የድሬዳዋ “ሳልቫጅ ተራ” በቃጠሎ ወደመ | Dire Dawa | market | fire | Ethiopia Insider

  Рет қаралды 54,373

Ethiopia Insider

Ethiopia Insider

23 күн бұрын

በድሬዳዋ ከተማ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 25፤ 2016 የተነሳው የእሳት ቃጠሎ፤ በተለምዶ “ሳልቫጅ ተራ” ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ “ሙሉ በሙሉ” እንዳወደመ የከተማው ከንቲባ ከድር ጁሀር ተናገሩ። ለአምስት ሰዓታት የዘለቀው ቃጠሎ “ሩዝ ተራ” እና “ማሽላ ተራ” የተባሉ አካባቢዎችን እንዳወደመ ከንቲባው ለከተማው የቴሌቪዥን ጣቢያ ገልጸዋል።
በተለምዶ አሸዋ ተብሎ በሚጠራው ዋነኛ የንግድ አካባቢ “ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ” የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎ፤ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ እኩለ ቀን ስድስት ሰዓት ድረስ መቆየቱን የድሬዳዋ ከተማ የመንግስት ኮምዩንኬሽን ቢሮ አስታውቋል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የድሬዳዋ ነዋሪዎች፤ እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ድረስ እሳቱ ሙሉ ለሙሉ አለመክሰሙን ገልጸዋል።
የእሳት አደጋ ማጥፊያ ምሽቱን ጭምር ወደ ስፍራው ሲመላለሱ እና ውሃ ሲረጩ እንደነበር ነዋሪዎቹ አስረድተዋል። የከተማይቱ ፖሊስ ነዋሪዎች አደጋው ወደ ደረሰበት ስፍራ እንዳይጠጉ ጥበቃ ሲያደርግ መመልከታቸውንም የዓይን እማኞቹ አክለዋል።
በዛሬው የእሳት ቃጠሎ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ለመኖሩ በድሬዳዋ ከተማ ከንቲባም ሆነ በአስተዳደሩ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ሆኖም ቃጠሎው “ሳልቫጅ ተራ” እና “ማሽላ ተራ” የተባሉት አካባቢዎች “ሙሉ በሙሉ” ማውደሙን ከንቲባ ከድር ለድሬ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ቃጠሎው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ይስፋፋል በሚል ስጋት በአቅራቢያው የነበሩ ነዋሪዎች ንብረቶቻቸውን ሲያሸሹ ተስተውለዋል።
ቃጠሎው በደረሰበት አቅራቢያ ያሉ ስፍራዎች “በከፊል” መትረፋቸውን ከንቲባ ከድር አመልክተዋል። የእሳት ቃጠሎውን ለመቆጣጠር የድሬዳዋ እና የሐረር ከተሞች የእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ እና ሌሎችም አካላት ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ከንቲባው ጨምረው ገልጸዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
-----------------------------------------------------------------------------------------
የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider.com​
ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaInsiderNews
ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

