በጉጉት ሲጠበቅ የነበረዉ የ_DNA ዉጤት | እርቅ ማዕድ ዱባይ ድረስ የደከሙበት የእናቴ አይደለሽም ዉዝግብ | የእርቅ ማእድ።

  Рет қаралды 92,658

Sami Studio

Sami Studio

2 жыл бұрын

#የእርቅ_ማእድ #Ethiopia #የሰላም_ገበታ Welcome to our channel,
Sami Studio that brings you highly educational videos and useful tips focused on youth life with a vision of bringing meaningful change on the relationship between family members.
- parents, children and love partners
- be with us. We are ready to serve you with loyalty and strong commitment.
- Your feedback is a backbone for our strength, So please don't hesitate to write us your comment.
- Sami Studio is happy to serve you, Stay with us!
ሳሚ ስቱድዮ፦
በተለይ ወጣቶችን ትኩረት አድርጎ በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር የሚሰራ የዩቲዩብ ቻናል ነዉ።
በቤተሰብ አያያዝ፤ በልጆች አስተዳደግ፤ በፍቅር ግንኙነት፤ ደስተኛ ስኬታማና የተሻለ ራእይ ያለዉ ቤተሰብ እንዲኖራችሁ እዉነተኛ ለዉጥ ለማምጣት የሚጥር ቻናል ነዉ።
ተከታተሉን እናንተን ስናገለግል ከልብ ደስ እያለን ነዉ!
አስተያየታችሁ ስህተታችንን እንድናርም ይጠቅመናልና ከመጻፍ አትቆጠቡ። ቤተሰብ ስለሆኑ ከልብ እናመሰግናለን።
ሳሚ ስቱድዮ

Пікірлер: 402
@SamuelWoldetsadik
@SamuelWoldetsadik 2 жыл бұрын
እርቅ ማዕድ ዱባይ ድረስ የደከሙበት በእናትና ልጅ መካከል እናቴ አይደለሽም ክርክር። የመጀመሪያዉን ክፍል ላልሰማችሁ ከስር ያለዉን ሊንክ ይጫኑ kzfaq.info/get/bejne/mMqajLKllrTZcmg.html
@yeneneshekebede9707
@yeneneshekebede9707 2 жыл бұрын
ድሮ ሰምተነዋል ይሄን ታሪክ ድጋሚ እኮ ነው
@wubalembonaya923
@wubalembonaya923 2 жыл бұрын
ሰምተናል
@user-dd4qo6fb7v
@user-dd4qo6fb7v 2 жыл бұрын
እናመሰግናለን እናንተን
@tekeleyodit9304
@tekeleyodit9304 2 жыл бұрын
@@yeneneshekebede9707 ጠኡኡኡኡኡአአአአአአአአ
@zulikayonis1607
@zulikayonis1607 2 жыл бұрын
P
@user-cs4oo2bu7q
@user-cs4oo2bu7q 2 жыл бұрын
እናትነት "እዉነት" የሚባለዉ ለዚህ ነዉ።እማማ አምጠዉ ስለወለዱ ነዉ ደፍረዉ የመጡት። ብቻ እግዚአብሔር ይመስገን☝🙏
@belaydagnew4334
@belaydagnew4334 2 жыл бұрын
እናትነት እውነት አባትነት እምነት ነው በጣም አሳዛኝ አሳፋሪ ነው ከዚህ መድረስ አልነበረበትም ግን መጨረሻው እንደሚያምር እርግጠኛ ነኝ።
@aselefechgezmu204
@aselefechgezmu204 2 жыл бұрын
አማማ አንኳን ደሰ ያልዋት በጣም ደሰ ይላል ለልጂዋት ይቅርታ አርጉላትለሷም ልብ ይሰጣት ለጎረቤቱም ልብ የሰጥ እማምዬ እንኳን አምላክ አንባዋትን አበሰው
@wegayehubiru1801
@wegayehubiru1801 2 жыл бұрын
በጣም የሚገር ታሪክ ነው አንዳንዴ እናትም አባትም ሳናውቅ ከልጅ ልጅ እናዳላለን ያደሞ በልጅ አይምሮ ላይ ትልቅ ተጽኖ ያመጣል ይህ ትምርት ሊሆነን ይገባል
@stmarytsegaye
@stmarytsegaye 2 жыл бұрын
በጣም ይህ የቆየ ታሪክ ቢሆንም ያስተምራል እኔ አባቴ በጣም ከእንጀራ እናቴ ጋር ሆኖ በጣም ያስከፋኝ ነበር ሌሎች እህቶቼን ሲንከባከብ ጎረቤት ሄጄ አባቴ ነው ብዬ ጠየኩኝ በወቅቱ ተቆጡኝ፣ መከሩኝ ተውኩ ። እንደዛሬ ግዜውም አልከፋም ነበር።
@mekidesmekides2032
@mekidesmekides2032 2 жыл бұрын
ሁል ግዜ ልጆችን እኩል አልማየት ትርፍ ይሄ ነው, እኔ favorite ልጅ ሲባል በጣም ተፀኖ ያመጣል በቀ ሩት ላይ!እባካችሁ Balance🙏🌹😘 እናድርግ
@msrthemsrthe
@msrthemsrthe Жыл бұрын
😅😅
@kikigetanhe7614
