Рет қаралды 14,609
ጭርት በጣም የተለመደ የቆዳ ኢንፌክሽን ሲሆን የሚፈጠረውምሉ ቲንያ በተባለ ፈንገስ ምክንያት ነው በዚህ ቪድዮ ከኬሚካል የነፃ የጭርት መድሃኒት ምንድን ነው ለሚለው ጥያቄ መልስ ያገኛሉ
ጭርት ለማጥፋት በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ ውህድ ለጭርት ፍቱን መላ Get Rid of ringworm at home
#Birabiro ቢራቢሮ #
ጭርት አንዳንድ ጊዜ አንድ ቦታ ብቻ ወይም ሁለት ሶስት ቦታ ላይ የሚወጣ ቆዳው ከሌላው በተለየ ሁኔታ የቀላና የተቆጣ የማሳከክ ባህሪ ያለው ክብ ቅርፅ ሆኖ እየቆየ የሚሰፋ በፈንገስ
ምክንያት የሚመጣ ተላላፊ የቆዳ በሽታ ነው
ጭርት ያለበት ሰው የነካቸውን ነገሮች ቁሳቁሶች በፈንገሱ የተበከለ አፈር : ከቤት እንስሳትን አቅፋችሁ: በጋራ የመታጠቢያ ቦታዎች በባዶ እግር በመሄድ፡ ይተላለፋል
የፀረ ፈንገስ ክሬሞችን በመጠቀም በቀላሉ ሊድን ይችላል
ቆዳን ንፁህና ደረቅ ማድረግ ምክንያቱም ፈንገስ እርጥበትን ስለሚወድ
በጋራ የመታጠቢያ ቦታዎች በባዶ እግር አለመሄድ፡ ጠባብ ጫማ አለማድረግ: ክፍት ጫማ ማድረግ፡ በጋራ አልባሳትን አለመጠቀም ፎጣን :አንሶላና የአልጋ ልብስ ጭርት ካለበት ሰው ጋር ያለመጋራት፡ እጅን ከንክኪ ቡሃላ በውሃና በሳሙና መታጠብ
ሻወር ከተጠቀሙ ቡሃላ ሙልጭ አድርጎ ማፅዳት
ፈንገሱ ወደሌሎች ቦታዎች እንዳይዛመት አለማከክ
በበሽታው የተጠቁ እንስሳትን (ድመትና ውሻ) ማሳከም
በተፈጥሮአዊ መንገድ ለማከም የሚቻል ሲሆን
ነጭ ሸንኩርት
የተፈጨ ነጭ ሽንኩርትን ከኮኮናት ወይም ከወይራ ዘይት ጋር አደባልቆ በቀን ሁለት ጊዜ ለሁለት ሰአታት ቀብቶ ሸፍኖ ማቆየትና መታጠብ
አፕል ሳይደር ቪኔጋር (አቼቶ)
በቀን ሶስት ጊዜ አፕል አቼቶን በጥጥ እየነከሩ ጭርቱ ያለበትን ቦታ መቀባት
እሬት
ፀረ ባክቴርያ ፀረ ፈንገስና ባህሪ ስላለው የእሬትን ጄል መቀባት የማሳከክና የማበጥ ችግሩን ያስታግሰዋል
የኮኮናት ዘይት
በኮኮናት ዘይት ውስጥ የሚገኙት ፋቲ አሲዶች የፈንገስ ሴሎችን ሴል ሜምብሬንን በማበላሸት ፈንገሶቹን ይገድሏቸዋል ስለዚህ በቀን 3 ጊዜ የኮኮናት ዘይት መቀባት
እርድ
እርድን በኮኮናት ዘይት በወፍራሙ በጥብጦ ቆዳውን መቀባትና እስኪደርቅ ድረስ መተው ከዛም መታጠብ
ቲ ትሪ ኦይል (ዘይት)
የተበረዘ ቲ ትሪ ኦይልና ኮኮናት ዘይት አደባልቆ በቀን 3 ጊዜ መቀባት የቆዳ አለርጂ ወይም ቶሎ የሚቆጣ ቆዳ ከሌለ ደግሞ ራሱን ቲ ትሪ ኦይል ሳይበረዝ መጠቀም ይቻላል
የኦሬጋኖ ዘይት (ዋይልድ ኦሬጋኖ)
የተበረዘ የኦሬጋኖ ዘይትን በቀን 3 ጊዜ መቀባት ቆዳን (ስትገዙ በደንብ ማየት ኮመን ኦሬጋኖ በብዛት ገበያ ላይ ያለ በመሆኑ)
ሌመን ግራስ ኦይል
የሌመን ግራስ ዘይት በሌላ እንደ ኮኮናት አይነት ዘይት በርዞ በቀን 2 ጊዜ በጥጥ እየነከሩ ቆዳውን መቀባት
መቼ ነው ዶክተር ጋር መሄድ ያለብን
እነዚህ መድሃኒቶች ተጠቅማችሁ ችግሩ ካልተወገደ ፀረ ፈንገስ ታብሌቶችን ፈንገሱ በሙሉ ሰውነታችሁ ላይ ከተዳረሰ ወይም ስር የሰደደ ከሆነ ወይም ክሬሞችን ሊያዝላችሁ ይችላል#Birabiro ቢራቢሮ#የጭርት መነሻ#የጭርት መንስኤ#የጭርት መዳኒት#የጭርት መድሀኒት#የጭርት መድሀኒት ምንድን ነው#የጭርት መድሐኒት#የጭርት ማጥፊያ#የጭርት በሽታ ምልክቶች#ጭርት መነሻው#ጭርት ምንድነው#ጭርትን በተፈጥሯዊ መንገድ ማጥፊያ/get rid of Ringworm naturally#የጭርት መተላለፊያ#ringworm treatment