No video

ፉዓድ ሸምሱ|| ሠላሜ |አዲስ| መንዙማ 2016||Fuad Shemsu||Selame ||New Menzuma2023

  Рет қаралды 748,818

Al Faruk Multimedia Production

Al Faruk Multimedia Production

4 ай бұрын

ማዲህ ፉአድ ሸምሱ
ግጥም ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ
ዜማ :ሙአዝ ሀቢብ
ተጨማሪ ዜማ :ኸይራቶች
ስቱዲዮ: ኑሩ ኡመር [ቦርከና]
ሚክሲንግ:ሶል( ሀመር)
ካሜራ :ሰዒድ ሙሐመድ
ምስል ቅንብር :ሰዒድ ሙሐመድ
ሌሪክስ ኤዲቲንግ : አሊ ሙሐመድ (Alif)
ግራፊክስ አድናን አማን
ኘሮዳክሽን ማናጀር :ፋሩቅ ጋሊብ
ኘሮዲዉሰር :አል-ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥
ሙሉ ግጥም
ሰላሜ
።።።።።።።
ኻሊቁ፣ ጀማል ጀላላን ጠቅልሎት ለሱ
ደፍቶለት፣ የኑሩን ዙፋን ዘውዱን ከራሱ
ላንዴ አይታው፣ ትዋልላለች የማንም ነፍሱ
አንተዬ እንደሱ፣ አንድ የለም ሚወደዲ
።።።።።።።።
ያንቱ ፊት፣ ጨለማን ገፎ ኑሩ ሲደንቀን
ምን ይባል፣ ፀሃይዋን ንቆ ሲያበራ በቀን
ቅኔውም፣ ተደበቀብን ሰም ወርቁ ራቀን፣
ወይ ገሎ አይለቀን፣ እንደነ አህመደል ሃዲ
።።።።።
ፀጉሩማ፣ ሲገርመን ወዙ መርገፍ ሳይቃጣው
አጀባው፣ ጠቁሮ ማብራትን ከዬት አመጣው
ወስዶብን፣ ይሄው ልባችን እኛም ስናጣው
ጉድ አርጎ አመጣው፣ ለጉድ እስኪሆን ጉዲ
።።።።
መሀባው፣ ወይ አይለመድ ወይ አልቀለለ
እንዳሻው፣ ስንቱን አነሳው ስንት እየጣለ
ወርውሮ ፣ውዱ የሳተው እስኪ ማን አለ
ልቡ ያልዛለ፣ ሲጠሩ ሙሐመዲ
።።።
ሙሐመድ፣ እንኳን መታከት መች ይጠገባል
ጆሮዬ፣ በሰማ ቁጥር ሙሐመድ ሲባል
ሙሐመድ፣ እየናፈቁኝ ሆዴ ይባባል
ድኗል እንዲባል፣ በሉ እስኪ ሙሐመዲ
።።
ወለላው፣ ያይኔ ማረፊያ ኗሪው በነፍሴ
ጀማላው፣ ካለርሱ አይሰራም ጅስሜም ህዋሴ
ስሙ ነው፣ ሳዝን መደሻ፣ ስታረዝ ልብሴ
ስሙ ነው ዋሴ፣ የኔ ወገን ዘመዲ
።።።።
ካበሻ፣ የሸውቁን ገመድ ጦይባ ቀጥሎ
እንደ ሰው፣ ጨርቅ ቢለብስም ልቡን ግን ጥሎ
ለይምሰል፣ ፈገግ የሚለው ውስጡ ተቃጥሎ
ላዩ ሰው መስሎ፣ ሲስቅ ሲቀልዲ
።።።።
በኔ ላይ፣ ምነው ጠና ባሰሳ ነገሩ
ምንድን ነው፣ ልቤ ተሻግሮ ጦይባ ማደሩ
እንዲህ ነው ለካ ትልቅ ሰው መውደድ ማፍቀሩ
ርቆኝ አገሩ፣ ሸውቁ ሲሰራኝ ጉዲ
።።።።።።።።
መልበሴ፣ ነው ያስመሰለኝ እንጂ ደህና ሰው
ሳቄ እንጂ፣ መች ታዬ አይኔ ናፍቆ ሚያለቅሰው
ማን አይቶ፣ ጀማሉ ውስጤን እንደሚያምሰው
ማልገልጠው ለሰው፣ ስንት አለ በኔ ሆዲ
።።።።።
ሳታገኝ፣ ሳይደርስህ ገና ያይኑ በረከት
አንድም ቀን ፣ጀንበሩን ፊቱን ሳትመለከት
መሳቅህ፣ ምንድን ከቶ ያንተ መንከትከት
እስኪ ተመልከት፣ ያን ናፋቂውን ግንዲ
።።።
በልቤ ቀበሌ አምባ፣ ተቸምችሞ ሙሀባ
ሌላማ እንዳያስገባ፣ ሞልቶታል ሙከረሙ
።።
መውደዱ አድሮ እያከለ፣ መቋቋሙን ያልቻለ
ሀበሻ ላይ ስንት አለ፣ የጠናበት መድከሙ
።።።።።