@kikigetanhe7614 2 жыл бұрын
በጣም ያሳዝናል እናትን የሚያስክድ ዘመንን መስማት እናት እናትሽ ነኝ ባትልም በአስደገችን ጊዜ ውጣውረዱዋ መንከራተቱዋ ብቻ በቂ ማሳመኛ ነበር እንኩዋን መልስ ተገኘ ይቅር ተባብሎ ወደፍቅር መለወጥ ነው ግንኙነቱን እናት እንኩዋን ደስ አለዎት 🙏🏼👍
@hiruttefra6996
@hiruttefra6996 2 жыл бұрын
ውይ ደስ ብሎኛል እንኳን ደስ አላችሁ በተለይ እናት ጭንቀታቸው ይገባኛል ጠላት ደስ አይበለው ፍቅራችሁ ይብዛ
@hjfhanalhff9128
@hjfhanalhff9128 2 жыл бұрын
እረ ይቅርታ
@seadaloveweloo4779
@seadaloveweloo4779 2 жыл бұрын
እናቲቱ አስለቀሰችኝ እኳን ደሳላችሁ እኔም በጣም ደስ ብሎኛል።
@zinashtekeste3314
@zinashtekeste3314 2 жыл бұрын
በጣም ደስ የላል፤ እናት በጣም ያሳዝናሉ እግዚአብሔር እንባቸውን አይቷል። በቃ ልጀቷ የማንነት ቀውስ አጋጥሟት ነበር፤ አንዳንዴ ቤተሰብ ውስጥ ከሚሰጠን እንክብካቤ የተነሳ የሚመስለን ነገር አለ ጭንቅላታችን የሚፈጥርብን ነገሮች እና ከዚህ በዋላ በህይወቷ ላይ ፀፀት እንዳይፈጠር ሊረዷት ይገባል እናት ም ሆኑ ሌላው የቤተሰብ አካል "አንቺኮ እናትሽን የካድሽ ነሽ" የሚል ነገር እንዳይጠቀሙ መጠንቀቅ ነው። በግጭት ሰአት አንዳንዴ የበፊቱን ጥፋት እያነሱ የመወቃቀስ ባህል አለብን።
@zubaydazubayda6188
@zubaydazubayda6188 2 жыл бұрын
እህቴ ተሳስተሻል መውለድ ማንም ይወልዳል ስላሳደጉሽ እንኴን ማመስገን ነበረበሽ ክብር ይገባቸዋል ማሳደጉ ውጣ ውረዱ ከባድ ነው
@mebratl.abraha5022
@mebratl.abraha5022 2 жыл бұрын
አሜን ብያለሁ ለእርቅ ማእድ የደስታ እምባ አምብቻለሁ😭😭😭😭😭 ምን አይነት ዘመን ደረስን ስንል፣ በአንጻሩም እንዲህ ማስተዋል የሞላባቸዉ ሚዲያዎች ስለተፈጠሩልን አመስጋኞችም ጭምር እንድንሆን አስተምረዉናል። እንኳን ደስ ያላችሁ💐💐💐
@hanieh4374
@hanieh4374 2 жыл бұрын
"የእናት ዉለታዋን ሳወሳ አለቅሳለዉ ደግናቷ ብዙ መሆኑን አዉቃለዉ" የሚለዉን የብዙዬ ዘፈን ደጋግመሸ እንድትሰሚዉ እጋብዝሻለዉ .. ክህደትሸ የመጣዉ ደካማ ሴት ስለሆንሸ ነዉ የሰዉ አሉባልታ እየሰማሸ የገዛ እናትሸን እንድትክጂ ያረገሸ ከስህተትሸ ተማሪ የገዛ እናትሸም እንኳን ባይሆኑ አሳድገዉሻል ለዛ ዋጋ ልሰጭዉ ይገባ ነበር ነገረኛ ሰዉ ዞሮ ዞሮ እራሱን ነዉ የሚጎዳዉ ሂወት ያሰተምርሸ..እርቅ መአድ ከልብ እናመሰግናለን ቢያንሰ ቢዬንስ ለምሰኪ እናትየዉ ሰለደረሳቹሁላቸዉ ማለት ችግሩን ሰለፈታችሁ
@uaeuae282
@uaeuae282 2 жыл бұрын
ወላሂ የልቤን ነዉ የፃፍሽዉ ዉዴ
@user-bg1cw1lu8p
@user-bg1cw1lu8p 2 жыл бұрын
ትክክል እህቴ እኚ እናት ላስደገቱ ውለታ በመክፈል ይህ ሁሉ ታሪክ ምንም ያስፈልጋል ። ወይ ዘመድ ያስኛት ። እናት ባይሆኑስ በጨዋ ደንብ ማነጋገር ነው።
@abebanati574
@abebanati574 2 жыл бұрын
ጎረቤቶች ችግር አለባችው እናትየው እንኳን ደስ አላችሁ ለልጅቷ የስነ ልቦና ክትትል ያስፈልጋታል
@jesusking7000
@jesusking7000 2 жыл бұрын
Betam ljitam chugr alebat
@zaaaaa6841
@zaaaaa6841 2 жыл бұрын
ምናልባት ልጁቱ ሴይጣን ነገር ተጠግተ፱ት እንዳይሆን እንደዚህ ያደርጋል እሡ ነው በቤተሰብ መሀል እየገባ የሚያበጣብጠው
@meazagenet4428
@meazagenet4428 2 жыл бұрын
ወይ ዘንድሮ ምንም መተማመኛ የለንም እኮ። ወልደን አሳድገን ሌላ የክህደት ጭቅጭቅ ¡ጉድ ዘንድሮ የማንሰማው ነገር የለም። ጌታ ሆይ አድነን
@user-uf9wp9tn2t
@user-uf9wp9tn2t 2 жыл бұрын
ለበጎ ያልታደለ አይምሮ ለተንኮል ተወዳዳሪ የለውም አለመታደል ለእናት የማይገባ።ን ፍርድ መስጠት ለእድሜልክሽ ጸጸትና ሐዘን ነው።
@wintakinfe9563
@wintakinfe9563 2 жыл бұрын
አስተያየት ሰጭዎች ምን ነካችሁ ነው እናት ፍቅር በመስጠቱ አንቺ አመቶ በመውለድ አይደለም ሳይወለዱ ፍቅር የሚሰጡ እናቶች አሉ ወልደው ጨካኝ እናቶች አሉ
@stmarytsegaye
@stmarytsegaye 2 жыл бұрын
ትክክል ይባል የለ እበትም ትል ይወልዳል !!!
