ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 1 / Saint Simon - Part 1

  Рет қаралды 175,303

የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik

የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik

5 жыл бұрын

ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው
ተአምረ ማርያም ላይ ከተጻፉት እና በትርጓሜ ወንጌልም ላይ በማቴ5÷29 ለሚገኘው ቃል እንደ ታሪካዊ ማስረጃ ከሚቀርቡት ታሪኮች አንዱ የስምዖን ጫማ ሰፊው ታሪክ ነው፡፡
በ979 ዓም የፋጢማይድ ሥርወ መንግሥት ግብጽን በሚያስተዳድርበት ወቅት በከሊፋ አል ሙኢዝ ሊ ዲን ኢላህ አል ፋጢሚ ዘመን እንዲህ ሆነ፡፡
ለሥልጣን ሲል ወደ እስልምና የተቀየረ ያዕቆብ ኢቢን ቂሊስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ነበር፡፡ ይህ አይሁዳዊ ምንም እንኳን ለሥልጣን ሲል እስልምናን ቢቀበልም ልቡ ግን ከአይሁድ ጋር ነበር፡፡ ክርስቲያኖችንም በጣም ይጠላ ነበር፡፡ ይህ ጥላቻው የመጣው በከሊፋው ዘንድ በሚወደድ እና እርሱ ይቀናቀነኛል ብሎ በሚያስበው በአንድ ክርስቲያን ምክንያት ነበር፡፡ ይህ ክርስቲያን ቁዝማን ኢቢን ሚና ይባል ነበር፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝ ደግ፣ ምክንያታዊ እና በሰዎች ነጻነት የሚያምን ዕውቀትንም የሚወድድ መሪ ነበር ይባላል፡፡ ምሁራን ሲከራከሩ መስማት የሚወድድ ሌላው ቀርቶ የእስልምና ምሁራን እስልምናን ከሚቃወሙ ሰዎች ጋር በነጻነት እንዲከራከሩ የሚፈቅድ ሰው ነበረ፡፡
ይህንን ጠባዩን የሚያውቀው ያዕቆብ ሙሴ የተባለውን የአይሁድ ረቢ ጠርቶ ከፓትርያርኩ ጋር እንዲከራከር እና ፓትርያርኩን እንዲያሳፍረው መከረው፡፡ ሙሴም ጥያቄውን ለከሊፋው አቀረበ፡፡ ከሊፋውም ለፓትርያርኩ መልእክት ላከ፡፡
በቀጠሮው ቀን በወቅቱ የእስክንድርያ ፓትርያርክ የነበረው አብርሃም ሶርያዊ በሃይማኖት ዕውቀቱ እና ትምህርቱ የታወቀውን ሳዊሮስ ዘእስሙናይን ይዞት መጣ፡፡ ሳዊሮስ ዘእስሙናይ «በከሊፋው ፊት ይሁዲን መናገር መልካም አይደለም» አለው፡፡
ይህንን ቋንቋ ሙሴ በሌላ ተርጉሞ «አላዋቂ ብለህ ሰደብከኝ» ሲል ተቆጣ፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝም «መከራከር እንጂ መቆጣት አያስፈልግህም» አለው፡፡
ያን ጊዜ ሳዊሮስ «አላዋቂ ብዬ የተናገርኩህ እኔ ሳልሆን ያንተው ነቢይ ኢሳይያስ ነው» ብሎ በትንቢተ ኢሳይያስ 1÷3 ላይ ያለውን ጠቀሰ፡፡ ከሊፋው ገረመውና «እንዲህ የሚል የእናንተ ነቢይ አለ?» ሲል ሙሴን ጠየቀው፡፡ ሙሴም «አዎ አለ» አለው፡፡ አባ ሳዊሮስም «እንዲያውም እንስሳት ከአንተ እንደሚሻሉም ገልጧል» አለው፡፡ ይሄን ጊዜ ከሊፋው ሳቀ፡፡ ክርክሩም እንዲቆም አዘዘ፡፡
ይህ ሁኔታ ያዕቆብን አበሳጨው፡፡ ራሱ ባመጣው ጣጣ በከሊፋው ፊት መዋረዱም ቆጨው፡፡ ስለዚህም ክርስቲያኖቹን የሚያጠቃበት ሌላ መንገድ መፈለግ ጀመረ፡፡ ሙሴንም አንዳች ጥቅስ ከወንጌል እንዲፈልግ ነገረው፡፡
ሙሴ በመጨረሻ በማቴ 17÷20 ያለውን «የስናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ተነሣ ብትሉት ይሆናል» የሚለውን አገኘ፡፡ ለያዕቆብም ነገረው፡፡ ያዕቆብም ወደ ከሊፋው በማምጣት «በክርስቲያኖች መጽሐፍ ላይ እንዲህ ስለሚል ይህንን ፓትርያርኩ ያሳየን» አለው፡፡ ከሊፋው ተገረመ፡፡ ፓትርያርኩንም ጠርቶ ጠየቀው፡፡ አብርሃም ሶርያዊ ይህ ቃል በእውነት እንዳለ ነገረው፡፡
