ኑር አምባ | ዋሪዳ 6 | NUR AMBA | WARIDA 6 | NEW ETHIOPIAN MENZUMA\NESHIDA | አዲስ መንዙማ\ነሺዳ

  Рет қаралды 1,826,725

Muaz Habib - official

Muaz Habib - official

10 ай бұрын

ኑር አምባ | ዋሪዳ 6 | NUR AMBA | WARIDA 6 | NEW ETHIOPIAN MENZUMA\NESHIDA | አዲስ መንዙማ\ነሺዳ
_____________
• ኑር አምባ | ዋሪዳ 6 | NUR A...
• ኑር አምባ | ዋሪዳ 6 | NUR A...
*************
Warida is the ultimate next generation Ethiopian Menzuma & Nasheed Groups
KZfaq: / @waridatubeoffcial
Telegram: t.me/WARIDATUBEOFFCIAL
Facebook: / waridatubeoffcial
⤵️⤵️⤵️➖➖⤵️⤵️➖➖⤵️⤵️
በKZfaq: / muazhabibofficial
በFacebook: / muazhabibofficial
በTelegram:
t.me/MuazHabibOfficial
*
ከላይ በተጠቀሱት አድራሻዎች Subscribe Like እና Join በማድረግ የስራዎቼ ተከታታይ ይሁኑ!
ሙዓዝ ሐቢብ ነኝ እወዳችኋለሁ !
#ኑር-አምባ ነሺዳ ግጥም
ከደጅዎ ሲጠጋ ሰባራ እኔነቴ፣
አልቃና አለኝ ተደፍቶ አንገቴ፣
እኔስ መጣሁ እንጂ ደፍሬ መዲና፣
መች ይገባኝ ነበር ይህ ክብር ይህ ዝና።
ተጠራሁ ልቤ ተነሳ
ደርሶልኝ ያ’ላህ ቀጠሮ፣
እግሬ ቢያንስብኝ ለጉዞ
ክንፍ አሻኝ ለመሄድ በርሮ፣
ኑር አምባው መሐል ደርሼ
ከጅዬ ‘ንዲሽር ህመሜ፣
ምን ጉድ ነው ሸውቁ ባሰብኝ
ሲፈታ የዘመን ህልሜ።
ሰምሮልኝ ዕድል ዕጣዬ
ብወፈቅ መድረስ ኑር አምባ፣
ወኔ አጣሁ ደፍሮ ለመዝለቅ
ከቅፅርዎ ከቶ እንዴት ልግባ፣
ታስሬ ሃያእ ጠፍሮኝ
ቆሜያለሁ ሰብሬ አንገቴን፣
ተስኖኝ ደጅዎ መጠጋት
አዝዬ ምስጢር ናፍቆቴን።
ከቀዬው ሳለ ወዳጅዎ
ናፍቆቱን ሠርክ ቢሰድም፣
አማናው የጎደለበት
እንዳሻው አይራመድም።
ቢከጅል መጠጋት ደጅዎ
ጥፋቱን ጉያው ሸሽጎ፣
እንደምን ከበርዎ ይድረስ
ተሳስሮ ኧረ እንዴት አድርጎ።
አልፊ ሰላለህ ዓለይካ
አልፊ ሰላሚ ዓለይካ
አንቱ የከውኑ ነጋሴ
ናፍቆትሁ የለውም ዲካ
ከረውዳው ለመድረስ ቢከጅልም ልቤ፣
ከቶ እንዴት ልጠጋ እንደምን ተስቤ፣
ቃል ማውጣት ተስኖኝ ታስሮ አንደበቴ፣