@annanmuse7380
@annanmuse7380 2 жыл бұрын
ልብ አንጠልጥል ታሪክ,ነበር,,ገላገለችሁን,እድሜ,ለቴክኖሎጂ አነኩዋን,ደስ,ያሎት,ወ/ሮ,በቀለች
@yordidemlie2594
@yordidemlie2594 2 жыл бұрын
እናትነት ሚስጥር ነው እህታችን እግዚአብሔር ወደ እራስሽ ይመልስሽ ተመስገን አምላኬ ።
@salamgedawn4047
@salamgedawn4047 2 жыл бұрын
እውነት ነው እናትነት ከባድ ነዉ አምጠው የወለዶትን ልጅ ማስካድ ይከብዳል እማማዬ የኔ እናት እንኳን ደስ አሎት
@hiowtabate69
@hiowtabate69 2 жыл бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን አንዳንድ ጓረቤት ችግር አለበት እኔ አውቅልሻለው የሚል 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭🙏🙏❤️
@zadebuna590
@zadebuna590 2 жыл бұрын
እናትነት እውነት ነው ይላል እንዳልክ 😍 ልጅቷ ላይ አልፈርድም የስደት ኑሮ ከዚህም በላይ ያስብላል እረዳታለው ፈጣሪ ፍቅሩን ይመልስላቸው🙏
@genettube277
@genettube277 2 жыл бұрын
የሚቀናባቸው ሊለያይ የሚፈልጉ ጠላት ይኖራል የሚመክራት ሠው ይኖራል ልፊ ሢላትኮነው ገንዘቧን ሢያከስራት ሰይጣን
@jojojo6083
@jojojo6083 2 жыл бұрын
Well said
@user-vf1jn7bi2z
@user-vf1jn7bi2z 2 жыл бұрын
Enatn yasikdal ende kebad new
@sarajeesas6922
@sarajeesas6922 2 жыл бұрын
Ewunat new 😊
@user-mo2so5xu2j
@user-mo2so5xu2j 2 жыл бұрын
እማማ እንኳን ደስ አለሆት በጣም ልቤ ተሰብሮ ነበር እህታችን ደግሞ በደንብ ፀበል ተፀበይ ወደራሰሽ ተመለሽ ማንኛዎ እውነተኛ እንደዎቹሁ አላውቅም ግን ወያላ ሁነሽ ሰርተሽ ቤተስብ ሰትረጅ የነበርሽ ጅግና እንዲሁም አንች ነሽ በእውነት እና እህቴ መተት እሚባል የደፍተራ ሰራ አለ አድርገውብኝ ነው ብለሽ አሰቢ ማማዬ በተረፈ የዚህ ሚዲያ ባለቤት እግዚአብሔር ኧረጅም እድሜ ይሰጣቹሁ ኑሩልን ጥሩ ሰራ ነው ቀጥሉበት
@user-yl2pq1ys4n
@user-yl2pq1ys4n 2 жыл бұрын
ብእውነት እናተ አዘጋጆች ፈጣሪ ይባርካችሁ በጣም ደስ የሚል ፕሮግራም ነው ለልጅቱግን ትንሽ ጤናዋላይ ያሳስባልአይ እናት ሽ አመት ኑሩልን በጣም ደስ ብሎኛል መጨረሻው እንዲህ በመሆኑ
@belayshebo3149
@belayshebo3149 2 жыл бұрын
Eko mine malate nawe asadigawe abira Nora baande biding bilha enate ayidolashhimme melaat
@-beteorthodoxchannel3244
@-beteorthodoxchannel3244 2 жыл бұрын
በቅንነት ቤተሰብ እንሁን የተዋህዶ ልጅ🙏💒
@etaferahuabebegebru1580
@etaferahuabebegebru1580 2 жыл бұрын
በጣም ደስ የላል የሚገርመው ነገር ደግሞ ማንም መለየት የሚችል ይመስለኛል ከእህቷ ጋር ድምፃቸው አንድ ነው፤ እናት በጣም ያሳዝናሉ እግዚአብሔር እንባቸውን አይቶ አበሰላቸው። በቃ ልጀቷ የማንነት ቀውስ አጋጥሟት ነበር፤ አንዳንዴ ቤተሰብ ውስጥ ከሚሰጠን እንክብካቤ የተነሳ የሌላ ሰው የሆንን የሚመስለን ብዙ ሰዎች እንኖራለን፡፡ ልጅቶ ወደፉት በፀፀት ስሜት አይምሮዋ እንዳይበላሽ ፡፡ ቤተሰብም ሞራል የሚነካ ንግግር ማለትም "እናትሽን የካድሽ ነሽ" የሚል ነገር እንዳይጠቀሙ መጠንቀቅ ነው። በግጭት ሰአት አንዳንዴ የበፊቱን ጥፋት እያነሱ የመወቃቀስ ነገር እንዳይኖር በጣም በዚህ ቤተሰብ መሰራት ይኖርበታል፡፡ ለአዘጋጆቹ እግዚአብሔር ይስጣችሁ፡፡
@ethiolal2148
@ethiolal2148 2 жыл бұрын
እማዬ እንኳን ደስ ያለዎት::
@ye_abam
@ye_abam 2 жыл бұрын
ይቺ ልጅ ግን 🙄ጤናዋ ያሳስበኛል
@tibaahmad8918
@tibaahmad8918 2 жыл бұрын
እድሜ ተቀንሶ የሚሰጥ ቢሆን ለናቴ ብሰጣትደስይለኝነበር እማየ የኔውድ ባለሽበት ሰላምሽ ይብዛ የስደትኑሮየን ጨርሽ በሰላምያገናኝነ
@sintayehubelay6929
@sintayehubelay6929 2 жыл бұрын
ዋው በጣም የኔ እናት እንኳን ደስ አሎት❤❤❤
@asseb9842
@asseb9842 2 жыл бұрын
በውጤቱ በጣም ነው ደስስስስስ ያለኝ እንባየም መጣ 😭😭😭
@yayashyayash1358
@yayashyayash1358 2 жыл бұрын
ዋዋዋዋዋ በጣም ደስ ይላ እናቴ እንኳ ደስ አለወት።
@menberebekele2374
@menberebekele2374 2 жыл бұрын
እርቅ ማእድ በጣም ጥሩ ፕሮግራም ነው አቅራቢዎቹም እግዚአብሔር ይባርካችሁ ይሄን ቤተሰብ ሰላም እንዲያገኝ በማድረጋችሁ ልትመሰገኑ ይገባል