ከሊፋውም «በእውነት የክርስቲያኖች ሃይማኖት እውነት ይሁን ውሸት ለመፈተኛ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ካቃታቸው ግን ሕዝቡን እያታለሉ ነውና መቀጣት አለባቸው» ብሎ አሰበ፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝ ለአባ አብርሃም አራት ምርጫ አቀረበለት
1. የሙካተምን ተራራ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ማዛወር ወይም
2. እስልምናን ተቀብሎ ክርስትናን መተው ወይም
3. ግብጽን ትቶ ወደ ሌላ ሀገር መሄድ ወይንም
4. በሰይፍ መጥፋት
ፓትርያርክ አብርሃም ውሳኔውን ለማሳወቅ የሦስት ቀን ጊዜ ጠየቀ፡፡ ከከሊፋው ዘንድ ከወጣ በኋላም ጳጳሳቱን፣ መነኮሳቱን፣ ካህናቱን፣ ዲያቆናቱን እና ምእመናኑን ሰበሰበ፡፡ ያጋጠመውንም ነገር ነግሮ በመላዋ ግብጽ የሦስት ቀን ጾም እና ጸሎት አወጀ፡፡
በሦስተኛው ቀን ማለዳ ቅድስት ድንግል ማርያም ለአባ አብርሃም ሶርያዊ ተገለጠችለት፡፡ «ይህንን ነገር የሚያደርግልህ አንድ ሰው አለ፡፡ ወደ ከተማው ገበያ ስትወጣ አንድ ዓይና የሆነ በገንቦ ውኃ የተሸከመ ሰው ታገኛለህ፡፡ እርሱ ይህንን ተአምር ያደርግልሃል» አለቺው፡፡
አባ አብርሃም ወዲያው ከመንበረ ጵጵስናው ወጥቶ ወደ ከተማው ገበያ መንገድ ጀመረ፡፡ በመካከሉም አንድ በገንቦ ውኃ የያዘ ሰው አገኘ፡፡ ያም ሰው አንድ ዓይና ነበረ፡፡ ጠራውና ወደ ግቢው አስገባው፡፡ የሆነውንም ነገረው፡፡
ያ ሰው «እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፤ ይህ እንዴት ይቻለኛል» አለው፡፡
አባ አብርሃምም ያዘዘቺው ድንግል ማርያም መሆንዋን ነገረው፡፡
ያ ሰው ስምዖን ጫማ ሰፊው ይባላል፡፡ አንዲት ሴት እየደጋገመች መጥታ «ይህንን ዓይንህን እወድደዋለሁ» ብትለው ጫማ በሚደፋበት ጉጠት አውጥቶ የሰጣት እርሱ ነው፡፡
«አባቴ ሕዝቡን ወደ ተራራው ሰብስብ፡፡ እኔ ከአንተ አጠገብ እሆናለሁ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ አንድ መቶ አንድ መቶ ጊዜ ኪርያላይሶን በሉ፡፡ ከዚያም ስገዱ፡፡ ከስግደቱ በኋላ ስታማትብ ተራራው ይነሣል » አለው፡፡
አባ አብርሃም ወደ ከሊፋው ሄዶ ተራራውን እንደሚያነሡት ነገረው፡፡
ኅዳር 15 ቀን 975 ዓም ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፣ አይሁድ፣ ሌሎችም ተሰበሰቡ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ ጸሎተ ዕጣን ተደርሶ ኪርያላይሶን ተባለ፡፡ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሰገዱ፡፡ ከስግደት ተነሥተው ጸጥ ሲሉ ኃይለኛ ድምፅ ተሰማና ተራራው ካለበት ተነሣ፤ ፈቀቅም አለ፡፡ እንደገና ሰገዱ፤ አሁንም ተነሥቶ ፈቀቅ አለ፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ ሰገዱ ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ከሊፋው በከፍተኛ ድምፅ ጮኸ፡፡ «በቃ፣ በቃ በዚህ ከቀጠለ ከተማዋ ትፈርሳለች» አለ፡፡ ክርስቲያኖቹ በደስታ አምላካቸውን አመሰገኑ፡፡ ከሳሾቻቸው አፈሩ፡፡ ስምዖን ጫማ ሰፊው ግን ጠፋ፡፡
አባ አብርሃም በብርቱ አስፈለገው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ሊያገኘው አልቻለም፡፡ አባ አብርሃም ሶርያዊ ይህንን የድንግል ማርያምን ተአምር ለማስታወስ ከነቢያት ጾም ጋር ተያይዞ እንዲጾም አዘዘ፡፡ በገና ጾም የመጀመርያዎቹ ሦስት ቀናት ይህንን ተአምር ለማስታወስ የምንጾማቸው ናቸው፡፡
