እንዴት ጓደኛ ሊኖረን ይችላል በዚህ ባህሪአችን‼️እንጠንቀቅ‼️ | EthioElsy | Ethiopian

  Рет қаралды 93,147

EthioElsy LifeStyle

EthioElsy LifeStyle

Жыл бұрын

Welcome to my channel I'm Elsa Getu , if you subscribe my channel we will share very useful information, healthy lifestyle and entertainments .
#EthioElsy #Ethiopia #ሀበሻ
/ elsa_fusion_lifestyle
/ elsa.getu22
EthioElsy LifeStayle , Ethiopia, EBS TV, Donkey Tube , Ashruka አሽሩካ channel, Seifu On EBS, Ethiopian tiktok, Feta Daily, Abel Birhanu, Ethioinfo , Eyoha Media , የገነት ቤተሰብ Reality Show , Dallo| Entertainment ,Jehoaddan X Jeoanna, EBC, Rakeb Alemayehu, Comedian Eshetu, elsy lifestyle, SHEGER INFO,

Пікірлер: 534
@tgethiopia381
@tgethiopia381 Жыл бұрын
ለፍቅርም መቸኮል ለፀብም መቸኮል አያስፈልግም ትላለች እናቴ በድርበቡና በስሱ ሁኚ የምትለኝ ምክር ጠቅሞኛል። ኤልሲ እንዳልሽዉ አብሶ የሰዉ ስም በሌለበት አንስቶ አብሮ መቦጨቅ ለራስ ዋጋ ያስከፍላል። ተባረኪ
@ethioelsylifestyle9486
@ethioelsylifestyle9486 Жыл бұрын
Tgye ውይ የትልቅ ሰው ንግግር ደስ ሲል በጣም ደስ የሚል አባባል 🙏♥️🙏
@Eyerusalem_
@Eyerusalem_ Жыл бұрын
ለምንድነው እናትሽ በስሱ ሁኚ ያሉሽ የሚገርም ምክር ነው
@tgethiopia381
@tgethiopia381 Жыл бұрын
@@Eyerusalem_ እናቴ በስሱ ሁኚ ያለችኝ የሴት ጓደኛ ስትይዢ መያዝ ያለብሽን የራስሽን ሚስጥር ለራስሽ መያዝ እንጂ እንዳታወሪ ማለቷ ነዉ ሌላዉ ቶሎ ቶሎ ጓደኛ ቤት እግር አለማብዛት እና በልቤ ያለዉን ሁሉ አለመንገር ነዉ። ምክሯ ጠቅሞኛል🙏
@sindubegashaw9329
@sindubegashaw9329 Жыл бұрын
@@ethioelsylifestyle9486 Thank you so much
@meazazerfu4492
@meazazerfu4492 Жыл бұрын
Yenem enat endhi new yemitilegn .rejim edme le enatochachin
@ritaaraya3439
@ritaaraya3439 Жыл бұрын
“ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።” - ሮሜ 12፥18
@genetgirma1056
@genetgirma1056 Жыл бұрын
ስለማይቻል እኮ ነው ቢቻላችሁ ያለን ፣በጌታ ብቻ ነው ደስ ይበላችሁ የተባልነው።
@user-ys7bs6uh9q
@user-ys7bs6uh9q Жыл бұрын
ጎደኛ የለኝም እግዚአብሔር ይመስገን ጥሩ ጎንም መጥፎ ጎንም አለው ግን ብቸኝነት በጣም ጥሩ ነው በአሁኑ ስአት
@BEst-tn4ir
@BEst-tn4ir Жыл бұрын
Solitude is the richness of self❤
@zumerazuzu1717
@zumerazuzu1717 Жыл бұрын
ሰደት ላይ እዉነት ለመናገር ጎደኛ የለም
@haimanotdemissie798
@haimanotdemissie798 Жыл бұрын
True
@user-mi8gz7dz8x
@user-mi8gz7dz8x Жыл бұрын
​@@haimanotdemissie798 በጣም ወላሂ
@user-sl6ds5nw4s
@user-sl6ds5nw4s 11 ай бұрын
የለም ነው ያለሽ ያረብ ሰደት ላይ ወላሂ ጎደኛ አለ አልሃምዱሊላህ ።
@lamrotdreij1516
@lamrotdreij1516 11 ай бұрын
በጣም
@richa1186
@richa1186 Жыл бұрын
ምርጥ ምክር ተባረኪ፧ ባንቺ ምክር ብዙ ተጠቅሜአለሁ በyoutube የተገኘሽ ምርጥ ጓደኛዬ ነሽ❤
@user-cb5yk2gj8p
@user-cb5yk2gj8p Жыл бұрын
ፈጣሪ ይመስገን በጣም ምርጥ ጓደኛ አለችኝ ሚገርመው ደሞ ወንድማማቾች አገባን እኔ ትንሹን አግብቼ የባሌን ታላቅ ወንድም ዳርኩላት
@user-bb7zo6yh3s
@user-bb7zo6yh3s Жыл бұрын
ትክክል ብለሻል ሰዉ እስክፋቱ ጥሩ ነዉ ይባላል አንዳዳንድ ጉደኞች አሉ እንዳልሽዉ በችግራቸው ግዜ ብቸኝነት በተሰማቸዉ ግዜ አማካሪያቸው ያረጉሽና አብረዉሽ ይወጡ ይወርዱና ችግቸዉን ሲያወሩልሽ አንችም ሰዉ አገኘሁብለሽ ጥሩ ጎደኛየ ናት ብለሽ ብዙ ነገሮችን አዉርተሽ በቃ ያላንች ሰዉ የለም ይሉሽና ልክ ኑሮቸዉ ለወጥ ሲል አንስተዉ ገደል ይከይከቱሻል በደናቀን ያወራሽዉን ጥሩ ነገር ሁሉ በመጥፎ ተርጉመዉ ሲቦጭቁሽ ይዉላሉ ጠልተዉ በምትወጅአቸዉ በምታከብሪያቸዉ ሰዉች ሲያስጠሉሽ ስታይ በጣም ያማል አንዳደየ ሰዉን ማወቅ ከባድ ነዉ።
@samrawetsamrawet2297
@samrawetsamrawet2297 Жыл бұрын
ትክክል ብለሻል እግዚአብሔር ይባርክሽ
@felekechgeberemeskel4933
@felekechgeberemeskel4933 Жыл бұрын
ትክክል ነሽ እኔ መያዝ ያልቻልኩትን ሚስጥር ማንም ሊይዘው አይችልም
@tigistjemal9444
@tigistjemal9444 Жыл бұрын
ኤልሲዬ ሰላም ነሽ? ስለጓደኛ ስትናገሪ በጣም ምክርሽ ደስ ብሎኛል። እንደ እኔ በጓደኛ የተገፋ ሰው ያለ አይመስለኝም ። ነገር ግን በጣም ክፉ ነገሮች ቶሎ ከአእምሮዬ ይጠፋሉ ። ይሔ ነገር በጣም ጠቅሞኛል ። ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር እሞክራለሁ ። ሰው ያልተመቸው ከመሠለኝ ቀስ ብዬ ሳልወቃቀስ እሸሻለሁ። አሁን ግን ሰው በትንሽ በትልቁ የከፋው ሆንዋል ። እና ልበ ሰፊ መሆንን ይጠይቃል ። በተለይ በእኛ ሀገር! እንደ ድሮ ጎረቤት በየቀኑ ተገናኝቶ ቀርቶ በሦስት ወር አይተሽው በተለይ አንዳንድ ሴቶች ዝግት አድርገውሽ ያልፋሉ ። ከቀለለኝ እኔ ነኝ ሰላም የምላቸው።ሰው በሀይማኖት ፅንፈኛ በዘር ፅንፈኛ በኑሮ standard ፅንፈኛ ሆኖ ተቸገርን! እግዚአብሔር ይማረን!