@leyaleya4383
@leyaleya4383 2 жыл бұрын
ወይኔ እንዴት ደስ ይላል የመጀመሪየውንም ታሪክ ሰምቼዋለሁ በጣም ልብ ይነካል እናቴ እንኳን ደስ አሎት በእውነት ውስጤን ተሰምቶኝነበረ እንኳን ደስ አላችሁ ሁላችሁም አንችም የሰው ወሬ ሰምተሽ እናትሽን አሳዘንሻቸው ከአንጀታቸው ይቅር እዲሉሽ ለምኛቸው
@mekilitkidist1542
@mekilitkidist1542 2 жыл бұрын
እኔ ልጅቷላይም አልፈርድም አንዳንዴ ቤተስብ ላይ ያለ ተፅኖ እና አድሎ እራሱ ምንም እንኳን ባትባልም ትልቅ ጥያቄ ይፈጥርብካል አብሶ ካልስራህ ወይም ስደት ኖርህ ሀገር ስገባ በጣም ብዙ ቤተስብ ልክ እንደ እህታችን ጥያቄ እንዲያድርብክ ነዉ የሚያደርጉት በዛ የተነሳ ሌላ ነገር ዉስጥ ሲከቱህ ድፍርት ያለዉ ልክ እንደህታችን ይጠይቃል የሌለዉ ዝብሎ ስለሚኖር ነዉ እና ቦታዉ ላይ ሆናችሁ ህመሙን የደርስባትን ተፅህኖ ሳትርዱ የመስላችሁን አግባብ ያልሆነ ኮሜንት አትስጡ አትፍርዱባት እህቴ እንኳንም ለጥያቄሽ ትክክለኛዉን መልስ አገኘሽ እንኳን ደስ አለሽ አላችሁ
@mellkimesewesemyeedayeteni8876
@mellkimesewesemyeedayeteni8876 2 жыл бұрын
የእኔእናትአሰሐቀሱኝ😢😢😢😢😢 የኔ እናት እንኳንደሰአሎትእኔንይዝጋኝ😭😭😭😢😢
@saadayimer8273
@saadayimer8273 2 жыл бұрын
ማሻአላህ ተባረክአላህ እንደት ደስ ይላል እኮን ደስ ያላችሁ ይህ ነገርኮ በጣም. ከባድ ነው እኔ አባቴ በልጅነቴ ድቃላ እያለ ይሰድበኝ ና ያገለኝ ነበር ይደበድበኝም ነበር እናም አረብ ሀገር ከመጣሁ ቡሃላ በጣም ላባቴ ጥላቻ ነበረብኝ ያኔ ህፃንም ስለነበርኩ በውስጤ ይዠ እዚህ ስመጣ ግን ባ12. አመቴ አረብ ሀገር መጣሁ 5 አመት 5ወር ስርች ሀገር ገባሁ ያኔም ጥሩ ፍቅር ለሶስት ቀን ይስጠኝ ነበር ከዛም ተመልሽ በመጣሁ ባ4ኛ አመቴ ለምን ነው ድቃሏ ብሎ ይስድበኝ የነበረው አባቴን ንገሩኝ ብየ ስስቅ ብየ አልቅሽ እህቴ አባቴን ተቆጥታ መክራ ስላልተማረ አንችን ያስከፋሻል ብሎ ስላላሰበንጅ አንች ልጃችው ነሽ እህቴ ነሽ አለችኝ እናቴንም አባቴን ንገሪኝ ስላት አባትሽ እሱ ነው ግን ስው እሜያስቀይመውንና እማያስቀይመውን ስለማያውቅ እኔ ና አባትሽ በምንጋጭበት ጊዜ ለኔ ስለምታደይ ነው እየተናደደ ነው አለችኝ ከዛም ልቤ አረፈ ማልቀሴንም ተውኩኝ ያኔ እናቶ እንደዜያ ቤያስረዶት ይህ ነገር ባልመጣ ነበር ለማንኛውም ደስ ይላል ወላጆች ልጆችን ሴያሳድጉ ካዱ አንዱ ባያዳሉ ጥሩ ነው
@user-dd4qo6fb7v
@user-dd4qo6fb7v 2 жыл бұрын
ወይ ጊዜ ለማንኛውም እንኳን ደስ ያላቹ እኔ እናቴ አባቴን በህይወት የሉም በልጅነቴ ነው ያጣሆቸው ግን ምናለ እናትሽ ወይ አባትሽ ነኝ ብሎ ቢመጣ ሰው ብዬ እመኛለሁ
@zebibaabate4026
@zebibaabate4026 2 жыл бұрын
ልጅቱ ህክምና ያስፈልጋታል የስና ልቦና ክትትል ያስፈልጋታል ጤነኛ አትመስለኝም እናቷን እንደት ትክዳለች እነዚያም ጎረቤቶቻቸው ግን አሁን ይፈሩ
@rahmarahma8209
@rahmarahma8209 2 жыл бұрын
😂😂😂😂በከባዲችግርአለባት ልጂቷ😂
@meremmuhammed5675
@meremmuhammed5675 2 жыл бұрын
ልጅቱ በጣም ችግር አለባትልል ነበር ግን አዳድ ወላጅወች ችግር አለበት ልጆችን ያበላልጣክሉ በፍቅር አያዩም ክፉ ብትሆንም ፍቅር መስጠት ግድ ነበር
@user-tz1hf4dl4j
@user-tz1hf4dl4j 2 жыл бұрын
ኦህህህህህ እኒህ እናት በጣም ነበር የሚያሳዝኑ በመጀመሪያው ክፍል ሰምቸዋለሁ እጅግ ልብ ይነካሉ ።ደግሞ ምንም አያስመስሉም ልክ እንደ ድሮ እናቶች እውነተኛ እና ቀጥተኛ ናቸው ።አንድ እናት አሳድገው ለፍተው ድንገት እናቴ አይደለሽም ሲባሉ የሰጡት ምላሽ ትክክለኛ እና በእሳቸው ግንዛቤ ሚጠበቅ ነው ። ጎረቤት ተብየወች ናቸው የእሳቱ አቀጣጣይ ልጅቱን ማሳመን ይችሉ ነበር ።በመጣች በነጋታው ንብረቱአን ይዛ ስትሄድ ዝም ብለው ተቀበሉአት መነጋገር እየተቻለ ። በቤተሰብ በኩል ብዙ ጊዜ በተለይ የበፊት እናቶች ልጆችን መመረቅ እወድሻለሁ ማለት ያሳሳቸዋል የሆነ ነገር እንደሚነጥቃቸው ነው ሚአስቡ ፍቅርን መግለፅ አሁን አሁን ነው እወድሻለሁ እወድሀለሁ ማለት የበዛ ።ስለዚህ እናትሽ ይህን ቃል እየተጠቀሙ ባያሳድጉሽ አትፍረጅ ።ሌላው ደግሞ እህት ወንድም የምንበሻሸቀው ነገር አለ እቤት አንች የኛ ልጅ አይደለሽም አንተ የኛ ልጅ አይደለህም በሚል እንበሻሸቃለን ግን ይህ ነገር ያድግና ለእንደዚህ አይነት ነገር ይዳረጋል ።ዘመድም እሰው ቤት ስንሄድ አንዱን ልጅ ውይይይ ይህ ልጅ በማን ወጥቶ ነው ማንንም አይመስልም የምንለው ነገር አለ ።እባካችሁ ትንሽዬ የምንላት ቃል አደገኛ ነገር ስለምታስከትል እናስተውል ። ውጤቱን የምጠብቀው ነበር ምክንያቱም የነበረው ጉዳይ ግልፅ ነበር ። እናመሰግናለን ሣሚ እና ምንቴ👏👏
