ከብፁዕ አቡነ ሰላማ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ | Abune Selama | ortodox tewhdo sibket 2023 | EOTC

  Рет қаралды 87,885

Mikha Denagil ምክሐ ደናግል

Mikha Denagil ምክሐ ደናግል

9 ай бұрын

አቡነ ሰላማ
የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ
ዜና ህይወቱ ለብፁዕ አቡነ ሰላማ (የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ)
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሥላሴ ገ/መድኀንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ ልዩ ስሙ በዓታ ለማርያም በተባለው ፲፱፴፬ ዓ/ም ተወለዱ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ ሀገራቸው ንባብና የቃል ትምህርት በሚገባ የተማሩ ሲሆን ለግብረ ዲቁና የሚገባውንም ትምህርት ከየኔታ ክነፈ
ርግብ ተምረዋል ፤ ዲቁና ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል።
ብፁዕነታቸው ለቤተክርስቲያንና ለመንፈሳዊ ዕውቀት ባላቸው ጥልቅ ፍቅር በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን የተማሩ ሲሆን
ዜማ፡- ከየኔታ ተክለ ማርቆስ ማየ አንበሳ ገዳም (ተንቤን)
- ቅኔ፡- ከየኔታ ንጉሤ መነዌ ገዳም (ተንቤን)
- ቅኔ፡- ከየኔታ አክሊሉ ደበጋ (ጐንደር)
• ትርጓሜ መጻሕፍት- ከየኔታ ኃ/ማርያም ቀረፃ ማርያም ከምትሀባል ገዳም
ቅኔና ትርጓሜ መጻሕፍት፡- እንድባ ጊዮርጊስ ከየኔታ ልሳነ ወርቅ (ጐጃም)
● ቅኔ፡- ከየኔታ ዲበኩሉ (ጐጃም) በሚገባ ከተማሩ በኋላ ለመምህር ነት በቅተዋል፡፡
ከዚህ በኋላ በጐጃም ክ/ሀገር በፈረስ ቤት ሚካኤል፣ በጅጋ ሚካ ኤል ወንበር ዘርግተው ለ፲፪ ዓመታት ቅኔ በማስተማር አያሌ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል፡
መዝገበ ቅዳሴ ከየኔታ ልዑል (ቦረራ ሚካኤል) ተምረዋል፤ በወ ቅቱ የጐጃም ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አሱነ ማርቆስ የቅስናና የምንኵስና መዐርግ ተቀብለዋል።
ብፁዕ አቡነ ሰላማ በ ፲፱፻፷፬ ዓ.ም ወደ አርሲ ክፍለ ሀገር በመሄድ በወቅቱ የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በነበሩት በብፁዕ አቡነ ሉቃስ መልካም ፈቃድ በሀገረ ስብከቱ በማስተማር፣ የአውራጃ ሰባኬ ወንጌል በመሆን፣ የወረዳ ሊቀ ካህናት በመ ሆን በተለያዩ የኃላፊነት ሥራዎች ተመድበው በመሥራት ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል፤ በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፍርተዋል፤ በዚሁ ሀገረ ስብከት ለ፳፪ ዓመታት በማስተማር ቆይተዋል፤ በዚህም ሰፊ ወቅት ብዙ ደቀ መዛሙርትን አውጥተው ለቤተ ክርስቲያን አበርክተዋል፡፡
ብፁዕነታቸው ከአርሲ ሀገረ ስብከት በ፲፱፻፹፮ ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ ውቅያኖስ በሆነው እውቀታቸውና በቅድስናቸው ቤተ ክርስቲያንንም ሆነ ምእመናንን እንደሚጠቅሙ በማሰብ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በቅዱሳን ፓትርያርኮች ፈቃድና ትእዛዝ እየተሾሙ፦-
⇨ በቡራዩ ፄዴንያ ማርያም፣
⇨ በመተሐራ መድኃኔ ዓለም፣
-በቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤልና ሳሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣
⇨ በሰዓሊተ ምሕረት፣
⇨ በደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት በአስተዳዳሪነት ተመድበው ለበር ካታ ዓመታት በማስተማር በሚያስመንነው ስብከታቸው ብዙ አማ ንያንን አበርክተዋል፤ ለምናኔም አብቅተዋል፤ በተሰጣቸው ሀብተ ፈውስ በጸሎታቸው አያሌ ሕሙማንን ፈውሰዋል፧ ሰበካ ጉባኤን አጠናክረዋልº ስብከተ ወንጌልን አስፋፍተዋል፧ በተለይም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቀ ሥልጣናት ሆነው ለ ዓመታት ያህል በአስተዳደሩበት ጊዜ ከፈጸሟቸው ተግባራት ዋና ዋናዎቹ ምእመናን በጣዕመ ስብከታቸውና በቅድስናቸው እየተማረኩ ለካቴድራሉ በሚያደርጉት የቦታና የገንዘብ ልግስና በርካታ የሆኑ የልማት ተግባራትን አከናውነዋል።