ካንቱ ወዲያ ሙሉነት፣ ካንቱማ ወዲያ ረህመት
ቢጤውም ሆኗል ዘበት፣ ላይገኝ ከአለሙ
በደም ተንክሮ ልብሱ ፣ተሸርፎም ውቡ ጥርሱ
ማርልኝ ሚል ምላሱ፣ ሌላው ሲል ተራገሙ
።።።።
ማን ይሆን ውቡን ጥርሶን፣ የመታው የሸረፈው
የኔውን ባራገፈው፣ አንቱ ደህና ሁነሁ
።።።
ስቃዮትን ልሰቃይ፣ ቅጣቶንም ልቀጣው
ላንቱ ስል ሁሉን ልጣው፣ ሾክ እንኳን አይንካሁ
።።።።።
።።።።
ልቅናን በጠቅላላ፣ ለሱ አድርጎለት መውላ
ወዶ ለጠራው ሁላ፣ መሻሪያ ሆኗል ስሙ
።።።።
አብዱሏህ ወዳጃቸው፣ ተሳሰረና እግራቸው
መነሳት ተሳናቸው፣ ደርሶ ድንገት ታመሙ
እስኪ እንደው ቢያስታግሰው ፣ዓፊያህን ቢመልሰው
አንተ ምትወደውን ሰው፣ ጥራ አሏቸው በስሙ
ከንብረት ከህይወትም፣ ከናት በላይ ካባትም
አብልጠው ሚወዱት፣ መች አለ እንደ ኢማሙ
ሲወዱም ነው ሙሐመድ፣ ሲናፍቁም በሙሐመድ
ሙሐመድ ነው ሙሐመድ ፣ቢድኑም ቢታመሙ
አብዱሏህ ወዳጃቸው፣ አሏህ እንዲያሽራቸው
ሙሐመድ ቢል አፋቸው፣ ከወዲያው ድነው ቆሙ
።።።።
የኒዕማዎች አይነታ፣ ወደር የለሽ ስጦታ
አንቱ ኖት የኔ ፈንታ፣ ዙል ኹሉቂን ዓዚሙ
ትልቅ ሰው ተሰጥቼ፣ ትልቅ ሰው ተጠግቼ
ምን ጎሎኝ ምን አጥቼ፣ ወደ ሌላ ማዝገሙ
ኑሮው ሲተናነቀኝ፣ ደስታ ሳቄም ቢርቀኝ፣
ሙሐመድ ስል ለቀቀኝ፣ ሀዘን ጭንቁ ህመሙ
።።።።።።
ልቤን ከጉድ ያዳነው፣ ጉድለቴን የከደነው
ቀና ያልኩት ባንቱ ነው፣ ሊጥሉኝ ሲሸከሙ
።።።
ምን ባጣ ብቸገርም፣ ዱንያው ሁላ ቢቀርም
ባንቱ አልደራደርም፣ ክብሬ ኖት ሙከረሙ
።።።
የተናቀው መላቁ፣ የጠፋው ለመድመቁ
ያዘነው ለመሳቁ፣ ሰም ወርቁ ሙከረሙ
።።።።
በልቤ ውስጥ ያለው፣ መግለፅ የማልችለው
ከምፅፈው በላይ፣ ሚበልጠው እሱ ነው
አንቱ ተናፋቂው፣ ተወዳጁም አንቱ
አንቱን እየያዘ፣ ባንቱ አማረ ስንቱ
ሙሐመድ ልበለው፣ በማታም በጧቱ
እንደስሙ ሚጣፍጥ፣ አትሰራም ንቢቱ
ሌላውን ረስቶ፣ ሁሉን ችላ ብሎ
ሙሐመድ ሲል ያድራል፣ ሙሐመድ ሲል ውሎ
ስፈታ እንዳልኖርኩኝ፣ ስንቱን ወርቅ ቅኔ
ቅኔ ናፍቆትሁ ግን፣ አቅቶኛል ለኔ
የሚያመልጠው የለው፣ አይርቁም አይሸሹ
እሱ ዳኛ ፈራጅ፣ እሱው ነው ከሳሹ
ናፍቆቱ ሃይሎ፣ እንዳላሳመመኝ
አጀብ ግን እሱው ነው፣ ሊያድን የሚያክመኝ
ፍቅሩ እያበረደው፣ ናፍቆትሁ ሲፈጀው
አንቱዬ ምን ይሁን፣ ልቤ ምን ይበጀው
በሸውቁ መንምኖ፣ ጅስሙ እንደ ጨርቅ አልቆ
ላዩን ደህና መሳይ፣ ውስጥ ውስጡን ማቅቆ
አትፍረዱ በሱ፣ ቢገኝ መሬት ወድቆ
ማን ሲድን አይተሃል፣ ትልቁን ሰው ናፍቆ
አልሰማህም ሸውቁ፣ የሰራውን ስራ
እንኳን ስጋ ለባሽ፣ አርገፍግፏል ጎራ
እሩህ የሌለውን፣ ግንዱን ሲያስለቅሰው
እኛ ሩህን ይዘን፣ ወዴት እንድረሰው
ስቃዩ አሳዝኖሁ፣ ብታቅፉት እኮ ነው
ህመሙ አባርቶለት፣ ግንዱ የሰከነው
ጠንቶ ሲያስለቅሰኝ፣ ሸውቁ ሲያዋልለኝ
ያላንቱ ሰይዲ፣ ማን አይዞህ ይበለኝ
።።።።።
ልቡ አንቱን ናፍቆ፣ መሀባው ሲረታው
አዝነሁ ካልደረሱ፣ ላይድን ነው በሽታው
።።።
ለኔም ኑልኝ እንጂ ፣ማዬቱ ይድረሰኝ
እንደዚያች ጨረቃ፣ ናፍቆትሁ ሳይገምሰኝ
