#ሐበሽይ_ነኝ

  Рет қаралды 974,135

AL Faruq Tube

AL Faruq Tube

Күн бұрын

#MUAZ HABIB
☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆
Like እና Share በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ
የKZfaq ቻናላችንን Subscribe በማድረግ በየጊዜው የሚለቀቁ Videoዎችን ይመልከቱ ||
/ alfaruqtube
የፌስቡክ ገፅ ||
/ ​​...​
ቴሌግራም ||
t.me/alfaruqtube
እንጉርጉሮ፡ (0:00)
ድቤ፡ (11:00)
የ መንዙማው ግጥም 👇👇
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
ቢስሚላሂ ብዬ ልጀምር ዚክር
የኑሩን ኮረብታ ጥቂት ልከርር
እንዲመቻት ነፍሴ በሁለት ሀገር
ሹመት እንዲሰጡኝ አርገው ጭምርምር
ይዘው እንዲያዘልቁኝ ከአሽከሮች እድር
ወደአንቱ ተስቤ ብያለው ድስቱር
የክብረቱን ቀሚስ ዝለቁና አልብሱኝ
ባዶ ሁኜ እንዳልቀር በዒናያው ዳብሱኝ
ሸራቦን አጠጡኝ በእጆ አጉሩሱኝ
የወዳችሆ ልጅ ነኝ ጌታዬ አይራቁኝ
በመደድ አግርቁኝ ከበልአዬ አርቁኝ
እንደ ወላጅሆ በውዱ ያክብሩኝ
ፌትሆን ፍቀድሉኝ እናዳየው በአይኔ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ
የንግስናው መጠን የሌለው ድንበር
በከውኑ ላይ ሲጎርፍ የኑሩ መጠን
ሀበሻ ላይ ዘንቦ ሲገጥመን ጀባር
ስንቱ ጀንት ዶሎ አሲይዞ መስመር
ጠንከር ከር አድርጎ በሁቡ ማገር
ሀቂቃቸው ራቀ አረ በተዓበረ
እነ ሰይድ ቢላ የሁቡ ባህር
ሀበሺቷ እናት በረካን ልዝከር
ስንቱን ጉድ ይዛለች ሀበሻ ሀገር
እኔም ከነሱ ነኝ ዘሬ ሲቆጠር
ሀበሻ ነኝ ይላል እንኳን ሩህ በደኔ
የመዲናው ኮሌ ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ ያ ሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
ዓጂብብ …… እጅጉን ከበሩ ተይዘው በውዱ
ከሌላ እረቀው ዚክረሆን ቢለምዱ
ከኛው ከሀበሻ በመደድ ያበዱ
ሩህና ጅስማቸው ባንተ ተጀረዱ
መሳይ የሌላቸው ሾንክዬ ዛሂዱ
የመውሊዱ ጠንሳሽ እነ ሙጃሂዱ
የባሌው ፍንጥቅጥቅ… ጃሚድ
የሸይኹል ቆርቻ አልፈቂህ አህመድ
አብሬት ቃጥባሮችም አልከስዬ ውዱ
ቁጥቡ ሰይድ ጫሌ የጠናቦት ክንዱ
የተውሂድ የተውሂድ አርበኛ
ሸይኽ ዓብዱሏህ ዘውዱ
መድህን የሆኑሉኝ ሌላ እንዳያይ አይኔ ያ ሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ
የተዳፈነ ወርቅ በመቃማ ጭሬ
ሀቂቃው ለራቀው ላቅርበው አንጥሬ
በገዛ ጥሪቷ ታጊጥ አምራ ሀገሬ
በሀበሻ ማዓድ ብሎም በማገሬ
በአሰሀመተ ነጃሽ በአዱ ሰፋሪ
በኑር ሁሴን ባሌ መርዷን ሁሏ አሻሪ
የጅህልና ……… በሆኑት መንጣሪ
በተውሂድ ወለላው በዓብዱሏህ ሀረሪ
በነብዩ ጥላ በሸይኽ አባድሪ
የመድሁን ወይን ጠጭ ማረጉን አዟሪ
በጫሊ በሾንኪይ በዓሊይ ጎንደሪ
በደቡቡ ……. ሸይኽ ዒሳ ቃጥባሪ
አማኑ አብሬትዬ ለኔ እንደ ብሌኔ
የመዲናው ኩሌ ያሙስጠፋ ያበደረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ ያሙስጠፋ ያበደረል ከማሌ
አልሀምዱሊላሂ ገለታ ይድረሰው
በሙሀባው ኩሎ ጅስሜን ላደሰው
እኝህን በመውደድ
ሩሄን ለሞሸረው
ከጠማማው መንገድ እግሬን ለቀየሰው
