No video

"ተንጋላ የሞተች የመንታ እናት ጣር አየሁት" አያ ሙሌ Eyos /እዮስ

  Рет қаралды 111

EYOS

EYOS

Ай бұрын

የገጣሚ ሙሉጌታ ተስፋዬ የህይወት ውጣ ውረድ
የጅዝብና (hippie) ሕይወትየኖረ፣ ትንሽ ኮስታራ ሕይወትን በስሱ ያጣጣመ የአንድ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ቅንጭብ ታሪክ፡፡ ሰውየው በ1946 ወልዲያ ተወልዶ በ1996 ዓለም ገና ሕይወቱ አለፈች፡፡ ትንሽ ትንሽ የጋሽ ስብሐትን የሚመስል ሕይወት፣ ትንሽ ትንሽ የብአዴን ታጋዮችን የሚመስል ሕይወት፣ ብዙ ብዙ የጎዳና ሕይወት ኖሯል፡፡ ይህ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ወይም አያ ሙሌ ይባላል፡፡
የአያ ሙሌ ነገር ግራ ነው! ሕይወቱም ሲበዛ ዥንጉርጉር ናት፡፡
ለምሳሌ ተራ ገጣሚ ነው እንዳንል እጅግ ተወዳጆቹ ሙዚቃዎች የርሱ አሻራ ያረፈባቸው ኾነው እናገኛለን፡፡ ብኩን ሰው ነው እንዳንል በኢህአፓ እሳት ፖለቲካ ዉስጥ ተወልዶ፣ በማርክሲዝም ሌኒኒዝም ነዶ፣ በብአዴን በስሎ፣ በNGO ደመወዝ ከብሮ፣ በኢህአዴግ ላዕላይ ቤት ገብቶ፣ በጋዜጠኝነት ሠርቶ፣ ከመንግሥት አፓርታማ ተበርክቶለት የሴኮ ቱሬ ጎረቤት ኾኖ የኖረ ሰው ነው፡፡
ደግሞ ያን ሰምተን ለአንቱታ ስናዘጋጀው ድንገት ሥራውን ጥሎ ይጠፋል፡፡ ዘበኛ፣ ኩሊ፣ ወዛደር፣ ጎዳና ተዳዳሪ ይሆናል፡፡ ብቻ ያያ ሙሌ ነገር ለወሬም አይመች፡፡
ያኔ ኢህአዴጎች እንደገቡ ሰሞን (ለነገሩ እጃቸውን ይዞ አዲሳባ ካስገቧቸው ሰዎች ዉስጥ አንዱ እሱ ራሱ ነው) አንድ የከበረ ወዳጁ ወደ አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ክበብ ይዞት ይገባል፡፡ የአያ ሙሌን ቆሸሽ ማለት የተመለከተ ታጋይ ዋርዲያ ‹‹አታ…ተመለስ!›› ሲል ሙሌን በቁጣ ያስቆመዋል፡፡ “አይ…ከኔ ጋር ነው ነው፣ ችግር የለም” ብሎ ወዳጁ ከለላ ሰጥቶ ያስገባዋል፡፡ ሙሌ ወደ ወስጥ ከመግባቱ በፊት ግን አንድ ነገር ከነከነው፤ ተመልሶ ወደ ታጋዩ ዋርዲያ ጆሮ ጠጋ ብሎ ‹‹ትናንት በበረባሶ አርገህ ገብተህ ዛሬ በረባሶ ያረገ መናቅ ጀመርክ?›› ብሎት ገባ፣ በትግርኛ፡፡