ዱንያው ጥንቅር ይበል፣ ይቅርብኝ ወረቱ
ሙሉ አርጎ ያኖራል፣ ያንቱን ፊት ማየቱ
የሚቻል አይደለም፣ አውቃለሁ ውበቱን
ያየ ያላየውን፣ ልብ መቀማቱን
አብረው የኖሩትም፣ ችለው መች ደንድነው
እንደኔ ያላዬው፣ ምን ይሆን ሚያድነው
ግን ታሞ ከመኖር፣ ናፍቆ አይንሁን አይኔ
አንዴም አይቶ መሞት፣ ይሻለኛል ለኔ
እስከ መች በሩቁ፣ ልንገብገብ ልሰቃይ
ልውደቅ አጠገብሁ፣ መታመሙ ይብቃኝ
ማንነት ሲረክስ፣ ጅህልናው ደንፍቶ
መብቷ አፈር ሲገባ፣ ሴትነቷ ጠፍቶ
አዛኝ ረህመት አርጎ፣ ጀሊሉ ቢያስገኘው
አንተው ሙሐመድ ነው፣ ሰውን ሰው ያሰኘው
አንድ ነው መንገዱ፣ መድረሻው ሰንሰሉ
እሱም ሙሐመድ ነው፣ ሙሐመድን ላሉ
ካለኛው ሙስጦፋ፣ ካለኛው ሙሐመድ
ሄዱት ሄዱት እንጂ፣ ዝግ ነው ሌላው መንገድ
ንቅንቅ የለም ካንቱ፣ ያቁረተል ዓይኔ
የሙሐመድ መባል፣ ይበቃኝል ለኔ
ከተውኩማ ስሙን፣ ልገኝ አይደል ሞቼ
ዛዲያ ማንን ልጥራ፣ ሙሐመድን ትቼ
ከሰይደል ውጁድ፣ ከሙሐመድ በቀር
ታዲያ ምን ሊወደድ፣ ከቶ ምን ሊፈቀር
እንዲያው ትንግርት ነው፣ ልቤ አይችልም ከቶ
ስሙን ትቶ ሃያት፣ መኖር መድሁን ትቶ
የጨቅላ ልጅ ጠረን፣ ያንገቱ ስር ሽታ
የወላጅን ስቃይ፣ ይነቅለዋል ባፍታ
እንኳን በሙሐመድ፣ ባወደሰው ጌታው
እናቱን ያገኘም፣ ይድናል በሽታው
እንኳን ሙሐመድን፣ የሚያምሩት ነብዬ
ስንቱ ጤና ሆኗል፣ እናቱን እንዳዬ
ስንቱ ቁስሉ ሽሯል፣ ወዳጁን ስላዬ
።።።።።።።።
✍ግጥም ዑስታዝ ሰዒድ አህመድ

Пікірлер: 728
@HamduIbrahim
@HamduIbrahim 4 ай бұрын
የኢትዮጵያን የመንዙማ እና የነሺዳን ስራ በደረጃ ከፍ ካደርጉ የሀገራችን ፈርጥ ግንባር ቀደሙ ነው!🤗እሱን አለማድነቅ ራስ ወዳድነት ነው!😔 ማሻ አላህ በማለት 🤘 አድናቆታችንን be like👍 እጅግ ድንቅ ስራ ፉአዴ✌️
@mukaPp-kb8pp
@mukaPp-kb8pp 4 ай бұрын
Kotetam music malleth new
@Temu-mw5xd
@Temu-mw5xd 3 ай бұрын
@@mukaPp-kb8pp ደንቆር ትንሽ ከግጥሙ እንኳን ልብህ አይራራም ደደብ ውሀብያ
@RahimaJ-gy2pu
@RahimaJ-gy2pu 3 ай бұрын
Essy😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂 Wey kenat😂😂😂😂😂😂😂
@user-in3lb1hi6r
@user-in3lb1hi6r 3 ай бұрын
Tryertdtdtwfhkj
@user-zg8qt8vr1l
@user-zg8qt8vr1l 3 ай бұрын
😂😂😂😂😂😂😂
@kebirmuhamed
@kebirmuhamed 4 ай бұрын
🎉🎉ማሻ አሏህ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ❤❤❤ እስኪ ፉዓድን የምትወዱት 👍👍👍
@user-Yerewduaw
@user-Yerewduaw 4 ай бұрын
ሀቢባችንን ጠርቶልን እንደት ነው ማንወደው ❤❤❤❤
@Muhamadofficial100
@Muhamadofficial100 4 ай бұрын
S......🎉A......🎉W....
