Рет қаралды 719,948
መኃልየ መኃልይ8
5 በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት?
ዛሬም በውዴ ላይ ተደግፌ
ትናንትን ትናንት አልኩ በእርሱ አልፌ
የሚያዩኝ በሙሉ ይለዩኛል
በውዷ ጥገኛ ናት ይሉኛል...ናት ይሉኛል
አይደለም ፈውሴን በልቼ
ልመለስ ምስጋና ረስቼ
ሰው ልጠብቅ ይቅርና
ሚያሳስበኝ ለምስጋና
ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት ፈልገዋለሁ ለሕይወት
ለመሰንበት፣ ለመቆየት ፈልገዋለሁ ለሕይወት {×፪}
ፍለጋዬ የዕድሜ ልኬ ነው
ጊዜዬ ቢለማ ቢከፋ
የቆመች ነፍስ አይደለሁም ወይ
በውዷ ላይ ተደግፋ
ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት ፈልገዋለሁ ለሕይወት
ለመሰንበት፣ ለመቆየት ፈልገዋለሁ ለሕይወት {×፪}
ጸሎት ተሰጠኝ ፍለጋ፣ ፍለጋ፣ ፍለጋ
ሁሌ እንዳልጠፋ እግሩ ጋር፣ እርሱ ጋር፣ እርሱ ጋር
እንጀራዬ ነው የዕለት፣ የዕለት፣ የዕለት
ሁሌ እንድጓደድበት፣ እንድደገፍበት
ጸሎት ሰጥቶኛል ፍለጋ፣ የዕድሜ ልክ ፍለጋ
ሁሌ እንዳልጠፋ እግሩ ጋር፣ እርሱ ጋር፣ እርሱ ጋር
እንጀራዬም ነው የዕለት፣ መች ብቻ የዓመት
ሁሌ እንድጓደድበት፣ እንድደገፍበት
አባብሎ ወሰደኝ ራቅ ወዳለው
የልቡን በልቤ እንዳኖረው
ምድረበዳው ሰርቶኝ አቅሜ ሲታይ
አስደግፎኝ ወጣሁ በውዴ ላይ...በኢየሱስ ላይ
ለአሳ ውኃ ሕይወቱ
ወጥቶ መች ይሞክረዋል?
በቂ ነው ብሎ ሰፍሮለት
በወጪት ማን ያረካዋል?
ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት ፈልገዋለሁ ለሕይወት
ለመሰንበት፣ ለመቆየት ፈልገዋለሁ ለሕይወት {×፪}
ለነፍሴም ኢየሱስ ግድ ነው
ለሕይወት ለዕለት ተግባሬ
ፊቱ ነው የሚያስቀጥለኝ
ሲኖር አይደል ወይ መኖሬ
ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት ፈልገዋለሁ ለሕይወት
ለመሰንበት(ለመተንፈስ)፣ ለመቆየት ፈልገዋለሁ ለሕይወት {×፪}
ጸሎት ተሰጠኝ ፍለጋ፣ ፍለጋ፣ ፍለጋ
ሁሌ እንዳልጠፋ እግሩ ጋር፣ እርሱ ጋር፣ እርሱ ጋር
እንጀራዬ ነው የዕለት፣ የዕለት፣ የዕለት
ሁሌ እንድጓደድበት፣ እንድደገፍበት
ጸሎት ሰጥቶኛል ፍለጋ፣ የዕድሜ ልክ ፍለጋ
ሁሌ እንዳልጠፋ እግሩ ጋር፣ እርሱ ጋር፣ እርሱ ጋር
እንጀራዬም ነው የዕለት፣ መች ብቻ የዓመት
ሁሌ እንድጓደድበት፣ እንድደገፍበት
ዘግነህልኝ በትልቁ እጅህ
ጠልቀህልኝ ከሰፊው ምንጭህ
ስንቱ ገባኝ እያስረዳኸኝ
መዝሙር ቀዳው እያስተማርከኝ
ከብዙዎች ንግግር መሃል
ደገፍ አልኩኝ በሰጠኸኝ ቃል
ተስፋ አጥቼ ልወድቅ ስል
ስንቴ አቅም ሆንከኝ ለመቀጠል
ዘግነህልኝ በትልቁ እጅህ
ጠልቀህልኝ ከሰፊው ምንጭህ
ስንቱ ገባኝ እያስረዳኸኝ
መዝሙር ጻፍኩኝ እያስተማርከኝ
ከጠቢባን ንግግር መሃል
ደገፍ አልኩኝ በሰጠኸኝ ቃል
ተስፋ አጥቼ ልተወው ስል
አቅም ሆንከኝ ለመቀጠል
ሸርተት ብዬ ልወድቅ ስል
አቅም ሆንከኝ ለመቀጠል
ተስፋ አጥቼ ልተወው ስል
አቅም ሆንከኝ ለመቀጠል
ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት ፈልግሃለሁ ለሕይወት
ለጤንነት፣ ለደህንነት ፈልግሃለሁ ለሕይወት
ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት፣ ዕለት ፈልግሃለሁ ለሕይወት
ለመሰንበት፣ ለመቆየት ፈልግሃለሁ ለሕይወት