የዱባ ጥቅም /የዱባ ጥቅሞች/ Pumpkin benefits

  Рет қаралды 440

Birabiro ቢራቢሮ

Birabiro ቢራቢሮ

8 ай бұрын

በዚህ ቪድዮ የተዘረዘሩትን የዱባ ጥቅም ካወቁ በኋላ አዘውትረው ይጠቀሙታል /ዱባ ጥቅም/ Pumpkin benefits
ዱባ የተለያየ መጠንና ቅርፅ እንዲሁም ቀለም አለው
የቆዳው ቀለም ነጭ ፈዛዛ አረንጓዴ ጎመኔ ወይም ቢጫና ብርቱካናማ ይሆናል ዱባ ብዙ አይነት ምግቦችንና ጣፋጮችን ለመስራት ይጠቅማል የዱባ አበባም የተለየ ጣእምና የስነምግብ ጥቅም ስላለው ይበላል
ቫይታሚኖች
ማእድናትና አንታይኦክሲዳንቶች ካልሲየም አይረን ማግኒዝየም ሶዲየም ፖታሲየም ዚንክ ፎሌት ኮፐር ቫይታሚን ኤ ቫይታሚን ሲ ቫይታሚን ቢ6 ቫይታሚን ኢ ታያሚን ኒያሲን ሪቦፍላቪን ፓንቶቴኒክ አሲድ ሉቴይን ዚያዛንቲን ፓይሪዶክሲን፣ ካርቦሃይድሬት፣ፕሮቲን ቫይታሚን ቢ5 እንዲሁም ቤታካሮቲን የዳበረ ነው እነዚህ ንጥረነገሮች በተለያየ መንገዶች ለጤናችን ይጠቅማሉ
የቆዳና የፀጉርን ጤንነት ለመጠበቅ፣ ካንሰርን የመከሰት አጋጣሚን ይቀንሳል የልብ ህመምን ይከላከላል እንዲሁም ክብደት ለመቀነሰ ይረዳል. በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል
እነማን መጠቀም ይችላሉ?
ዱባን በየቀኑ ሳይበዛ መጠቀም የሚቻል ሲሆን የዱባ አለርጂ የሌለበት ሰው በሙሉ ሊመገበው ወይም ሊጠቀመው ይችላል
አለርጂ ያለባቸው ሰዎች ዱባ ከተመገቡ የጨጓራ ህመም ተቅማጥ፣ ማቅለሽለሽ፣ ማሳከክ፣ ሽፍታ፣ የመሳሰሉት ይከሰቱባቸዋል
የዱባ ጥቅም በዝርዝር ስናይ ደግሞ
ለቆዳ የሚሰጠው ጥቅም
ለሁሉም የቆዳ አይነቶች የሚሆን ሲሆን በተለይ በአካባቢ መበከል ምክንያት ለተጎዳና ለሴንሲቲቭ ቆዳ መጠቀም ይቻላል
ለቆዳ የሚሰጠውን ጥቅም በዝርዝር ስናይ ደግሞ
1. ቅባታማ ቆዳን ለማስተካከል
ቅባታማ ቆዳ ካላችሁ ለቅባታማ ቆዳ 1 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ዱባ 1 የሻይ ማንኪያ አፕል ሳይደር ቪኔገር ሁለቱን አንድ ላይ አዋህዶ በውሃ በራሰ ፊት ላይ መቀባትና እስኪደርቅ ድረስ ማቆየት ከዛም ለብ ባለ ውሃ መታጠብና በቀዝቃዛ ውሃ ማለቅለቅ የቆዳውን ቅባታማነት ለማስወገድ ይረዳል
2. ለደረቅ ቆዳ
ሁለት የሻይ ማንኪያ በስሎ የተፈጨ ዱባ ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ማር ሩብ የሻይ ማንኪያ ወተት ሩብ የሻይ ማንኪያ ክሬም እነዚህን በደንብ አዋህዶ ፊትን በማዳረስ መቀባት አይን አካባቢ ሳይነኩ ከዛም 15 ደቂቃ አቆይቶ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ
ይሄ ማስክ የሞቱ የቆዳ ህዋሶችን ያነሳል ቆዳን ይመግባል እንዲሁም ድርቀትን ይከላከልለታል
3. ቆዳ እንዳያረጅ
ዱባ ሃይለኛ አንታይኦክሲዳንት በሆነው በቫይታሚን ሲ ዳበረ በመሆኑና ቤታ ካሮቲንን ስለያዘ በ UV ምክንያት የተከሰተን ጉዳት ያድናል እንዲሁም የቆዳን ልስላሴ ያሻሽላል. የኮላጅን ምርት እንዲጨምር ይረዳል, በዚህም የተነሳ የቆዳ ቀለም እንዲያምርና የመለጠጥ ችሎታው እንዲጨምር ያደርጋል. ቆዳ ተጎድቶ እንዳያረጅ (እንዳይሸበሸብ በተጨማሪም በካንሰር እንዳይጠቃ ይከላከልለታል.
4. ጥቋቁር ነጠብጣቦችን ለማጥፋት
ጥቋቁር ነጠብጣቦችን ለማደብዘዝና ለማጥፋት 1 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ዱባ, 1 የሻይ ማንኪያ ማር, 1 የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ and 1 የሻይ ማንኪያ የቫይታሚን E ዘይት. ሁሉንም አደባልቆ በንፁህ ፊት ላይ መቀባትና እስኪደርቅ አቆይቶ ለብ ባለውሃ መታጠብ
5. የዱባ የሰውነት ማስክ
የሚያድስ refreshing የሚያደርግ የሰውነት ማስክ መስራት ይቻላል የሚያስፈልገው ግማሽ ኩባያ በስሎ የተፈጨ ዱባ ግማሽ ኩባያ ኮኮናት ፍቅፋቂ pumpkin puree with ½ cup coconut solids and ½ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ቀረፋ. ሙሉ ሰውነትን መቀባትና በስሱ ማሳጅ ማድረግ ከዛም ለ10 ደቂቃ አቆይቶ ለብ ባለውሃ መለቅለቅ This will refresh and relax your skin.