@AnwarHussen-hx1hw
@AnwarHussen-hx1hw 4 ай бұрын
በአሏህ(ሱ.ወ.) አንድነትና በነብዩ ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ.) መልዕክተኛነት ያመነና አወዳሽ የሆነ እንዴት አይወደድ?ለአሏህ ብዬ እወደwaለሁ።
@user-Yerewduaw
@user-Yerewduaw 4 ай бұрын
አሏህ የሀቂቃ ሁብ ይስጠን ያሠላም ያሠላም ወሏሂ እኔም ለአሏህ ብየ የነቢ ወዳጆችን እወዳችሗለሁ
@kebirmuhamed
@kebirmuhamed 4 ай бұрын
@@user-Yerewduaw አሚን ❤
@lemlem-ur9ph
@lemlem-ur9ph 3 ай бұрын
ክርስቲያን ነኝ ግን መዙማዉን በጣም እወደዋለሁ
@ekramebrahim415
@ekramebrahim415 Ай бұрын
❤❤❤❤
@muradseid8302
@muradseid8302 22 күн бұрын
Nb 😅😅j
@solomon243
@solomon243 4 ай бұрын
ክርስቲያን ብሆንም መንዙማ ሲበዛ እወዳለሁ።ማሻአላህ ያምራል
@user-os7en6yd3l
@user-os7en6yd3l 4 ай бұрын
Allhe yimerhe
@EkuNejm
@EkuNejm 4 ай бұрын
Thanks egnam enwedhalen
@user-ml3sosna
@user-ml3sosna 3 ай бұрын
❤❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉💋💋💋💋
@MararealHabeshanboy
@MararealHabeshanboy 2 ай бұрын
I like masha alah
@ekramebrahim415
@ekramebrahim415 Ай бұрын
Allah yetebekeh
@mussemamuzemil6980
@mussemamuzemil6980 4 ай бұрын
ኡስታዝ ሰዒድ አንቱ ባንትኖሩ .........❤❤❤❤❤❤❤
@YusufSani-zi5zr
@YusufSani-zi5zr 3 ай бұрын
Shek hajji Hussein yinoru nbr
@user-ps6nt2xe7e
@user-ps6nt2xe7e 3 ай бұрын
@BeriBoss-yn5vx
@BeriBoss-yn5vx 2 ай бұрын
ማርያምን እወደዋለው ይሄንን ነሺዳ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰ሰላሚ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🙁
@kedir_yimer
@kedir_yimer 4 ай бұрын
እየሰማን እስኪ በውዱ ረሱላችን ላይ ሶለዋት እናውርድ
@Musa-le2te
@Musa-le2te 4 ай бұрын
ሰለላ አለይሂም ወሰለም💙💙
@Semirahasen-nv1vg
@Semirahasen-nv1vg 4 ай бұрын
Selelahu alyhi weselm ❤❤❤😊
@YusufSani-zi5zr
@YusufSani-zi5zr 3 ай бұрын
SAW❤❤❤❤
@Ye-Nurhusen-Lij.21-47
@Ye-Nurhusen-Lij.21-47 3 ай бұрын
SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE ALEYE SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM WESALAM ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM SALALAHU ALEYE WESALAM🖤🖤🖤💘💘💘💔💔💔❣️❣️❣️💗💗💗💓💓💓💞💞💕💕💕🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍
@user-uq8mx2ie4y
@user-uq8mx2ie4y 3 ай бұрын
Sallalahu aleyhi wasalam 💚
@sofii3558
@sofii3558 4 ай бұрын
እንኳን ሙሐመድን የሚያምሩት ነብዬ ስንቱ ቁስሉ ሽሯል እናቱን ስላዬ❤
@user-en5yf1xz5n
@user-en5yf1xz5n 4 ай бұрын
💜❤️❤️❤️
@user-hc8hf4pq4i
@user-hc8hf4pq4i 4 ай бұрын
Mashallaa
@AL-SHAFEEUTube-yv6ri
@AL-SHAFEEUTube-yv6ri 3 ай бұрын
@jemukedir45
@jemukedir45 4 ай бұрын
ሲወዱም ነው ሙሀመድ ሲናፍቁም በሙሀመድ ሙሀመድ ነው ሙሀመድ ቢድኑም ቢታመሙ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም😍😍😍😍😍😍😍😍😍
@yarsulelah
@yarsulelah 4 ай бұрын
እንደው ኡስታዝ ሰኢድ ብዕራችሁም ብራናችሁም እስከጀነት ይታዘዛችሁ ወላሂ አቤት የቃላት ስብጥር ሀያት ብያለሁ እንዲሁም ይህን የመሰለ ግጥም ወደ ጆሮአችን ለስለስ ባለ አንደበትህ ስላደርስክልን እንደው በ ረመዳኑ ይሁንበት ድምፅህ እሳቸውን ጀባ ይበልህ እሳቸውን ብማወደስ ድምፅህ ይለቅ አቦ ሀያያያትትትትትት ወላሂ❤❤❤❤❤❤
@KalishKa-io2qk
@KalishKa-io2qk 2 ай бұрын
Aminnnnn❤❤
@onelove4538
@onelove4538 2 ай бұрын
Amin
@Abedirehem
@Abedirehem 4 ай бұрын
እንከን የማያወጣላት መንዙማ ክቡር ለገጣሚው ኡስታዝ ሰኢድ❤❤😊😊❤
@KismetAbdulaziz
@KismetAbdulaziz 4 ай бұрын
Allah yakoylen❤
@ABDREMAME
@ABDREMAME 4 ай бұрын
እስቲ ፉአዴን አናበረታታው👍👍👍👍👍🤜🤜
@hekmahekmmma9538
@hekmahekmmma9538 4 ай бұрын
ፉአድ ሸምሱ ሰኢድ ሸይኽ ሙዘሚል ቢላል ፋሪስ ምርጥ ማድሆች💞💞💞
@Guragemusic3
@Guragemusic3 4 ай бұрын
ምርጫህ ምርጫዬ ነው
@YusufSani-zi5zr
@YusufSani-zi5zr 3 ай бұрын
Muaz habibi ❤️❤️❤️ Fuad ❤️❤️❤️
@Behaer199
@Behaer199 4 ай бұрын
የጨቅላ ልጅ ጠረን የአንገቱ ሰር ሽታዉ የወላደጅን ስቃይ ይነቅለዋል በአፍታዉ እንኳን በሙሐመድ ባወደሰዉ ጌታዉ እናቱን ያገኘ ይድናል በሽታዉ😢😢❤
@Akislamic7
@Akislamic7 4 ай бұрын
Kefetay gete brehan wubet yayen nure hulum mgeb s a w
@Sititt-bn7we
@Sititt-bn7we 4 ай бұрын
❤❤❤
@nouran373
@nouran373 4 ай бұрын
💚💚💚
@MunikJJ
@MunikJJ 4 ай бұрын
ናፋቂዎቹ የታላቹ ፉአዴ ወላሂ ምርጥ ስራ አላህ ከወደድነው የድርገን አሚን ...
