ዐርፎ ተቀብሯል::
††† ቅዱሱ ለሶርያ ብቻ ሳይሆን እመቤታችንን ለምንወድ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ሞገሳችን ሆኗል:: ስለዚህም እንዲህ እያልን እንጠራዋለን:-
1.ቅዱስ ኤፍሬም
2.ማሪ ኤፍሬም
3.አፈ በረከት ኤፍሬም
4.ሊቀ ሊቃውንት ኤፍሬም
5.ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም
6.አበ ምዕመናን ኤፍሬም
7.ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን አንተ ነህ::
††† ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::
ምንጭ፡ “ዝክረ ቅዱሳን Saints Of The Orthodox Church” (facebook page)

Пікірлер: 542
@yekidusantarik
@yekidusantarik 4 жыл бұрын
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ - ክፍል 2 = kzfaq.info/get/bejne/n5t6iLheqMetgYk.html
@sjsjdkkskss6088
@sjsjdkkskss6088 3 жыл бұрын
🕯🕯🕯
@sjsjdkkskss6088
@sjsjdkkskss6088 3 жыл бұрын
🕯🕯🕯
@sjsjdkkskss6088
@sjsjdkkskss6088 3 жыл бұрын
🕆🕆🕆
@slamsa3490
@slamsa3490 3 жыл бұрын
♦️🙏♦️
@bockitprivet7395
@bockitprivet7395 3 жыл бұрын
🙏🙏🙏🙏🙏😍😍
@user-to9gr4vq2e
@user-to9gr4vq2e 2 ай бұрын
የቅዱሳን በረከት እረዴት ይደርብን የቅዱስ ኤፍሬም በረከት እረዴት አይለየን አሜን
@user-xw5op1nb9o
@user-xw5op1nb9o 5 жыл бұрын
ኡፍፍፍ ሆዴን ትርምስምስ አረገው 😢ምህረቱን ይላክልን በረከቱ ይደርብን የቅዱስ ኤፍሬም አሜን
@Israel9563
@Israel9563 Жыл бұрын
Amen amen amen
@abebaembiale3452
@abebaembiale3452 Жыл бұрын
Amen❤❤
@user-xo7ll7dr3n
@user-xo7ll7dr3n 10 ай бұрын
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ምን ይሰኣነው
@hennaab9136
@hennaab9136 5 жыл бұрын
እግዚአብሔር አምላክ አስተዋይ ልቦና ይስጠን ሰሚ ጆሮ ይስጠን የቅዱሳን ፀሎት ይጠብቀን😢😢
@semharkiroskiros1960
@semharkiroskiros1960 3 жыл бұрын
አሜን
@henokmamo1041
@henokmamo1041 3 жыл бұрын
አያል
@henokmamo1041
@henokmamo1041 3 жыл бұрын
አሜን
@user-eh2xp8fc1z
@user-eh2xp8fc1z Жыл бұрын
አሜን "፫
@Israel9563
@Israel9563 Жыл бұрын
Amen amen amen
@Mona-de3wx
@Mona-de3wx Жыл бұрын
ያባአቱቻችን በረከት ይደረብን ቃለ ህይውት ያሰማልን😢😢😢😢😢😢
@girmamamo3159
@girmamamo3159 5 жыл бұрын
እግዚአብሔር አምላክ አስተዋይ ልቦና ይስጠን ሰሚ ጆሮ ይስጠን የቅዱሳን ፀሎት ይጠብቀን!!!
