ወንጌላዊ ደረጀ ከበደ/ Evangelist Dereje Kebede/ Apostolic Church of Ethiopia

  Рет қаралды 12,582

Iso Yisehak Ab

Iso Yisehak Ab

2 жыл бұрын

ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 02/2013 ድረስ በሐዋሳ እናት አጥቢያ በተዘጋጀው ዓመታዊ የአባቶች ጉባዔ ላይ "ንጉሡንና ጽዮንን እያየህ ኑር እያየህ ሙት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ደረጀ ከበደ የቀረበ መደመጥ ያለበት መልዕክት
ኢሳ 33:17:-... ጽዮንን ተመልከት...ዓይኖችህ ኢየሩሳሌምን ያያሉ።
ዕብ 11:13:-... የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ...
#ንጉሱንና_ጽዮንን(ኢየሩሳሌምን)_እያየህ_ኑር_እያየህ_ሙት።
- ገሃነምን የምናሸንፍበት ብቸኛው መንገድ ንጉሡንና ጽዮንን ማየት ነው።
ራዕ 21:1:-...አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባልዋ እንደተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሠማይ ስትወርድ አየሁ።...
ራዕ 17:1
- የጋለሞታዋ መንፈስ ዓለምን ተቆጣጥሮ ነው ያለው። የምድር ርኩሰት እናት ነች።
- ሁለት የሚታዩ ነገሮች አሉ 👇👇
👉1. አንድ የሚገለጥ ንጉሥና አገር አለ
👉2. እዚሁ እያጓጓች ልታስቀር የምትጥር የምድር ርኩሰት ንግሥት አለች
- አባቶቻችን ሲገረፉም፣ ሲደበደቡም፣ በመጋዝ ሲሰነጠቁም ዓይናቸው ያይ የነበረው ንጉሡንና አገራቸውን ነበር።
- ጽዮንን አሁን የሚያያት ነው የሚወርሳት።
- እግዚአብሔር አምላካችን ተብሎ ሊጠራ የማያፍርብን የምድርን ርኩሰት ንቀን ዓይናችንን ወደ እርሱ ስናነሳ ብቻ ነው።
- የምድር ርኩሰት ንግሥት የሰውን ልጅ በምቾት፣ ጊዜ በማሳጣት፣ አንዳንዴም በጥልቅ ድህነት ንጉሡን እንዳናይና እንድንረሳው ታደርጋለች።
** ንጉሡንና ጽዮንን እያየህ ኑር እያየህ ሙት **
- ኢዮብ ሚስቱንም ሰይጣንንም ያሸነፈበት ሚስጥር ንጉሡን ብቻ ያይ ስለነበር ነው።
(ኢዮብ 19:25
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፥
²⁶ ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ።
²⁷ እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼም ይመለከቱታል፥ ከእኔም ሌላ አይደለም። ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል።)
- ኢዮብ በተስፋ የሚቤዠኝን አየዋለሁ አለ፤ እኛ ግን የተቤዠንን እናየዋለን።
- የምድር እናት ምድርን በሶስት ነገር ተቆጣጥራዋለች👇👇👇
👉1. በርኩሰት:- የወንድ ለወንድ እና የሴት ለሴት ጋብቻን በምድር በማሰራጨት።
- የጋለሞታን መንፈስ (አንድ ባል የሌላት) በምድር ላይ በመልቀቅ አማልክቶችን አብዝታለች።
- ከእግዚአብሔር ይልቅ በእኛ ላይ የሚሰለጥን ዕውቀት፣ ሀብት፣ ሰው፣ ክፉ ቴክኖሎጂ ሌላም ነገር በሙሉ አማልክት ነው።
👉2. በስካር:- የሰዉን ሕይወት በሙሉ በሚያጓጓ እና በሚያሰክር (ገንዘብን በመውደድ፣ በኑሮ ውድነት፣ በበሽታ...) ነገር ታመሰቃቅላለች።
- ሰካራም ጉዱን የሚያውቀው ሲነጋበት ነው።
ራእይ 18:1:-...
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² በብርቱም ድምፅ፦ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤
… ...
⁴ ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤
⁵ ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና፥ እግዚአብሔርም ዓመፃዋን አሰበ።
- ጽዮንን አለማየትና አለመጠበቅ ሲነጋ ዋይታ ነው።
- እግዚአብሔር ከወደደኝ እርሱንና መንግሥቱን ያሳየኝ።
- ሰይጣን የሚያሳየን ብዙ ነው አጥርተን/ለይተን ማየት የእኛ ድርሻ ነው።
- አሁን የምንኖረው ሕይወት ነው መጨረሻችንን የሚያሳውቀን። አሁን የምናየውን ነው ኋላ የምናገኘው።
ራእይ 22:12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።

¹⁷ መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ ና ይላሉ። የሚሰማም፦ ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።
- የእኛ መንፈስ ና ይላል ወይስ???
- ሰማይን የሚያይ ሰማይ ይሄዳል ምድርን የሚያይ ምድር ይቀራል።
*****
ዓይኖቼን ከሚታየው ነገር አንስቼ
በሰጠኸኝ ተስፋ በእምነቴ በርትቼ
ደመናና ንፋሱን መጠበቄን ትቼ
ግራ ቀኜን ሳልል ወደአንተ አቅንቼ
አንተን ብቻ እያየሁ በትዕግስት ኖራለሁ
አንተን ብቻ እያየሁ እጠብቅሃለሁ
አንተን ብቻ እያየሁ ተስፋ አደርግሃለሁ
አንተን ብቻ እያየሁ በእምነት ኖራለሁ
ቢጎድል ባይጎድል እኔ አላማርርም
ዘገየብኝ ብዬ አላጉረመርምም
ነገሬን በጊዜው ውብ ታደርገዋለህ
በትዕግሥት ልጠብቅ አምላኬ ታማኝ ነህ
ለእኔ ታማኝ ነህ አንተ |3x
ለእኔ መልካም ነህ አንተ |3x
ለእኔ በቂ ነህ አንተ |3x
*****