@yoditkere5693
@yoditkere5693 Жыл бұрын
ኤልሲዬ የኔን ልንገርሽ እኔ በስደት አለም ስኖር ብቻዬን ያለጓደኛ 5 አመት ያህል ኖርኩኝና አበሻ ይኖርበታል ብዬ በማላስብበት ቦታ ሙቭ ሳረግ ሀበሻ እህቶች አገኘው ማመን አልቻልኩም ከምር እህት ያገኘው መሰለኝ ያውም ጎረቤት እና ጥልቅ ብዬ ገባሁ የማልነግራት ነገር አልነበረም የቤቴን ገመና ሁሉ ቢቀለኝ እያልኩ አወራት ነበር ከዛ የሆነ ሰአት ላይ ሆዳችን ሻከረ የሆነ ግብዣ ላይ ስለኔ ሰታወራ ፊት ለፊት አየዋት ሰማዋትም ማመን አቃተኝ ውስጤ በጣም አዘነ አይ የሰው ነገር አስባለኝ ምንናለ ያን ሁሉ ነገር ባላወራዋት ብዬ ተቆጨው እና እህቶቼ ከኔ ትምህርት ውሰዱ ሰውን ማመን በጣም ከባድ ነው በሷ የተነሳ እኔ አካባቢ ላይ ያሉት ሀበሾች ሁሉ አስጠሉኝ እንደሌላ ጊዜ ሶሸብል መሆን አቃተኝ እና ኤልሲዬ ምን ትመክሪኛለሽ
@meseretsemaw
@meseretsemaw Жыл бұрын
መጣላት አለና ሚስጥር አትናገር መታረቅ አለና ክፉም አትናገር ይባል የለ ስለዙሀሰ ሁሉን በልክ ማድረጉና በመጠን መኖሩ መልካም ነው። በትክክል እናመሠግናለን ❤
@misrakaragaw7930
@misrakaragaw7930 Жыл бұрын
ምርጥና ወሳኝ ነገር አነሳሽ ኤልሲ በትዳር አለም ውስጥ 19አመት ኖሪያለው ሰው በጣም ወሳኝ ነው አያያዙን ካወቅሽበት ወረት አልወድም አሁንም በማለፍ በመቻቻል አብሬ እየኖርኩ ነው በህይወቴ ከብዙ እህቶች ጋር አሳልፌያለው ስለሰው የሚያነሳ ሰው እውነት ነው መጠንቀቅ ነው ሰው ሲታማ ለኔ ብለህ ስማ ይባላል ታማኝነትን ያሳጣል እግዚያብሔር ሲባርክ ሰው ነው የሚሰጠው ቤት ሳይሆን ጎረቤት ግዙ ትላለች እናቴ በጣም ተጠንቅቄ ነው የምኖረው ደርበብ ብዬ ምክርሽ ልዩ ነው የኔ ቅመም ተባረኪልኝ እወድሻለሁ።
@kiyayemaryamlij3585
@kiyayemaryamlij3585 Жыл бұрын
Else ትልቅ መልዕክት ነዉ በእዉነት እናመሰግናለን ይህን ሁሉ ጭቅጭቅ ስለ ምጠላ ነው ይሄው 5 አመት ሆነኝ ብቸኛ ነኝ ትንሽ አኩራፍም ነኝ ጌን ቶሎ እረሳለሁ ብቻ እግዚአብሔር ያዉቃል
@babyflower5176
@babyflower5176 Жыл бұрын
ኤልስዬ አንችኮ ትለያለሽ የሰውነገር የገባሽ የምታውቂውን የምታሳውቂን የምታስምሪን ሰው የምታነቂው በጣም ጥሩነትሽን ቀናነትሽን ነው የሚያሳየን እኔ ከምትሰሪልን ነገሮች ከምትነግሪን ከምትመክሪን ነገር አንዱንም አልጥልም ሁሉንም በተቻለኝ እተገብራለሁ እመቤቴ ማርያም የልጆችሽ እናት ታድርግሽ እድሜና ጤና ይሰጥሽ የኔ ቆንጆ😍😍😍😘🙏
@user-dz2iu8lp9x
@user-dz2iu8lp9x Жыл бұрын
እውነት ነው በአሁኑ ሰአት ጓደኛ የለኝም አያስፈልገኝም በተለይ በስደት ሀገር እውነተኛ የሴት ጓደኛ ማግኘት ይከብዳል በስደት ሀገር ስኖር ከአስራ አምስት አመት በላይ ሆኖኛል። እግዜአብሄር ይመስገን ሁለት ሴት ልጆች ሰጥቶኛል ጓደኞቼም አማካሪዎቼም ልጆቼ ናቸው።
@fasikaseyoum145
@fasikaseyoum145 Жыл бұрын
Tikikel beleshal kebad new betam
@rahelw4920
@rahelw4920 Жыл бұрын
እኔም እንዳንቺ
@alganeshbahre8598
@alganeshbahre8598 Жыл бұрын
For me too
@meronzergaw5719
@meronzergaw5719 Жыл бұрын
ጥበበኛ ሴት ነሽ : እግዚአብሔር ይባርክሽ🙏🏽🙏🏽🙏🏽💕
@helengezahegn4794
@helengezahegn4794 Жыл бұрын
Betam arif mikir newu
@blentube3002
@blentube3002 Жыл бұрын
@@helengezahegn4794 ደምሩኝ😍😍
@ethioelsylifestyle9486
@ethioelsylifestyle9486 Жыл бұрын
አሜን ውዴ 🙏♥️🙏
@yematialemayehu4304
