Z Yegerem Anger Gutin Oromifa

  Рет қаралды 157

 ዘ-ይገርም

ዘ-ይገርም

21 күн бұрын

አብርሃም(ኢትዮጵያዊ ወዳጆቹ እንደሚጠሩት) ወይም ብራም ሄይቦር (Bram Heijboer ) በከዛሬ 50 ዓመታት በፊት የአንገር ጉትንን የሰፈራ ፕሮጀክት ከመሠረቱት መሃል የመጀመሪያው ሰው ነበር። የአውሮፓን ኑሮ ትቶ ከወንድሞቹ ጋር ለኑሮ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ በርካታ መሠናክሎችን አልፎ በአንገር ጉትንና በአካባቢው የነበሩ የመሬት አልባ አርሶ-አደር ዜጎችን ህይወት ለመቀየርና ለራሳቸው ለቤተሠባቸው እንዲሁም ለሃገራቸው እንዲተርፉ በመርዳት የወጣትነት ህይወቱን አሳልፏል። መሬት አልባ አርሶ-አደሮች መሬት አግኝተው የተሻሻለ የግብርና ስራዎችንን ሰርተው የተሻለ የምርት ገበያ የሚያገኙበትን ስራ ደርግ ፕሮጀክቱን አስኪወርሰው ድረስ ከፊት ሆኖ መርቷል። የደርግ ወደስልጣን መምጣት ፕሮጀችቱን ለመቀጠል የማያስችሉ በአስቸጋሪ ሁኔታዎችን በመፍጠሩ ኢትዮጵያን ለቆ ቢሄድም ልቡ ግን አንገር ጉትን ቀርቶ ነበር። :
አብርሃም ከማለፉ ሶስት ወይ አራት ሰምንታት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ለሁለት ሰዓት ያህል ተገናኝተን አውርተን ነበር። በጊዜው እያደረገ የነበረው ጉዞ የመጨረሻው ጉዞ እንደሆነና መስከረም ላይ ኢትዮጵያ አንገር ጉትን መሄድ እንደሚፈልግ ነገረኝ። ምንም እንኳን ከኢትዮጵያ የሄደው ከ50 ዓመታት በፊት ቢሆንም በንቃት ስለኢትዮጵያ ይከታተል ነበር። በወሬያችን መሃል አሁን በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ በተለይ ደግሞ ስለ የብሔር መካረረር አንስተን አወራን። አንገር ጉትንና አካባቢው አሁን ሰው በብሔሩ ከሚፈናቀልባቸው ቦታዎች አንዱ ከመሆኑ አንፃር እሱ በነበረበት ጊዜ ምን ይመስል እንደነበር ጠየኩት።
ቃል በቃል ባይሆንም እንዲህ አለኝ ...
"እኔ በነበርኩበት ጊዜ እንዲህ እንዳሁኑ የብሔር መካረር አልነበረም። በጊዜው በአካባቢው የኦሮሞ ተወጆች ስለነበሩ አብዛኛው በፕሮጀክቱ ውስጥ አንገርር ጉትን ላይ ያሰፈርናቸው አርሶ አደሮች ከዚህ ብሔር የመጡ ነበሩ። ነገር ግን በተለያየ ስራ ምክንያት የመጡ የሌሎች ብሔር ተወላጆች በሰፈራ ፕሮጀክቱ ለመሳተፈፍ በጠየቁ ጊዜ ጥያቄውን ይዘን የአካባቢውን ሽማግሌዎች አናገርን። ሽማግሌዎቹም 'እንዴ እነዚህ ይስፈሩ የተባሉ ከሌላ ቦታ የመጡ ሰዎች እንደኛ ሰዎች አይደሉም እንዴ? ሰርተው ራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ከቀየሩ ምን አለበት' አሉን። አሁን ያለው አስተሳሰብ ከየት እንደመጣ አላውቅም።" አለኝ::
ሌላው ስለ አንገር-ጉትን በመፅሃፉ ውስጥ የተጠቀሰው ደግሞ ሃይማኖትን በተመለከተ የነበረው ሁኔታ ነው። አብርሃም የላዛሪስት ሚሽንን በቅስና ያገለገለና በጊዜው የላዛሪስት ሚሽንን ወክሎ የሚንቀሳቀስ ቢሆንም ቢሆንም፣ የሰፈራ ፕሮጀችቱን በሚያስተዳድርበት ጊዜ ሠፈራው ላይ ያሉ አርሶ-አደሮች የየመረጡትን ይሃይማኖት ተቋም በሰፈራ ፕሮጀኩ አካባቢ ላይ እንዲመሰርቱ ማበረታታቱ ነበር። ይህ ለኔ ከአስገረመኝና 'የሰው ልጅን ህይወት ማስተካከል' ከሚል አላማ ውጪ ሌላ ምንም ሌላ አላማ እንዳልነበረው እንድረዳ ያደረገኝ ታሪክ ነው። በጊዜው በቦታው ያቋቋሟቸው የተለያዩ የእምነት ተቋማት እስከ አሁን ድረስም ህዝብ እያገለገሉ እንደሆነ ሲረዳ በጣም ተደስቶ ነበር።
አብርሃም በጊዜው አንድ እንዳረግለት የጠየቀኝ ነገር ቢኖር ስለ አንገር ጉትን በአማርኛ የተሰራውን የዩቲቡብ ቪዲዮ በኦሮሚኛም እንዲተርጎም ነበር። በኦሮሚኛ ማንበብ ለሚፈልግ ሊንኩን ከታጭ አስቀምጬዋለሁ። ለኦሮሚኛ ትርጉም እና ትረካ ወዳጄ ሽመልስ ጥላሁንን ከልብ አመሰግናለሁ።
በስተመጨረሻም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጎረቤቴ የሆኑት የአብርሃምን እህትን ለቅሶ ልንደርስ ከቤተሠቤ ጋር ቤታቸው ሄድን። ስለ አብርሃም የመጨረሻ ሰዓቶች ከነገሩን በኋላ የመጨረሻ ኑዛዜውንም በተጨማሪ ነገሩን። በኑዛዜውና በሚከተለው እምነት መሠረት በተፈጽመው ስርዓት አስክሬኑ ተቃጥሎ አመዱ ለሶስት ተከፍሎ ወደ ወላጆቹ ሃገር ማለትም ፈረንሳይ፣ ወደሚኖርባት የኤንዶኔዢያ ከተማ እና ወደ እትዮጵያ አንገር ጉትን እንዲላክ በማለት ተናዞ ነበር። ነገር ግን በእምነቱ መሰረት ይህ ስለማይፈቀድ ቤተሰቡ ከሶስቱ አንዱን ቦታ እንዲመረጥ በወሰኑት መሰረት ለልቡ ቀርብ ወደሆነችው አንገር-ጉትን ቅሪቱ እንዲላክ ወሰነው ነበር። አሁን በሃገራችን ባለው የደህንነት ሁኔት ለጊዜው ይህ የሚፈጸም አይሆንም።
ሰዎች ህይወት በተለያየ መልኩ ይኖራሉ። አንዳንዶች የግል ህይወታቸውን ብቻ ኖረው ያልፋሉ። ሌሎች ደግሞ ህይወታቸውን የሌሎችን ህይወት በማስተካከል ላይ ተሰጥተው ኖረው ይልፋሉ። ሁሉም ዓይነት የህይወት ምርጫ የሰውን ልጅ እስካልጎዳ ድረስ ስህተት ነው ብዬ አላምንም። ነገር ግን ሌሎች ህይውታቸውን እንዲለውጡና ለራሳቸውም ሆነ ለሃገራቸው ብሎም ለአለም እንዲተርፉ የሚያግዙ ሰዎች የተለዩ ናቸው ብዬ አስባለሁ። አቶ አብርሃም (Bram Highbour) በዚህ መልኩ ህይወቱን ኖሮ አልፏል። ነፍሱ በለላም ትረፍ።
የእንግሊዘኛ፣ እንዲሁም የአማርኛና ኦሮሚኛ ትርጉም መጽሃፉን በዚህ መስፈንጠሪያ ያገኙታል
www.theangar-gutinsettlement1...