@khalidseman8922
@khalidseman8922 4 ай бұрын
ኡስታዝ ሰይድ አህመድ ❤❤❤ ዳግማዊ ሰጊድ ጫሌ ናችህ ሀያት❤❤❤
@user-ox3if6sz4p
@user-ox3if6sz4p 4 ай бұрын
ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም❤😢 ሩህ የሌለውን ግንዱን ሲያስለቅሰው እኛ እሩህን ይዘን ወደት እንዲረሰው ስቃዩ አሳዝኖት ብታቅፉት እኮ ነው ህመሙ አባርቶ ግንዱ የሰከነው 😢
@Temu-mw5xd
@Temu-mw5xd 3 ай бұрын
እረ ዑስታዝ ሰይድ አንቱ ብቻ ፃፉ ግጥም መገን የሙሀባ አገላለፅ ሀያት አላህ ይስጣቹ ❤❤❤❤❤❤❤❤
@AsiyamohmedAsiyamohamed
@AsiyamohmedAsiyamohamed 3 ай бұрын
L
@user-fw4gu6gd9j
@user-fw4gu6gd9j 4 ай бұрын
ሰለላሁ ኣለይሂ ወሰለም ሃድራ ጉድ ይዛለች ኣላህ ይጠብቅህ😢 ሰሉ ኣለ ነቢ 🥁💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
@user-qr6cd3ku1s
@user-qr6cd3ku1s 3 ай бұрын
ወላሂ በቀን ስንቴ እንደምሰማው የማይጠገብ 😢አላሁመሶሊ አላሃቢቡና ሙሐመድ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
@user-jn8ym6fo4w
@user-jn8ym6fo4w 4 ай бұрын
በጣም ደስ ይላል ሁኔት እኔ ክርስትያን ነይኝ ግን በጣም wodjyalewu🙏🙏👑👑
@nudanejib
@nudanejib 4 ай бұрын
ንቅ ንቅ የለም ካንቱ ያቁረተል አይኔ የሙሀመድ መባል ይበቃኛል እኔ❤️ ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ❤️🙏🏼
@Esam628
@Esam628 4 ай бұрын
ድንቅ ስራ ብዙ የተለፋበት መሆኑ ያስታውቃል አላህ ያበርታቹ ከዚህም የተሻለ እንደምትሠሩ እርግጥ ነው በርቱልን ❤👏 🕌💚ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም💚 🕋
@anwarmovie-qq1vv
@anwarmovie-qq1vv 4 ай бұрын
ማን ይሆን ውቡን ጥርሶን፣ የመታው የሸረፈው የኔውን ባራገፈው፣ አንቱ ደህና ሁነሁ አሏህ አሏህ አሏህ አሏህ አሏህ አሏህ አሏህ አሏህ አሏህ👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
@user-Yerewduaw
@user-Yerewduaw 4 ай бұрын
አሏህ አሏህ አፊያ ሆንኩኝ እኔስ ሲገለኝ ሙሀባው❤❤❤❤❤❤ይለያል ወሏሂ 🌼ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም..አሏህ ሁባችንን ይጨምርልን አህባቡ ሁሉ ይጨምርላችሁ
@user-qr6cd3ku1s
@user-qr6cd3ku1s 3 ай бұрын
😭አላሁመሶሊ አለሃቢቡና ሙሐመድ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም 😢ስንቴ እንደደጋገምከት ሲጀመር ፉአድ በጣም ነው የምወደው አሪፍ አቀራረብ አደራ በዚሀ ቀጥል አልፋሩቅ ❤ ሀድራ ነኝ የ01
@user-ex2hy3wg6e
@user-ex2hy3wg6e 4 ай бұрын
ሱብሃነሏህ አቤት ግጥም አቤት ዜማ አሏህ ይጨምርል ወንድሜ ናፍቆት ይጨራል ነብዪን ሚያወድስ ሁሉ አሏህ ከፍ ያደርገዋል❤❤❤
@mamemanofishial
@mamemanofishial 4 ай бұрын
ምን ላርግክ ፉአዴ ግን አለም ላይ የሌለ መንዙማ ነው እኮ ዜማው:ግጥሙ :ፊውቸሩ ዋው❤❤❤❤❤❤❤
@ImoImo-fw2xv
@ImoImo-fw2xv 4 ай бұрын
Betam stebkew nebr ketebekut belay mret new fuade mashallah wow
@kalid__mussa
@kalid__mussa 4 ай бұрын
የሙሐመድ ሙሀባ በቀልቤ የገባ ሁሌም ያለቅሳል አይኑ ያነባህ 😭🙏🥰 S A W 👈 community በሰሎዋት እናድምቀው እንሻላህ ❤
@SamiraHawasa-ethiopia
@SamiraHawasa-ethiopia 4 ай бұрын
S a w❤
@Akislamic7
