Рет қаралды 12,072
ሰብስክራይብና ሼር በማድረግ የዳዕዋ ስራችንን ይደግፉ።
፟---
በዚህ ቪድዮ የተለያዩ ቁርአናዊ እና ሐዲሳዊ ማስረጃዎችና የዘመኑ ዑለሞች ፈትዋዎች ተካተዋል። ሙሉ ቪድዮውን በመከታተል ተጠቃሚ ይሁኑ። ቪድዮዉንም ለሌሎች ሼር ያድርጉ።
---
የርስዎ ሼር ማድረግ ለዳዕዋው ስፋትና ተደራሽነት ትልቅ ሚና አለውና ሼር ማድረግ አትሰስቱ። አላህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን።
---
አልኮረሚ / Alkoremi
ይከታተሉን || follow us:
ዩትዩብ || bit.ly/32DX97o
ፌስቡክ || alkoremi
===
በፅሁፍ እንደሚከተለው ቀርቧል።
===
«ጫት መቃም»
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
2፥219 *"አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው"*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ
"ጫት"Catha edulis" አእምሮን የሚያመረቅን እና በጤና፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ ሕይወት ላይ እክል ከሚያጋጥሙ እና አሉታዊ የጎንዮሽ ተፅእኖ"negative side effect" ከሚያሳድሩ ነገሮች መካከል እንደሆነ የመስኩ ምሁራን ያትታሉ፥ በኢሥላም ጫት ከኸምር ይመደባል። “ኸምር” خَمْرየሚለው ቃል "ኸመረ" خَمَرَ ማለትም "ሸፈነ" "ደበቀ" "ሰወረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን አእምሮን "የሚሸፍን" "የሚደብቅ" "የሚሰውር" ማለት ነው፥ የሒጃብ አይነት ከሆኑት መካለል "ጉፍታ" እራሱ በቁርኣን “ኺማር” خِمَار ይባላል፦
24፥31 *ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ*፡፡ وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ
"ጉፍታዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል “ኹሙር” خُمُر ሲሆን በነጠላ ደግሞ “ኺማር” خِمَار ነው፥ “ኺማር” خِمَار የሚለው ቃል ልክ እንደ “ኸምር” خَمْر ሥርወ-ቃሉ "ኸመረ" خَمَرَ ነው። ጉፍታ ራስን ስለሚሸፍን “ኺማር” خِمَار እንሚባል ሁሉ አእምሮን የሚቃወም ማንኛውም ነገር “ኸምር” خَمْر ይባላል፥ አስካሪ መጠጥ"alcohol" ሆነ "አደንዛዥ ዕፅ"drug" አእምሮን የሚሸፍን ሰለሆነ ኸምር ነው፦
2፥219 *"አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው"*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ
ቁማር መሠረቱ ገንዘብ ነው፥ ገንዘብ ለሰዎች ጥቅም አለው። አልክሆል ሆነ ድራግ በህክምና አገልግሎት ለሰዎች ጥቅም አለው። ነገር ግን ኸምር ሆነ ቁማር ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ስለሆነ ታላቅ ኃጢኣት አለባቸው። አልክሆል ውስጥ የሚካተቱት ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄ፣ ውስኪ፣ ቮድካ ወዘተ.. ሲሆኑ ድራግ ውስጥ የሚካተቱት ደግሞ ሲጋራ፣ ቶባኮ፣ ሲሻ፣ ጫት፣ ኮኬይን፣ ማሪዋና፣ ናርኮት፣ ሄሮይን ወዘተ ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 14
ኢብኑ ዑመር"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ዑመር በአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" አትሮንስ ላይ ኹጥባህ ሲያደርግ እንዲህ አለ፦ *"ኸምር ሐራም መሆኑ የሚናገረው የወረደው ከአምስት ነገር ማለትም ከወይን፣ ከተምር፣ ከስንዴ፣ ከገብስ እና ከማር ስለሚዘጋጁት ኸምር ናቸው። ዐቅልን የሚሰውር ሁሉ ኸምር ነው"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ خَطَبَ عُمَرُ عَلَى مِنْبَرِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ إِنَّهُ قَدْ نَزَلَ تَحْرِيمُ الْخَمْرِ، وَهْىَ مِنْ خَمْسَةِ أَشْيَاءَ الْعِنَبِ وَالتَّمْرِ وَالْحِنْطَةِ وَالشَّعِيرِ وَالْعَسَلِ، وَالْخَمْرُ مَا خَامَرَ الْعَقْلَ