❖ በዚህም መሠረት በትምህርታቸው በጎ አድራጊዎችንና ምእመናንን በማስተባበር በካቴድራሉ ስም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትና ከፍተኛ ክሊኒክ አሠርተው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ አክ ሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተባርኮ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው፡፡
⇨ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለ፭ ዓመታት ካገለገሉ በኋላ በእን ጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም በአስተዳዳሪነት አገልግለዋል።
⇨ ብፁዕ አቡነ ሰላማ ሙሉ የቤተ ክርስቲያን ትምህርታቸውን አጠናቅቀው በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር በአብነት መምህርነታቸው በተለይም በቅኔ መምህርነታቸው በተለያዩ አህጉረ ስብከት ወንበር ዘርግተው በማስተማር እስከ ጵጵስና ደረጃ የደረሱ አያሌ ምሁራንን አፍርተው ለቤተ ክርስቲያን ያስረከቡ፣ በልዩ የስብከት ችሎታቸው የታወቁ ሰባክያነ ወንጌልን ያፈሩና አማንያንን ያበዙ፣ ቅድስናን ከሙያ ጋር አስተባብረው የያዙ፣ የቅዱሳኑ፣ የፍጹማኑ ረድኤት ያልተለያቸው፣ እንደ አባቶቻቸው ቅዱሳን ሐዋር ያት አጋንንትን የማስወጣትና ሌላውንም ደዌ ሁሉ የመፈወስ ሀብተ ፈውስ የተሰጣቸው፣ በጥላቸው ብቻ ሕሙማንን የሚፈ ውሱ፣ የበቁ (ፍጹም) አባት ነበሩ።
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸው ተውህቦ የተወሰነ አይደለም ሀብተ ጸጋቸው ብዙ ነው! ጣዕመ ስብከታቸው ካለ መጠገቡም በላይ በተመስጦ በአካለ ሥጋ ያሳርጋልI ቅኔያቸውም ልዩ ጣዕም አለው ከማር ከወተት ይጣ ፍጣል! ፈጣሪያቸውን ብቻ አይደ ለም የሚያከብሩት፣ ሲበዛ ሰው አክባሪ ናቸው‥ ምንም ይሁን ምን በአርአያ እግዚአብሔር የተፈጠረውን ትልቁንም ትንሹንም ሁሉ በአክብሮት የሚወዱ አባት ነበሩ።
በአጠቃላይ ብፁዕ አቡነ ሰላማ የቤተ ክርስቲያናችን ጸጋና በረከት ነበሩ።በዚህ ቅድስና ቸው፣ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሙሉ ችሎታቸው፣ በአብነት መምህርነታቸው በርካታ ምሁራንን በማፍራታቸውና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናቸው ባበረከቱት ሰፊ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው ተመዝነው ብቁና ፍጹም አባት ሆነው በመገኘታቸው ሐምሌ ፱ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም በተደረገው የጳጳሳት ምርጫ ከሌሎች ዕጩ ቆሞሳት ጋር ተወዳድረው የድምፅ ብልጫ ስለ አገኙ የአክሱምና ማዕከላዊ ዞን ሃገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ሆነው የተመደቡ ሲሆን ከታኅሣሥ ፱/ ፪ሺ፪ ዓ/ም ጀምሮ የሰሜን ምዕራብ ሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከትን ደርበው እየሰሩ እስከ ግንቦት ፳፰/፪ሺ፭ ዓ/ም ድረስ ሐዋርያዊ ተግባራቸውን ሲፈጽሙ ቆይተዋል።
ግንቦት ፳፰ /፪ሺ፭ ዓ/ም ከትግራይ ማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተዛውረው የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም እና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው በ ፪ሺ፮ ዓ/ም የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ለ፮ ዓመታት በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ከፍተኛ ሐዋርያዊ አገልግሎትን ፈጽመዋል።
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከህዳር ፳፻ ፲፪ዓ/ም ጀምሮ በድጋሚ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም እና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ኃላፊ ሆነው በበአታቸው በመወሰን ሲያገለግሉ ቆይተው ባደረባቸው ሕመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም ፲፰ቀን፳፻ ፲ወ፮ ዓ/ም ይህን ዓለም በዕረፍተ ሥጋ ተለይተው ወደ ሰማያዊው አባታቸው ተጉዘዋል። በረከታቸው ይደረሰን
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም ቴሌግራም ቻናል
Telegram t.me/Mikhadenagil
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም ኢንስታግራም
Instagram / mikhadenagi. .