5. ብጉርን ለማዳን
ዱባ የቫይታሚን ቢ ጥሩ መገኛ ነው ኒያሲን ሪቦፍላቪን ፎሌት አለው ኒያሲን የደም ዝውውር እንዲጨምር ያደርጋል በዚህ የተነሳም ብጉርን ለማከም ጠቃሚ ነው
ፎሌት ደግሞ የደም ዝውውር እንዲሻሻል በማድረግ የሞቱ የቆዳ ህዋሶች ቶሎ እንዲቀየሩና እንዲታደሱ ያደርጋል
አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት በዱባ ውስጥ የሚገኘው አንታይኦክሲዳንቶች ብጉርን ለማጥፋት ይረዳል
ለቆዳ እንክብካቤ ከሚሰጠው ጥቅም በተጨማሪ ዱባ ለፀጉርም ብዙ ጥቅሞች ይሰጣል የፀጉር ስሮች ለማደግና ጤናማ እንዲሆን
6. ለፀጉር እድገት ያግዛል
ዱባ እንደ አልፋ ካሮቲን ፖታሲየምና ዚንክ ባሉ ማእድናት የዳበረ ነው ፖታሲየም ፀጉርን ጤናማ እንዲሆንና እንዲያድግ ያደርጋል ዚንክ ደግሞ helps maintain collagen and thus plays an important role in promoting healthy hair. የዱባ ፍሬ ዘይት ደግሞ የደም ዝውውርን በማሻሻል የፀጉር እድገት እንዲፋጠን በማድረግ ችሎታው ይታወቃል
6 የደረቀ ፀጉርን ያለሰልሳል ልክ እንደኮንድሽነር ሆኖ ያገለግላል
ደረቅ ፀጉር ካላችሁ በቀላሉ ዱባን ተጠቅማችሁ እንደ ኮንድሽነር የሚያገለግላችሁን የፀጉር ማስክ ለማዘጋጀት ትችላላችሁ 2 ኩባያ በስሎ የተፈጨ ዱባ 1 የሾርባ ማንኪያ የኮኮናት ዘይት 1 የሾርባ ማንኪያ ማር 1 የሾርባ ማንኪያ እርጎ አዘጋጅታችሁ እነዚህን በአንድ ላይ አደባልቆ በደንብ መፍጨትና ከዛም በእርጥብ ፀጉር ላይ ተቀብቶ ለ15 ደቂቃ በላስቲክ ሸፍኖ ማቆየት ከዛ መታጠብ
ዱባ ለጤና ጥቅም
7. በቤታ ካሮቲን የበለፀገ ነው
በቤታ ካሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን የሚመገቡ ሰዎች በካንሰር ብዙ አይያዙም
የሚያጨሱ ሰዎች ዱባን ቢመገቡ ይጠቀማሉ ምክንያቱም በዱባ ውስጥ የሚገኙት ቤታ ክሪፕቶዛንቲን እና ካሮቲኖይዶች Beta-Cryptoxanthin በሳንባ ካንሰር የመያዝ አጋጣሚያቸውን በጣም ይቀንሰዋል ኢንፍላሜሽንም እንዲቀንስላቸው ይረዳቸዋል
20. ከፕሮስቴት ካንሰር ይከላከላል
በዱባ ውስጥ በዛ ብለው የሚገኙት ካሮቲኖይዶችና ዚንክ ፕሮስቴት ካንሰርን ይከላከላሉ
8. የደም ግፊትን ለመቀነስ
በፋይቶኤስትሮጂን የተሞላ ስለሆነ የደም ግፊትን ለመቀነስና እንዳይከሰት ለመከላከል ይጠቅማል
9. የጨጓራና የአንጀት ቁስለት እንዳይከሰት ይከላከላል
ዱባ አስደናቂ ውስጥን የሚያፀዳ detoxifying ምግብ ነው. መርዛማ ነገሮችንና ቆሻሻን ከሰውነት አጣጥቦ በፈሳሽ መልክ ለማስወገድ ይረዳል የመድሃኒትነት ባህሪው ደግሞ ጨጓራና አንጀት እንዲረጋጉ በማድረግ የአንጀት የጨጓራና የደንዳኔ ቁስለትን ይከላከላል
10. በፋይበር የበለፀገ ነው
ዱባ የቫይታሚ ኤ አይነት የሆነው የቤታ ካሮቲን አስደናቂ መገኛ ነው ይሄም የምግብ መፈጨትን ያግዛል እንዲሁም የሆድ ድርቀትን ይከላከላል
ለረጅም ሰአታት የጥጋብ ስሜት እንዲኖር ያደርጋል
11. በሽታ የመከላከል አቅምን ለማሳደግ
ቤታ ካሮቲንና ቫይታሚን ሲ በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋሉ እንዲሁም ጉንፋን ኢንፌክሽንና አለርጂንም ይከላከላሉ
አንታይኦክሲዳንት ባህሪው ዱባ የመተንፈሻ አካላትን ኢንፌክሽኖች እንዳይከሰቱና አስም እንዲቀንስ ቶሎቶሎ እንዳይነሳ ያደርገዋል
12. ለልብ ህመምን እንዳንጋለጥ
በዱባ ውስጥ ያለው በዛ ያለ አንታይኦክሲዳንት አርተሮስክለሮሲስ (የደም ቅዳ መደደር).እንዳይፈጠር በማድረግ የልብ ህመምንና እስትሮክን ይከላከላል ለደም ግፊት የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል
ዱባ ፋይቶስቴሮል በብዛት አለው ይሄ ከኮሌስትሮል ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ በደም ውስጥ የሚገኘውን ኮሌስትሮል መጠን እንዳይጨምር ይከላከላል
ዱባ ተፈጥሯዊ ፀረ ድባቴ በመሆኑ እስትረስና ድባቴ እንዳያጠቃዎት
የእንቅልፍ ማጣት ችግርን ይከላከላል
የቫይታሚን ኬ ዋነኛ መገኛ ነው ቫይታሚን ኬ ለአጥንት እድገት ለልብ ጤናና ለአካላት ጥገና አስፈላጊ ነው .