በሸይኾቼ ሀድራ ገፍላዬን ላበሰው
ተሳብኩኝ ወደ አንቱ በወዳጁ ላይ
ዘብ በሆኑት ለዲን በሸይኽ አብደሪይ
ዒልማቸው በነካው እርቆ ሰማይ
አሏህን ባጠሩት ከታችም ከላይ
አንድ ቀን ቀልባቸው ዱንያን ሳያይ
ከሳዳቶች ማድ ዒልምን ሲገበይ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሊ
አሰላሙዓለይኩም ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
ሙሀባው የገባው አካሉን ሰርስሮ
የዘመኑ አሽከር በሸውቅ ዓለም በሩ
በጫሊ ቁንጮ ላይ ሲሆን ውሎ አዳሩ
በንጉስ በገታ ሲንገዋለል ፊክሩ
ከነሙጃሂድ ዘንድ ተወደው ሲጠሩ
ካንቱ አደለም ወይ የሁሉ መግቢያ በሩ
የነ ሙፍቲ ራያ ዓብደሏህ መስመሩ
ነጅሙ ቁጥብ ናቸው አቅጣጫ ጠቋሚ
የመዲናው ኮሌ ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
ዛሬስ ይሄ ልቤ ሟሟ እንደ በረዶ
የከውኑን ነጋሴ ያለ ቀድሩ ወዶ
የትዝታው ፍሙ አንጀቴ ውስጥ ወርዶ
ያ መሞት ይሻዋል በገዛ እጁ ታርዶ
እየሸነቆጠው ትዛተውን ሰዶ
የናፍቆት ንዳድ ውስጥ አካላቶን ማግዶ
ሲርገበገብ ያድራል ሌቱን ተንገዳግዶ
እያገረሸበት ጦት ማታ ጀድዶ
ጨርቁን አስቀድዶ ለዚህ አይነ ኩሌ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኩሌ ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
ይፋጃል እንደ እሳት የሚፋቸው እንባ
ልቡ እያረጎደው ሆዱ እየባባ
አካላቱን ሁሉ በዝቶበት ድብደባ
በናፍቆት አለንጋ ሲወጣም ሲገባ
ጠዋት ማታ እያከመ ቁስል በቁስል ላይ
ዘልቆ ባየው ቁጥር ያን የን ኑርኑን እንጉዳይ
የብርሀን አበባ አብርቶ እንደ ፀሀይ
ከወጋው አይድንም ሽታው እልብ ላይ
ያደረግዋል ዋላይ ገብቶ በኑር ጀሌ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኩሌ ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
ያሀም እዛ ያሀም እዛ በያለበት ወድቆ
ጥይት እንደመታው ልቡ ተሰንጥቆ
አቅሉ ተወግዶ እያሰበ አርቆ
እያንገበገበው ያን ጨረቃ ናፍቆ
እስኪታየው ድረስ ዛቱ ተፈልቅቆ
ደምቆ ከጨረቃ ፀሀይቱን አስንቆ
አለሙን የሚያሰምጥ ጮራውን ፈንጥቆ
ጅስሙ እንደ ጨርቅ አልቆ ይጠብቃል ሁሌ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኩሌ ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
ሙሂብ የተባለን እያንደፋደፈው ለጥቆ
አስመስሎ ታረር የገረፈው በየ ስፍራው
ወድቆ እየተረፈረፈው የናፍቆቱ ዝለት ጉበቱን ሲከትፈው
ሰባት ብልቱን ዘልቆ ነው ሚከትፈው
በናፍቆቱ ምላጭ ውስጡን የሚገፈው
አጥንቱን ከስክሶ ስጋውን ሲከትፈው
እያቃጠለው ነው የሚንሰፈሰፈው
አደዱን ልለፈው አይችልም ሊሳኔ
የመዲናው ኩሌ ያ ሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም ያራህመተል ዓለም
አሰላሙ ዓለይኩም ያ ጦሀ ሙቀረብ
አሰላሙ ዓለይኩም አነድ አምሳያ የለው
በመድሁ ልታመም ጠና መዋለሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የአዘሉ ውዴ
አሰላሙ ዓለይኩም ሰይዱል አስያዴ
አሰላሙ ዓለይኩም አህመድ ሙሀመዴ
አሰላሙ ዓለይኩም አጠጡኝ ሰይዲ ከመደድሆ መደድ