ሙሌ ትግርኛ ብቻ ነው እንዴ ታዲያ አቀላጥፎ የሚናገር? ግዕዙስ፣ አፋርኛስ፣ ኦሮሚኛውስ፣ አረብኛና እንግሊዝኛወስ፣ ፈረንሳይኛውስ…በሁሉም ይቀኝባቸዋል፡፡ ትንሽ ልጅ እያለ እንደውም ‹‹ጋይድ›› ነበር፡፡ ሊስትሮም ነበር፡፡ ሊስትሮ እያለ የአንድ ደንበኛውን ካልሲ በቀለም ቡሩሽ አበላሽቶ እጅግ ጥብቅ ኩርኩም ቀምሷል፡፡ ያቺ ኩርኩም እስከዛሬም ታመኛለች ይል ነበር፣ በሕይወት ሳለ፡፡ ታዲያ ለመጀመርያ ጊዜ ኤን ጂ ኦ ተቀጥሮ ረብጣ ብር ያገኘ ለት በሲሶው ጠርሙስ ዉስኪ ገዝቶ ጫማ ይጠርግባት የነበረችው ቦታ ላይ ሄደና ዉስኪውን ሙሉ እዚያው አርከፈከፈው፡፡ ሙሌ በቀለኛ ሳይሆን አይቀርም፡፡
በቀለኛ ቢኾን ግን ሐብታም ኾኖ መኖር ነበረበት እኮ!
ደግሞ ማርክሲስት ብለነው ልናልፍ ስንል መጽሐፍ ቅዱስን ከፍ ባለ ደረጃ አጥንቷል፣ ከቤተክርሲያ ደጅ አይጠፋም፡፡ ዉሎ አዳሩም እዛው ነበር ይሉናል፣ የሚያውቁት፡፡ ታዲያ ቆራጥ ክርስቲያን ነበራ! ስንል ቁርዓንን 30 ጁዝ “ሀፍዟል* ይሉናል፡፡ እንዲያው ወሎ ዉስጥ ከቄሶችና ከሼካዎች እኩል ማውራት ይቻለዋል ብለው ይመሰክሩለታል፡፡ ብቻ የአያ ሙሌ ነገር ግራ ነው፡፡
በ1992 ለወጣው ፈርጥ መጽሔት ትንሽ ስለአስተዳደጉ ፍንጭ ሰጥቶ ነበር፣ ያን ዕለት ለጋዜጠኛ እንዲህ አለው…፡፡
“…ምንመሰለህ፣ እኔ ዲቃላ ነኝ፤ አባቴ ትግሬ ናቸው፤ እናቴ የዋድላ ደላንታ ሴት ናት፡፡ ወልዲያ ዉስጥ ሙጋድ የሚባል ቦታ እናቴ ከፊት ለፊት ጠላ ትሸጥ ነበር፡፡ አባቴ ደግሞ በጓሮ በኩል ጨው ይሸጣል፡፡ እናቴ ጠላውን እየሸጠች ታንጎራጉራለች፡፡ እንጉርጉሮዋ የኒህን ቄስ ቀልብ ጠለፈ፡፡ ቄሱ ሽማግሌ ቢልኩ አይሆንም ይባላሉ፡፡ እናቴና አባቴን የምታገናኝ አንዲት በር ነበረች፡፡ ቄሱ አይሆንም ሲባሉ በሯን ገንጥለው ገቡ፡፡ እኔ ተወለድኩ፡፡…”
ብጽአት ስዩም ‹‹አደራ ልጄን አደራ›› እያለች በእንባ የምታዜመውን ግጥም የጻፈላት ሙሌ ነው፡፡ ለአበበ ተካ ‹‹ወፊቱ››ን የጻፈለት ሙሌ ነው፡፡ ለሀና ሸንቁጤ፣ ለኩኩ ሰብስቤ እያልን ብንቀጥል ማቆምያ የለንም፡፡ ቆንጥሮ እየሰጠ አንበሽብሿቸዋል፤ ፍዝ ኾኖ አድምቋቸዋል፡፡ እነሱን የዝና ማማ ላይ ሰቅሎ እሱ እታች ወርዶ ይተኛል፡፡ ጎዳና፡፡
ሙሌ ድሮ ድሮ እንደ ኢህአፓም እንደ ብአዴን አድርጎት ነበር፡፡ ምን አድርጎት ነበር ብቻ! ቆራጥ ታጋይ ነበር እንጂ፡፡ በኢህአዴግ አምናለሁ ይል ነበር፣ አፍ አውጥቶ፡፡ ከተበላሹም አለቃቸውም እያለ ይዝት ነበር፡፡ እነ በረከት፣ እነ ታምራት ላይኔ፣ እነ ሕላዌ ዮሴፍ የሙሌ ግጥም ነፍሳቸው ነበር፡፡ ሙሌ የወልዲያ ልጅ ይሆን እነጂ አባቱ የትግራይ ሰው ናቸው፡፡ ለትግልና ለታጋዮች የቀረበውም ለዚሁ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የኢህዲን (ብአዴን) 20ኛ ዓመት ላይ ግጥም እንዲያቀርብ ተጋበዘ፡፡