@jemilaaki7703
@jemilaaki7703 8 жыл бұрын
የአባታችን ይቅዱስ ኤፍሬም በርከታቸው ይደርብን አሜን አሜን
@mostata9850
@mostata9850 7 жыл бұрын
Jemila Aki
@flimongebrehaweriaamenamen9252
@flimongebrehaweriaamenamen9252 7 жыл бұрын
አማን አማን አማን
@askanderaskander2847
@askanderaskander2847 6 жыл бұрын
Jemila Aki አሜን። አሜን። አሜን
@ayuamanu6229
@ayuamanu6229 4 жыл бұрын
Amen Amen Amen
@user-tp9sp1dd8j
@user-tp9sp1dd8j 6 жыл бұрын
እግዛብሄር ይባርካቹ እህት ወንድሞቼ አሜን አሜን አሜን ቃለ ሂወት ያስማልን ቁድስ ኤፍሬም ብምላጁ አይለየን ክብር ለንተ ይሁን ቁዱስ ሆይ
@amegirma6736
@amegirma6736 6 жыл бұрын
አቤት የኛስ መድረሻ የት ይሆን የፃድቃኖች አባቶቻችን በረከት ይደርብን ምንም ለማይከፈልህ ንጉስ አባታችን መድሀንያለም ስምህ ይባረክ
@betiyedniglmariyamlij8346
@betiyedniglmariyamlij8346 8 жыл бұрын
የእግዚአብሔር ስም ይክበር ይመስገን ይህን በረከት እንዲያይና እዲሰማ ፈቃድህ ሆኖልኛል አመሰግንሀለሁ ያባቶቻችን በረከት ይደርብን ቃል ህይዎት ያሰማልን ተስፋ መንግስታ ሰማያት ያውርስልን አሜን
@user-vu6jw2lr9u
@user-vu6jw2lr9u 6 жыл бұрын
Beti yednigl mariyam lij አሜንንንን አሜንንንንን አሜንንንንንንን
@kakinuka9065
@kakinuka9065 7 жыл бұрын
ተባረክ ወንድማችን ቃል ህይወት ያስማልን የቅዱስ ኤፍሬም በረከት ና ምልጃዉ አይለየን አሜንንን
@mayatekeba4985
@mayatekeba4985 7 жыл бұрын
አሜን !
@ilvoeyuo3807
@ilvoeyuo3807 7 жыл бұрын
mahi tekeba አሜን
@alemgeda7530
@alemgeda7530 7 жыл бұрын
kaል kiዳን nuጉስ kaሊ አሜን አመን አሜን
@user-pl3lw3xi9p
@user-pl3lw3xi9p 7 жыл бұрын
kaል kiዳን nuጉስ kaሊ amen mar Lehulachn
@fantafanta678
@fantafanta678 6 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን
@user-vd8zt8fi6m
@user-vd8zt8fi6m 7 жыл бұрын
amen ጌታየ ሆይ ልቦናየን ክፈትልኚ ህያው ቃልህንም ሞላ
@user-et3ug2gh7l
@user-et3ug2gh7l 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን የአባታችን ቅዱስ ኤፍሬም ረድኤት በረከት ይደርብን ቃለ ህይወት ያሰማልን እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመናቹህ ይባርክልን አሜን
@user-zy2oh8ts5o
@user-zy2oh8ts5o 8 жыл бұрын
አሜን♥አሜን♥አሜን♥በረከቱው ይደርብን ቃለህይወትያሰማልን
@user-ix6ns7yu4m
@user-ix6ns7yu4m 7 жыл бұрын
ሠላማችሁ፡ይብዛ------ቃለህይወት ያሠማልን አባትቻችን እናመሠግናለን ያገልግሎት ዘመናችሁን ይባርክልን በድሜ፡በፀጋ፡ያቆይልን፡የቅዱስ፡ኢፍሬም በረከት ይደረበን ኡሜን አሜን አሜን
@kebrealmeysamsung9772
@kebrealmeysamsung9772 3 жыл бұрын
እባክህ ጌታሆይ በፈተና እድፀና ብርታትን ስጠኚ የአባታችን የቅዱስ ኤፍሬም በርአት ይደርብን አሜን፫
@desbeletberih878
@desbeletberih878 Жыл бұрын
እሜቤተ ቅድስቲ ማርያም ንቁዱስ ኤፍረም ሴራዎ ከም ዝባረክዮ ንዕይ ሓጣቴና ባርክኒ ባርክኒ
@tigestshemlash9709
@tigestshemlash9709 8 жыл бұрын
አሜንንንንንንን ቃለ ህይወት ያሠማልን በእውነት ደሥ ይላል አቤት የእኛ ድካሞችሽ ምን ይሆን ሥራችን አባት ሆይ የተላለፈው በድል ሀፅያታአችን አትቆጥርብን
@addesmakdies7233
@addesmakdies7233 7 жыл бұрын
Tigest Shemlash አሜን አሜን አሜን
@metamenlerasnowmetamenlera6270
@metamenlerasnowmetamenlera6270 6 жыл бұрын
Tigest Shemlash አሜን አሜን አሜን
@user-tg2ek5wx5l
@user-tg2ek5wx5l 6 жыл бұрын
Tigest Shemlash አሜን አሜን
@user-yt6bj9ww6w
@user-yt6bj9ww6w 6 жыл бұрын
Tigest Shemlash matahafa
@shaamshaam7986
@shaamshaam7986 5 жыл бұрын
Tigest Shemlash አሜን አሜን አሜን ቃለሄወትያሠማኝልን
@werkneshsahela.7185
@werkneshsahela.7185 8 жыл бұрын
አሜን ቃለ ሂወት ያሠማልን ጌታ ሆይ እኛንም በሀይማኖታችን አፅናን
@user-gf6ye8no7i
@user-gf6ye8no7i 6 жыл бұрын
አሜን! የቅዱስ ኤፍሬም በረከት ይደርብን ሁሉም በልባችን ይደር አሜን! አሜን !አሜን! !!!!!