Пікірлер: 33
@user-cb4wt4ym4v
@user-cb4wt4ym4v 21 күн бұрын
ደጉ ህዝብ ሆይ ደጉ አምላክ ይደግፍህ
@sendomalakumalaku5713
@sendomalakumalaku5713 21 күн бұрын
💔💔💔💔💔ድሬ አዝኛለሁ
@seadi83
@seadi83 21 күн бұрын
ውይይይይይይይይ😢😢😢እውነት ነው ወይኔ ሰው ተረፈ በምን ምክንይት ነው ይረብ
@seid8713
@seid8713 19 күн бұрын
😭😭😭Azegalhy💔💔💔
@wubekassa
@wubekassa 21 күн бұрын
በጣም ያሳዝናል ሰው ተርፋል ወይየሚገርመው እሳት እየነደደ ቆሞ የሚቀርጸው ሰው በጣም ይገርማል፡፡
@nasranasra1960
@nasranasra1960 20 күн бұрын
የአላህ አላህ ይድረስልን የእኛ ወንጀል ነወ የሱ ቁጣ መብረጃ የለወም በዲአ በምህረት ቢሆን እጅ
@tgyadingilmariyamlijtg1381
@tgyadingilmariyamlijtg1381 22 күн бұрын
Wayine amilake ladire dawa hizib ihe ayigabam faxari hoy dirasilachaw baxam yamal yasazinal waganoche igziabiher yiridachihu🖤🖤😭😭😭😭😭🤲🤲🤲🤲🤲
@YasminAbdulwahab
@YasminAbdulwahab 19 күн бұрын
Waayii diree rabbiin imaan haa kenuf waraa horiin sani gubate😢😢😢😢😢
@saditaqueenfouad2409
@saditaqueenfouad2409 17 күн бұрын
Dire dawa may love😢😢😢😢😢
@Abdi_king_671
@Abdi_king_671 22 күн бұрын
Yallah😢
@user-tl1ui2yj1u
@user-tl1ui2yj1u 22 күн бұрын
😢
@abebechalamni1777
@abebechalamni1777 14 күн бұрын
😢😢😢😢😢😢
@Semiraahmed-zf2rz
@Semiraahmed-zf2rz 15 күн бұрын
Batam yesesnal
@abebechalamni1777
@abebechalamni1777 14 күн бұрын
አሁን ይህ ምን ይሉታል ንብረት እየወደመ እያየን ማልቀስ ነው ወይስ ቪድወ ማንሳት ይቅር ይበለን ለድሬ ህዝብ ይህ አይገባውም ፍቅር ነበር አንድነት ነበር ከነሱ የተማርን ብቻ ምን ማድረግ ይቻላል እይዞችሁ እናተ የፍቅር ሰው እናግዛለን
@user-jf7xn4uw5f
@user-jf7xn4uw5f 21 күн бұрын
😭😭😭
@ethiopia6344
@ethiopia6344 21 күн бұрын
መቸነው ያአላህ
@user-ts5jp9cx1r
@user-ts5jp9cx1r 21 күн бұрын
😢😢😢🤲🤲🤲🤲
@abrashuae2199
@abrashuae2199 20 күн бұрын
አራበጌታስም😢😢😢😢😢
@saditaqueenfouad2409
@saditaqueenfouad2409 17 күн бұрын
Dire dawa alleh ha ka karkaro
@HaileBeza
@HaileBeza 20 күн бұрын
አይዟችሁ ድሬዎች
@user-hr7ir9it1z
@user-hr7ir9it1z 21 күн бұрын
Fetar. Stnatun. Yisitachew
@HamdiyaHassen
@HamdiyaHassen 21 күн бұрын
😢😢😢😢ay dire yalfal
@user-jv9qo5mt5c
@user-jv9qo5mt5c 20 күн бұрын
Akatlwearsute
@user-gn2qh8pt6y
@user-gn2qh8pt6y 20 күн бұрын
ሰው ግን ተረፈ?
@AddisalemNegussie
@AddisalemNegussie 19 күн бұрын
ድሬ ላንቺ አይገባሽም
@dekahirsi3126
@dekahirsi3126 21 күн бұрын
😢😢🥱
@user-ey9ok6fk4p
@user-ey9ok6fk4p 21 күн бұрын
Way ethiopia mangisti indazi hoone
@matthewassefa1925
@matthewassefa1925 22 күн бұрын
Saddddd
@user-jv9qo5mt5c
@user-jv9qo5mt5c 20 күн бұрын
Ysaznale
@maruwerku
@maruwerku 19 күн бұрын
ስራ አጥ በማብዛት ወጣቱ አማርሮ እንዲወጣ የሚገፋፋው በስስ ስሜቱ ገብቶ ተቃውሞ እሚወጣበት እየተገፋፋ ነው
50 YouTubers Fight For $1,000,000
41:27
MrBeast
Рет қаралды 188 МЛН
How Many Balloons Does It Take To Fly?
00:18
MrBeast
Рет қаралды 166 МЛН
DEFINITELY NOT HAPPENING ON MY WATCH! 😒
00:12
Laro Benz
Рет қаралды 58 МЛН
Diree dhawaa Naannoo Ashawaa Ibbida  qabate
7:27
Direwood
Рет қаралды 31 М.
3ቱ የድሬ የገበያ ቦታዎች  | Diredawa market places
19:30