አሰላሙ ዓለይኩም ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም ልበለው ያን ዓረብ
አሰላሙ ዓለይኩም ብዬ ልበል ቀረብ
አሰላሙ ዓለይኩም ዱዓዑል ሙጀረብ
ውበት ቢደራረብ አይመስልም ያን ኮሌ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ ያ ሙስጠፋ ያ በድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም ጨረቃ ጀንበሩ
አሰላሙ ዓለይኩም ኑሩ ሙነወሩ
አሰላሙ ዓለይኩም ሚስክ ወርዴ አንበሩ
አሰላሙ ዓለይኩም ወላዬ ማሩ
ማርኮኝ ነው ኸበሩ እንዲህ መዋለሌ
ያ ሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የዓሩሰል ጠይባ
አሰላሙ ዓለይኩም አንቱ የኑር አበባ
አሰላሙ ዓለይኩም የ አህባቦች ካባ
አሰላሙ ዓለይኩም የ አባ ዘይነባ
አርሂብ በሉኝ ልግባ ናፍቆኝ ነው ያ ኮሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የዓውነ ዷዓፋ
አሰላሙ ዓለይኩም ሰይዲ ሙስጠፋ
አሰላሙ ዓለይኩም …… ሙሰፋ
አሰላሙ ዓለይኩም የአህባቦች ማዒራፋ
አሰላሙ ዓለይኩም ዛሬ ባቱ ይጥፋ የበዛው ወንጀሌ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ ያ ሙስጠፋ ያ በድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም ያ ኸይረል ሰመር
አሰላሙ ዓለይኩም የራህመቱ ባህር
አሰላሙ ዓለይኩም የከውኑ ጀንበር
አሰላሙ ዓለይኩም አንተ የኔ ክብር
አሰላሙ ዓለይኩም እኔ ያነቱ አሽከር አንቱ ኖት እድሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ ያ ሙስጠፋ ያ በድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም ንግስ እና ካባዬ
አሰላሙ ዓለይኩም ውበቴ ሀይባዬ
አሰላሙ ዓለይኩም ማጌጫ አበባዬ
አሰላሙ ዓለይኩም መክበሪያ ገቢያዬ
ይመስክር እንባዬ አጉል መቃጠሌ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ ያ ሙስጠፋ ያ በድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም አንቱ የኔ ጎብላላ
አሰላሙ ዓለይኩም የዓለሙ ጥላ
አሰላሙ ዓለይኩም ዓለሙን የሞላ
አሰላሙ ዓለይኩም ያ ኢማሙን ሩስላ
አሰላሙ ዓለይኩም ካንተ በቀር ሌላ አይከጅልም ሀሌ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ ያ ሙስጠፋ ያ በድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም ንግስናዬ ድርቤ
አሰላሙ ዓለይኩም ማዴዋ ቀለቤ
አሰላሙ ዓለይኩም መደዴ ሸራቤ
አሰላሙ ዓለይኩም ልበሎት ቀርቤ
ልምጣ ወይ ቀርቤ ጠፍቶልኝ ወንጀሌ
ያሙስጠፋ ያበድረል ከማሌ
አሰላሙ ዓለይኩም የመዲናው ኮሌ ያ ሙስጠፋ ያ በድረል ከማሌ

Пікірлер: 1 200
НЫСАНА КОНЦЕРТ 2024
2:26:34
Нысана театры
Рет қаралды 1,5 МЛН
ሶለላህ_ዓላ_ሙሀመድ ||ፉዐድ ሸምሱ(አል ቡርዳ)
14:59
Al Faruk Multimedia Production
Рет қаралды 578 М.
23 July 2024
8:43
Nejat abdulukdir Abdulukadir
Рет қаралды 6 М.