በዚህ መጽሐፍ የተወሱ በርካታ ገጠመኞች ሙሉጌታ ተስፋዬን የሱፊ ፈላስፋ፣ የከተማ ባህታዊ አንዳንዴም ንግርት አዋቂ ያስመስሉታል፤ ሊኾንም ይችላል፡፡
አንድ ቀን ሙሌ አዲስ ጫማ ገዝቶ መንገድ ሲያቀና አንድ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ የኔ ቢጤ አይቶ ይጠራቸውና፣ “እስቲ ይሄን ይለኩት” ይላቸዋል፡፡ “የኔ ቢጤውም ልኬ ነው ይሆነኛል” ይሉታል፡፡ “በሉ ይሂዱ” ብሏቸው እርሱ በባዶ እግሩ መንገዱን ቀጠለ፡፡
አያሙሌ በየአድባሩ በየአገሩ በአብያተ ክርስቲያኑ ሁሉ እየዞረ እንደ ለማኞች ሆኖ ለምኖ የተሰጠውን መልሶ ለለማኞቹ ማደል ጀምሮ ነበር፡፡ እንዲያውም አንድ ጊዜ የአለቃ ተስፋዬ ልጅ ሚካኤል ሲለምን ታዬ ተብሎ ተወራበት፡፡ እሱ ግን ግድ አልነበረውም፡፡ “እብዶች” አያ ሙሌን ካዩ አይለቁትም፡፡ ይከተሉታል፤ ይወዱታል፡፡ በተሻለ ያወሩታል፡፡ ለምሳሌ ወልዲያ አባ ግርሻ የሚባሉ አንድም ሰው የማይቀርባቸው በአእመሮ መታወክ የሚሰቃዩ ሰው ነበሩ፡፡ ሙሌ ግን ጠጅ ቤት ወስዶ አብሯቸው ዉሎ ያድር ነበር፡፡ በሰላም፡፡
አንድቀን ደግሞ አንድ እንጨት የተሸከሙ ሰውዬን በመንገድ ያገኝና ‹‹እስካሁን አልሸጡትም?›› ይላቸዋል፡፡ ሰውየውን ለካ ሌላ መንገድ ላይ ሲዳክሩ ቀደም ብሎ አይቷቸው ነበር፡፡ “ገዥ አጣሁ ልጄ” አሉት፡፡ “ስንት ነው?” ይላቸዋል፡፡ ሁለት ብር መኾኑን ሲነግሩት አምስት ብር ሰጥቶ “በሉ ይጣሉትና ሄደው ይረፉ” ብሎ አሰናበታቸው፡፡
አያሙሌ በደህናው ጊዜ በቤተመንግሥት በከፍተኛ የመንግሥት ስብሰባዎች መዝጊያ ላይ ሁሉ ግጥሞችን ያቀርብ ነበር፡፡ ቦረና ድረስ ሄዶ የዋለልኝ መኮንን ታዋቂ ዘጋቢ ፊልም ለመጀመርያ ጊዜ የሠራውም እሱ ነበር፡፡ መንግሥታዊ መጽሔትና ጋዜጣ ላይ ሂሳዊ ጽሑፎችን እያቀረበ የተደላደለ ኑሮ ሲኖር ቆየ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ድንገት ከኢህአዴግ ሰዎች ራቀ፡፡ ሽጉጡን አስረክቦ፣ መንግሥት የሰጠውን ቤት ጥሎ ጎዳና ወጣ፡፡ ላይመለስ፡፡
የኾነቀን ግን ወዳጆቹ ፈልገው አፈላልገው ደመወዙን ይዘውለት መጡ፡፡ ያልሠራሁበትን አልበላም ብሎ ሳይቀበል ቀረ፡፡ ሕይወቱንም በኬሻ በጠረባ አደረገ፡፡ አንድ ጊዜ ደግሞ የኾነ መልዕክተኛ ታምራት ላይኔ በጥብቅ እንደሚፈልገውና እርሱም ሊያደርሰው እንደመጣ ይነግረዋል፡፡ አያ ሙሌ አጭር መልስ ሰጠ ‹‹ አመሰግናለሁ፤ መንገዴን ለይቻለሁ!››
