Рет қаралды 289
Amhara Education Bureau
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2015 የትምህርት ዘመን የመምህራንን ቀንን አክብሯል፡፡ በእለቱም ለውጤታማ አንጋፋ መምህራን እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ /ዶክተር/ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት መምህራን የቀጣይ ትውልድ ተስፋ ፈንጣቂ የትውልድ ብርሃን ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