@samera7043
@samera7043 3 жыл бұрын
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃል ሂወት የሰማዓልን
@user-qk3yc3di9j
@user-qk3yc3di9j 4 жыл бұрын
እግዚአብሔር ንፁህ ልቦናን ያድለን በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን ⛪️✝️✝️🙏🙏🙏
@user-rz3oo5lb9b
@user-rz3oo5lb9b 7 жыл бұрын
እግዝኣብሄር ስሙ የተባረከ ይሁን ኣሜን ኣሜን ኣሜን
@shsh3659
@shsh3659 4 жыл бұрын
Ok
@marriaamtrubr2595
@marriaamtrubr2595 8 жыл бұрын
አቤቱ አባታችን አንደቅዱሣኖችህ አምነት ጵናትን ሥጠን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን
@gam123ha9
@gam123ha9 7 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለህወትያሠማልን
@nobelgebru7952
@nobelgebru7952 7 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ለሀለቹም ቃል ህወትን ያስማል ብእውነት ፀጋውን ያብዛላቹ የአባታችን ቸርነትና የመብርሀን አማላጅነት የፃድቃን ስማኣታትን ምልጃቸው ክሁላቺን ህዝበ ክርስትያን ይሁን አሜን፫
@miratfaily6749
@miratfaily6749 6 жыл бұрын
Nobel Gebru the best
@gebtsawtigebysawtt1192
@gebtsawtigebysawtt1192 4 жыл бұрын
Amen amen amen
@user-pj3ry1qk1h
@user-pj3ry1qk1h 6 жыл бұрын
ኣሜን ኣሜን ኣሜን እግዚኣብሔር ይመስገን ሰላምህ ይብዛ ወንድማችን የኣባቶቻችን በረከትና ሬድኤት ኣይለየን ኣቤቱ ኣምላኬ ሆይ ይህንን ኩፉ ዘመን ኣርቅልን ልጆችህ ታደግ ኣሜን መልካም ቀን
@nodthil6934
@nodthil6934 Жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን የቅዱሥ ኤፍሬም ረድኤት በረከት አይለየኝ ዋ ነፍሤ መጨረሻሽ ምን ይሆን እግዚአብሔር ሆይ እኔ ሀፂያተኛ እና በደለኛ ነኝ ይቅር በለኝ አቤቱ የሠራዊት ጌታ😢😢😢😢😢😢😢😢
@user-vb8oo8kr1t
@user-vb8oo8kr1t 3 ай бұрын
ያባታችን ያፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም በረከት እረደኤት ይደርብን አሜን😢😢❤❤❤💒💒💒
@milymilykelkel6441
@milymilykelkel6441 6 жыл бұрын
አሜን ቃል ህይውት ያስማልን. ብርክት እና ሬድእት አይለይን
@rgatlove1403
@rgatlove1403 7 жыл бұрын
ቃል ህይወት ዩስማልን።እግዚአብሔር በምህረቱ ዩዘክረን ኣሜን ኣሜን ኣሜን
@tinbebtinbeb5267
@tinbebtinbeb5267 8 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር አምላክ ለዘላለም የከበረ ነው
@Ll-pz7lj
@Ll-pz7lj 6 жыл бұрын
አቤቱ አምላኬ ሆይ ስለቅዱሳን አባቶቻችን ብለህ በደሌንና መተላለፌን ደምስስልኝ አቤቱ ይቅር በለኝ
@addesmakdies7233
@addesmakdies7233 7 жыл бұрын
የአባታችን የ ቅድስ የኤፍሬም በረከት እረድኤቱ አይለየን አሜን፫
@loveLove-cf7hd
@loveLove-cf7hd 7 жыл бұрын
በረከታቸው ይደርብን አሜን እግዚአብሔር ይስጥልን
@eyuaddis2399
@eyuaddis2399 3 жыл бұрын
አባታችን ቅዱስ ኤፍሬም በረከታቸው ይደርብን
@user-jx2pk4yp2t
@user-jx2pk4yp2t 7 жыл бұрын
ቃለ ሂወት ያሰማልን. አሜን አሜን አሜን
@meserettsedalumeserettsedd8388
@meserettsedalumeserettsedd8388 8 жыл бұрын
የአባታችን የቅዱስ ኤፍሬም ምልጃና ፀሎት አይለይን አሜን
@teklemariamabrha7387
@teklemariamabrha7387 6 жыл бұрын
ኣሜን ጸጋ ኣባ ኤፍሬም ኣይ ፈለየና፡ብጣዓሚ ጽቡቅ ኣምላኽ ቕዱሳን ይባርኩም?