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም የዩቱብ ቻናል
KZfaq kzfaq.info/love/IiC...
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም ቴሌግራም ቻናል
Telegram t.me/Mikhadenagil
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም ኢንስታግራም
Instagram / mikhadenagi. .
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም የዩቱብ ቻናል
KZfaq kzfaq.info/love/IiC...
የማኅበራችን የምክሐ ደናግል ማርያም
| sibket ethiopian orthodox film | ethiopian orthodox sibket new 2023 | mezmur orthodox ethiopia | ethiopian orthodox kidase full | Ethiopia & Ethiopian Ortodox Tewahdo chruch documentary
ሰልክ ቁጥር +251975424242
#MikhaDenagil #EOTC #Ethiopia #abuneselama #tewodros_yosef #ethiopia #tewodrosbelete
unauthorised use, distribution and re upload of this content is strictly prohibited
Copyright ©2023 Mikha Denagil
#Ethiopia #EOTC #Ethiopia&EthiopianOrtodoxTewahdochruch #amharicmovie #ethiopia

Пікірлер: 300
@abebayelema5176
@abebayelema5176 9 ай бұрын
አቡነ ሰላማ በረከቶ ይደርብን። እንዲህ አይነት አባት ከትውልዱ እንዴት ደብቃችሁ ቤተክርስቲያንና የጠፋውን ህዝብ ሊያድኑ ሊገስጹ ፣ የሚችሉትን ጥበባቸውንና እውቀታቸውን አፍናችሁ ስጦታቸውን፣ በረከታቸውን ሳናገኝ ምነው ካለፋ በኋላ እንደዚህ ታስለቅሱናላችሁ ያሳዝናል። ዝር ይብስ ሀዘኔን ጨመራችሁት። አባቴ አቡነ ሰላማ ካለፋ ጀምሮ ልብ አዝናለች። ልዑል እግዚአብሔር እስቲ እባክህ እንደነዚህ አይነት ተስፋና መጽናኛ የሚሆኑትን አባት አትውሰድብን። የወስድካቸውንም ደግሞ በረከታቸውን፣ ምልጃቸውን በፍጥነት ላክልን። እኛንም ሀጢአታችንን ይቅር ብለህ የቸርነትህን ላክልን። ያንተን ጽኑ ፍቅር በልባችን አትመህ ከመጥፋት ታደገን። አሜን አሜን አሜን በረከትእህ በምድሪቷ እንደስራችን ሳታይ ንደምህረትህ ዝራልን፣ አፍስስልን። ክፋና ተሳዳቢ ጾር አንደበቶችንና ልባችን ግታልን፣ አርቅልን። በፍቅርህ ለውጥልን።
@amalajekidusan6360
@amalajekidusan6360 9 ай бұрын
ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ በነፍስም በስጋም ቤተክህነቱ ነዉ: EOTC TV ነዉ:: ብዙ ማለት ይቻላል ግን ለጊዜው በዚህ ልተወዉ:: በደሙ የተገነባችዉን ቅድት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን በፈጣሪ ፈቃድ የምትፀዳበትን ጊዜ ፈጣሪ ያሳየናል ብዬ አምናለሁ:: በጸሎት እንበርታ::
@user-ze1ow4sz9p
@user-ze1ow4sz9p 9 ай бұрын
ትልቅ ዋርካ ወደቁ ዋ ለኔ😢ይፍቱን አባታችን በረከቷ ይድረሰን ሀገራችንን በላይ በሰማይ በጸሎት አሳስቡልን ሠላሙን ይሰጠን ዘንድ🙏