Пікірлер: 77
@Fares-zz4pn
@Fares-zz4pn
የኔ አበት ወንጌለዊ ደረጄ ከበደ ጌታ ኢየሱስ በብዙ በረከትና በብዙ ጸጋ እየበረካ ይበርኮት በረዢም እድሜም ጭምር የሱስ ይበርኮት ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@ayalewbelete1450
@ayalewbelete1450
የእግዚአብሔር ባሪያ ሰይፈ እጅግ ,መንገዴን አደራ የሚል ርዕስ
@Fares-zz4pn
@Fares-zz4pn
አሜን ጌታ እየሱስ አንቴን ንጉስ የሆንከውን እያያሁኝ ጽሆኖወን እተመለከት ከዝህ ከእርኩሰት እንደመልጥ እርደኝ የሱስ ስትገለጥ በክብር አንቴን ለመያት አብቃን 😢
@user-ku8xs7uw8i
@user-ku8xs7uw8i
ንፋስ ጽዮንን እያየሽ ኑር ጽዮንን እያየሽ ሙቺ አሜን አሜን አሜን አሜን 🙇🙇😭😭🤲🤲🙏🙏
@saradebaba5682
@saradebaba5682
አሜን አሜን ሃደራ ኢየሱስ🙏🙏🙌🙌😭😭❤❤🙌🙌
@almaztamirat8331
@almaztamirat8331 2 жыл бұрын
አሳየኝ የኢየሩሣሌም ራዕይ 😢😢😢😢😢AMEN 💜
@Dutamoergicho
@Dutamoergicho 14 күн бұрын
amen amen🙌
@asnakechfitamo3080
@asnakechfitamo3080
Eysuse yemsgne amne amne❤❤❤❤❤❤
@leletayely6102
@leletayely6102 Жыл бұрын
Geta iysus ybarekh wendm Drege ❤❤❤❤❤
@user-vf9lp5zo2p
@user-vf9lp5zo2p 2 жыл бұрын
በእዉነት ዘበኖት ይለምልም የኛ ዉድ አባት ጸጋዉን ያብዛሎት የማይጠገብ ትምርት በእዉነት አስተላልፈዋል ኢየሱስ ይመስገን ክብር ሁሉ ባርያዎቹን የሳት ንብልባል አድርጎ ለኛ የሰጠ አምላክ ይመስገን ኡፍፍፍፍፍ ኢየሱስ ይመስገን የማይጠገብ አምላክ 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭❤️❤️❤️❤️🙏🙏🙏🙏
@apostolic5964
@apostolic5964
ይርዳን አሙላክ ሃደራ 😭😭🙏🙏🙏
@liliabeje4683
@liliabeje4683 2 жыл бұрын
ameeeen ameeeen tesfa alegn
@marymayrit3421
@marymayrit3421
Ameen ameen 🤲🤲🤲🤲🤲🙏🙏🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️❤️
@alain870
@alain870 2 жыл бұрын
Amen amen geta eyesus
@eyakidane2933
@eyakidane2933
Abatachin sile enante yesus yibarrk
@AsterAster-js5gt
@AsterAster-js5gt
kawodadikagni.tsihoninaa.iyesusini.Asayagni.oh......AMEN Aniteni.bichaa.iyayahu.batigisiti.noralew❤❤Eg/r.Abizito.yibarikotii.
@desuaposto4842
@desuaposto4842 2 жыл бұрын
አቤቱ ፅዮንና ንጉሡዋን እያየው እንድኖር እርዳኝ ከዝህ ከዓለም እርኩሰት ጠብቀኝ አደራ😭😭😭😭😭😭
@user-up9fk3yk1h
@user-up9fk3yk1h
አሜን አሜን አሜን አሜን ❤️❤️❤️❤️
@leletayely6102
@leletayely6102 Жыл бұрын
🙏🙏🙏🙏Jesus 🙏🙏🙏🙏❤❤❤❤❤❤❤❤🌸🌸🙏🙏🙏🙏🙏🙏haleluja haleluja haleluja haleluja haleluja haleluja haleluja
@arabtowers9123
@arabtowers9123
አሜን አሜን አሜን አሜን ሃሌሉያ ሃሌሉያ 😭😭😭😭❤❤❤❤
Stay on your way 🛤️✨
00:34
A4
Рет қаралды 26 МЛН
Playing hide and seek with my dog 🐶
00:25
Zach King
Рет қаралды 37 МЛН
ያመንከውን ከማን ሰማኸው? |Evangelist Solomon Kebede|ወንጌላዊ ሰለሞን ከበደ|
1:24:17
የዘመን ሙሊት  የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ከቄስ ሰይፉ እጅጉ #apostolic churchof salem Mezmur festival
33:44
sol tube የሆሳዕና ሐዋርያዊት ቤተ-ክርስትያን
Рет қаралды 6 М.
እመኑ ይሆንላችሁማል|ቢሾፕ ደጉ ከበደ| #apostolic_church_of_ethiopia #apostolicsong
57:33
Stay on your way 🛤️✨
00:34
A4
Рет қаралды 26 МЛН