@yematialemayehu4304 Жыл бұрын
አቤት አቤት የኔ ቆንጆ የምታነሽው እርህስ በጣም የተጨበጨበለት ነው፡፡ የሰው ልብ ውሥጥ ስምጥ እኮ ነው የምትይው፡፡ ተባረኪ፡፡ Thank you so much my dear.🙏
@user-hq9rh9ig7s
@user-hq9rh9ig7s Жыл бұрын
በርግጥ ስደት ላይ የልብ ጓደኛ ማግኘት በጣም ከባድ ነው ምክንያቱም ሁላችንም ከ አንድ አገር ብንመጣም የተለያየ ባህል የተለያየ አካባብ እንዲሁም የተለያየ የአናኑዋር ዘዴ ካለበት ማህበረሰብ ስለመጣን ብዙ የሚያመሳስሉን ነገቶች እንዳሉ ሆነው የሚያለያዩን ነገሮች እንዳሉ መገንዘብ አለብን። ጓደኛ አስፈላጊ ነው ስለዚህ መቻቻልን መልመድ አለብን ሰዎችን መቀየር ላንችል እንችላለን ግን የሰዎችን ድክመት ተረድተን በመቻቻል አብሮ መኖር እንችላለን ብዬ አስባለሁ። ለሰው ልጅ ሰው አስፈላጊ ነው በዚህ አጋጣሚ በአገራችን የ ፖለቲካ ልዩነት ያጣሁዋችሁ ጓደኞቼ ባላቹበት ሰላማችሁ ይብዛ እላለሁ፡ አሁንም ቢሆን ለይቅርታ በሬም ልቤም ክፍት ነው ያጠፋሁት ነገር ባለመኖሩ ምንም ቅር የሚለኝ ነገር የለም።
@meseretdemissie8229
@meseretdemissie8229 Жыл бұрын
ያልሺዉ በሙሉ በትክክል እውነት ነው ኤልሲዬ ካንቺ ብዙ ተምሬያለሁ እንኳን ከጓደኛ ከቤተሰብም ተቻችሎ ነው 😊
@nardosmekonnen5481
@nardosmekonnen5481 Жыл бұрын
አንች ብልህ ሴት እግዚአብሔር የመረቀሽ የምታቀርቢያቼው ነገሮች ሁሉ አስተማሪና መካሪ ከውስጥ የማይወጡ ናቼው በውነት በዙሪያሽ ያሉ ሰወች አንች ስላለሻቼው እንዴት የታደሉ ናቼው ከምንም በላይ በውስጥሽ ያለው ግብረገብ በእውነት ወላጆችሽ ይባረኩ ይህ አብሮሽ ያደገ ባህሪሽ እንደሆነ ያሳያል በርች እህቴ እድሜ ይስጥሽ::
@tezitaalemu6758
@tezitaalemu6758 Жыл бұрын
ኤልሲ በጣም ጥሩ ነገር ያነሳሽው የኛ የሴቶች ትልቁ ችግር ይኼ ነው ምክርሽ ጥሩ ነው እንደዚህ አይነት አስተማሪ የሆነ ለኛ ለሴቶች የሚጠቅም ነገር በሌላም ግዜ ብታነሽና ብንማማር ጠቃሚ ነው እናመሰግናለን ።
@inspireteachers1500
@inspireteachers1500 Жыл бұрын
ኤልስዬ ተባረኪ በእውነት በጣም ደስ የሚል ምክር ነዉ :: እራሴን አሳየሽኝ . Thank You
@AdanechKitchen
@AdanechKitchen Жыл бұрын
ኤልስዬ በጣም ጠቃሚ ምክር ነው ያካፈልሽን ሁሉ ነገር ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ከሰው ጋር ነው አስተዋይ ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ይላል በግልፅ ነት ከልብ በሆነ ባልንጀራችንን መውደድ ይሁንልን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክሽ 🙏❤😘
@luamamsalu6079
@luamamsalu6079 Жыл бұрын
Finally ስርአት የሚያስተምር ሰው ተገኘ
@lifeat2401
@lifeat2401 Жыл бұрын
ኤልሲዬ ሲሪን አልፈልጋትም ስትይ ከጎደኛ ሲሪ የደረሰችልኝን ግዜ አስታወሽኝ አንዴ ከጎደኞቼ እራት እንውጣ ተባብለን አንዶ እንከታተል አለችኝ ቦታውን ስለማለውቀው እሺ ብዬ ስንከታተል እስፒድ እያደተገች ጠፉችብኝ እኔም አቆምኩና iPad መኪናዬ ውስጥ ስለነበር ላወጣው ስል በድንገት ተጫንኮት መሰል what can I help you አለችኝ እኔም ውይ ሲሪዬ በይ አንቺ ምሪኝ አልኩና አድራሻውን ልነግራት እያልኩ I am sorry I don't get you አለችኝ አማርኛው ስላልገባት hold on sir አልኩና አድራሻውን ስነግራት ወደ ግራ ወደ ቀኝ እያለች ስትወስደኝ አይ ሲሪዬ ከአጉል ጎደኛ አንቺ ተሻልሽኝ ስል መምራቱን ትታ I don't get you ስትለኝ don't worry go on ብዬ እሶ እየመራችኝ የምፈልገው ቦታ አደረስችኝ እኔም ስደርስ ጎደኛዬን ዛሬ ሲሪዬ ባትኖር አልመጣም ነበር ብዬ ታሪኩን ነግሬ አሳኮቸው ሲሪ እኮ ከአጉል ጎደኛ ትችላለች ሚስጥርሽን ጠብቃ ትመክርሻለች😀 ለጫወታው ድምቀት ነው ቴክኖሎጂን ከተከተልን ቤታችንን ዘግተን እንድንኖር ያደርገናል እና የሚሆነንን ጎደኛ እንምረጥ