@user-cw4co7ct7s
@user-cw4co7ct7s 3 жыл бұрын
አሜን ቃለሂወትየስመአና
@abababab7409
@abababab7409 8 жыл бұрын
አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን
@mulukasaw3801
@mulukasaw3801 8 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለሂወትን ያሰማልን
@user-ez8rt4bi1o
@user-ez8rt4bi1o 8 жыл бұрын
ቃለ ህወትን ያሰማልን ያባታችን በረከት ከሁላችን ይሁን ኣሜን
@user-gh1vu1eq9f
@user-gh1vu1eq9f 6 жыл бұрын
እናመሰግናለን በረከቱ በኛ ላይ ይደር የሶሬያዊው ኤፍሬም አምላክ ሀገሩን ሰላም ያርግላቸው በግፍ እየተቀጠፍ ላሉት የሶሪያ ህፃናትን ስለቁዱሱ ኤፍሬም ብለህ ጎብኛቸው አምላኬ ሆይ ምንም የማያቁ ጨቅላዎችን ታደግልን በቸርነትህ አስበን በምህረት ተመልከተን ክብር ምስጋና ለስምህ አሜን
@androidphones6437
@androidphones6437 6 жыл бұрын
ቃል ሂውት ያሰማልን በጣም ደስ የሚል ትምህርት ነው አሜን በሁላችንም ላይ በርከት ይደር
@addisayele1090
@addisayele1090 8 жыл бұрын
ያባታችን በረከት ይደርብን ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን
@kahsakahsa8280
@kahsakahsa8280 6 жыл бұрын
ኦ እግዚኣብሔር ኣምላክ ሆይ ልሰማ ሰለፈቀድከለኝ ኣመሰግናለሁ ሰለሁሉም ነገር እግዚኣብሔር ይመስገን ቃል ህይወት ያሰማልን
@user-yx6yn5gn8o
@user-yx6yn5gn8o 5 жыл бұрын
ቃለ ሂወት ያሰማለው ብጣዕሚ ያምራል ኣሰራርሓ ጸጋና በረኸት ያብዛላቸው እግዚኣብሄር
@user-mk4qc4cf3s
@user-mk4qc4cf3s 5 жыл бұрын
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ሂወት ያሰማልን በረከት ይደርብን ኣሜን።
@tigistashuma6088
@tigistashuma6088 4 ай бұрын
እግዚያብሄር ፣ይመስገን፣አሜን፣አሜን፣አሜን፣የቅድስኤፍሬም፣በረከቱ፣ረዴቱ፣ከእኛ፣ጋር፣ይሁን
@ageraasmer1921
@ageraasmer1921 Жыл бұрын
በእውነት ወንድማችን ቃለ ህይወት ያሰማልን የቅዱሳን በረከት ምልጃ ጸሎት አይለየን
@alemgoytom2451
@alemgoytom2451 4 жыл бұрын
Amen Amen Amen kale hiwet yesmelana
@user-rd7bs9wj1j
@user-rd7bs9wj1j 5 жыл бұрын
አሜን፫ቃለህወት ያሰማለን የቅዱስ ኤፍረም በረከት ረድኤት ይደረበን
@user-ii7pc3sc3w
@user-ii7pc3sc3w 7 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር አምላካችን በቅዱሳኑ ፀሎት ይማረን አሜን
@user-gw5rc9dq8b
@user-gw5rc9dq8b 7 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን
@enewaalebachew7226
@enewaalebachew7226 6 жыл бұрын
ቃወህይወት ያሰማልን
@wekinesha5301
@wekinesha5301 8 жыл бұрын
Amen berket redaetachew yedrbin Kale hewot Yasemalin!!!