@Selam27
@Selam27 9 ай бұрын
አሜን!አሜን!አሜን!😢
@meazagenet4428
@meazagenet4428 9 ай бұрын
🙏🙏🙏
@amalajekidusan6360
@amalajekidusan6360 9 ай бұрын
አሜን:: መካሪ አባቶቻችን እየተለዩን ነዉ:: አምላካችን ለቤተክርስቲያናችን እነሱን የሚተካ አባት ያድለን:: ተስፋ ከድንግል ማርያም አይለየን:: ኢትዮጵያን ሕዝቧን ሰላም ያድርግልን ጠላቶችዋን ይደምስስልን:: አባታችን በረከቶ ይደርብን:: አሜን
@semanawitkibrom5430
@semanawitkibrom5430 9 ай бұрын
እሚን
@milkanatube4685
@milkanatube4685 9 ай бұрын
Amen Amen Amen
@leykunbirhanu5915
@leykunbirhanu5915 9 ай бұрын
ቅዱስ አባታችን በረከትዎ ይድረሰን!አሜን አሜን አሜን!
@hanamareyam6394
@hanamareyam6394 9 ай бұрын
አባታችን በረከቶት ይደርብን እማይጠገብ ነፍስን የምታለመልም ጡኡም ትምህርት
@zelealemakele3686
@zelealemakele3686 7 ай бұрын
አባታችን አቡነ ሰላማ ቸሩ መድኒአለም ለእኛ ቀሩ ብን
@mblfj7608
@mblfj7608 9 ай бұрын
አባቴ በረከቶት ይደርብኝ እኔ ሀጤያተኛዋ ልጆትን በፀሎት ያስቡን 😢ነፍስዎት በሰላም ትረፍልን❤😢
@milkanatube4685
@milkanatube4685 9 ай бұрын
Amen Amen Amen
@senainebyou2592
@senainebyou2592 9 ай бұрын
ይፍቱኝ አባ። በረከቶት አይለየን
@yaredbekele
@yaredbekele 9 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን
@arsamamikale9653
@arsamamikale9653 8 ай бұрын
አባቴ በረከትዎ አይለየኝ
@yemariamforever8624
@yemariamforever8624 9 ай бұрын
ውድ አባታችን መምህር ታዬ ቃለ ህይወት ያሰማልን ይህን የመሰለ ታሪክ ለኛ አዘጋጅተው ማስቀምጥዎት አባቴ አቡነ ሰላማ በርከትዎት ይደርብን ምርቃትዎት እስከ እለተ ሞት ይጠብቀን
@user-zg6mz6nb8f
@user-zg6mz6nb8f 9 ай бұрын
የአባታችን በረከታቸው ረድኤታቸው ፀሎታቸው ከእኛ ከሀጢያተኞቹ ልጅዎት ጋር ይኑርልን ይብላኝ ለኔ ምንምፅድቅ ለሌለኝ እሳቸው ሙሉ ዘመናቸውን ላገለገሉት አምላካቸው ጋር ነው የሄዱት 😢
@Dengle64
@Dengle64 8 ай бұрын
ቅዱስ አባታችን በረከትዎ ይድረሰን።
@fairoozfairooz3607
@fairoozfairooz3607 9 ай бұрын
ወለተ ማርያም አሜን ፫የብጽእ አባታችን በረኸታቸው ይደርብን
@asegedechligaba1137
@asegedechligaba1137 9 ай бұрын
አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን አሜንንን
@sindushenkut6693
@sindushenkut6693 9 ай бұрын
ኣሜን ኣባታችን በረከትዎ ይድረሰን :: እግዚአብሔር ነፍሶትን በ ኣፀደ ገነት ያኑርልን
@biskut6932
@biskut6932 8 ай бұрын
የአባቶቻችን ፀሎት ሀገራችንን ሰላም ፍቅርን ይስጠን ጌታሆይ አንተ ትችላለህ የዘረኝነት ን መንፈስ ከገራችን አስወግድልን የአባቶቻችን ፀሎት የእናታችን ምልጃ ብለህ ኢትዮጵያ የገባውን ሴጣናዊ መንፈስ አስወግድልን ልጆችህ ተጨንቀናል