ዛሬ ተራራው ከሦስት ቦታ ተከፍሎ ይታያል፡፡ ከምዕራብም ወደ ምሥራቅ ሸሽቷል፡፡ «ሙከተም» ማለትም «የተቆራረጠ» ማለት ነው ይባላል፡፡ ይህ ተራራ ዛሬ በአሮጌዋ ካይሮ ይገኛል፡፡
ከዚህ ተአምር በኋላ ከሊፋ አል ሙኢዝ ለቤተ ክርስቲያን ብዙ ነገር አድርጓል፡፡ አያሌ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናት ተጠግነዋል፡፡ አዳዲሶቹም ተሠርተዋል፡፡ ይህ ተአምር የግብጽ ፓትርያርኮች ታሪክ በተሰኘው ጥንታዊ መጽሐፍ እና በሌሎችም መዛግብት ተመዝግቧል:: በተአምረ ማርያም ላይ የምናገኘው ታሪክ ከእነዚህ ጥንታውያን መዛገብት የተገኘ ነው፡፡ በሌላም በኩል ተራራው እና በአሮጌዋ ካይሮ የመዓልቃ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዙርያ የተደረጉ የአርኬዎሎጂ ቁፋሮዎችም ይህንን መስክረዋል፡፡
በኋላ ግን ቦታው ሆን ተብሎ የካይሮ የቆሻሻ መጣያ ተደረገ፡፡ ክርስቲያኖቹ ወደ አካባቢው የሚጣለውን ቆሻሻ በመጥረግ ታሪኩ እንዳይጠፋ ታገሉ፡፡ በመጨረሻም ነገር ሁሉ ለበጎ ነውና ቆሻሻዎቹን እንደገና ለአገልግሎት በማዋል /ሪሳይክሊንግ/ መጠቀም ጀመሩ፡፡ ዛሬ ለብዙዎች የሥራ እድል ከፍቶላቸዋል፡፡
የአል ሙከተም ተራራ ተፈልፍሎ የስምዖን ጫማ ሰፊው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ መቅደስ ክፍት ነው፡፡ ወንበሩ 25000 ምእመናን ይይዛል፡፡ የስምዖን ዐጽምም በመዓልቃ ቤተ ክርስቲያን በተደረገው ቁፋሮ ተገኝቶ በዚሁ የተራራ ቤተ ክርስቲያን በክብር አርፏል፡፡
----------------------------------------
ዲ.ን ዳንኤል ክብረት

Пікірлер: 276
@sara-nd8mw
@sara-nd8mw 3 жыл бұрын
ተመስገን አምላኬ በባእድ ሀገር ሆኘ ይህን የመሰሉ ቁዱሳን አባቶ ታሪክ እንድሰማ ስለፈቀድክልኝ ተመስገን የቅዱሳኑ በረከት ይገርብን
@user-dy5gd5hu1d
@user-dy5gd5hu1d 5 жыл бұрын
ተመሰገን አምላኬ የቅዱሰ ሰሞኦን ታሪክ እንዳይ ሰለረዳህኝ ተመሰገን።።ጌታዬ።።
@Ggg-vs1iy
@Ggg-vs1iy
አሜን የቅዱስ ስምኦን ረደት በረከት ምልጃና ፀሎት አይለየን አሜን💚💐💚💛💛💛❤❤❤❤⛪👏🙏🙏👏⛪
@kibrealemye8319
@kibrealemye8319 5 жыл бұрын
በእውነት ልኡል እግዚያብሄር እረዥም እድሜና ጤናን ይስጥልን ብዙ ጥራችሁ መንፈሳዊ ህይወትን ለምታስተምሩን ወድም እህቶቸ ፀጋውን ያብዛላችሁ እናም ይህንን የተመረጠና የተባረከ ትምህርትን እባካችሁ ሌላም የቅዱሳን ፌልም ልቀቁልን
@senayit7198
@senayit7198 5 жыл бұрын
የአባቶቻችን እረዴት በረከታቸው ይደርብን አሜን፫
@enatmesfin
@enatmesfin 4 жыл бұрын
በረከታቸው ይደርብን ይሄንን መንፈሳዊ ፊልም ላይ የተሳተፋችት ሁሉ እግዚአብሔር በማይጠፋው በሰማያዊው ቀለም ስማችሁን ይጻፍ አመሰግናለሁ ቃለ ሕይወት ያሰማልን እግዚአብሔር ለሁለተኛ ጊዜ ነው ያየሁት
@redidani5893
@redidani5893
እንዴት ደስ እንዳለኝ በስመአብ ብዙ ብዙ ስራልን እሽ እእእ ንጉስ ሰለሞን አዳምና ሄዋን የልጅነት ትውስታዎቼ ናቸው 😔😔😔😔
@MmMm-ls9iy
@MmMm-ls9iy
የአባቶቻችን እረዴት በረከታቸው ይደርብን አሜን፫🙏💙🌿
@alebachwoenywoenywo8855
@alebachwoenywoenywo8855
እንደዚያይነት መንፈሳውይ ስራወችን የምታስተምሩ እህትነ ወንድሞች ፈጣሪ እድሜነ ጤነ ይስጣቹ