በሌላጊዜ ደግሞ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የነበረው በረከት ስምኦን አያ ሙሌ ያለበት ድረስ ደፍሮ በመምጣት በግል አናግሮት ነበር፡፡ ‹‹እንዲህ ለመሆን ነው ሥራህን የተውከው? በል ወደ ሥራህ ተመለስ፣ ቢያንስ ጥለኻት የመጣሃትን የ11 ዓመት ሕጻን ልጅህ አታሳዝንህም?›› ይለዋል፡፡ አያ ሙሌ ቱግ ብሎ ምላሽ ሰጠ፡፡ “የኔ ልጅ ሕጻን አይደለችም፣ አንተን በአንድ ዓመት ትበልጠሀለች፡፡”
የአያሙሌ ወዳጆችና የነፍስ ልጆች
በርከትያሉ አድናቂዎችና የነፍስ ልጆች ነበሩት፡፡ ብዙዎቹ የጎዳና ልጆች ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ የጥበብ ወዳጆች፡፡
አንድ ጊዜ ደግሞ አሜሪካን ግቢ ከመንፈስ ልጁ ጋር በችግር ጎዳና ላይ ሳለ ሙሌ ድንገት ከጎዳናው እምር ብሎ ተነስቶ አንድ ሙስሊም ሰውዬን በአረብኛ ያናግራቸውና ተመልሶ ጎዳናው ላይ ቁጭ ይላል፡፡ ሰውየው ቆየት ብለው የታሰረ ረብጣ ብር በሾፌራቸው ይልኩለታል፡፡ ሙሌም ‹‹መልስላቸው፣ እኔ ለማኝ አይደለሁም ›› ሲል ብሩን ሳይቀበል ቀርቷል፡፡
አያ ሙሌ ከአፍቅሮተ ነዋይ የራቀ የከተማ መናኝ ነበር፡፡ መታወቂያ፣ ስልክ፣ እድር፣ የመኖርያ ቤትም ሆነ ቋሚ አድራሻ አልነበረውም፡፡ ወገን ዘመድ የሚለው ሰውም እንዲሁ፡፡ የሚኖረውም በእምነት ነው ‹‹እንደ ወፊቱ ልዋል›› ይል ነበር፣ አዘውትሮ፡፡ ከሥራዎቹ ሁሉ የአበበ ተካን ወፊቱን አብልጦ የሚወደው ለዚሁ ይሆን?
#ethiopia #amharic #ethiopianentertainment
#ግጥም

Пікірлер: 14
ОБЯЗАТЕЛЬНО СОВЕРШАЙТЕ ДОБРО!❤❤❤
00:45
SPILLED CHOCKY MILK PRANK ON BROTHER 😂 #shorts
00:12
Savage Vlogs
Рет қаралды 44 МЛН
Smart Sigma Kid #funny #sigma #comedy
00:40
CRAZY GREAPA
Рет қаралды 37 МЛН
Girum Tereka - ግሩም ትረካ - የሙላ ናስሩዲን ቀልዶች - በግሩም ተበጀ Girum Tebeje Tereka
39:07
ግሩም ትረካ - በግሩም ተበጀ (Girum Tereka - By Girum Tebeje
Рет қаралды 21 М.
ጥቅስታት ኣልበርት-ኣንስታይን
7:43
yumun-tube
Рет қаралды 53
ትረካ ፡ አፍ - አዳም ረታ - Amharic Audiobook - Ethiopia 2024
42:04
ትረካ - Tireka Tube
Рет қаралды 9 М.
አስደንጋጮቹ ፍጥረታት
30:01
Elda Media / ኤልዳ ሚዲያ
Рет қаралды 81 М.