@Sintayehu912
@Sintayehu912 Жыл бұрын
😂😂😂😂
@jojolove791
@jojolove791 Жыл бұрын
ኢልሲ ከልጅነት በቤተሰብ ደረጃ የሚያቅሽማ መጣም መናናቅ አለ እንዴ አላቃትም እንዴ እንዲህ ነበረች እኮ ዛሬ እዝህ ደርሳ ትመፃደቃለች ነው ትርፉ ብዙ ሞክሬያለሁ ከአብሮ አደጎቼ ጋር ጎደኝነት ግን አልተሳካልኝም ሰሜ ደጅ ነው በዛ ላይ ፉክክሩ አጠይቅኝ እናም የምትከበሪው በአጋጣሚ ያወቅሽው በዛሬው ማንነትሽ ይወድሻል ያከብርሻል መልካም ከሆንሽ ጥሩ ጎደኛ ይሆናሉ እንጂ አወኩሽ ናኩሽ ናቸው የሚጎዳሽ የሚያቅሽ ነው
@ruhamatube627
@ruhamatube627 Жыл бұрын
ልክነሽ ውይ
@saraabebemulgeta4931
@saraabebemulgeta4931 Жыл бұрын
Hi sisterሰውን አትጥሉ ሰውን የጠላችሁ ቀን ያቺ ቀን ትልቅ ጥፉት እንደሆነች እወቁ! ሰው ለደስታም ለሃዘንም ❤️👌🤗🙏💪
@EthiopicMedia
@EthiopicMedia Жыл бұрын
ኤልስይ ትልቁ ትእዛዝ ጓደኛህን እንደ እራስህ ውደድ ነው ትልቅ ትምህርት ነው የሰጠሽን እግዚአብሔር ይስትሽ
@hiwel9209
@hiwel9209 Жыл бұрын
ኤልሲዬ ሁሉም ሰው አንድ አይደለም ወዶ የሚቀየም ወይ ከሰው የሚርቅ እኮ የለም ግን ሲበዛስ የሰው ነገር ጭራሽ ከራሳችን እየበለጠ የቤት ስራ ሲሆንስ ?በተለይ በተለይ ስደት ላይ ሲሆን እኮ ብዙ ሆድ የሚያስብስና የሚያስከፋ ነገር ሲኖር የገዛ የሀገር ልጅ የበለጠ ቀድሞ መቶ መንገድ ከማሳየት ይልቅ የበለጠ ክፋት ይዞት ግራ ሲያጋባንስ ?እንዴት ከሰው አይራቅ ኤልሲዬ ወዶ ከስው ማንም መራቅና ብቸኛ መሆን የሚፈልግ ያለ አይመስለኝም በትክክል ኢንፎርሜሽን ያስፈልጋል ግን ደግሞ ለዛ ተብሎ አስመሳይ መሆንና ተፈጥሮን ማጣትስ ለምን አስፈለገ ቻይ ለመሆንም እኮ የግድ እራስን ማስጨነቅ ወይ አስመሳይ ሆኖ ከማንነት መውጣት ይከብዳል ፈጣሪ ከስጠን እሱን ያከበረ ስለራሱ መልካም የሆነ ለሌላውም ይሆናልና ከተቻለ አለበለዛ ጎግል ላይ ኢንፎርሜሽን ዛሬ በደንብ ይገኛል እኮ እንደመጣሁ ንፁ ንፁ ልብ ይዤ መጥቼ በገዛ የሀገሬ ልጆች በጣም በጣም አዝኜ አዝኜ ነበር በቃ ከሰላምታ ጀምሮ እስከ ስራ ፍለጋና ሀገሩን መልመድ ግን ስጠይቃቸውም ሆነ ሰላምታ ስሰጣቸው እጅግ በጣም ተቃራኒ ከመሆናቸው የተነሳ የመጣሁበትን አላማ እስከመዘንጋት ደርሼ ለምን ግን እንዲ ይሆናሉ ለምን ግን ለምን ግን እያልኩ ሰክሬ ሰክሬ ከስንት ግዜ በኃላ ወደራሴ ለመመለስ ትግል ልይ ነኝ ኤልሲ ሰው ወዶ አይደለም ከውሻም ሆነ ከሲሪጋ መሆን የፈለገው በቃ ትልቁና ዋናው ጉዳይ አስመሳይ መሆን የማይችል ሰው ለሰው ብሎ እራሱን መቀየር ላይችል ይችላል ስንት ከጦጣ የባሱ አሉ እኔ እንደነሱ ለመሆን ምን አስጨነቀኝ ስንሰደድ እኮ ፈጣሪን እንጂ ሰውን አይተን አይደለም እኔ በበኩሌ ሀገሬ ላይ እጅግ በጣም የምወዳቸው የማከብራቸው እነሱም እንደዛው የሆኑ ብዙዎች አሉ እዚ የውጪው አለም ላይ ግን ፈተና ፈተና የሆኑብኝ ምናልባትም የሆንኩባቸውም አሉ ለምን ምንም ምክንያት የለም በቃ ልቀርባቸው ፈልጌ ስለሀገሩ ስለአኗኗሩም ኢንፎርሜሽን ፍለጋ ያላስከፈሉኝ መስዋትነት የለም ጭራሽ የሀገር ልጅ እንዲ ከሆነ የሌላው የማላውቀው እንዴት ይሆን ብዬ ፈርቼ ሁሉ ነበር ከራሴ ይሆናል ሁሉም ብዬ እነሱንም ለመምሰል ሞክሬም ነበር ያልተፈጠርኩበትን ግን እንዴት ልቻልበት ሀሜት ጠላቴ ነው መስረቅም እንደዛው አረ ስንት አለ ስራ ካስገቡሽ ሲሰርቁ ተባባሪ ካልሆንሽ ጠላት ነሽ ሲያሙ አብረሽ እውነት ነው ካላልሽም ጠላት ታዲያ የምትጠይቂያትን የምትነግርሽ ሲሪ አትሻልም ?