@azeb8385
@azeb8385 2 жыл бұрын
ተመስገን እንዴት ደስ ይላል አይዝዋችሁ ሁሌ ጠላት በስው ልብ ውስጥ ክፋትን እያስቀመጠ ቤተስብን አገርን ይበጠብጣል ልጅትዋ ላይ ማንም አይፉረድ የተስማትን ገልፃለች ከውጭ ስዎችም የሆነ የሆነ ነገር ይልዋት ይሆናል ብዙ ልብን መጠት ጥሩ አይደለም እውነቱ ስለተገለጠ እግዚአብሔር ይመስገን እናት እህቶችዋም በፉቅር እቀፉዋት አንድ ነገር ብታጠፋ ጥፋትዋን እያነሳችሁ እንዳትወቅስዋት እራስዋን ለቤተስብዋ መስዋእት ያደረገች ነች ከታሪኩ እንደስማነው በርቱ
@tigistmamo7604
@tigistmamo7604 2 жыл бұрын
ማስተዋል የተሳናት አጭበርባሪ ናት ልጅ እናቱን ከሞት አያድንም እናትየዋ ከሷ ጭቅጭቅ በሰላም በጤና ከነ ድህነታቸዉ ቢኖሩ ይሻላል
@hanna8382
@hanna8382 2 жыл бұрын
Tikikle
@medinaseidmuhammed1313
@medinaseidmuhammed1313 2 жыл бұрын
በጣም ወሏህ
@belayshebo3149
@belayshebo3149 2 жыл бұрын
Yich lije lije honaam atixakimem wuxetun kawoku Matawan nawe yelabachchawe
@jesusking7000
@jesusking7000 2 жыл бұрын
Betkkl wshetam nechu demo msgana tfelgalechu sladeregechu
@semret978
@semret978 2 жыл бұрын
ትክክል
@taz3739
@taz3739 2 жыл бұрын
ክብር ይስጣቹ እውነቱን በማውጣት ቤተሰቡን ሰላም የፈጠራቹ ❤
@user-bg5sf8sz2c
@user-bg5sf8sz2c 2 жыл бұрын
የኔ እናት እንኳን ደስ አሎት እኔ ለእሳቸው ነበር የጨነቀኝ እረ በሰው ሕይወት እየገባችው የምትበጠብጡ ሰውች ፈጣሪ ልቦና ይስጣችው
@baytaworwatube4556
@baytaworwatube4556 Жыл бұрын
እኔ የመጨርሻ ልጂ ነኝ እና እናቴ ለኔ ታደላለች ይህ ማለትሌሎቹ ልጆቿ አይደሉም ማለት አይደለም የመጨርሻ ልጂ ስለሚሳሳለት ብቻ ነው ብዚህም እህቶቼ አይከፍቸውም ❤❤❤❤እናቴ እድሜሽን እርሞልኝ መጥቼ ናፍቆቴ ብሶቴን የምነግርሽ ያርገኝ ❤እማ እዎድሻለሁ ❤❤
@sarafaris5018
@sarafaris5018 2 жыл бұрын
ውይ በጣም ደስ ይላል ልጅቱ ግን ትገርሚያለሽ።
@Bwrrlt
@Bwrrlt 2 жыл бұрын
አይዞሽ እህቴ ወደሽ አይመስለኝም እንዲህ አይነቱ ክፉ ሀሳብ ወደ ውስጥሽ የገባ የዲያቢሎስ ስራ ነው በርትተሽ በፀበል ድራሹን አጥፊ እሱ ነው ሰውን ከሰው የሚለያየው
@userLubaba-iq3po7cj1e
@userLubaba-iq3po7cj1e 2 жыл бұрын
ልጅትዋ ህክምና ያስፈልጋታል ከራስዋጋ አይደለችም. ነገሮችን ሁሉ ገልብጣነው እምትተተጉመው. አድርጋ እንዳላደረገች ሰርታእንዳልሰራች ቤቱሰብሁሉእንደሚጠላት ነው አሁንላይ እሚሰማት እናትየው ግን ያሳዝናለው
@etaferzeleke4643
@etaferzeleke4643 2 жыл бұрын
ያጋጥማል እኔም እንደዚህ አይነት ሀሳብ አንስቸ አውቃለሁ ዋናው ነገር እውነቱን ማወቅ ነው
@bezuayehubekele7174
@bezuayehubekele7174 2 жыл бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን!!!እናንተም ተባረኩ።
@zuzuahahzuzu1279
@zuzuahahzuzu1279 2 жыл бұрын
እንኳን ደሰ አላችሁ በጣም ደስ ይላል አላህ ፍቅራችሀን ይመልስላችሁ እንዳልክ የስንቱ ድአ ይጠብቅሀል
@meseretlema9655
@meseretlema9655 2 жыл бұрын
እሰይ እንኳን ደስ አላችሁ ሰይጣን ነው የሚጫወትባት እውነት ክፉ መንፈስ እንደው አሁንም ፀበል ያስፈልጋታል
@user-wo3fn3sn3z
@user-wo3fn3sn3z 2 жыл бұрын
የኔ እናት እንኳን ደስ ኣሎት👍👍
@eliasedris700
@eliasedris700 2 жыл бұрын
እንዴት ደስ ይላል በጉጉት ነበር የምጠብቀው እናት ምንግዜም እናት ናት
@metages9762
@metages9762 2 жыл бұрын
በእውነት በጣም ነው ደስ ያለኝ ኡፍፍ ባለፈ አዝኜ ነበር
@ritagashaw7188
@ritagashaw7188 2 жыл бұрын
እናት እውነት አባት እምነት በጣም ነው እናትዋ ያሳዘኑኝ በስተርጂና ተሰቃዩ ልጅ ግን የእናት ሀዘን ጥሩ አደለም እናትሽን በጣም ይቅርታ ልትያቸው ይገባል ካሻቸው ያለፈው አልፎል መስሎሽ ይሆናል !! ለማንኛውም እንኳን ደስ አላችሁ መጨረሻው ያምራል
@zenebugebreyes976
@zenebugebreyes976 2 жыл бұрын
እንኳን ደስ አላችሁ እናንተም ተባረኩ