@rahelgebreyesus8361
@rahelgebreyesus8361 9 ай бұрын
ፍፁም የፀሎት አባት
@lionali1149
@lionali1149 9 ай бұрын
ቅዱስ አባታችን ብርክት ረዲኤትዋን አይለየን
@nanigebre3747
@nanigebre3747 9 ай бұрын
ብጹእ አባታችን በረከትዎ ይደርብኝ። ቅድስት ነፍስዎ በአጸደ ቅዱሳን ከአምላክዎ ትለምንልን ሀገራችንንም ሰላም ታድርግልን። የሚወዷት ከአፍዎ የማትጠፋው እመቤታችንን ለምኑልን።
@user-qr2ck3wg6o
@user-qr2ck3wg6o 9 ай бұрын
ቅዱስ አባታችን በረከትዎ ይድረሰን!!!
@fikreselamwoldetsadik8551
@fikreselamwoldetsadik8551 9 ай бұрын
የብጹዕ አባታችን በረከት ይደርብን እንዲህ ያሉ አባት ሊቅነትን ከቅድስና ጋር አስተባብረው የያዙ ናቸው
@heerankaliyam3318
@heerankaliyam3318 9 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን
@wsasews4395
@wsasews4395 9 ай бұрын
አባታችን በረከትዎ አይለየንአሜን
@KuriWolde
@KuriWolde 9 ай бұрын
የአባታች በረከታቸው ይደርብን
@Hanzmariam
@Hanzmariam 9 ай бұрын
ጋሽ ታዬ እግዚአብሄር በእድሜ በጸጋው ያቆይልን። አባታችን በረከታቸው ይደርብን ።
@zemenewoldeyes7662
@zemenewoldeyes7662 9 ай бұрын
አባታችን በረከትዎ ይድረሰኝ ይፍቱኝ ከማእሰርተ ሐጢአት
@elfeneshamenu3322
@elfeneshamenu3322 9 ай бұрын
ብፁነትዎ አባታችን ቡራኬዎ ይድረሰን አገራችን ሠላም ያደርግልን ዘንድ እኛንም ከበደል ያነፃን ዘንድ ዝም ብለን ነጠላ አመሳቅለን ለምንመላለሠው የነነዌ ህዝብ በ3 ቀን ነፃ ያወጣ የነኤልያሥ የነሙሴ የነዳዊት የአብረሀም የኖህ አባት ዛሬም ከእኛጋ ሆኖ ንፁህ ሌቦና ሰጥቶን በቅድስና በንፅህና ኤኔድንመላለሥ ቸርነቱ ይርዳስ ስለቄድሴት እናቱ ብሎ ይታረቀን
@messeretshibeshi3245
@messeretshibeshi3245 9 ай бұрын
የአባታችን በረከት በሕዝባችን ላይ ይደርብን ፣አሜን
@user-jh3zu5hz5f
@user-jh3zu5hz5f 8 ай бұрын
ቅድስ አባታችን በረካት ይደረሰን
@biuletesgakassa6680
@biuletesgakassa6680 9 ай бұрын
አቤት አለመታደላችን ታላቅ ቅዱስ አባት ነዉ ያጣነዉ ያስቡኝ አባዬ
@emano5974
@emano5974 9 ай бұрын
😢😢😢
@user-un7wd8bg3w
@user-un7wd8bg3w 8 ай бұрын
ምናለ ሥለኢትዮጵያ ቢጠይቁልን የወደፉት ህወታችን
@yaredbekele
@yaredbekele 9 ай бұрын
አባታችን በረከቶ ይደርብ አሜን
@aftd6975
@aftd6975 7 ай бұрын
በረከትዎ ይደርብን አባታችን
@elizabethlaffe4066
@elizabethlaffe4066 9 ай бұрын
አባታችን በረከቶ ይደርብኝ
@askaltibebuworede1490
@askaltibebuworede1490 9 ай бұрын
ብፁ አባታችን አንዴት ደግ ሰው አክባሪ እንደሆኑ ባይኔ አይቻለሁ ትልቅነው ትንሽ ነው ሳይሉ የሚያከብሩ የእውነት እረኛ ናቸው በረከትወት ይደርብን!