ለማንኛውም ሁሉም ሰው ይለያያል እኔ እያስመሰልኩ ከምኖር ወደ ፈጣሪዬ እጄን ዘርግቼ ሁሌም መልስ አገኛለሁ በሰው ተከብቤ የሰው ረሀብ ነበረብኝ ያን ደግሞ ከፈጣሪ በላይ ክፍተቴን የሞላልኝ እንደሌለ ነው የተረዳሁት ባህር ውስጥ ቆም ሰው እንዴት ውሀ ይጠማል ብዬ እራሴን እጠይቅ ነበር ዛሬ እግዚአብሄር ይመስገን ከማንም በላይ እሱ ጋደኛዬ መሪዬ የኢንፎርሜሽኔም ምንጭ እሱ ነው
@HB-kv6xf
@HB-kv6xf Жыл бұрын
እኔም እንዳችው ተሸውጄ ነበር
@medihabeshawit8582
@medihabeshawit8582 Жыл бұрын
በጣም ትክክል ሰው ወዶ ብቸኝነት አይመርጥም የልቤን ነው የተናገርሽው🙏
@hanaayela2023
@hanaayela2023 Жыл бұрын
ኤሊሲዬ ተባርኪ ሁሌ የምትናገራቸው ነገሮች ትልቅ ትምህርት አለው. ካንች ብዙ ተምራለሁ ሰላምሽ ይብዛ የኔ ልዩ ሴት
@user-kx3jp3in9w
@user-kx3jp3in9w Жыл бұрын
በጣም ኣመስገናለው የኔ ውድ እንየ ሳልፈልግ በፍጥነት ኣኮርፋለው ማለት ቅም ኣይዝም ግን በፍጥነት ነው እማከርፈው ለምን ድነው የማኮርፈው ብየ ራስየ በራስየ በጣም ነው እምናደደው ፈጣር ለሁላችንም ትእግስት ይስጠን
@brktiazmara9736
@brktiazmara9736 Жыл бұрын
ወይ ኤልስየየየ የልቤን አወራሽልኝ በእውት እንዳቺ የለም ስለ ሁሉም ነገር አሰተማረ ነሽ እግዚአብሔር ያክብርሽ እኔ በበኩሌ በጣምም አመሰግንሻለሁ ❤️❤️❤️❤️❤️
@LoveAndPeace2424
@LoveAndPeace2424 Жыл бұрын
ዋው! ለህይወታችን ለእኛ ሴቶች በጣም ጠቃሚ ምክር ነው ያካፈልሽን። በተለይ ከነጥቦቹ መሀል የሌላውን ሰው አመለካከትና ውሣኔን ስለማክበርና ያልሽን፣ አሁን ሀይማኖትን በተመለከተ ስለአንቺ እያወቁ ቆራቢም ትሆኛለሽ ነገር ግን እኛ የምንከተለውን ተከተይ ምናምን ይሉሻል፣ ይሉኝታ ይዞሽ የማታስቀይሚያቸው ሰዎች ናቸው እንዴት ከባድ ነው።
@ZiniTube
@ZiniTube Жыл бұрын
You are like a fresh air elsiye ❤❤❤❤❤ ቃለ ህይወት ያሰማልን😃 🙏🏽
@zaharaahmed6290
@zaharaahmed6290 Жыл бұрын
አይ አንቺ ቅመም! እንዴት ሰነበትሽ? (ጥልል ) ማድረግ ያልሻት ቃል ተመችታኛለች! like!!!
@ethioelsylifestyle9486
@ethioelsylifestyle9486 Жыл бұрын
Zaharaye ማጥለል ስትለምጅ መከፋት ታቆሚያለሽ 🤩♥️🙏
@aidabelay4749
@aidabelay4749 Жыл бұрын
mmm wow powerful message በሁሉ ቋንቋዎች ቢተረጎም አስተማሪ ነው ኢልሳ ሸኮር ልባም
@onelovehabeshal7934
@onelovehabeshal7934 Жыл бұрын
I like your positivity..you have good vibes and good energy which comes from intelligence and positive thinking. I wish i could be like you.GBU.ግን comment memeles kenseshal.😉
@halimatube6731
@halimatube6731 Жыл бұрын
የኔ ውድ እህት ጀግና ነሽ ከልብ እናመሰግናለን በጣም አሪፍ ምክር ነው ነገ በኔ ብሎ ማሰብ ይኖርብናል እውነት በጣም ነው ምናመሰግነው
@berhanehaleke4358
@berhanehaleke4358 Жыл бұрын
ምክርሽን ተቀብያለሁ ላስተዋለው በጣም ብዙ ጠቃሚ ምክር እራሳችንን ልናይበት የሚገባ ምክር ነው ተባረኪልኝ
@bertukansisay760
@bertukansisay760 Жыл бұрын