@hananhp4217
@hananhp4217 10 ай бұрын
ያባታችን የቅዱስ ኤፍሬም በረከታቸዉ ይደርብን 👏👏👏👏
@MinasEsrael
@MinasEsrael 2 ай бұрын
በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ውዳሴ ማርያምን የደረሰ የቅዱስ ኤፍሬም በረከት ይደርብን ።
@user-ne1fd6gj7j
@user-ne1fd6gj7j 3 жыл бұрын
የእመቤታችን ቅድስት ድንግልማሪያምልችጌታችን መድሀኒታችንየእየሱስ ክርስቶስ ስም ይክበር አሜን🙏
@user-rw1is9sr1o
@user-rw1is9sr1o 8 жыл бұрын
የቅድስ አባ ኤፍሬም በረከት ለሁላችንም ይደረብን
@fanosyegata947
@fanosyegata947 4 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን
@sjsjdkkskss6088
@sjsjdkkskss6088 3 жыл бұрын
📖📖📖
@user-sp5xi1jo1l
@user-sp5xi1jo1l 6 жыл бұрын
አቤቱ አምላክየ ሆይ ሃጥያታችን ይቅር በለኝ ለንሳሃ ሞት አብቃኝ።እንየማ ወየልን ቆሽሻሎህ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ለዘላለም ትኑር።ብሞትም እንካን ደስተኛ ነኝ
@metamenlerasnowmetamenlera6270
@metamenlerasnowmetamenlera6270 6 жыл бұрын
ቃለሂወት ያሰማልኝ የሁሉም ጻድቃናት በረከታቸዉ ይደርብኝ አሜን አሜን አሜን ፈጣሪ በሀይማኖታችኝ ያጽናኝ ተዋህዶ ኦርቶዶኩስ ለዘልአለም ትኑር
@user-pt7sn9lp5z
@user-pt7sn9lp5z 8 ай бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን አሜን አሜን አሜን💒🙏🌿🌾🕊🕊🕊💚💛❤🕊🕊🕊🤲
@user-bq7ml8dj1z
@user-bq7ml8dj1z 7 жыл бұрын
ቃል ህይወት ያስማልን አሜን አሜን አሜን♥♥♥♥
@birhanaaa5624
@birhanaaa5624 8 жыл бұрын
ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይውት ያስማልን
@obsinetalamayyo9716
@obsinetalamayyo9716 5 жыл бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን አሜን ለአባትችን ቃለ ህይወት ያሰማልን
@debesayshambel3806
@debesayshambel3806 7 жыл бұрын
ኣሜን ኣሜን ኣሜን
@Genet8983
@Genet8983 Жыл бұрын
እግዚአብሔር አምላክ ልቦናችንን ይክፈትልን የሠማነውን በልቦናችን ያሣድርብን የቅዱሳን በረከታቸው በውነት አይለየን በተሠጣቸው ቃልኪዳናቸው ይጠብቁን ይባርኩንም ሠላም ከኛ እርቋልና ሠላምን ይስጡን የቅዱስ ኤፍሬም በረከቱ አይለየን በተሠጠው ቃልኪዳኑ ይባርከን አሜን አሜን አሜን ክፍል 2 እንጠብቃለን
@user-vv7ol5tt8e
@user-vv7ol5tt8e 3 ай бұрын
አሜን //3//❤🙏🙏🙏
@yamaryamliji7476
@yamaryamliji7476 6 жыл бұрын
አሜን ቃለ ህይወት ያስማልን የቅዱስ ኤፍሬም በረከት ረዴኤት ምልጃ ፍቅሩ ይደርብን አሜን
@user-tn1jz5cw5d
@user-tn1jz5cw5d 6 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን እግዚአብሄር ይባርክህ ወድምችን ቃል ሄውት ያሰማን ቅዱስ ኤፍሬም ባለንበት ይጠብቀን አሜን፫
@dejenetamiru7544
@dejenetamiru7544 7 жыл бұрын
amen amen amen galanii fi ulfinii waqaayof haa taa'uu
@tigistigazahanyi299
@tigistigazahanyi299 4 жыл бұрын
Amen amen amen kale hiwote yasemaline tsegahune yabizalechuwe amen 😭👏👍
@Sarahsarah-xm6yo
@Sarahsarah-xm6yo 4 жыл бұрын
Amen kalhiwot yasemalin ya afrem berakat yedaribin Amen
@weltemaryameweltemaryame6875
@weltemaryameweltemaryame6875 6 жыл бұрын
ቃል ህይውት ያስማልን አሜን አሜን አሜን በረከት የድረብን
@mazseidmazseid4613
@mazseidmazseid4613 6 жыл бұрын
አሜን ቃለ ሂወት ያሰማልን