@tedlamulugeta9895
@tedlamulugeta9895 9 ай бұрын
አባታችን በረከተዎ ይደርብን
@zewdhabte6585
@zewdhabte6585 9 ай бұрын
በረከታቸው ይደርብን አሜን ፣አሜን፣ አሜን
@adanadanish6456
@adanadanish6456 9 ай бұрын
አሜን አባታችን በረከታቸው ይደርብን አጥንት የሚያለመልም ትምህረት ነዉ ቃሊወት ያሰማልን ተስፍ መንግስተ ሰማያት ያዋረሰልን
@user-cq4kq6ec6m
@user-cq4kq6ec6m 6 ай бұрын
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ኣባታችን በረከታቹ ይደርብን ❤ በጸሎታቹ ይማረን
@user-tm7ho2tt3t
@user-tm7ho2tt3t 9 ай бұрын
አባታችን በረከትዎ በአምላክ አገልጋይ ይደርብኝ
@makimimi3650
@makimimi3650 9 ай бұрын
አሜን አባቴ❤❤❤ በረከቶት ይደርብኝ❤❤❤
@girmayemiru5403
@girmayemiru5403 9 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን ። የ እባታችን በረከት ከሁላችን ጋር ይህንን አሜን አሜን አሜን ።
@merreytube9473
@merreytube9473 9 ай бұрын
ቅዱስ አባታችን በረከታቸንው ይደርብን አሜን አሜን አሜን ።
@sosinahaddis7967
@sosinahaddis7967 9 ай бұрын
የቅዱሳን አባቶቻችን ረድኤት በረከት ይደርብን
@amarechtezera2004
@amarechtezera2004 7 ай бұрын
አባቴ በረክቶ ይደርብን
@mekidesbirhanu
@mekidesbirhanu 9 ай бұрын
አባቴ በረከቶት ይደርብኝ
@GiasBd-rh7bj
@GiasBd-rh7bj 9 ай бұрын
አባታችን በርከቶ ይዴርብን
@tsinat982
@tsinat982 8 ай бұрын
እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ብዬ ስማን ለመጥራት በምልጃዋ ለማመን እግዚአብሔር ስለፈቀደልኝ አመሰግነዋለሁ አባታችን በረከትዎ ይደርብን
@mesererthaile7348
@mesererthaile7348 9 ай бұрын
በረከቶ ይደርብን
@user-vf6uj6gz6k
@user-vf6uj6gz6k 8 ай бұрын
Amen Amen Amen bereketwo ydresen abate aba Selama
@MimiMimi-bf5gg
@MimiMimi-bf5gg 9 ай бұрын
በርከትዎ ይደርብን 😢.
@bezatamirat1161
@bezatamirat1161 8 ай бұрын
በረከቶ ይደርብን🙏
@freweinigebrehiwot2680
@freweinigebrehiwot2680 9 ай бұрын
ብፁዕ አባታችን በረከትዎ ይደርብን :
@melesezewdei5597
@melesezewdei5597 9 ай бұрын
💐💐🌺አሜን አባታኝችን።እንዲህ ያሉትን አባቶች እግዚአብሔር አያሳጣን።💐💐🌺💚💛♥️
@genetkebede4858
@genetkebede4858 9 ай бұрын
በረከተዎ ይደርብን
@freselambelachew2712
@freselambelachew2712 9 ай бұрын
በረከታቸው ይደርብን
@edenmeasho
@edenmeasho 9 ай бұрын
አሜን ብጹእ አባታችን በረከትዎ ይድረሰን🙏🙏🙏
@fekadumamo7854
@fekadumamo7854 9 ай бұрын
በረከቶት የደረብን !!!