ኤልሲ በናትሽ አንች ምናልባት ተሳክቶልሻል ግን የኔ የምትይው ሰው ማግኘት ወይም በጣም ከባድ ነው አንዳንዴ ሲሪ ትችል ይሆን ትያለሽ ለማንኛውም እናመሰግናለን
@nunubelete8142
@nunubelete8142 Жыл бұрын
ኤልሲ እንደ ሁልግዜ ጠቃሚ ምክር ነው ተባረኪልን 🤗✌️
@Master_ofElements
@Master_ofElements Жыл бұрын
ልክ ነሽ ቶሎ መቀየም አያስፈልግም ኡፍ እኔ በትንሹ ነዉ የማኮርፈዉ አሁን መተዉ አለብኝ ሰምቶ እንዳልሰማ መሆን ነዉ የሚያስፈልገዉ የዉሻዉ ላልሺዉ እኔም በጣም ነዉ ለዉሻ እንደዚህ ሲሆኑ የሚያናድዱኝ
@joshsur7407
@joshsur7407 Жыл бұрын
ኤልሲ በጣም ነው የማከብርሽ ስለሰጠሽን ምክር እናመሰግናለን ተባረኪ ቅን ነሽ❤❤❤❤❤❤❤
@meazaaraya8080
@meazaaraya8080 Жыл бұрын
ጥሩ ነበር እሚመረጥ ሰው ቢገኝ መምረጥ ይቻል ነበር ፡ግን ሁሉም ያው ነው , ኣንድም ከኣንድም ኣቻልም ፡ ጥሩ ሰው የለም ።
@whatislove7252
@whatislove7252 Жыл бұрын
I agree with you 💯✅
@zayedzedan389
@zayedzedan389 Жыл бұрын
Me tooo sister especially at this time friend Made in China
@mere7099
@mere7099 Жыл бұрын
ኡፍፍፍ እንዴት እንደምወድሽ ኮ የኔ ቆንጆ በጣም ብዙ ነገር ካንቺ ተምሬያለው thanks 🙏
@mayasura9916
@mayasura9916 Жыл бұрын
ኤልስዬ ከአበሻ ጎደኛ እባብ ባሳድግ ጊንጥ ባላምድ እመርጣለሁ ኤልስዬ ከአንቺ በጣም እለያለሁ
@ethioelsylifestyle9486
@ethioelsylifestyle9486 Жыл бұрын
Mayaye ውይ ማሬ እንዴት ልብሽ ቁስል ቢል ነው 🥲ሁሉንም እርግፍ አርገሽ እንድትረሽው አርጎ ልብሽን ይፈውስሽ 🙏♥️🙏
@mayasura9916
@mayasura9916 Жыл бұрын
@@ethioelsylifestyle9486 amen
@mayasura9916
@mayasura9916 Жыл бұрын
@@ethioelsylifestyle9486 ኤልስዬ የስነልቦና መፀሀፍ ትን ለማንበብ ሞከርኩ ችግሩ ከኔ ቢሆን ነዉ ብዬ የተፈጠርነዉ ብቻችንን ምሉእ ተደርገን ነዉ የልብ ወዳጅ እንዲኖረን አደለም የልብ ወዳጃችን ጎደኛችን እግዚአብሔር ብቻ ነዉ መሆን ያለበት ሸዉ ያስፈልገኛል ከብለን ካሰብን አዎ ያስፈልገናል ግን እንደዉም ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ናቸዉ ሰዉ የሚፈልጉቱ ኤልስዬ ይቅርታ
@hamgf1951
@hamgf1951 Жыл бұрын
ኤልስዬ እንዳንቺ አይነት ምርጥ እህት ያብዛልን እቅጩን ነው የምትናገሪው እስተዋይ ነሽ በጣም ነው የምወድሽ የማከብርሽ ❤❤❤
@user-zy9wx8wt3y
@user-zy9wx8wt3y Жыл бұрын
ኤልሲየ አንደበትሽን እግዚአብሔር አምላክህ ይባርክዉ!!! 🙏❤️❤️
@yoditbeyene5075
@yoditbeyene5075 Жыл бұрын
የዛሬው ልዮ ነዉ!! ብዙ ቁም ነገር አግኝችቤታለሁ ። አመሰግናለሁ ኤልሲ
@duressotesso3082
@duressotesso3082 Жыл бұрын
ስለምክርም ጥሩ ብለሻል አለማስተዋል ይሁን አላቅም አንድን ነገር ካለፈ ቦሀላ ወደ መረዳት ስመጣ እከለ ያኔ ለምን አልነገረኝም ከነ ጋር አመታትን ሳይቆይ የማስተካክለውን ብዬ የማዝንባቸው ነገሮች ስላሉ ለራሴ ግን አንድ ሰው የተሳሳተውን ማለፍ አልችልም ሰው ለሆነ ሁሉ ያውም ዝግነትን ሳልመርጥ እና አግባብ ባይሆንም ግን በቅንነት ማድረገን የሚረዱኝ ይበልጣሉ እኔም እርካታን አገኝበታለው እናም ክፉም ይሁኑ መልካም ባለንበት ሁሉ የሰዎቹ ማንነት ሳይገደን መልሰን ለማናገኘው መንገደኛ የተሰማንን እንደሚያስፈልጋቸው ሁሉ በቅንነት እወታው እላለው ይቅርታ ስለ ፅሁፉ ብዛት !