@destagatu5063
@destagatu5063 2 жыл бұрын
የእውነት በጣም ከባድ ግን ለምን እናት እናት ናት ለዘላለም ኑሪ
@mulusara8866
@mulusara8866 2 жыл бұрын
መከራዋን አይታ አሳድጋ እንጨት ተሸክማ በባዶ እግሯ እየሄደች ቄጤማ ሽጬ አለች የእኔ እናት😭 ለዚች እናት ክህደት አይገባትም ነበር። ባትወልዳት እንኳን እንዲህ ላሳደገች እናት ክህደት አይገባትም ነበር እናቴ እማዬ ምንም ብትበድል መካድ ሳይሆን መካስ ነበር ለታደለ ከልቧ ይቅርታ ጠይቃ እድሜ ልኳን ልታገለግላት ይገባል።
@user-uf9wp9tn2t
@user-uf9wp9tn2t 2 жыл бұрын
ነበር ልጅቷ አልታደለችም
@yanaedsanaat282
@yanaedsanaat282 2 жыл бұрын
ይቺልጅ መታከም አለባት ህመም ነው እኔ በታመምኩኝ ጊዜ የነበረብኝ ምልክት ነው መጠራጠር ያልተባለ መስማት የሰው ፊት እና አካል እስከመቀያየር የሚየደርስ ነው አባካቹ
@addisalemtesfaye9767
@addisalemtesfaye9767 2 жыл бұрын
ወልደሽ እይው ያኔ እናትነት ይገባሻል
@Hundumak
@Hundumak 2 жыл бұрын
ልጅቷ አይምሯዋን ሰይጠን ተቆጣጥሮ ነው እንጂ ምክንያቱ አሳማኝ አልነበረም ። እማማ እንኳን ደስ አሎት 🙏🙏🙏
@user-vf1jn7bi2z
@user-vf1jn7bi2z 2 жыл бұрын
Ewnet new kebad new bayweldu enkan asadgew yele Askeyami bahri new
@tigistbirru4622
@tigistbirru4622 2 жыл бұрын
ከፍቷት ነው አድሎ ክፉ ነው
@soniyatesfaye7241
@soniyatesfaye7241 2 жыл бұрын
የልጅቷን ችግር ማንም አያውቅም እናት ስለሆነ አያጠፋም ማለት አይደለም የእናት በደል ማንም አያውቀውም
@user-tz1hf4dl4j
@user-tz1hf4dl4j 2 жыл бұрын
ብዙ የ DNA ውጤቶችን አልነገራችሁንም ከምን ደረሱ ?! ከ 28 አመት በፊት ልጅህ ነኝ ብላ የመጣችው ? ሁለት መንታ ወልዳ አንደኛው ቀይ አንደኛው ጥቁር ሆነ ያለው ? በአንድ ቀን ከሁለት ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበራት ልጁአ የማን እንደሆነ የማታውቅ ?!! ንገሩን መጨረሻውን 👏👏
@watermelonyuh3810
@watermelonyuh3810 2 жыл бұрын
ተመልሷል አባት ነው
@dubairolla5936
@dubairolla5936 2 жыл бұрын
@@watermelonyuh3810 መቸ ቀረቡ??🙄
@QwerQwer-pt1dr
@QwerQwer-pt1dr 2 жыл бұрын
ሌጅቷ ክፉ መንፈስ ይዟት ነው እናቴ ያለቻት ሴትም እጅ ያለበት ይመስለኛል ሌጅቱ ደገ ስለሆነች ገንዘቧን ልትቀባበላት የፈለች ይመስለኛል እናትየው የዋህነታቸው ያስታውቃል
@aynalemderbew4511
@aynalemderbew4511 2 жыл бұрын
ደሰ ይላል እዉነት በመሆኑ ዉጤቱ እ/ር ይመሰገን
@user-yl6er7tk9s
@user-yl6er7tk9s 2 жыл бұрын
ልጂቶ ያማታል ሆሆሆ ሁላቺንም ተገርፈን ተቆጥጠን ነዉ ያደግነዉ እኔም እናቴን አስቀይሚት ነበር ግን አሁን ሰላምነን ነዉ
@mershaabebayehu3095
@mershaabebayehu3095 2 жыл бұрын
እብድ ነሽ።
@mershaabebayehu3095
@mershaabebayehu3095 2 жыл бұрын
እብድ ነሽ።
@tigistbirru4622
@tigistbirru4622 2 жыл бұрын
ልጅ ማበላለጥ መጥፎ ነው😭😭
@serawitbekele2413
@serawitbekele2413 2 жыл бұрын
ልጅ እናትሽን በጣም አሳዝነሻልና ከልብሽ ነሰሀ ግቢ፣
@saraamagreedavid6763
@saraamagreedavid6763 2 жыл бұрын
በልጅትዋ አይፈረድም ሁኔታዎች እንድትል አስገድዷታል እውነትንም ለማወቅ ነው ጥረት ያደረገችው።
@afinchet1282
@afinchet1282 2 жыл бұрын
ወይ በቅዬ ምንመጣ ባችሁ ማዚም እኮ ያሳደግሻት ነች እረ ይቅር ተባባሉ እግዚአብሔር አምላክ ሁላችሁም ይጠብቃችሁ።
@bekiiache5805
@bekiiache5805 2 жыл бұрын
ይገርማል እናቴ እንካን ደስ አሎዎት
@senaithagos8089
@senaithagos8089 2 жыл бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን ግን አንዳንድ መርዝ እህቶች ቤተሰብ ሚበጠብጡ አሉ እህትይው ነት ጭቅላቷን የቀየረችው ጥሩ ያልሆኑ ንግግሮች ልብ ይሰብራል ቤተሰብ ምሀል በንግግር የሰው ጭቅላት በቀላሉ ያበላሻል ማስተዋል ያስፈልጋል
@senait1912
@senait1912 2 жыл бұрын
ፍፃሜው ደስ የሚል ታሪክ ነው እግዚአብሔር ይመስገን ሰይጣን አፍሯል!!!!