@azebmulugeta5233
@azebmulugeta5233 9 ай бұрын
ኣባታችን በረከትዎ ይድረሰን ::
@user-md1qq8yj1r
@user-md1qq8yj1r 9 ай бұрын
እድሜ ይስጥልን አበ
@amarechtezera2004
@amarechtezera2004 7 ай бұрын
አባቴ ይፍቱን ይባርኩን.
@trufatargaw593
@trufatargaw593 9 ай бұрын
Kale hiwet yasemalen abatachen ❤❤❤❤ ❤❤❤❤
@genetteklu1537
@genetteklu1537 9 ай бұрын
Amen abatchen! Bereketwona zelotro ayeleyen🙏🏾
@emano5974
@emano5974 9 ай бұрын
በረከተወ ይድረሰን ይፍቱኝ።ይባርኩኝ❤❤❤😢😢😢😢
@user-gi5ei6mh2y
@user-gi5ei6mh2y 9 ай бұрын
በረከታቸዉ ይደርብን😢😢
@aydengitsualegeta8216
@aydengitsualegeta8216 9 ай бұрын
Abate yiftugn bereketwo yidresegn
@delbaniali5574
@delbaniali5574 9 ай бұрын
😭😭😭😭አይይይ ወየውልኝ ለኔ ለሀጥያተኛዋ አለቃ!!በረከቶት ይደርብንን አባ ሰላማ አባታችን ☝☝☝እምዬዋዬ አባቶቻችን ጠብቂልን እድሜና ጤና ስጪልኝ እመቤቴቴቴቴቴቴቴቴቴቴ❤ 21❤!!
@user-il7on9hb2z
@user-il7on9hb2z 9 ай бұрын
ጋሺ ታይዬ የኔ አባት መምህሬ አንተ ያሥተማርከን ነው ለዛሪ ብርታት ሐይል የሆነን ኑርልኝ
@kalkidangobezie4078
@kalkidangobezie4078 9 ай бұрын
አባተችን ፡ በረከትዋ ፡ ይደርብን ይፍቱኝ
@user-ew4rp4zu3x
@user-ew4rp4zu3x 9 ай бұрын
በርከታችው ይደረብን😢😢
@jhonnytube5128
@jhonnytube5128 9 ай бұрын
ወቅዱስ አባታችን በረከትዎ ይደርብን
@derejedemissiew1795
@derejedemissiew1795 9 ай бұрын
አባታችን በረከትዎ ይድረሠን።
@user-md5ur5uk7o
@user-md5ur5uk7o 9 ай бұрын
አባታችንበረከትሁይድረሰን❤🎉😮❤🎉😮❤🎉😮
@genetdubei9894
@genetdubei9894 9 ай бұрын
❤አባታችን ትንሽ ምነዉ ቢቆዩልን ምንይዋጠን ለራሳችነዉ ማልቀስ ያለብን ድንቅ ትምርት ቀረብን ወይየኛ እድል😂😂😂
@SjsJej-pi2qv
@SjsJej-pi2qv 9 ай бұрын
የአባታችን በረከታቸው ይደርብን💚💛❤
@omegabiherzere8758
@omegabiherzere8758 9 ай бұрын
ቅዱስ አባታችን በረከቶት ይደርብን ❤💔💔💔
@amesalubarega760
@amesalubarega760 9 ай бұрын
በረከቶይደርብን
@user-ck1rt1vb2s
@user-ck1rt1vb2s 9 ай бұрын
ቅዱስ አባታችን በረከትዎ ይደርብን
@Filisltan
@Filisltan 9 ай бұрын
ኣባታችን በረከታቸው ይድረሰን ።
@weynubelste9857
@weynubelste9857 9 ай бұрын
አባታችን በረከትዎ ፀልዎትዎ ይደርብኝ
@yaredkebede2571
@yaredkebede2571 9 ай бұрын
በረከተዎት ይደርብን አባታችን ።
@Orthodoxawi12
@Orthodoxawi12 9 ай бұрын
ይፍቱኝ በረከትዎም ይደርብኝ
@fantukelecha522
@fantukelecha522 9 ай бұрын
አሜን ! ብጹዕ አባታችን በረከትዎ አይለየን 🙏 በሕይወት በአሉቴ አባቶች ላይ አድሮ ይኑር 🙏
@EphremBerhane
@EphremBerhane 9 ай бұрын
Amen
@user-mz6zb4qx1k
@user-mz6zb4qx1k 9 ай бұрын
❤❤❤
@meseretadana109
@meseretadana109 9 ай бұрын
ቅዱስ አባታችን በረከት ረድኤቶ ይድረሰን 🙏
@user-xn7kp7xo1u
@user-xn7kp7xo1u 8 ай бұрын
እምየ ኢትዮጵያውያ እነዚህን የመስሉ ቅዱስ ልጆች አሉሽ እግዚአብሔር የባርካት ትልቅ የቅዱሳን ሀገር ነሽ እና አምላካችን አይተወንም
@shawelm
@shawelm 9 ай бұрын
ፍፁም የፀሎት አባት😢በረከታቸው ፀሎታቸው ይደርብን!