@user-lh6bx6od2v
@user-lh6bx6od2v 6 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የአገልግሎት ዘመናችሁ ያርዝምልን መንግስተ ሰማያት ያውርስልን የቅዱሳን በረከት ይደርብን አሜን፫
@user-so5ge3wn6y
@user-so5ge3wn6y Жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን በረከታቸው ይደርብን አሜን፫
@user-yl4wn8qx9q
@user-yl4wn8qx9q Жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ቃለ በረከትን ያሰማልን እግዚአብሔር ያገልግሎት ዘመናችህን ያረዝምልን የቅዱስ ኤፍሬም እረዴት በረከቱ ያደረብን አሜን አሜን አሜን
@user-pg5bl6iv5p
@user-pg5bl6iv5p 3 жыл бұрын
የቅዱስ ኤፍሬም ፆለት እና በረከት ምልጃውም አይለየን አሜን ፫ ጌታሆይ እኔ ባርያህ ሃጥያቴ በዝቶን እና ይቅር በለኝ አቤቱ እየሱስ ይቅር በለኝ ለልዑሎ እግዚያብሔር ክብር ምስጋና ይሁን አሜን ፫
@fuch9239
@fuch9239 Жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃል ሂወት ያሰማልን
@eteneshyoutub4873
@eteneshyoutub4873 6 жыл бұрын
ቃለህይወት ያሰማልን የአገልግልሎት ዘመናችሁን ያርዝም እግዚአብሄር አሜን አሜን
@trooktafara1336
@trooktafara1336 3 жыл бұрын
አሜን አሜን የቅዱሳን በረከት ይደርብን
@user-iu8wu6un8p
@user-iu8wu6un8p 6 жыл бұрын
ቃለ ህይወትን ያሰማልን ለሁሉም ለተሳተፉት ተርጉማችሁ ላቀረባችሁም የቅዱሳኑ ሁሉ በረከትና ጸሎት አይለየን
@idependongod8638
@idependongod8638 6 жыл бұрын
ኣሜን🙏🏼ኣሜን 🙏🏼ኣሜን የአባታችን የቅዱስ ኤፍሬም በረከት እረእዴታቸው ይደርብን🙏🏼🙏🏼
@asmaihet5675
@asmaihet5675 7 жыл бұрын
አሜን የቅዱስ ኤፋሬም በረከታችው ይደረብን
@user-dm8jh9ol2b
@user-dm8jh9ol2b 11 ай бұрын
የአባታችን ቅዱስ ኤፍሬም በረከቱ ና ፀሎቱ ከእኛ አይለየን ለዘላለሙ አሜን🙏🙏🙏💚💛❤️
@mohammedahamed7680
@mohammedahamed7680 7 жыл бұрын
ቃል ሂወት ያሰማልን የቅዱስ ኤፍሬም በረከት አይለየን አሜን አሜን አሜን
@tub9919
@tub9919 7 жыл бұрын
Amen kalehiyi wete yasemalni yabatachin yekdusi efireme bereket yasaderbn
@ypyb2027
@ypyb2027 6 жыл бұрын
እግዝዕብሔር ይባርክህ ወንድማችን የቅዱስ ኤፍሬም በረከት ይደርብን አሜን አሜን። አሜን
@starsphone5548
@starsphone5548 2 жыл бұрын
ameen qalhiyoot yasemaln yee qiduusan barakat radietuu yideribin yee abbatachiin qidus efreem soriyaa tsalotachuu yideribiin yee getachiin madanitachiin iyeesus kiristoos yiqirtana charinetuu ayilenyin ameen
@user-zf7hd1rd3o
@user-zf7hd1rd3o 6 жыл бұрын
አቤቱ ጌታ ሆይ ምን ይጀ ይሆን ከፊትህ የምቆመዉ ጨነቀኝ ፈራሁ ቅንጣት የምታህል እኳ መልካም ስራ የለኝም
@hannasalam672
@hannasalam672 Жыл бұрын
አባታችን ቅዱስ ኤፍሬም እረዴት በረከታቸው ፀሎታቸው አይለየን አሜን አሜን አሜን❤❤❤
@betiykalay6042
@betiykalay6042 7 жыл бұрын
Kale Hiwet yasemalen 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 ⛪ ⛪ amen ❤ ❤ ❤ ❤ ❤ ❤ ❤ ❤ ❤
@user-ot7pk1un4p
@user-ot7pk1un4p 2 ай бұрын
Egziabher yimesgen 💚💛❤🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@user-qz3os2mv4s
@user-qz3os2mv4s 8 жыл бұрын
AMEN AMEN AMEN ye aba efram tsnatu ena tegstu ysten kale hiwet yasemaln AMEN YE yeba berekt yderbn!!