ደጅሁን አያለሁ ቢታገስ ናፍቆቴ።
ሃያትን በሚዘይነው
የስክነት ሸማን አልብሶ፣
በኑር መስክ ላይ መገኘት
መድመቅ ነው ብርሃን ተውሶ።
ዕጣው ቢደርሰኝ ከረህማን
በደጅዎ ‘ሚያመላልሰኝ፣
እንዲያ ናፍቄ እንዳልከነፍኩ
እውነቱን ማመን ተሳነኝ።
ሲከንፍ የመጣ ናፋቂ
ጨክኖ ካገርዎ ደርሶ፣
ሲያነባ ይነጋበታል
ላይወጣ ናፍቆት በልቅሶ፣
ምን አለኝ ብዬ ልጠጋ
ጎድሎብኝ ያንቱ አማና፣
እንደምን ልድረስ ከደጅዎ
በፀፀት እንዴት ልቃና፣
ቆሜያለሁ ህመም ታቅፌ
የሩቅ ሰው ባይተዋር ሆኜ፣
ቁጭቴን ጉያዬ አኑሬ
ኑር አምባ መሃል መንኜ።
ተመኘሁ ወኔውን መዋስ
ከሰልማን ከፋርሱ አበባ፣
ዘይሬሁ እንዲወጣልኝ
በናፍቆት ረውዳ እንድገባ።
ብትከዝ ቀኔ ጨልሞ
ሃለቴ ካንቱ ቢርቅም፣
የረህማን እዝነት ኪዳን ኖት
አፍሬስ ቤትዎን አለቅም።
ሞልቶልኝ ጦይባ ደርሼ
ብቆምም ጠርዙን ታክኬ፣
ቢያቅተኝ እግሬን ማላወስ
ቁዘማው ቢሆንም ልኬ፣
ሊምረኝ ሽቶ ነው እንጂ
ያመጣኝ ልቤን ቀስቅሶ፣
አዳልጦኝ ብወድቅ እንደሰው
መች ቀጣኝ ረሂም ታግሶ፣
ሙሂቡ ከሚነግስበት
ዓለሙ ሙራዱ ሞልቶ፣
ቆሜያለሁ ተራ እስኪደርሰኝ
ቢያይልም ብርቱ ናፍቆቶ።
ቁስለኛው አማና አጉዳዩ፣
የቆመው ሃረምዎ ላይ፣
አፍሮ እንጂ ሃሉ ቢዛነፍ
ነበረው ብርቱ ጉዳይ፣
አልፊ ሰለላህ አለይካ አልፊ ሰላሚ ዓለይካ
አንቱ የከውኑ ነጋሴ ናፍቆቶ የለውም ዲካ×2
የሸውቅዎ ወጀብ ወርውሮት
ስላንቱ ሰርክ እንዳለመ፣
ኸበርዎን እያደመጠ
ሳያዮት እንደታመመ፣
ሚለብሰው እራፊ አጥቶ
በሀሩር እየተቀጣ፣
መሃባ እያንሳፈፈው
ጆንያ ታጥቆ እንደወጣ፣
የዐይኑን ረሃብ ሊያስታግስ
ኬላውን ጥሶ ድንበሩን፣
እረፍቱ ትጋቱ ሆኖ
ሰይዲን እስኪያይ ጀንበሩን፣
ዘለቀ ጦይባ ከተመ
ሞልቶለት ደጆ ደረሰ፣
ናፋቂ ምን አካል አለው
ጆንያም ሃርም ለበሰ፣
ናፍቆቱን የዓይኑን ሲሳይ
በስስት እያየ አሻግሮ፣
ተጠጉት ሰይዲ መጡ
ምን ይሁን ቆመ አቀርቅሮ፣
ባገለደመው ጆንያ
በሸውቁ ህመም ማህተሙ፣
ዙል ቢጃ ደይን ብለው
ሰየሙት ሰይዲ ልቡን አከሙ፣
የናፍቆት ህመሜ ሲያይል
መሃባው ደርሶ ሲንጠኝ፣
ስናፍቅ የኑር አምባዎን
አጀሌ ሲያስደነግጠኝ፣
የዙልቢጃደይን ወዳጅዎ
እየታወሰኝ ሃለቱ፣
ሸውቅ ላስጌጠው ጆንያው
በሆንኩኝ ዝምዝም ጥለቱ፣
ባረገኝ የሸውቁ ወራሽ
የሚያከንፍ ወደ ኑር አምባ፣
ስም እንዲያወጡልኝ ሰይዲ
በስኬት ቤቴ እንድገባ!!
ግጥም:- ሙሀመድ ፈረጀ
ዜማ :- ሙዓዝ ሀቢብ