@user-mm5nd9mp5f
@user-mm5nd9mp5f 9 ай бұрын
Amen Amen Amen berkto ydrben talak abat
@user-kz3is6gl7n
@user-kz3is6gl7n 9 ай бұрын
አሜን አሜን!! ብፁዕ አባታችን ቡራኬዎ ይድረሰነኝ
@asegedechligaba1137
@asegedechligaba1137 9 ай бұрын
ያባታችን በረከታቸ ው ይደርብን እመቤታ ድግል ማርያም በገነት ታንርልን አሜንንን አሜንንን አሜንንን
@yenenshyimer8570
@yenenshyimer8570 9 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን በረከትዎ ይደርብን ብፁዕ አባታችን
@heremelawesene
@heremelawesene 9 ай бұрын
አባታችን በረከቶዎ ይደርብን😭😭💔
@tube-hk8nt
@tube-hk8nt 9 ай бұрын
ሠላም ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሰላም ለቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ለአለም አባታችን ብፅነታቸው አቤት መታደል ይህን ከንቱ አለም ተለዩት እፍፍፍ በረከታቸው ይደርብን😢
@Kalkidan727
@Kalkidan727 9 ай бұрын
በረከትዎ ይደርብን አባታችን🙏🙏🙏
@ye_mikael
@ye_mikael 9 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን😢ነፍሶትን ከአብርሀም ጎን ይኑርልን
@lakechbeyene9243
@lakechbeyene9243 9 ай бұрын
የብፁዕ፡ አባታችን፡ በረከታቸው፡ ትድረሰኝ፤፤
@rahelhmariam5647
@rahelhmariam5647 9 ай бұрын
ቅዱስ አባታችን ይፍቱን ይባርኩን በረከትዎ ይድረሰን❤
@liltya3613
@liltya3613 9 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን ብፁዕ አባታችን በረከተዎት ይድረስን❤️❤️❤️💛💛💛💚💚💚🙏🙏🙏
@mezemirtiumelisan8114
@mezemirtiumelisan8114 9 ай бұрын
በረከቶት ይደርብን አባታችን
@mikiyas-h
@mikiyas-h 9 ай бұрын
እመቤቴ ያምላክ እናት ላመስግንሽ ቀን ከለሊት
KINDNESS ALWAYS COME BACK
00:59
dednahype
Рет қаралды 167 МЛН
Cool Items! New Gadgets, Smart Appliances 🌟 By 123 GO! House
00:18
123 GO! HOUSE
Рет қаралды 17 МЛН
100❤️
00:19
MY💝No War🤝
Рет қаралды 23 МЛН
Little girl's dream of a giant teddy bear is about to come true #shorts
00:32
ዝክረ አቡነ ጳዉሎስ #ሥርዓተ-ጳጳሳት
20:06
መጥሮጶሊስ ቲዩብ
Рет қаралды 10 М.
Ethiopia: በብጹዕ አቡነ እንድርያስ ሊቀ ጳጳስ "ውጦ አሰጠመው" - Abune Endriyas |EOTC |Sibket |
27:39
KINDNESS ALWAYS COME BACK
00:59
dednahype
Рет қаралды 167 МЛН