የሮማን ቅጠል ጥቅሞች/ Pomegranate leaf/ የሮማን ቅጠል

  Рет қаралды 1,171

Birabiro ቢራቢሮ

Birabiro ቢራቢሮ

Жыл бұрын

የሮማን ቅጠል ጥቅሞች
የሮማን ተክል እያንዳንዱ ክፍሉ ለምሳሌ ፍሬው፣ አበባው፣ ልጣጩ፣ ቅጠሎቹና ቅርፊቱ መድሃኒት ናቸው #የሮማን ቅጠል
#የሮማን ቅጠል ጥቅሞች
የሮማን ቅጠል በጠቃሚ ንጥረነገሮች የተሞላና ብዙ አይነት የጤና ጥቅሞችን የሚሰጥ ነው የሮማን ቅጠል ጭማቂ ወይም ሻይ የወፍ በሽታን ለማከም ይውላል
የሮማን ቅጠል ፀረ ባክቴርያና ፀረ ኦክሲዳንት ባህሪ አለው ይሄም በአፍ ውስጥ የሚገኝን ባክቴርያ ለማጥፋት ስለሚረዳ አፍ ውስጥ የሚከሰት ቁስለትን ለማከም ይረዳል
በአፍ በከንፈር በጉሮሮና በምላስ ላይ የሚከሰቱ ትናንሽ እብጠቶችና ነጫጭ ቁስለቶችን ለማከም የሮማን ቅጠልን አፍልቶ ውሃውን በማቀዝቀዝ ቁስለቱን በውሃው ማጠብ ወይም መጉመጥመጥ ችግሩን ያስታግሰዋል
የሮማን ቅጠልን አፍልቶ በቀን ሁለት ጊዜ መጠጣት በሽታ የመከላከል ብቃትን ለመጨመር፣ ለጉንፋንና የጉሮሮ ኢንፌክሽንን ለማጥፋት ይረዳል
የሮማን ቅጠልን ከበሶብላ ቅጠል ጋር አፍልቶ መጠጣት ደግሞ ሳልን ለማስታገስ ይረዳል
ሻዩን ለማዘጋጀት እርጥቡን ወይም የደረቀውን የሮማን ቅጠል መጠቀም ይቻላል
እንቅልፍ የመተኛት ችግር የሚያስቸግራቸው ሰዎች ይህን ችግር ለመፍታት
3 ግራም እርጥብ የሮማን ቅጠሎችን በ200 ሚሊ ግራም ውሃ ውስጥ ጨምሮ ውሃውን 50 ሚሊ ግራም እስኪደርስ ድረስ ማንተክተክ ከዛም ማታ ከመኝታ በፊት ይህን ሻይ በመጠጣት ችግሩን ማስወገድና ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ይችላሉ
4.ከብጉር የፀዳ ቆዳ እንዲኖር
የሮማን ቅጠል ለጋና የታጠበ የሮማን ቅጠልን ፈጭቶ ቆዳን መቀባት ብጉርን ከቆዳ ላይ ስለሚያስወግድ ብጉሩ ያለበትን ቦታ በሙሉ መቀባትና 30 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ
ይሄን ማስክ ከተቀቡ በኋላ በጣም ጥሩ ለውጥ ማየት ይጀምራሉ
የሮማንን ጭማቂ ለፊት ማፅጃነት ቢጠቀሙ የተከፈቱ የቆዳ ቀዳዳዎች እንዲዘጉና ያማረ ቆዳን ያጎናፅፎታል
ስር የሰደደ የቆዳ ማሳከክና ችፌ የሚያስቸግራቸው ሰዎች እርጥቡን የሮማን ቅጠል ፈጭተው ችግሩ ባለበት አካባቢ ቢቀቡት እፎይታ ያገኛሉ
የሮማን ቅጠል ጁስን በመጠጣት ስብንና የሆድ ቦርጭን ማጥፋት ይቻላል
ለስኳር ህመምተኞች ጠቃሚ ነው
በሮማን ውስጥ የሚገኘው ፀረ ኦክሲዳንት የኢንሱሊን ሬዚስታንስንና በደም ውስጥ የስኳር መጠንን ይቆጣጠራል
በሮማን ቅጠል ውስጥ የሚገኙት ማዕድናት የምግብ መፈጨት ሂደትን ስለሚያፋጥኑ ሰውነት በቂ ጉልበት ያገኛል እንዲሁም ምግብ ያለመፈጨት ችግሮችንና ተቅማጥን ያስወግዳል ለዚህም የሮማን ቅጠልን አፍልቶ እንደሻይ መጠጣት ጠቃሚ ነው
ለጋ ቅጠሎችን በሰላጣ በጁስ ውስጥ በመጨመር የስፒናች ወይም የቆስጣ አማራጭ ይሆናል፣ ለፓስታ ስጎ፣ ለሾርባና ለመሳሰሉት መጠቀምም ይቻላል
የሮማን ቅጠል በፀረ እብጠት (ኢንፍላሜሽን) ባህሪው ይታወቃል በዚህ የተነሳ በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል እንዲሁም ከአቅም መዳከም ጋር ተያይዞ የሚመጡ ህመሞችን ይከላከላል
የሮማን ቅጠል ጭማቂን በሳምንት ሁለት ጊዜ በመጠጣት የጤናና የውበት ጥቅሞቹን ማግኘት ትችላላችሁ ነገር ግን አብዝቶ መጠቀም የጎንዮሽ ጉዳቶችን ስለሚያስከትል ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል

Пікірлер: 13
@MesiGemechu
@MesiGemechu Жыл бұрын
Tetefafan 🥰🥰
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
አዎ መሲዬ አልመች ብሎኝ ነው
@alawyasuleyman7199
@alawyasuleyman7199 Жыл бұрын
tnx for sharing !
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
It's nice of you my dear. ❤️❤️❤️
@MesiGemechu
@MesiGemechu Жыл бұрын
Yene qonjo selam neshlgn 😘😘😘
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
መሲዬ አለሁ ክብሩ ይስፋ ❤️❤️❤️
@alemashmeles6630
@alemashmeles6630 6 ай бұрын
ኢትዮጵያ የት ይገኛል
@birabiro1626
@birabiro1626 6 ай бұрын
አዲስ አበባ ውስጥ ኩዊንስ ሲፐርማርኬት እና ፒያሳ ኤንሪኮ ኬክ ቤት በሩ ላይ የሚሸጡ አሉ
@NebeyuBerhe-zy5eq
@NebeyuBerhe-zy5eq 3 ай бұрын
ተክሉ የት እንደሚገኝ ጠቁሙን እንጂ በብዙ ቻነሎች እየተመላለሰ ነው
@birabiro1626
@birabiro1626 3 ай бұрын
ችግኝ መሸጫ ቦታዎች ላይ ጠይቂ ታገኚዋለሽ ብዙ ቦታ አለ
@NebeyuBerhe-zy5eq
@NebeyuBerhe-zy5eq 3 ай бұрын
@@birabiro1626 ኸረ የለም ችግኙ ሳይሆን የሚበላውን ራሱ ፈልጌ ሳጣ ነው የጠየቅኩት
@birabiro1626
@birabiro1626 3 ай бұрын
ፍሬው አዲስ አበባ ውስጥ ፍሬሽ ኮርነር፣ ኩዊንስ ሱፐርማርኬትና አትክልት ተራ አለ የኔ ውድ ችግኙን ጨርቆስ እና ጀርመን አደባባይ ችግኝ መሸጫ ታገኚዋለሽ እዛ አይቼዋለሁ
@NebeyuBerhe-zy5eq
@NebeyuBerhe-zy5eq 3 ай бұрын
@@birabiro1626 በሴት ፆታ ስለጠራሽኝ/ኸኝ ግን ከፍቶኛል
Why pomegranate flowers are not converting to fruits
5:58
Gardening and Cooking
Рет қаралды 101 М.
Amazing weight loss transformation !! 😱😱
00:24
Tibo InShape
Рет қаралды 55 МЛН
마시멜로우로 체감되는 요즘 물가
00:20
진영민yeongmin
Рет қаралды 33 МЛН
아이스크림으로 체감되는 요즘 물가
00:16
진영민yeongmin
Рет қаралды 61 МЛН
Clown takes blame for missing candy 🍬🤣 #shorts
00:49
Yoeslan
Рет қаралды 40 МЛН
የጦስኝ 7 የጤና ጥቅሞች| 7 health benefits of thyme leaf
5:31
Health Education - ስለ ጤናዎ ይወቁ
Рет қаралды 10 М.
የቡና ችግኝ ዝግጅት በጅማ ዞን
4:02
Fana Television
Рет қаралды 737
የጎመን ጁስ (ውህድ) 5 የጤና ጥቅም ና አዘገጃጅት/ Cabbage Juice.
8:40
ጤናዬን ሚድያ-Tenayen Media
Рет қаралды 14 М.
Amazing weight loss transformation !! 😱😱
00:24
Tibo InShape
Рет қаралды 55 МЛН