Пікірлер: 484
@TofikYusuf
@TofikYusuf
ቆምያለሁ ተራ እስኪደርሰኝ ሳይገለኝ ብርቱ ናፍቆቶ የኔ ነብይ😢😢 ወላሂ ባሰብኝ 😢 አላህ ይውደድላቹ
@MohammedAwol-ph3ex
@MohammedAwol-ph3ex
አላህ ሁላቺንንም የእውነት የነብዩ ሰ.ዐ.ወ ወዳጅ ያድርገን አሚን
@mamemome8341
@mamemome8341
መንዙማዉ ኢማን ያጠናክራል። የአላህን ቁድራ፣ ራህመት፣ እዝነት፣ ታጋሸነት እና ርህራሄ ያመላክታል። ክብሩ ይሰፋ፣ በሰራጠል ሙሰተቂም ላይ ያሰብተን። ከሰይጣን ተንኮልና ሸር ይጠብቀን።
@sadiaabduseid8825
@sadiaabduseid8825
ሙአዝ ሀቢብ ይህሁሉ ያንተ ውጤትነው አንተ ትለያለህ ማሻአላህ ዋሪዳ አንደኛ ናችሁ❤❤❤❤
@JemalMehamed-ss7ng
@JemalMehamed-ss7ng 12 сағат бұрын
ማሻአላህ ውዱየኔ ነቢእወድወታለሁ ❤❤
@user-ts1ir7bp5l
@user-ts1ir7bp5l
😢😢😢😢😢 ያረብ ስሰማዉ አለማልቀስ አልቻልኩም
@selhadinsala4223
@selhadinsala4223
ያረቢ እኛንም ወፍቀንና ውዱ ሰውን❤ እንዘይር 🤲🤲🤲
@EKRAMAFRE
@EKRAMAFRE
የኔውዶች አላህ ይጨምርላቹህ 😢😢😢
@user-ho5gk3sp3q
@user-ho5gk3sp3q
የኛ ዉድ ነብይ ረሱል ሶለላአለይ ወሰለም❤❤❤❤እኖዳችኋለን ❤❤❤❤❤
@rahimaabdul921
@rahimaabdul921 14 күн бұрын
Masha allah❤❤❤❤❤❤❤
@fuadmseman7416
@fuadmseman7416
ሊምረኝ ሽቶ ነው እንጂ
@AishaAbrahim-ee5hk
@AishaAbrahim-ee5hk
አላሁ መሰሊ አላ ሙሐመድ ሰለላሁ ዓሌሒ ወሰለም ያአ ሐቢቢ ያአ ረሱሉላህ እንኳን አብሮ አደረሰ❤ለሐቢቡና ሙሐመድ መወሊድ❤አላሁ መሰሊ አላ አሸራፊል ኸልቂላህ❤ያረብ በረህመትህ ጀናት ጉርብትናቻወን ወፍቀኝ አሚን አላሁማ አሚን ❤ወድ ወንድሞች ጀዛኩሙላሁ አልፍ ኸይረ ጀዛአ❤
@user-br8eg2fh4f
@user-br8eg2fh4f
ماشاءالله ماشاءالله ماشاءالله ماشاءالله اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد صلى الله عليه وسلم 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
@user-qs5sj5nj9c
@user-qs5sj5nj9c
እኔስ መጣው እንጂ ደፋሬ መዲና መች ይገባኝ ነበር ይክብር ይዝና😢❤❤❤❤❤❤
@user-ny8uz6ee7y
@user-ny8uz6ee7y
Wellahi yihen ssema anbayen mekotater yaktegnal
@foziyahaile9418
@foziyahaile9418
አላህ ይጨምርላችሁ ማሻአላህ ምቀኛችሁ ድብን ይበል በዚሁ ቀጥሉበት
@user-zx7qw4uy9m
@user-zx7qw4uy9m
የኔ ውድ ነቢይ ናፍቆቴ
@HamduIbrahim
@HamduIbrahim
እጅግ ድንቅ ስራ ወላሂ!
@Habbu605
@Habbu605 Күн бұрын
Saw mashalla mashalla mashalla 😢😢❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@Rifan-Sherif
@Rifan-Sherif
Perfect combination Muaz and Mohammed Ferej.👏🏼
MISS CIRCLE STUDENTS BULLY ME!
00:12
Andreas Eskander
Рет қаралды 20 МЛН
23 July 2024
8:43
Nejat abdulukdir Abdulukadir
Рет қаралды 6 М.
ሀያተል ዐለም/ Hayatel Alem Fuad shemsu new menzuma video clip 2022
15:47
FUAD SHEMSU OFFICIAL
Рет қаралды 4,3 МЛН
ባትመጡማ በአዲስ መልኩ በሀረር ዋሪዳ 5 የመድረክ ዝግጅት ላይ የቀረበ| BATMETUMA HARAR WARIDA 5
13:49
Warida Islamic Art Group ዋሪዳ ኢስላማዊ የጥበብ ቡድን
Рет қаралды 1,8 МЛН
ያ አህለል ጀና (የጀነት ሰዎች) | #ዋሪዳ_6 |  YA AHLEL JENNAH | አዲስ ነሺዳ
12:35
Warida Islamic Art Group ዋሪዳ ኢስላማዊ የጥበብ ቡድን
Рет қаралды 938 М.