@hhb98ndndn58
@hhb98ndndn58 2 жыл бұрын
እሰይይይ እማማ እንኳን ደሰአለዎት
@Ahmed-bj3dz
@Ahmed-bj3dz 2 жыл бұрын
አእምሮዎ አሞታ ይሆናል ልጅቱ
@belaynehfantaye8486
@belaynehfantaye8486 2 жыл бұрын
ማንነት የጠየቀችው እህቴ ትንሽ አምሮዋ ተነክቶ stress ነው፣ አትፍረዱባት፣ ብዙ ጊዜ አረብ አገር የከረመ ሰው ጤንነቱ ይታወካል
@genetdubei9894
@genetdubei9894 2 жыл бұрын
አንዳዴ ስደት አምሮን ይበርዛል ልቦናዋን ይመልስ ባይሆንኳ እንዴት ይባላል አይወላድ ስንት ፈተናአለ
@noreyyaibrahim7190
@noreyyaibrahim7190 2 жыл бұрын
እናት እንካን ደስ አለዎት ይገርማል
@user-bg1cw1lu8p
@user-bg1cw1lu8p 2 жыл бұрын
እናት ባይሆኑም እንኳን እሳቸው እንዳያዝኑ መሆን አለበት ።ምክንያቱም አሳድገውሻል ። ቀስ ብለሽ በዘዴ መጠቀም ማንነትሽ ማረጋገጥ ነው ።እነዚህ ቤተስቦችሽን እንዳይቀየሙ መሆን አለበት።
@bedryaahmed6896
@bedryaahmed6896 2 жыл бұрын
ደስ ብሎኛል እንኩዋን ደስ አላችሁ በእውነት
@aishanuri2750
@aishanuri2750 2 жыл бұрын
በጣም ደስ ይላል እናት እንኩዋን ደስ ያሎት
@happyhappy-qq4nc
@happyhappy-qq4nc 2 жыл бұрын
ወ/ሮ በቀለች እህትየው እንኳንደስ አላችሁ እመቤትለምንእንዲህተሰማሽ አልልም በየቤቱልጃች የተለያየፍቅር ይሰጣቸዋል ለፋተኛ ልጆችቸልይባላሉ ስለዚህ እኔ የዚህቤተሰብ ልጅአይደለሁም ይላሉ አንዳንድነገሮች መስማትይፈልጋሉ ግንመልካምየሆነውንለመስማትመጣርነው ጥያቄሽስለተመለሰልሽደስብሎኛልእንደቀድሞ ፍቅርሽን ድጋፍሽ አድርጊእንኳን ይሄንሳታውቂ አልሞቱብሽ እናትሽ አይዟሽ መልካምደግልጅነሽ ፈጣሪ ሰላሙን አብዝቶ ይስጣችሁ እርቅ መአዳች እናመሠግናለን ።
@Ewoyn_Tewod_84
@Ewoyn_Tewod_84 2 жыл бұрын
የእውነት አምላክ እንኳን አንድ አደረጋቸው! በኛ ማህበረሰብ ውስጥ ብዙ እናቶች ፍቅር በልባቸው ሞልቶ ተርፎ ሳለ የሚታዘዛቸውን ፤ ተሯሩጦ ያገኘውን የሚሰጣቸውን ልጅ "ተባረክ/ኪ በወጣው ይተካልሽ!" ለማለትም እንኳ መልካም ባህርዩን የሚቀይርባቸው ስለሚመስላቸው በአንፃሩ ሌሎቹን ግን ስንትም ዓመት ሠርተውም አግኝተውም "እማዬ እኔኮ አልሳካልኝም ። ለፍቼም እንደፈለግሁት አልሆነም...እትትት ... ብትትት....." ለሚሏቸው አንጀታቸው ይንሠፈሰፋል። እንዲያውም አለፍ ሲል ከዛኛው አፈር ግጦ ያመጣውን የተቀበሉትን ሁሉ አንስተው ይሰጣሉ። ይህች ልጅኮ ከበፊቱም ስነልቦናዋ ተጎድቷል። ታላቅ መጀመሪያ የሄደችበት ሃገር እየሰራችም "አልተሳካልኝም ነበር " እያለች የሶስተኛ ታናሽ ባሬላ ስትሸከም ወያላነት ስትሰራ የቀን ስራ ያውም ከ18 ዓመት በታች ሆና ከሃገር ወጥታም "የህክምና ... የአስቤዛ ..." እያለች የምትልከው ስትመለስ ለራሷ የጤና ምርመራ ማድረጊያ ሠባራ ሳንቲም አልጠበቃትም። ታላቅዬዋ ግን "ይህንን አድርጊ ያንን አታድርጊ !" ከማለት ባለፈ ራሷስ ለምን ሃላፊነቷን አትወጣም ነበር? ደግሞም " የተነጋገሩትን ምኑም አላውቅም...አልሰማሁም..." መጀመሪያ ማን በለኮሰው እሳት ነው እንዳለችው "ጎረቤት ነገሩን ያባባሰው?" ንግግር ማሳመር ብቻውን እውነተኛ አያስብልም። ከጅምሩ ጫናውን አቅልላችሁላት ፣ በንግግርም በተግባርም እየተረዳዳችሁ የራሷንም ህይወት ህይወት እንድትመራ ድጋፋችሁ ባይለያት እዚህም አትደርስም። እናት እንባቸው ያሳዝናል። የኔ ቆንጆ አንቺም ለሰዎች አሉባልታ ጆሮ አትስጪ። እናት ምንም ትሁን ምን በማንም አትተካም። ያልወለደችም ብትሆን አቅፋ ካሳደገች ያው ነው። እንኳን ህይወት እያሉ እግራቸው ላይ ለመውደቅ አበቃሽ! እማዬ እርስዎም በየዋህነትዎ ከልጅነት እስከ ዕውቀት የለፋችበትን ሳትስት የምትሰጥ ደጋፊ ልጅዎን በተራ አሉባልታ እና በተንኮለኞች ግፊት አጥተው ነበር። የጎደለባትን ፍቅር ሠጥታችሁ በሰላም ኑሩ ። ተጨማሪ የስነልቦና ህክምናም ክትትል ያስፈልጋታል። እግዚአብሔር የቀደመ ፍቅራችሁን ይመልስ! 🙏🙏🙏
@samerasamer9335
@samerasamer9335 2 жыл бұрын
በጣም ይገርማል መረመራ ባይኖር ምን እንሆነበር
@genetteferi9552
@genetteferi9552 2 жыл бұрын
የኔናት እንኳን ደስ አሉዎት ።
@watermelonyuh3810
@watermelonyuh3810 2 жыл бұрын