Пікірлер: 1
@abdumohammedawol6423
@abdumohammedawol6423 8 ай бұрын
በጣም አመሰግናለሁ
የዱባ ፍሬ ጭማቂ (Pumpkin Seeds Juice)
7:34
Hilina's Ideal Life
Рет қаралды 1,5 М.
Became invisible for one day!  #funny #wednesday #memes
00:25
Watch Me
Рет қаралды 60 МЛН
- А что в креме? - Это кАкАооо! #КондитерДети
00:24
Телеканал ПЯТНИЦА
Рет қаралды 7 МЛН
НРАВИТСЯ ЭТОТ ФОРМАТ??
00:37
МЯТНАЯ ФАНТА
Рет қаралды 4,9 МЛН
MISS CIRCLE STUDENTS BULLY ME!
00:12
Andreas Eskander
Рет қаралды 13 МЛН
Šalavijas gydo
18:54
Dalia Sekmokienė
Рет қаралды 2,2 М.
Ask Dr Mehret -  ዶ/ር ምህረት ይጠየቃል
15:35
MindseTube
Рет қаралды 5 М.
የሰኔ ጎልጎታ
25:14
Mahedere Tewahedo
Рет қаралды 2 МЛН
Became invisible for one day!  #funny #wednesday #memes
00:25
Watch Me
Рет қаралды 60 МЛН