@Akislamic7 4 ай бұрын
Yayen nur yasin fekere felaget yemenor gete s a w❤❤❤❤❤❤😢😢😢😢😢❤❤❤❤❤ nfekot
@samiraamna-zr2qz
@samiraamna-zr2qz 4 ай бұрын
S❤ A❤ W❤❤
@user-sp2fp9ph9o
@user-sp2fp9ph9o 4 ай бұрын
ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ♥️ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ♥️ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ♥️♥️♥️♥️♥️♥️♥️♥️
@AbdulfetaNur
@AbdulfetaNur 4 ай бұрын
አልሠማህም ሸውቁ የሰራውን ስራ እንኳን ስጋ ለባሽ አርገፍግፏል ጎራ
@MWGM_FX
@MWGM_FX 4 ай бұрын
አረ ወላሂ ለአዚም ምንም ማለት አልችልም አላህ የልብን ያድርስልክ ዛሬ ገና መንዙማ መስማት ጀመርኩኝ 👵👵👵👵👵👵👳‍♂️👳‍♂️👳‍♂️👳‍♂️👳‍♂️👳‍♂️👳‍♂️👳‍♂️
@user-zc7qg1ep4f
@user-zc7qg1ep4f 3 ай бұрын
1) fuad shemsu ♾️♾️💯💯💯 2) idris muhammed 💯💯💯 3) muaz habib 💯💯 techlalachu beka
@hussenyimer9437
@hussenyimer9437 4 ай бұрын
Welahi ende fuad yemwedew munshid yelm yesun bisemaw bisemaw ayiselechegm haqiqa berta habibi
@Hayeyans
@Hayeyans 3 ай бұрын
☝☝ኋሊቁ ጀማል ጀላላን ጠቅልሎ ለሱ ደፍቶለት፣ የኑር ዙፋን ዘዉዱን ከራሱ አንተየ እንደሱ አንድ የለም ሚወደድ❤❤😍 አለይኩም ዛዴ ሰይድ አህመድ ሙሀመድ
@user-vq5xq6rt3r
@user-vq5xq6rt3r 4 ай бұрын
ዋው ማሻ አላህ አላህ ያስደስታቹ ኡስታዝ ሰኢድና ፉአዴ ልብ ያረሰርሳል እንኳን ሙሀመድን የሚያምሩት ነብዬ ስንቱ ጤና ሆናል እናቱን እንዳየ ስንቱ ቁስሉ ሽሯል ወዳጁን ስላየ
@Ye-Nurhusen-Lij.21-47
@Ye-Nurhusen-Lij.21-47 3 ай бұрын
Wallahi shilila shilila seyidi mujahid yemilawun menzuma ena Nurhuseyn yemilawun betam nw yemwedan Wallahi yehona ken Abiyoooooooo seyidul arifin Bemenam ayehugn kezam seyid Mujahid ayewachew ena Wallahi betam nw yagarmgn muhabm yelgn allah lmn endsyegn alkm becha bensu yehunbt be akeram kenasu ayleyn Wallahi
@MameMame-uz2lt
@MameMame-uz2lt 4 ай бұрын
ሙሂቦች አላህ ሀያታቹ የርዝመው ❤❤ረሞዳን አላህ አመት.ከአመት.ያድርርሰን፡በአንድነት..አላህ.አገራችንን.ሰላም የአድርገው፡አሚን❤❤❤
@seniyashifa3343
@seniyashifa3343 26 күн бұрын
ማንይሆን ጥርሶን የመታው የሽርፈው የኔውን ባራገፋው አንቱ ደህና ሁነሁ❤❤❤❤❤
@user-zt4xs4qw9p
@user-zt4xs4qw9p 4 ай бұрын
እስከዛሬ ከተሰራው ሁሉ ይለያል. ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም❤
@user-yr6sy3xn7r
@user-yr6sy3xn7r 4 ай бұрын
Ustaz seid hayat belenal Yermedan mert sera
@MunirrSultan
@MunirrSultan 23 сағат бұрын
Menzuma bemuslim aychalem estewkfurelah
@AnwarHussen-hx1hw
@AnwarHussen-hx1hw 4 ай бұрын
ማሻ አሏህ።አሏህ(ሱ.ወ.) ይቀበልህ፣ይመንዳህ፣ያስደስት እንዳስደሰትከኝ ኢስቲqaማውን ይስጥህ።ሰላሚ አለይኩሙ ሰላቲ አለይኩሙ፣ሰላሚ አለይኩሙ ጠሀ ያሙከረሙ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሰ.ዐ.ወ. ሰ.ዐ.ወ.