ለመፍረድ በዛ ሰው ጫማ ውስጥ መግባት አለብን እግዚአብሔር ይርዳችሁ
@alemalem7864
@alemalem7864 2 жыл бұрын
ልጅቷ ደነዝ ጥፋተኛ ልጅቷ ናት እርበሰማም
@azebabebe3702
@azebabebe3702 2 жыл бұрын
እናት እዉነትናት አባት እምነት
@moneali7435
@moneali7435 2 жыл бұрын
እኔ በበኩሌ እናት በጣም ነው ያሳዘኑኝ ለማንኛውም እናንተ እግዛብሔር ይስጣችሁ እነሱንም እደ መጀመሬያቸው ያዋዳቸው
@mamijimma5414
@mamijimma5414 2 жыл бұрын
እንኳን በሰላም መጣቹ ሳሚዬ
@thutthut4051
@thutthut4051 2 жыл бұрын
የአረብሀገር ጭንቀት ተደራረባት አየዞሽ እህተ ጌታ ፍቅር ይስጣችሁ
@user-xu8us6kl6u
@user-xu8us6kl6u 2 жыл бұрын
የእርቅ ማእዶች ወደርየላችሁም እናመሰግናለን እነዚህ ክፉ ጎረቤቶች ምክር ያስፈልጋቸዋል ልጅከናአት የሚያጣሉ እግዚኦ
@leiladavid.2632
@leiladavid.2632 2 жыл бұрын
ልጅቱ የጭንቅላት ችግር አለባት ወደ ፀበል 😁
@gjhtdgtu5131
@gjhtdgtu5131 Жыл бұрын
እናትዬው ሲያሳዘኑ እናት አታልቅስ እግዚአብሔር ረጀም ግድም ይስጣት እፍፍፍፍ
@fatimahassan1795
@fatimahassan1795 2 жыл бұрын
ድምጿ ራሱ ከእህቷ ጋ ይቀራረባል
@leiladavid.2632
@leiladavid.2632 2 жыл бұрын
አንድ ሰዉ የሚያወራ ነዉ የሚመሰለዉ 😁
@fatimahassan1795
@fatimahassan1795 2 жыл бұрын
@@leiladavid.2632 በጣም ይገርማል ምን አይነት ጊዜ ላይ እንዳለን እንዴት በእናቱ ጥርጣሬ ይገባዋል ሰው የኣባት እንኳን ቢሆን ያስኬዳል
@leiladavid.2632
@leiladavid.2632 2 жыл бұрын
@@fatimahassan1795 በጣም ይገርማል ልጅቱ የጭንቅላት ችግር ሊኖርባት ይችላል አርዳታ ያሰፍልጋታል 🤔
@fatimahassan1795
@fatimahassan1795 2 жыл бұрын
@@leiladavid.2632 ኢንሻአላህ እርቅ መአዶች የስነልቡና ባለሙያዎች ይረዷታል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ
@raheltadesse7578
@raheltadesse7578 Жыл бұрын
እናቷ ባይሆኑም አሳድገዋል እናትም ከሆኑ ደስ ይላል ፈጣሪ እውነታውን ያውጣው
@hanamajeed9117
@hanamajeed9117 2 жыл бұрын
አረብ አገር ምን አያሳስብ አይ እኛ እብደት ይነሰን።
@selamawitlemma5742
@selamawitlemma5742 2 жыл бұрын
እናት እውነት አባት እምነት መሆኑን አትነግሯትም ነበር የእኛን ልብ ዝቅ ፣ቀጥ ከማድረጋቹ በፊት?
@HanaHana-io3bq
@HanaHana-io3bq 2 жыл бұрын
እሰይ እልልልልልልልል እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ደስ ያለሽ እናት አለም ክብር ለናቶቻችን!!!
@-beteorthodoxchannel3244
@-beteorthodoxchannel3244 2 жыл бұрын
በቅንነት ቤተሰብ እንሁን የተዋህዶ ልጅ🙏💒
@HanaHana-io3bq
@HanaHana-io3bq 2 жыл бұрын
@@-beteorthodoxchannel3244 እሺ እህቴ
@yaniyani8683
@yaniyani8683 2 жыл бұрын
ልጅቷ አጋንንት ሰፍሮባት ነው ቤተሰቧን ያስካዳት ጌታ ሆይ ልብ ይስጣት
@mmadura1232
@mmadura1232 2 жыл бұрын
በልጅቷ አትፍረዱ እናቶች እዛ ላሉት እጂ ስደት ላሉት ፍቅር አይሰጡም
Как бесплатно замутить iphone 15 pro max
00:59
ЖЕЛЕЗНЫЙ КОРОЛЬ
Рет қаралды 6 МЛН
🤔Какой Орган самый длинный ? #shorts
00:42
Sigma girl and soap bubbles by Secret Vlog
00:37
Secret Vlog
Рет қаралды 12 МЛН
Jaloliddin Ahmadaliyev - Kuydurgi (Official Music Video)
4:49
NevoMusic
Рет қаралды 8 МЛН
Duman - мен болмасам кім? (Mood Video)
2:35
Duman Marat
Рет қаралды 71 М.
Әділет Жауғашар & SUNDET MUSLIM - Бір оқиға [M/V]
3:05
Әділет Жауғашар
Рет қаралды 125 М.