@MrGetamesaye
@MrGetamesaye 4 жыл бұрын
A
@user-zm2du3hx5d
@user-zm2du3hx5d 7 жыл бұрын
አሜን ቃለህይወት ያሰማልን
@teamehaile9355
@teamehaile9355 4 жыл бұрын
Amen Amen Amen kal hiwet yesmalna
@mifatmohammed4095
@mifatmohammed4095 2 ай бұрын
ቃለህይወትያሰማልንአሜንአሜን
@gorefeneshhemecha8143
@gorefeneshhemecha8143 3 жыл бұрын
እግዚአብሔር ይመሰገን እናንተ የተሰጠ በረከት የደ ሰን
@user-li2me1go1s
@user-li2me1go1s 7 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን
@tesfaneshmazengiya5867
@tesfaneshmazengiya5867 6 жыл бұрын
ቃለሂውትን ያሰማልን! !
@tgstfantu7216
@tgstfantu7216 5 жыл бұрын
አቤቶ አምላኪ ሆይ እባክህን እርዳኝ ከዚች ከከቶ አለም ታደገኝ ወንጌልክን ለአለም እመስክር ዘንድ እባክህን ፍቀድልኝ የቅዱስ ኤፍሪም ፁሉት ልመና ይድርስልኝ
@user-sl2nr5jq5u
@user-sl2nr5jq5u Жыл бұрын
ኣሜን ፫ ቃል ህይወት ያሰማልን የቅዱስ የኤፍሬም በረከቱ ይደርብን
@user-ne1fd6gj7j
@user-ne1fd6gj7j 3 жыл бұрын
ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አስተዋይ ልብንይስጠን ጌታሆይ ክብር ምስጋና ለዘላለሙ ላንተይሁን አሜን🙏
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ - ክፍል 2 / St. Ephrem Syrian part-2
33:45
የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Рет қаралды 481 М.
የዓርብ ውዳሴ ማርያም - Wudase Mariam Friday
15:42
CHOCKY MILK.. 🤣 #shorts
00:20
Savage Vlogs
Рет қаралды 27 МЛН
哈莉奎因以为小丑不爱她了#joker #cosplay #Harriet Quinn
00:22
佐助与鸣人
Рет қаралды 10 МЛН
黑天使遇到什么了?#short #angel #clown
00:34
Super Beauty team
Рет қаралды 37 МЛН
የእመቤታችን ድንግል ማርያም  እረፍቷ፣ ትንሳኤዋና እርገቷ አጭር ትረካ
25:53
ብሰማርያ ኣቢሉ ኺሓልፍ ከኣ ግዲ ኾኖ ብዲ/ን ኣስመላሽ ገ/ሕይወት
56:45
የተፈተነ እምነት: የአብርሃም የሳራ የሎጥ ሙሉ ታሪክ
37:21
ከታሪክ ማህተም KETARIK MAHITEM
Рет қаралды 82 М.
መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit -  ዓርብ (መዝ 111-130)
34:42
ዜማ ተዋህዶ Zema Tewahdo
Рет қаралды 63 М.
ቅዱስ ሙሴ ፀሊም መንፈሳዊ ፊልም || saint moses black spritual full orthodox movie
1:53:53
Abba Heylemelekot yhays Tube አባ ኃይለ መለኮት ይኄይስ ቲዩብ
Рет қаралды 22 М.