Пікірлер
Iron Chin ✅ Isaih made this look too easy
00:13
Power Slap
Рет қаралды 35 МЛН
Red❤️+Green💚=
00:38
ISSEI / いっせい
Рет қаралды 80 МЛН
Looks realistic #tiktok
00:22
Анастасия Тарасова
Рет қаралды 105 МЛН
እንደማይወዳት ነገራት ለሚዲያ ብቻ ነው የፈለኩሽ አላት
16:44
Eyobel tube-እዮቤል ቲዩብ
Рет қаралды 16 М.
ዮአዳን (ክፍል 16)
38:07
ለዛ
Рет қаралды 233 М.
ዘ-ይገርም  - የ1904ቱ ኦሎምፒክ ማራቶን ታሪክ
13:53
My wife said she wants to show me her true skills
0:27
昕昕一家人
Рет қаралды 43 МЛН
Это ежегодное настроение 😉 #tiktok #юмор #жиза #funny
0:10
Ангелина и Тая
Рет қаралды 4,9 МЛН
ToRung short film: the robber pretended to be a statue😬
0:30
The thieves pulled a prank on the Policeman ! 😬👮🤣
0:38
BOGDANCHIKI
Рет қаралды 10 МЛН
La emociones de Bluey #歌ってみた #bluey #burrikiki
0:13
Bluey y BurriKiKi
Рет қаралды 27 МЛН