@EkramAbdu-pn5tw
@EkramAbdu-pn5tw 4 ай бұрын
ሰላሚ ምርጥ መንዙማ አሪፍ አቀራርብ ማሻአላህ ይብላኝ ላልታመመው ለማይፈልቀው እንባው አፊያ ሆንኩኝ እኔ ሲገለኝ ሙሀባው ሰላሜ ሰ ዐ ወ❤❤❤
@JIRENmedia114
@JIRENmedia114 3 ай бұрын
ሩህ የሌለውን ግንዱን ሲያስለቅሰው እኛ እሩህን ይዘን ወደት እንዲረሰው ስቃዩ አሳዝኖት ብታቅፉት እኮ ነው ህመሙ አባርቶ ግንዱ የሰከነው 😥 ስለላሁ እልህ ወሰለም ሀቢብ አላህ❤❤❤
@hayredinkemal7850
@hayredinkemal7850 4 ай бұрын
ሸህ ሰዒድ እጅህ ይባረክ
@TewodrosAmsalu-en5lx
@TewodrosAmsalu-en5lx 4 ай бұрын
አዳማጭ አለ ተጠቃሚ ያርገን
@inspirefair6327
@inspirefair6327 4 ай бұрын
የሙሀመድ መባል ይበቃኛል እኔ🥺🖤🖤🖤
@yishak_Abrar
@yishak_Abrar 2 ай бұрын
ከንቱ ወዲያ ሙሉነት ከንቱማ ወዲያ ራህመት 👏👏👏👏
@RAMSAMEDIA
@RAMSAMEDIA 4 ай бұрын
ማሻአላህ ❤❤❤ ወንድም ፋአድ እና አልፋሩቆች በጣም ቆንጆ የሆነ ስራ ነው የሰራችሁት !!! በርቱልን ከናንተ ብዙ እንጠብቃለን !❤
@jemilzakir
@jemilzakir 18 күн бұрын
ማ ሻ አለ ህ❤❤❤❤🎉🎉🎉😊😊👍👍👍👍👍👍 16:07 16:09
@ALISLAMChannel-lf6vk
@ALISLAMChannel-lf6vk 4 ай бұрын
Waw 🎉 Masha Allah Fuade ❤❤❤
@soof-umartube
@soof-umartube 4 ай бұрын
ما شاء الله تبارك الرحمن اللهم صل على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد ❤💚❤
@GMaryamNega-rz6px
@GMaryamNega-rz6px 2 ай бұрын
ይሔንመንዙማስሰማራሱቀልቤይርሳልማሻአላሕ❤❤❤❤❤❤❤🎉
@fuadnesro6403
@fuadnesro6403 4 ай бұрын
ወላሂ ቃል አጣሁለት ማሻ አላህ ሁስታዝ ሰኢድ አላህ ይጠብቆት ሞክሼ አንተንም
@HanisaWeliyu-uv5kz
@HanisaWeliyu-uv5kz Ай бұрын
ማሻአላህ ፉአዴ የሚገርም መንዙማ ነው ከምልህበላይ አላህ ይጠብቅ በጣም ነው የወደድኩት የመጀመሪያክ እስኪመስለኝ ድረስ ምንም ቃል የለኝም አንደኛ ነው👍👍👍👍👍
@alimohammed-bs1is
@alimohammed-bs1is 4 ай бұрын
ሶለሏሁ አለይሂ ወአላ አሊሂ ወሳህቢሂ ወሰሊም… ያሰላም…አይን የሚያስለቅስ አንጀት የሚያርስ ምርጥ መንዙማ…ግጥሙ ዜማው የመድህ ጥግ ይታይበታል… ማዲህ ፉአድም ኡስታዝ ሰኢድም ሀያታችሁን ረዥም አሏህ ያድርገው😥😥😥
@lil_shadi5179
@lil_shadi5179 4 ай бұрын
ዜማውን አንደዚህ አጣፍቶ የሰራው ሙአዝ ሃቢብንም መርሳት የለበትም ምስጋና ይገባዋል
@muaznasredin8642
@muaznasredin8642 4 ай бұрын
Alaykum zadi sayid ahmed muhamedi ♥️ 😍
@user-kl6ob2bm4q
@user-kl6ob2bm4q 4 ай бұрын
Eman hayate tena yehanene manzuma lasarute ena lamiaute hulu remadane mubarake allahe yewedadachu ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@MuradMohammod
@MuradMohammod 4 ай бұрын
የአረብ ላአንተም ለኡስታዛችንም ሀያት
@muhaelias8919
@muhaelias8919 4 ай бұрын
Hulum menzumawoch mrt nachew allah ychemrlh ❤❤
@SiruDino
@SiruDino 4 ай бұрын
selelahu Aleyhi Weselm Mash Alah Siwedh
@Simacr7759gh
@Simacr7759gh 3 ай бұрын
ፋአድዬ ወንድሜ በጣም ነው የምወድህ መጀመሪያህ እንዳማረ መጨረሻህንም አላህ ያሳምረው የስራ ሁሉ ማማሩ መጨረሻው ሲያምር ነው
@user-ge1fd7ml8w
@user-ge1fd7ml8w 4 ай бұрын
Welahi Allah yenebin muhaba chemiro Allah ysixih
@kalid__mussa
@kalid__mussa 4 ай бұрын
Asc
@Anwarlight
@Anwarlight 4 ай бұрын
ameen ysten
@user-ye6vb9tm2r
@user-ye6vb9tm2r 4 ай бұрын
S A W From South Africa I love Somalia neshida ❤
@mussemamuzemil6980
@mussemamuzemil6980 4 ай бұрын
Actually the nasheed is from Ethiopia , but anyways it is what it is.......