@mxmmxm8889
@mxmmxm8889 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ይህነን ቅድሰ ቃል ልመሰተ ሰልፍቅድከለኘ ከብረ አነ መሰገን ለተ ይሁን ይአባታችን ብረከተ ይድረብን
@user-zn2sk5nr8j
@user-zn2sk5nr8j 5 жыл бұрын
ስላም ላንተ ይሁን ወንድሜ እባክህን ሌሎች ፊልሞችን ልቀቅልን ይህንን በሌላ ተለቆ ነበር ብዙ ያላናያቸው መንፍሳዊ ፊልሞች አሉ ለምሳሌ የአባ ሚናስ ፣ የአባኖፍር ፣ አባ ፍልቶኦስ ፣ ቅዱስ መርሚና ብዙዎች አሉ እባክህን ልቀቅልን እግዚአብሔር ይስጥልኝ
@Tewab
@Tewab 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን
@user-wu4kv3eu1c
@user-wu4kv3eu1c 5 жыл бұрын
@melkamaddis9582
@melkamaddis9582 5 жыл бұрын
አሜን የቅዱሳን አባቶቻችን በረከት ይደርብን
@user-vl7ch2fu5l
@user-vl7ch2fu5l 3 жыл бұрын
የኣቦታችን በረከት እና ረዲኤት ይደርብን ኣሜን፫
@user-jc1tm1jl8r
@user-jc1tm1jl8r 5 жыл бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባታችን የቅዱስ ስምኦን በርከት በህዝብ ክርስቲያን ላይ ይደርብን አሜን አሜን አሜን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር አሜን ❤💛💚
@user-pd5if3fs2u
@user-pd5if3fs2u 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለህይወትን ያሰማልን የቅዱሳኖቹ በርከታቸው ይደርብን
@user-ls4em3xj6g
@user-ls4em3xj6g
አግዚኣቢሄር ይመስገን ኣሜን ኣሜን ኣሜን🙏✝️⛪️
@enesyemaryamnegnyemaryam2770
@enesyemaryamnegnyemaryam2770 5 жыл бұрын
አሜን ቃለሁወት ያሰማልን የቅዱሳን በረከታቸዉ ይደርብን ቃለሂወት ያሰማልን
@fikrtbahru6525
@fikrtbahru6525
የአባታችን በረከት አይለየን
ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 2 / Saint Simon - Part 2
44:10
የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Рет қаралды 97 М.
Я нашел кто меня пранкует!
00:51
Аришнев
Рет қаралды 4,4 МЛН
ነቢዩ ኤልያስ | የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች (ከብሉይ ኪዳን)
34:04
መርሐ ተዋሕዶ - Merha Tewahedo
Рет қаралды 28 М.
ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ክፍል 1 / Saint Moses the Black Part - 1
54:20
የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Рет қаралды 230 М.
ወንጌል የዉሃንስ
2:06:36
Ruth Tv 📺 Channel
Рет қаралды 1,1 МЛН
ናይ ንግሆ  ጸሎት
44:56
ኖላዊ ( NOLAWI)
Рет қаралды 366 М.
ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ክፍል 2 / Saint Moses the Black Part - 2
1:02:37
የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Рет қаралды 156 М.