@user-se7zo4wd5d
@user-se7zo4wd5d Жыл бұрын
በጣም ቆንጆና ምጥን ያለች ትምህርት ነዉ እናመሰግናለን እኔ እኳ ጎደኛ የለኝም ለወደፊቱ ይሆነኛል
@ethioelsylifestyle9486
@ethioelsylifestyle9486 Жыл бұрын
ዘሀራዬ ማሬ ጓደኛ በጣም ያስፈልገናል ውዴ 🙏♥️🙏
@jimmaworkurgessa8247
@jimmaworkurgessa8247 Жыл бұрын
በተለይ በሰው ሐገር ትልቁ ችግር ትክክለኛ ጓደኛ ማግኘት ነው::
@user-yi5ny5jg5i
@user-yi5ny5jg5i 7 ай бұрын
በተለይ በውጪ የምንኖር ሰዎች የ ልብ ጉአ ደኛ ከየት ይመጣል!? አብዛኛው ሰው ምስጢሩን እስክ ሞት ድረስ ነው የምደብቀው::ቢቀርብሺም ከ አንገት በላይ ነው::ከእንደዚ አይነት ሰው ብቸግንነት ይሻላል አልሲ::በውጪ የሚኖር ሰው ሰው የለውም ከ ፈጣሪ ውጪ::እሱ ብቻ አይጣለን የሰውንማ አይወራም::
@AlkelimatuTeyebaSedeka
@AlkelimatuTeyebaSedeka Жыл бұрын
ኤልሲ❤❤ የኔ ውድ አንቺኮ በእውነት ነው ምልሽ ወረቢ ህይወትን መስመር ታሲዣለሽ አንቺን የተከተለ ኤልሲ ህይወትን ባለው አቅም አጣጥሞ ይኖራል ኢልስዬ ❤የኔ ህይወት አላህ ይጠብቅሽ ከቤተሠብሽ ከምትወጅዉ ሁሉ ከክፉ ይጠብቅሽ ምክርሽ ከማር በላይ ይጣፍጣል ተባረኪ እህቴ 😘😍ስለራስ ሚስጥር ማውራት ስትዬ እራሴን ታዘብኩ የህይወቴን ሚስጥር በየዋህነት አዉርቼ ተሸማቀኩኝ ቢሆንም ግን በራሴ ጥፋት ስለሆነ ማንንም አልተቀየምኩም ግን ትምህርት አገኘሁበት ኤልሲዬ ምናለበት ድሮም ማውቅሽ ቢሆን 😢😘😍 قلوبنا مليئه بحبكم عامــــــــــــــــره باحترامكم حالمه بأن تكونوا في أحسن حال نرسل الود ولانرتقب الــــــرد ذاك حديث القلــــب للَـقلــــب احاطكم الله برعايــته ومٌنَ عليكم بمغفرتـــــــــــه وأمدكم بالصحة والعافيـــــــه ورزقكم اللُُه قًبّوَلُ الدعـــــــاء وبركة العمر،والعـافـيةمن البلاء وحفظكم الله من كل مكروه🌹 👆ኤልሲ ጸሎት በሚቀለኝ ቋንቋ ነዉ ያረኩልሽ ከልቤ ❤ስለምወድሽ ኢንሻአላህ ተረድተሽ እንደምትደሰቺ ተስፋ አደርጋለሁ አመሰግናለሁ 😘😍
@ethioelsylifestyle9486
@ethioelsylifestyle9486 Жыл бұрын
የኔ ማር ክብር ይስጥልኝ ተባረኩልኝ ሁላችሁም በያላችሁበት ውዶችዬ 🙏♥️🙏
@asamnewasamnew1069
@asamnewasamnew1069 Жыл бұрын
የኔ ምርጥ ሴት ጀግና ነሽ ፈጣሪ ይጠብቅሽ ከነቤተሰብሽ!!!
@mekdeswolde2287
@mekdeswolde2287 Жыл бұрын
በጣም ነው የምወድሸ በብዙ ነገር ምሳሌ የምትሆኚ ነሽ ብዙ ነገርም ተምሬያለሁ አመሰግናለሁ
@jesusislord6649
@jesusislord6649 Жыл бұрын
እሱ መርቆ ካልሰጠ ችግር ነው አብዛኛው ለጥቅም ነው የሚቀርቡት
@akelisiyangusi8802
@akelisiyangusi8802 Жыл бұрын
ኤልሲዬ ግሩም ርእስ ነው ያነሳሽው! እናመሠግናለን! አስተዋይ ልቦና, ሰሚ ጆሮ; ቅን አንደበትን ያድለን አሜን! ከ ባል ቤተሰቦች (አማች) ጋር ስላለ የአቀራረብ ሁኔታ ከ ልምድሽ ተነስተሽ እባክሽ ፕሮግራም ስሪልን?
@amarecht3464
@amarecht3464 Жыл бұрын
ተባረክ!!❤️ what an amazing thought. I felt that you spoke on behalf of me. Thank you!
@birtukanao4sa808
@birtukanao4sa808 Жыл бұрын
እውነትናዉ የኔአስተዋይ ❤️እናመሰግናለን 🙏
@tigisttessema673
@tigisttessema673 Жыл бұрын
ኤልሲ ይህ ምክር በተለይ በውጭ ለምንኖር ስዎች በጣም ጠቃሚ ምክር ነው። በውጪ የምንኖር ሰዎች ጋደኛ ማግኘት ቀላል አይደለም እንደ አንድ ስራ መፈለግ ያክል ነው እና ብልሃትም ያስፈልጋል እንዳልሽው ሆደ ሰፊ መሆን ወሳኝ ነው። እግዚአብሔር ይባርክሽ!🙌
@hannaabate5830
@hannaabate5830 Жыл бұрын
Thanks so much for your advice!!!!
@azebassefa270
@azebassefa270 Жыл бұрын
ኤልስዬ ጠቃሚ ምክሮች ናቸው እናመሰግናለን ተባረኪ❤️😘
@sebelsolo6381
@sebelsolo6381 Жыл бұрын
ወይ ጎደኛ እንኮን ጎደኛ ኖሮኚ ወሪ ላወራ ልተች ቀርቶ ካገሪ ከወጣሁ በሆላ ጎደኛ የምለው 🤔ምናልባት ስራዬ እና በስራ አካባቢ ዙሪያ የምለው ይሆናል ጎደኛዬ ! 🙏🏾💚💛❤️✌🏽🕊
@alganeshbahre8598
@alganeshbahre8598 Жыл бұрын
Me too
@hirutcolongo6107
@hirutcolongo6107 Жыл бұрын
ኤልሲ ቆንጆ ጥሩ ምክር ነው እግዚአብሔር የሚወደውን ስራ ነው የመከርሽ እናመሰግናለን 🙏🙏🙏
@360asbestosremoval2
@360asbestosremoval2 Жыл бұрын
ምርጥ ነሽ ኤሊሲ ሁሉንም ነገር ተረድተሽዋል ትክክል ነሽ
@ayuniayuni7145
@ayuniayuni7145 Жыл бұрын
በጣም ነዉ ምትመቺኝ የማየዉን movi ዘግቼ ነዉ የ ሰማሁሽ
@zeinabamohamed2872
@zeinabamohamed2872 Жыл бұрын
You right thanks ❤
@affymyoutube8869
@affymyoutube8869 Жыл бұрын
ማአሻአላህ ምርጥ ሰው ምርጥ ምክር አላህ ይባርክሽ::
@selamawitberhe4283
@selamawitberhe4283 11 ай бұрын
Very good advice . God bless you
@hopeful9719
@hopeful9719 Жыл бұрын
Elsiya, Thank you for offering your valuable advice.♥️
@betlhemmesfin3352
@betlhemmesfin3352 Жыл бұрын
ኤልሰዬ ተባረኪ በጣም መልካም ምክር ነው!!
