Рет қаралды 195,016
ካለሽ አንቺ
ከፍቅር ጸበል ስንቴ አጠጣሽኝ
ከጥንካሬሽ ስንቴ አካፈልሽኝ
ተስፋ እንዳልቆርጥ ስንቴ አጠነከርሽኝ
ስበረታም አይዞህ አለሁ እያልሽኝ
እንዳልደክምብሽ ሁል ጊዜ ትፈልጊያለሽ
ያለሽን ጊዜ በሙላ እኔ ላይ ታጠፊዋለሽ
ካለሽ አንቺ ለኔ ካለሽ አንቺ ሚከብደኝም ይቀላል ያሰብኩትም ይቃናል
ግን ደግሞ አለሽ አንቺ ለኔ አለሽ አንቺ ብርታቴንም ጨምረሽ ድካሜንም አጥፍተሸ
ኦሆ ኦሆ ኦሆ አለሽ አንቺ
ኦሆ ኦሆ ኦሆ አለሽ አንቺ
አይኔ ላይ ልቤም ላይ ከልቤም ላይ አለሽ አንቺ
ሀሳቤም ላይ ቃሌም ላይ የማየውም ላይ አለሽ አንቺ
በደንብ እኔን ስላወቅሽኝ ነፃ ሰው አርገሽኛል
ለቤት ለፍቅራችን እንዴት እንምሆን አስተምረሽኛል
እንዳልደክምብሽ ሁል ጊዜ ትፈልጊያለሽ
ያለሽን ጊዜ በሙላ እኔ ላይ ታጠፊዋለሽ
ካለሽ አንቺ ለኔ ካለሽ አንቺ ሚከብደኝም ይቀላል ያሰብኩትም ይቃናል
ግን ደግሞ አለሽ አንቺ ለኔ አለሽ አንቺ ብርታቴንም ጨምረሽ ድካሜንም አጥፍተሽ
ሳቄም ላይ ደስታዬም ላይ ስኬቴም ላይ አለሽ አንቺ
ጭንቀቴም ላይ ሀዘኔም ላይ እምባዬም ላይ አለሽ አንቺ
የኔ ቆንጆ ባታውቀው ነው እንጂ አንተም ለኔም ያው ነህ
ቃል ያጥረኛል አንተን ምጠራበት ምን ብዬ ልግለፅህ
ካንተ ጋር ሁሌም መኖር ነው የኔም ፍላጎቴ
ሀዘኔም ላይ ደስታዬም ላይ ሳቄም ላይ አለህ
ሰው በምድር ላይ ሲኖር አጋር ይሻልእና
ለኔም አንችን ሰጠኝ ልመናዬን ሰምቷልና
ካለሽ አንቺ ለኔ ካለሽ አንቺ ሚከብደኝም ይቀላል ያሰብኩትም ይቃናል
ግን ደግሞ አለሽ አንቺ ለኔ አለሽ አንቺ ብርታቴንም ጨምረሽ ድካሜንም አጥፍተሽ
ፊውቸሪንግ ቤተል መንበሩ
ግጥምና ዜማ ሳሚ-ዳን
ቅንብር ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ኤንዲ ቤተ ዜማ