@samiromar8795
@samiromar8795 4 ай бұрын
Manzuma from Ethiopia
@migrationeth3676
@migrationeth3676 4 ай бұрын
Woow mashalla እድሜ ይስጣችው አፈልቁት ብዙ አለ ያልተሰማ የጅማ ሀድራ በርቱ
@Roma_Tube_
@Roma_Tube_ 4 ай бұрын
ማሻ አሏህ 💚💚💚💚💚💚
@AbdulsemedDebelo
@AbdulsemedDebelo 4 ай бұрын
ማሻአላ ናቸው ውሉም ስራዎችህ አላህ ይቀበልህ እኔ አፈቅራቸዋለው ነሺዳዎች
@ShadiaAbd-fv6gh
@ShadiaAbd-fv6gh Ай бұрын
❤ንቅንቅ የለም ከአንቱ ያኩረት አይኔ የሙሀመድ /ሰአወ /መባል ይበቃኛልእኔ መድሀኒታችሁን ውሰዱኝል እንኩ መዳን ያሳመኛል ህመሜን አትንኩ❤
@jemilseid7385
@jemilseid7385 4 ай бұрын
Subhan ALLHE Endat yale getme nw Endat yale bere nw wedja leba leze bere dema kelme yehon ❤berehe ayntefe Fouad yedawed family voice jeba teblhale s.a.w
@ABDULAZIZAbDELLA
@ABDULAZIZAbDELLA 4 ай бұрын
Marsha allah
@jafardejene
@jafardejene 4 ай бұрын
Hayi masha Allah Allah yichemirilih
@Ron_Aldo-oi6ur
@Ron_Aldo-oi6ur 4 ай бұрын
Masha allah wow wow fuad shi amet nur allah
@user-df4zt7ii5w
@user-df4zt7ii5w 4 ай бұрын
ሰ.ዐ.ወ በጣም ቆንጆና ድንቅ ስራ ነው ❤❤ በርታልን ፉአዳቺን ❤❤❤
@user-df4zt7ii5w
@user-df4zt7ii5w 4 ай бұрын
ሠላሜ እውነትም ሠላማቺን ነወት ሰሉ ያጀማአ ሰ.ዐ.ወ ❤❤❤
@Nurhusan-ud7jt
@Nurhusan-ud7jt 2 ай бұрын
ማሻ አሏህ
@HazikTube
@HazikTube 2 ай бұрын
በጣም ደስ ይላል የናንተስ❤❤❤❤
@FezekirenayeFezekir
@FezekirenayeFezekir 16 сағат бұрын
waw fuade betame adnakehe nege
@abdurehussen8107
@abdurehussen8107 Ай бұрын
Masallah allah yechemrelk
@MameMuhe-vp6fu
@MameMuhe-vp6fu 4 ай бұрын
👍👌👍👌👌👌👌👌masha allah “selellahu aleyhi weselm”
@user-ly3bt2ey9k
@user-ly3bt2ey9k 25 күн бұрын
Masha Allah Masha Allah
@Abdulaziz-ni8cz
@Abdulaziz-ni8cz 4 ай бұрын
ዋይ ዋይ አቤት መደድ እንዴት ደስ ይላል አቦ ማሻአላህ ሀያት ሀያት...ፉአድዬ
@user-ko2nd5tb2k
@user-ko2nd5tb2k 4 ай бұрын
ماشاء الله تبارك الله ❤❤صلى الله على محمد صلى الله عليه وسلم صلى الله عليه وسلم صلى الله عليه وسلم ❤❤❤
@user-Yerewduaw
@user-Yerewduaw 4 ай бұрын
❤❤❤❤ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ያሠላም ልዩ ነው ወሏሂ ,,ሠላሜ,,
@usmailyasiin
@usmailyasiin 4 ай бұрын
Woow yemigerm manzu ❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@QqQq-jn7hp
@QqQq-jn7hp 4 ай бұрын
ماشاءالله تبارك الله وتقبل الله طاعتكم يا حبيبي ❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉
@NusraNusnetsi
@NusraNusnetsi Ай бұрын
Mashallah betam des ylal
@user-bu3jl9ih1u
@user-bu3jl9ih1u 4 ай бұрын
Heyyy masha allah 😢 muhamed
@GMaryamNega-rz6px
@GMaryamNega-rz6px 2 ай бұрын
❤mashaAllha❤
@user-jn8ym6fo4w
@user-jn8ym6fo4w 4 ай бұрын
ፉአድ በጣም ነው ሚዎደው 👍👍
@MuradAman-vl1fp
@MuradAman-vl1fp 2 ай бұрын
Mashaallah ❤❤❤❤❤
@abukiabuki9068
@abukiabuki9068 4 ай бұрын
Wow new zelqo sigeba kante miweta ayemeslim bertalin👍👍👍👍
@tomiyesuf1147
@tomiyesuf1147 4 ай бұрын
ማሻላህ ፉአዴ ምርጥ መንዙማ ነው ያወጣከው አንደኛ
@sualihahmed42
@sualihahmed42 4 ай бұрын
Fuade konjo sra❤
@FNe-gl3iv
@FNe-gl3iv 4 ай бұрын
Enkuan mMohammedn Yemiyamrut nebiyen Sentu tena honuale enatun selaye❤❤❤❤❤❤❤😢😢😢😢😢😢😢😢😢
@jimijx7501
@jimijx7501 4 ай бұрын
💓💓👏👏👏👏👏 ዑስታዛ ሰይድ አክመድ አላህ ረጅም ሀያትትት😍😍 fuada አረረረረ አላህ ይጠብቅክ አላህ ያስደስትክ ነቢዩም ሰ.ዐ.ወ ይደሰቱብክ ሀያያያትትትት👏👏🙏🙏🙏🙏
@RamadanCreativeEthiopia
@RamadanCreativeEthiopia 4 ай бұрын
ስለላሁ እልህ ወሰለም ሀቢብ አላህ
@LizaAbdela
@LizaAbdela 3 ай бұрын
Saw saw🥹😍😍😍 Masha Allah
@jundijundela
@jundijundela 4 ай бұрын
mashalhe wendme berka hun❤❤❤❤❤❤❤❤
@emumeryem6766
@emumeryem6766 2 ай бұрын
ይህ መንዙማ ግን ይለያል ❤❤❤❤❤❤❤ ❤❤❤❤❤❤❤ ማሻአላህ
@user-uw2mm3mh5l
@user-uw2mm3mh5l 3 ай бұрын
❤❤❤❤😢😢😢🎉🎉🎉 i love you fuad
@Safiay-sb8cl
@Safiay-sb8cl 4 ай бұрын
ماشاءالله💚💚💚💚💚💚🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
Mama vs Son vs Daddy 😭🤣
00:13
DADDYSON SHOW
Рет қаралды 51 МЛН
ለትውስታ ፉአድ ሸምሱ|Fuad_shemsu new cover menzuma
11:15
FUAD SHEMSU OFFICIAL
Рет қаралды 1 МЛН