@fatishow4466
@fatishow4466 Жыл бұрын
fatare edet argo new gen yefetereesh woow masha allah hullu negersh adeloshal shi amet nurelen bezu neger kanch tamrelew thank you my sister😍💚💚
@meazasolomon1367
@meazasolomon1367 Жыл бұрын
u r so right, tnx for sharing ❤
@rahwagebreselassie7017
@rahwagebreselassie7017 Жыл бұрын
እኔም ኣዲስ የቅርብ ሰው ወይም ጓደኛ ኣልይዝም ብዬ ወስኛለሁ፡ ግን እንዳልሽው ሚስጥርህን በሆድህ ይዘህ የማይመለከትህን ከመጠየቅ ተቆጥበህ፡ ርቀትህን ጠብቀህ መቀራረብ ነው፡ ያው ከሰው ጋር እየኖርክ መተዋወቁ ግድ ስለሆነ፡ እንጂ ሁሉም ሰው ወሬ ባቀባበል ብቻ ሆኗል ስራው፡ በጣም ጠቃሚ ምክር ነው የተናገርሽው፡ እግዚያብሄር ይስጥሽ
@yewubdarmamo6641
@yewubdarmamo6641 Жыл бұрын
you are right Elsy
@debbietefera3718
@debbietefera3718 Жыл бұрын
Sooo true. Tks Elsu
@hanitamitta7758
@hanitamitta7758 Жыл бұрын
Aber elsiye teru Neger new 👌 ቪዲዬሽን ግን ባላለቀ እያልኩ ነው እማየው ግን ደሞ ቶሎ ያልቅብኛል 😔❤️❤️❤️
@godisgood153
@godisgood153 Жыл бұрын
Elsie I am agree with you!! Stay blessed 🙏
@berkategirma407
@berkategirma407 Жыл бұрын
ደስ የሚል ምክር ነው ተባረኪ
@bruktaytabate3497
@bruktaytabate3497 Жыл бұрын
Good points,I learned a lot God bless 🙌 🙏 😘
@selamtesfa
@selamtesfa Жыл бұрын
Thanks you so much 💗 I always learn a lot from you ❤
@meronfisseha9999
@meronfisseha9999 Жыл бұрын
Tebareki Elsye konjo mikir enaten meselshihn zares Ejig betam amesegnalew❤😘😘🙏🙏
@prix205
@prix205 Жыл бұрын
Such a wise lady ❤
@tigistgirma621
@tigistgirma621 Жыл бұрын
Thank you my sister,amazing job God bless you !!!🙏👏🥰
@semiraeyob2153
@semiraeyob2153 Жыл бұрын
Wowwww thanks so much 🙏
@hesresistsxy6333
@hesresistsxy6333 Жыл бұрын
በጣም አመሰግናለሁ በቅድሚያ የእኔን ነገር ወጥተሽ ተናገርሽ እንደ ጓደኛ እንደ ዘመድ ቀረቢቸው የሚቀረኝ ነገር የለም በስተመጨረሻ ለልጄ ትምህርት እንዳታገኝ በጣም ተመቃኙ በነፃ ለሚገኝ እድል በተጨማሪም በቅንነት በማወራው ሰለገዛ ህይወቴ ቀኑ በዛውም ጠሉኝ አሰተማሪ ነሽ ይቅር ብያቸዋለሁ በአንቺ ቪድዮ የተነሳ
@sirun4047
@sirun4047 Жыл бұрын
Thank you so much you gave me a lot of advice. Thank you agian.❤❤❤
@hamerewerku9908
@hamerewerku9908 Жыл бұрын
ተባረኪ 🙏🙏
@kidistberhane5375
@kidistberhane5375 Жыл бұрын
Thanks for blessings you are. Egzhaber makary yhunehe.
@selamgh3379
@selamgh3379 Жыл бұрын
you absolutely right thanks for sharing sis god bless you and your family 🙏🙏🙏❤️❤️❤️
@mulumassa9214
@mulumassa9214 Жыл бұрын
Thanks is a good advise Sess
@azmimogs9271
@azmimogs9271 Жыл бұрын
ኤልሲየ በጣም ትክክል እናመሰግናለን 🙏
@demarisafrasa957
@demarisafrasa957 Жыл бұрын
Very Wise advice👍👍👍
@nandan6150
@nandan6150 Жыл бұрын
Thanks for sharing, I agree with you its good to be positive but, we also have to be mindful of our associates bc simply being nice is not gone solve the problem with a toxic person, respect is earned not given so we simply have to choose a positive circle rather than pretending 😉
@sarahwelcome2560
@sarahwelcome2560 Жыл бұрын
Thank you very much
@sebleseyoum9639
@sebleseyoum9639 Жыл бұрын
Very true and good topics ❤
@misrakbereka3075
@misrakbereka3075 Жыл бұрын
You definitely correct about friendship and communication skills .
@amruahmed4462
@amruahmed4462 Жыл бұрын
I like your idea.
@fevenasefa7766
@fevenasefa7766 Ай бұрын
Thank you so much!!
Jumping off balcony pulls her tooth! 🫣🦷
01:00
Justin Flom
Рет қаралды 26 МЛН
Sigma girl and soap bubbles by Secret Vlog
00:37
Secret Vlog
Рет қаралды 14 МЛН
A teacher captured the cutest moment at the nursery #shorts
00:33
Fabiosa Stories
Рет қаралды 52 МЛН
አንገቴን አስደፍተሀኛል አለችው 🥺
17:20
haileye royal
Рет қаралды 6 М.
Ask Dr Mehret -  ዶ/ር ምህረት ይጠየቃል Q122
14:55
KARMA AT SCHOOL 🏫 Stop time
0:32
dednahype
Рет қаралды 49 МЛН
I'm Excited To see If Kelly Can Meet This Challenge!
0:16
Mini Katana
Рет қаралды 24 МЛН
Doing This Instead Of Studying.. 😳
0:12
Jojo Sim
Рет қаралды 8 МЛН
бим бам бум💥💥 типа..
0:18
Ma1x1
Рет қаралды 7 МЛН
Don’t Stealing 👵Moral Stories for kids #kidsvideos #goodhabits #youtubekids #cartoon
0:21
Elizabeth and Briceida Learning & Fun
Рет қаралды 15 МЛН