እዚህ ሐዲስ ላይ "የሚሰውር" ለሚለው የገባው ቃል "ኻመረ" خَامَرَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄ፣ ውስኪ፣ ቮድካ የሚል ስለሌለ መጠጣቱ ይፈቀዳል እንደማንል እና ቂያሥ በማድረግ ሐራም ነው እንደምንል ሁሉ ሲጋራ፣ ቶባኮ፣ ሲሻ፣ ጫት፣ ኮኬይን፣ ማሪዋና፣ ናርኮት፣ ሄሮይን የሚል ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ስለሌለ ሐላል ነው አንልም፥ እንዲሁ ቂያሥ በማድረግ ሐራም ነው እንላለን። “ቂያሥ” قِيَاس የሚለው ቃል “ቃሠ” قَاسَ ማለትም “አመጣጠነ” “አመዛዘነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመጣጠን” “ማመዛዘን” ማለት ነው። በሸሪዓህ ቂያሥ ከሚደረጉት እሳቦት አንዱ ኸምር ነው፥ አስካሪ መጠጥ ሆነ አደንዛዥ ዕፅ አእምሮን የሚያነቃቃ እና የሚያደነዝዝ እስከሆነ ድረስ ሙሥኪር ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 36, ሐዲስ 95
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ"፦ "ሙሥኪር ሁሉ ኸምር ነው፥ ኸምር ሁሉ ሐራም ነው" ሲሉ እንጂ ሌላ ዐላውቅም"። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ وَلاَ أَعْلَمُهُ إِلاَّ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " كُلُّ مُسْكِرٍ خَمْرٌ وَكُلُّ خَمْرٍ حَرَامٌ "
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 3514
ሙዓዊያህ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቼ ነበር፦ *"ሙሥኪር ሁሉ ለሁሉም ምእመናን ሐራም ነው"*። سَمِعْتُ مُعَاوِيَةَ، يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ " كُلُّ مُسْكِرٍ حَرَامٌ عَلَى كُلِّ مُؤْمِنٍ "
"ሙሥኪር" مُسْكِر የሚለው ቃል "ሠኪረ" سَكِرَ
ማለትም "ደነዘዘ" "ሰከረ" "ነፈዘ" "መረቀነ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሚያደነዝዝ" "የሚያሰክር" "የሚያነፍዝ" "የሚያመረቅን" ማለት ነው። "ሠከር" سَكَر እራሱ "አደንዛዥ" "አነፋዥ" "አመርቃኝ" "አስካሪ"intoxicant" ማለት ሲሆን "ሡክር" سُكْر ደግሞ "አደንዛዥነት" "አነፋዥነት" "አመርቃኝነት" "አስካሪነት"intoxication" ማለት ነው። የዘመናችን ስመ-ጥርና አንጋፋ ምሁራን ጫት"Catha edulis" ሐራም እንደሆነ ፈትዋ ሰተዋል። ለምሳሌ ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ኢብኑ ባዛ ስለ ጫት እና ሲጋራ ተጠይቀው፦ *"ጫት እና ሲጋራ ሐራም መሆናቸው ምንም ጥርጥር የለውም፥ የጫትን ሐራምነት አስመልክቶ ዑለሞች በርካታ ኪታቦችን ከትበዋል፡፡ ከእነሱም መካከል የቀድሞው የአሥ-ሠዑዲ ዐረቢያህ ሙፍቲ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል-ሸይኽ"ረሒመሁሏህ" አንዱ ናቸው። በጥቅሉ ሙሥሊሞች ጫትና ሲጋራን ሊተዋቸው እና ሊጠነቀቋቸው ይገባል፥ ጫትና ሲጋራን ማንኛውም ሙሥሊም የመተው ግዴታ አለበት። ጫትና ሲጋራን መግዛትም ሆነ መሸጥ እናም በእነርሱ መነገድ አይቻልም፥ ሐራም ነው፡፡ የጫትና ሲጋራ ገንዘብ ሐራም ናቸው፥ ሙሥሊሞችን ከእነዚህ ነገሮች አላህ ያርቃቸው ዘንድ እንማፀነዋለን" ብለዋል።
ሸይኽ ሷሊሕ አል-ፈውዛን"ሃፊዘሁሏህ" ስለ ጫት ተጠይቀው፦ *"ጫት ሐራም ነው፥ ጫት ከሲጋራ የበለጠ ጉዳት አለው፡፡ እርሱ(ጫት) ሐራም ነው" ብለዋል።
ምንጭ አል-ፈትዋ 257/2 ይመልከቱ!
ስለዚህ ጫት መቃም ትክክል ወይም ስህተት መሆን የሚችለው አንድ ግለሰብ ጫትን ስለሚቅም እና ስለማይቅም ሳይሆን ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው መስፈት ነው። ጫት መቃም የእርድና ምልክት፥ አለመቃም የፋርነት መለኪያ አይደለም፥ ይህ አስተሳሰብ መሰልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው። እንግዲያውስ ጫት የምትቅሙ፣ የምታስቅሙ፣ የምታቃቅሙ ቆም ብላችሁ ይህንን ፈሣድ ተመልከቱት! አሏህ ከጫት እና በጫት ከሚመጡ ፈሣዶች ይጠብቀን! አሚን።
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም