ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 2 / Saint Simon - Part 2

  Рет қаралды 98,455

የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik

የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik

5 жыл бұрын

ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው
ተአምረ ማርያም ላይ ከተጻፉት እና በትርጓሜ ወንጌልም ላይ በማቴ5÷29 ለሚገኘው ቃል እንደ ታሪካዊ ማስረጃ ከሚቀርቡት ታሪኮች አንዱ የስምዖን ጫማ ሰፊው ታሪክ ነው፡፡
በ979 ዓም የፋጢማይድ ሥርወ መንግሥት ግብጽን በሚያስተዳድርበት ወቅት በከሊፋ አል ሙኢዝ ሊ ዲን ኢላህ አል ፋጢሚ ዘመን እንዲህ ሆነ፡፡
ለሥልጣን ሲል ወደ እስልምና የተቀየረ ያዕቆብ ኢቢን ቂሊስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ነበር፡፡ ይህ አይሁዳዊ ምንም እንኳን ለሥልጣን ሲል እስልምናን ቢቀበልም ልቡ ግን ከአይሁድ ጋር ነበር፡፡ ክርስቲያኖችንም በጣም ይጠላ ነበር፡፡ ይህ ጥላቻው የመጣው በከሊፋው ዘንድ በሚወደድ እና እርሱ ይቀናቀነኛል ብሎ በሚያስበው በአንድ ክርስቲያን ምክንያት ነበር፡፡ ይህ ክርስቲያን ቁዝማን ኢቢን ሚና ይባል ነበር፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝ ደግ፣ ምክንያታዊ እና በሰዎች ነጻነት የሚያምን ዕውቀትንም የሚወድድ መሪ ነበር ይባላል፡፡ ምሁራን ሲከራከሩ መስማት የሚወድድ ሌላው ቀርቶ የእስልምና ምሁራን እስልምናን ከሚቃወሙ ሰዎች ጋር በነጻነት እንዲከራከሩ የሚፈቅድ ሰው ነበረ፡፡
ይህንን ጠባዩን የሚያውቀው ያዕቆብ ሙሴ የተባለውን የአይሁድ ረቢ ጠርቶ ከፓትርያርኩ ጋር እንዲከራከር እና ፓትርያርኩን እንዲያሳፍረው መከረው፡፡ ሙሴም ጥያቄውን ለከሊፋው አቀረበ፡፡ ከሊፋውም ለፓትርያርኩ መልእክት ላከ፡፡
በቀጠሮው ቀን በወቅቱ የእስክንድርያ ፓትርያርክ የነበረው አብርሃም ሶርያዊ በሃይማኖት ዕውቀቱ እና ትምህርቱ የታወቀውን ሳዊሮስ ዘእስሙናይን ይዞት መጣ፡፡ ሳዊሮስ ዘእስሙናይ «በከሊፋው ፊት ይሁዲን መናገር መልካም አይደለም» አለው፡፡
ይህንን ቋንቋ ሙሴ በሌላ ተርጉሞ «አላዋቂ ብለህ ሰደብከኝ» ሲል ተቆጣ፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝም «መከራከር እንጂ መቆጣት አያስፈልግህም» አለው፡፡
ያን ጊዜ ሳዊሮስ «አላዋቂ ብዬ የተናገርኩህ እኔ ሳልሆን ያንተው ነቢይ ኢሳይያስ ነው» ብሎ በትንቢተ ኢሳይያስ 1÷3 ላይ ያለውን ጠቀሰ፡፡ ከሊፋው ገረመውና «እንዲህ የሚል የእናንተ ነቢይ አለ?» ሲል ሙሴን ጠየቀው፡፡ ሙሴም «አዎ አለ» አለው፡፡ አባ ሳዊሮስም «እንዲያውም እንስሳት ከአንተ እንደሚሻሉም ገልጧል» አለው፡፡ ይሄን ጊዜ ከሊፋው ሳቀ፡፡ ክርክሩም እንዲቆም አዘዘ፡፡
ይህ ሁኔታ ያዕቆብን አበሳጨው፡፡ ራሱ ባመጣው ጣጣ በከሊፋው ፊት መዋረዱም ቆጨው፡፡ ስለዚህም ክርስቲያኖቹን የሚያጠቃበት ሌላ መንገድ መፈለግ ጀመረ፡፡ ሙሴንም አንዳች ጥቅስ ከወንጌል እንዲፈልግ ነገረው፡፡
ሙሴ በመጨረሻ በማቴ 17÷20 ያለውን «የስናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ተነሣ ብትሉት ይሆናል» የሚለውን አገኘ፡፡ ለያዕቆብም ነገረው፡፡ ያዕቆብም ወደ ከሊፋው በማምጣት «በክርስቲያኖች መጽሐፍ ላይ እንዲህ ስለሚል ይህንን ፓትርያርኩ ያሳየን» አለው፡፡ ከሊፋው ተገረመ፡፡ ፓትርያርኩንም ጠርቶ ጠየቀው፡፡ አብርሃም ሶርያዊ ይህ ቃል በእውነት እንዳለ ነገረው፡፡
ከሊፋውም «በእውነት የክርስቲያኖች ሃይማኖት እውነት ይሁን ውሸት ለመፈተኛ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ካቃታቸው ግን ሕዝቡን እያታለሉ ነውና መቀጣት አለባቸው» ብሎ አሰበ፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝ ለአባ አብርሃም አራት ምርጫ አቀረበለት
1. የሙካተምን ተራራ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ማዛወር ወይም
2. እስልምናን ተቀብሎ ክርስትናን መተው ወይም
3. ግብጽን ትቶ ወደ ሌላ ሀገር መሄድ ወይንም
4. በሰይፍ መጥፋት
ፓትርያርክ አብርሃም ውሳኔውን ለማሳወቅ የሦስት ቀን ጊዜ ጠየቀ፡፡ ከከሊፋው ዘንድ ከወጣ በኋላም ጳጳሳቱን፣ መነኮሳቱን፣ ካህናቱን፣ ዲያቆናቱን እና ምእመናኑን ሰበሰበ፡፡ ያጋጠመውንም ነገር ነግሮ በመላዋ ግብጽ የሦስት ቀን ጾም እና ጸሎት አወጀ፡፡
በሦስተኛው ቀን ማለዳ ቅድስት ድንግል ማርያም ለአባ አብርሃም ሶርያዊ ተገለጠችለት፡፡ «ይህንን ነገር የሚያደርግልህ አንድ ሰው አለ፡፡ ወደ ከተማው ገበያ ስትወጣ አንድ ዓይና የሆነ በገንቦ ውኃ የተሸከመ ሰው ታገኛለህ፡፡ እርሱ ይህንን ተአምር ያደርግልሃል» አለቺው፡፡
አባ አብርሃም ወዲያው ከመንበረ ጵጵስናው ወጥቶ ወደ ከተማው ገበያ መንገድ ጀመረ፡፡ በመካከሉም አንድ በገንቦ ውኃ የያዘ ሰው አገኘ፡፡ ያም ሰው አንድ ዓይና ነበረ፡፡ ጠራውና ወደ ግቢው አስገባው፡፡ የሆነውንም ነገረው፡፡
ያ ሰው «እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፤ ይህ እንዴት ይቻለኛል» አለው፡፡
አባ አብርሃምም ያዘዘቺው ድንግል ማርያም መሆንዋን ነገረው፡፡
ያ ሰው ስምዖን ጫማ ሰፊው ይባላል፡፡ አንዲት ሴት እየደጋገመች መጥታ «ይህንን ዓይንህን እወድደዋለሁ» ብትለው ጫማ በሚደፋበት ጉጠት አውጥቶ የሰጣት እርሱ ነው፡፡
«አባቴ ሕዝቡን ወደ ተራራው ሰብስብ፡፡ እኔ ከአንተ አጠገብ እሆናለሁ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ አንድ መቶ አንድ መቶ ጊዜ ኪርያላይሶን በሉ፡፡ ከዚያም ስገዱ፡፡ ከስግደቱ በኋላ ስታማትብ ተራራው ይነሣል » አለው፡፡
አባ አብርሃም ወደ ከሊፋው ሄዶ ተራራውን እንደሚያነሡት ነገረው፡፡
ኅዳር 15 ቀን 975 ዓም ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፣ አይሁድ፣ ሌሎችም ተሰበሰቡ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ ጸሎተ ዕጣን ተደርሶ ኪርያላይሶን ተባለ፡፡ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሰገዱ፡፡ ከስግደት ተነሥተው ጸጥ ሲሉ ኃይለኛ ድምፅ ተሰማና ተራራው ካለበት ተነሣ፤ ፈቀቅም አለ፡፡ እንደገና ሰገዱ፤ አሁንም ተነሥቶ ፈቀቅ አለ፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ ሰገዱ ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ከሊፋው በከፍተኛ ድምፅ ጮኸ፡፡ «በቃ፣ በቃ በዚህ ከቀጠለ ከተማዋ ትፈርሳለች» አለ፡፡ ክርስቲያኖቹ በደስታ አምላካቸውን አመሰገኑ፡፡ ከሳሾቻቸው አፈሩ፡፡ ስምዖን ጫማ ሰፊው ግን ጠፋ፡፡
አባ አብርሃም በብርቱ አስፈለገው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ሊያገኘው አልቻለም፡፡ አባ አብርሃም ሶርያዊ ይህንን የድንግል ማርያምን ተአምር ለማስታወስ ከነቢያት ጾም ጋር ተያይዞ እንዲጾም አዘዘ፡፡ በገና ጾም የመጀመርያዎቹ ሦስት ቀናት ይህንን ተአምር ለማስታወስ የምንጾማቸው ናቸው፡፡
ዛሬ ተራራው ከሦስት ቦታ ተከፍሎ ይታያል፡፡ ከምዕራብም ወደ ምሥራቅ ሸሽቷል፡፡ «ሙከተም» ማለትም «የተቆራረጠ» ማለት ነው ይባላል፡፡ ይህ ተራራ ዛሬ በአሮጌዋ ካይሮ ይገኛል፡፡
ከዚህ ተአምር በኋላ ከሊፋ አል ሙኢዝ ለቤተ ክርስቲያን ብዙ ነገር አድርጓል፡፡ አያሌ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናት ተጠግነዋል፡፡ አዳዲሶቹም ተሠርተዋል፡፡ ይህ ተአምር የግብጽ ፓትርያርኮች ታሪክ በተሰኘው ጥንታዊ መጽሐፍ እና በሌሎችም መዛግብት ተመዝግቧል:: በተአምረ ማርያም ላይ የምናገኘው ታሪክ ከእነዚህ ጥንታውያን መዛገብት የተገኘ ነው፡፡ በሌላም በኩል ተራራው እና በአሮጌዋ ካይሮ የመዓልቃ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዙርያ የተደረጉ የአርኬዎሎጂ ቁፋሮዎችም ይህንን መስክረዋል፡፡
በኋላ ግን ቦታው ሆን ተብሎ የካይሮ የቆሻሻ መጣያ ተደረገ፡፡ ክርስቲያኖቹ ወደ አካባቢው የሚጣለውን ቆሻሻ በመጥረግ ታሪኩ እንዳይጠፋ ታገሉ፡፡ በመጨረሻም ነገር ሁሉ ለበጎ ነውና ቆሻሻዎቹን እንደገና ለአገልግሎት በማዋል /ሪሳይክሊንግ/ መጠቀም ጀመሩ፡፡ ዛሬ ለብዙዎች የሥራ እድል ከፍቶላቸዋል፡፡
የአል ሙከተም ተራራ ተፈልፍሎ የስምዖን ጫማ ሰፊው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ መቅደስ ክፍት ነው፡፡ ወንበሩ 25000 ምእመናን ይይዛል፡፡ የስምዖን ዐጽምም በመዓልቃ ቤተ ክርስቲያን በተደረገው ቁፋሮ ተገኝቶ በዚሁ የተራራ ቤተ ክርስቲያን በክብር አርፏል፡፡
----------------------------------------
ዲ.ን ዳንኤል ክብረት

Пікірлер: 318
@tsedielegesse1346
@tsedielegesse1346 11 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን በእውነት ቃለሕይወትን ያሰማልኝ የቅዱሳን አባቶች ረድኤት በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደርብን ሀገራችን ላይ ያለውን ችግርና ፈተና ያርቅልን🤲🤲🤲🥰🥰
@user-pi8pd7bs4g
@user-pi8pd7bs4g 29 күн бұрын
አሜን አሜን አሜን
@desalegndamtew6265
@desalegndamtew6265 2 ай бұрын
የሀን እድናይ የፈቀደ አምላካች ሰሙ የተመስገነ ይሁን ተሪገማቹ ሰለአቀርባቹሁልን እናመስግን አለን የ አባታች ቅዱስ ስሙኦን በርከት ረደኤት ከሁላችን ጋ ይሁን እድሁም አብረዉ ባሉ አባተቻቻን ፆሎት አይለየን አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏
@user-pi8pd7bs4g
@user-pi8pd7bs4g 29 күн бұрын
አሜን አሜን አሜን
@azmeruderdar4540
@azmeruderdar4540 Жыл бұрын
ናይ ኣቦና ቅድስ ስምኦን ን ኣቦታትና .ንብዓት.ፆሎት .ቃል ኪዳን ምስ ኩላትና ይከን. ኣመላከ እስራኤል ነዚ ቅድስ ኣቦ ክረአ ዝፈቀድካለይ ኣመላክ ክብሪ ምስጋና ንዓካ ይኩን ኣሜን
@MmMm-ls9iy
@MmMm-ls9iy 5 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን🙏🙏🙏💙😢😢😢
@tigistashuma6088
@tigistashuma6088 6 ай бұрын
እግዚያብሔር፣ይመስገን፣አሜን፣አሜን፣አሜን፣የቅድስ፣ስሞኦን፣በረከቱ፣ረዴቱ፣ከእኛ፣ጋር፣ይሁን፣አሜን፣እሜን፣አሜን
@user-pi8pd7bs4g
@user-pi8pd7bs4g 29 күн бұрын
አሜን አሜን አሜን
@bbppbbpp9897
@bbppbbpp9897 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን አሜን ቃል ህይውት ያሠማልን፡፡ የቅዱሣን በረከታቸው ይደረብን😭😭 የእወነት በጣም ደሥ የሚል መንፈስን የሚያድሥ ነው፡፡ኦረቶዶክሥ ተዋህዶ ለዘላለም ፀንታ ትኑረ፡፡ ተረጉማችሁ ለምትለቁልን እግዚአብሔረ ይባረካችሁ፡፡በረቱልን በዚህ ፌልም ብዙ ነፍስ ትድናለች፡፡ አሜን አሜን አሜን
@user-pi8pd7bs4g
@user-pi8pd7bs4g 29 күн бұрын
አሜን አሜን አሜን
@hanagosaye4686
@hanagosaye4686 2 жыл бұрын
የቅዱስ ስምኦን በረከት ይደርብን የኛ ፆን ፀሎት ከበረታ ምንም ማድረግ እንችላለን መፅም መፀሉይ ጥቅመ ብዙ ነው አጋንንት ያርቃል ለሀገር ስላም ይልካል
@Hana-ul9xi
@Hana-ul9xi 18 күн бұрын
ይሄን ድንቅ ስራ እና ተአምርህን እንዳይ ይቺን ሰአት እና ይችን ደቂቃ ባርከህ ስለሰጥኽኝ ጌታዬና መደሀኒቴ እየሱስ ክርስቶስ ክብር እና ምስጋና ለአንተ ይሁን አሜን (፫)❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@user-li5jf1pt1d
@user-li5jf1pt1d Жыл бұрын
ተመስገን ተመስገን ተመስገን የኔ ገይታ በእውነት የነዚህ ኣባቶች ፀሎት ኣይለየን🙏😢⛪
@BelayneshNigatu
@BelayneshNigatu 3 ай бұрын
Amen amen amen 🤲🤲🤲🤲
@demekecheadugna9642
@demekecheadugna9642 Жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የቅዱሳን በረከት ይደርብን ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@Meme-gq9iu
@Meme-gq9iu 18 күн бұрын
እግዚአብሔር ይመሰገን አሜን አሜን አሜን የቅድሰ ሰሞኦን በረከቱ ረዴቱ ከእኛ ጋር ይሁን አሜን አሜን አሜን❤❤❤
@user-ie1bi8zn7j
@user-ie1bi8zn7j 4 жыл бұрын
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ጌታ ሆይ ስምህ ካለም ጫፍ እስከ አርያም የተመሰገነ ይሁን አሜን የቅዱሳኑ እርድኤት በርከታቸው አይለየን አሜን ፫ ለሁላችሁም ቃለ ህይወት ያሰማልን
@MuMu-ls4fx
@MuMu-ls4fx 9 ай бұрын
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን 🙏🙏🙏
@genatgenat1148
@genatgenat1148 5 жыл бұрын
ቃለሂወት ያሰማልን ያባቶቻችን እረዴት በረከት ይደርብን አሜን ፫ ኦርቶዶክስ ለዘላለም ጸንታ ትኑር
@hannasalam672
@hannasalam672 Жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን❤❤
@Zet2023-fs1tt
@Zet2023-fs1tt 4 ай бұрын
በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር በድሜ በፀጋ ይጠብቅልን 🙏🙏🙏
@akezaberhe6216
@akezaberhe6216 Жыл бұрын
_ቃለ ህይወት የስመዐልና ብሓቂ እግዚአብሔር ኣምላክ ንፅህ ልቢ ያዓድለና ናይ ተግባር ሰባት ይግበረና_
@user-ri1qh5zn2g
@user-ri1qh5zn2g 2 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን ቅዱስ ሳምኦን በርከታቸው ይደርብን
@fggghjii4311
@fggghjii4311 Жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሠማልን የአባቶቻችን በረከት ትድረሰን😢🥰🥰🥰❤️❤️❤️
@hannasalam672
@hannasalam672 Жыл бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን ሁሉ የሚቻለው አምላክ ያባቶቻችን እረዴት በረከታቸው ይደርብን አሜን❤❤❤
@kalkidenadisu3487
@kalkidenadisu3487 3 жыл бұрын
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነቴ / እምነታችን ለዘለአለም ትኑር !!!!ይች ናት እምነቴ !!!!
@MmMm-sh8vi
@MmMm-sh8vi 2 жыл бұрын
🤲🤲🤲🤲🙏🙏
@user-pi8pd7bs4g
@user-pi8pd7bs4g 29 күн бұрын
አዎ እውነት አሜን አሜን አሜን
@user-kz3mf5in1z
@user-kz3mf5in1z 3 жыл бұрын
ቃለ ሂወትን ያሰማልን የናታችን የንፅህት ድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን መዳኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስሙ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ የተመሰገነ ይሁን የቅዱስን በረከት አይለየን
@asnew8192
@asnew8192 2 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባታችን የስሞኦን በረከት ይደርብን አሜን፫ ግሩም ነው
@user-df7jp2gs7q
@user-df7jp2gs7q 5 жыл бұрын
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን የአባታችን ቅዱስ ስምኦን በረክፕት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ተርግማችሁ ላቀረባችሁ እግዚአብሔር እድሜ ጤና ይስጣችሁ እናመሰግናለን
@user-px6wk1cy8x
@user-px6wk1cy8x 2 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን በረከታቸዉ ይደርብን 🙏🙏🙏
@zebaasrat9290
@zebaasrat9290 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለህወት ያስማልን ያባቶቻችን በርከት የደርብን በርቱ
@user-qp8fl2lv7t
@user-qp8fl2lv7t 3 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን
@betibeti72
@betibeti72 2 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለህወት ያሰማልን ያባቶቻችን በርከት የደርብን በርቱ 🙏🙏🙏🙏😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
@betibeti72
@betibeti72 2 жыл бұрын
😭😭🙏🙏🙏🙏🙏😭😭😭😭😭😭
@asmertasmert783
@asmertasmert783 3 жыл бұрын
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይወት የስመዐልና ክብራት ኣቦታትና በረኸቱን ፀግኡን የብዘሐልኹም እግዚኣብሄር ኣምላኽ🍃📖🍃
@ejiguakebede457
@ejiguakebede457 14 күн бұрын
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሄር ይመስገን 🙏🙏🙏🙏 አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏
@user-sc6pf7mu4p
@user-sc6pf7mu4p Жыл бұрын
ቃለህይወት ያሰማልን የቅዱስ ስምኦን በረከት በሁላችንም ላይ ይደርብን
@WeyniMurad
@WeyniMurad 4 ай бұрын
Aemennnnnnn nay aebotatna bereketin xelotin aeb hizbi kirstyan yihder🛐🙏🛐🙏🛐🙏🛐🙌🙌🙌🙌💖💖💖
@bini1623
@bini1623 Жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳኑ በረከታቸው ትድረሰን
@user-wt8mq9ho8l
@user-wt8mq9ho8l 8 ай бұрын
የቅዱሳን ረድኤት በረከት አይለየን አሜን አሜን አሜን🙏አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ የቅዱሳኑን ታሪክ አይ ዘድ ሰለፈቀድክልኝ አመሰግናለሁ😭🙏
@user-ds4pv9by5r
@user-ds4pv9by5r 2 жыл бұрын
ናይ አቦና ስምኦን ጸሎቶም አይፈለየና አሜን በረከቶም ይሕደረና አሜን
@mooodeal1909
@mooodeal1909 2 жыл бұрын
እግዚአብሔር ከብር ምሰጋና ለንተይሁን የቅዱሳን አምላክ በረከታቸው ይድርሰን
@user-bw1ih9cn9l
@user-bw1ih9cn9l 2 жыл бұрын
በእውነት እንዴት ያለ ተአምር ነው አቤቱ ጌታ ሆይ ትሁት አድርገኝ ይህንን የምትሰሩልን እግዝአብሔር ይባርካችሁ
@user-kl5hn1ss7h
@user-kl5hn1ss7h 5 жыл бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባቶቻችን ፀሎት በረከት አይለየን አሜንንንን••••• በጣም ልብን ደስስስስ የሚያሰኝ ታሪክ ነው እህት ወንድሞቼ አሁን እርጉዝ ነኝ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወንድ ከሆነ እምወልደው "ስምዖን" እለዋለሁ ስሙን •••••!!!
@mangestu4336
@mangestu4336 5 жыл бұрын
የበኪ እናት ዉይ የኔ እናት እመቤታችን ታገላግልሽ እህቴ እንደ ፍላጎትሽ ይሰጥሻል ፈጣሪ
@yekidusantarik
@yekidusantarik 5 жыл бұрын
አሜን እግዚአብሔር ያሰብሽውን ይስጥሽ
@habshihabshi7549
@habshihabshi7549 5 жыл бұрын
እህቴ ቡእውነት የቅድስት ሙራኤል ጸሎት የልብሺን ትሥጥሺ ውይይይይይይእመብርሀን ትዳብስሺ
@user-kl5hn1ss7h
@user-kl5hn1ss7h 5 жыл бұрын
አሜንንንንንንን
@user-jk3uc1gn5t
@user-jk3uc1gn5t 4 жыл бұрын
@@user-kl5hn1ss7h ወለድሽ
@user-xg9hs6bh4q
@user-xg9hs6bh4q 2 жыл бұрын
AMEEN AMEEN AMEEN kale heyoten yasamalen ye Abatichen barakati ye darabeni ⛪✝️📚💯💯💯💯👏👏👏👏🍇🍇🍇
@user-wu4kv3eu1c
@user-wu4kv3eu1c 5 жыл бұрын
በእውነት "ሳያዩ የሚያምኑ በፁዓን ንኡዳን ናቸወ"የተባለው ቃል እንባዬን አመጣው ይች ናት እምነት በ#ተዋህዶ የከበረውን በ#ድንግል #ልጅ #አምላክ በሆነው በ#ክርስቶስ #ኢየሱስ ማመን የ#ቅዱሱ አባት የስምኦን በረከት እረዴትም ይደርብን አሜን🇨🇬🇨🇬🇨🇬
@user-cu2ub2zb2z
@user-cu2ub2zb2z Жыл бұрын
የቅዱሳኑ እረዴትና በረከታቸው ይደርብን አሜን አምላከ ቅዱሳን ይርዳን ይቅር ይበለን
@meaziyoutube7899
@meaziyoutube7899 5 жыл бұрын
ቃለ ሂወት ያሰማልን ያባታችን በረከታቸው የደርብን አሜን
@adeladel5396
@adeladel5396 4 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃላ ህይወት ያሰማልን❤
@Angel-rg3xn
@Angel-rg3xn Жыл бұрын
ቃለህይወት ያሠማልን የቅዱሣኑ አባቶቻችን ኧረዴታቸዉ በረከታቸዉ ይደርብን አሜን
@werkitazarra4338
@werkitazarra4338 Жыл бұрын
ስለሁሉምነገር፣እግዚአብሔርስሙ፣የተመሠገነይሁን፣የአባቶቻችን፣በረከታቸው፣ይድረሰን፣አሜንአሜን
@saaa-ht5vs
@saaa-ht5vs 2 жыл бұрын
Amen amen amen kalehiwet yasemaln yekudus smon bereket riedaiet yderben
@tewenmhreteab7189
@tewenmhreteab7189 5 жыл бұрын
ኣሜንንንንንንንንንንንን ቃል ሂወት የስማልና በረከቶምን ጸሎቶምን ናይ ቅድሳን ኣይፈለየና።
@galwukro
@galwukro 6 ай бұрын
የአባታችን በረከታቸው ይደርብን❤
@abcdefghhjklmnopabcdefghjk1255
@abcdefghhjklmnopabcdefghjk1255 5 жыл бұрын
ጌታ ሆይ ላንተ ምን ይሳንሀል ክብርና መጎስ ላንተ ይሁን
@user-ey8el2qw3l
@user-ey8el2qw3l 2 ай бұрын
Amen Amen Amen kale hiwot yasemaln ❤❤❤
@teduadaayal2841
@teduadaayal2841 2 жыл бұрын
እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል እግዚአብሔር ይመስገን🙏🙏🙏አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏
@user-dx2fy1rh4v
@user-dx2fy1rh4v 3 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ክርስቲአን ያርከኝ ጌታየ አመሰግንሀለሁ
@asilphone9368
@asilphone9368 2 жыл бұрын
Amen Amen Amen Yee Kidusa simone Barktu Yee Darben Amen Amen Amen
@user-eg3bh6ox9n
@user-eg3bh6ox9n Жыл бұрын
እረዴታቸው በረከታቸው ይደርብን አሜን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏
@mezerberha5269
@mezerberha5269 Жыл бұрын
ቃል ህይወት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን 🙏🙏🙏❤
@rahelmamo4970
@rahelmamo4970 Жыл бұрын
Abate KEDUSE SEMEON Radeat Baraketh Yedareben AMEN AMEN AMEN!!!
@tggg8973
@tggg8973 Жыл бұрын
ቃለሕይወት ያሠማልን አሜን አሜን አሜንክብርለናተለአባቶቻችንይሑን
@hannalaila9555
@hannalaila9555 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃልህዉትያስማልን የአባታችን እርደትና በርከት ከሁላችንም ይደርብን
@user-lp5ig3pf5b
@user-lp5ig3pf5b 4 жыл бұрын
አሜን ፫ ቃለህይወት ያሰማልን እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ይህን እዳይ የረዳሀኝ አመሰግናለሁ ተመስጌን እኔ አፅተኛ ነኝና ይቅር በለኝ ማረኝም እየሱስ አባቴ 🙏
@user-cg7is4sl6r
@user-cg7is4sl6r 4 жыл бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን ቃል ህይወት ያስማልን ፀጋውን ያብዛላች የቅዱሳን ረደኤት በርከት ይድርበን የእመቤታችን የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅንት አይለየን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችን ለዘላለም ትኑር አሜን አሜን አሜን
@user-cq1me3qe7u
@user-cq1me3qe7u 10 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን አሜን ቃለሂወት ያምስል ን
@user-hj9vx1tz4o
@user-hj9vx1tz4o 5 жыл бұрын
Abeatu ye kdusan amilak erzabihar hoy kbir misgana ydresih yedingl mariyam lij Ye kusan semaetat melaktan milija bereket ayleyen hulun chayun ye weledishiw dingl mareyam kbir misgana ydiresish Eme birihen be milijashi lenisihe lesom leselot abikagni amen amen amen Lasitemarachuhun wenidimochachin kale hiyot yasemalin
@yriga
@yriga 2 жыл бұрын
amen amen amen kbriy leamlak smh ykber ymesgen lezelalemu amen
@mesi557
@mesi557 8 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያሠማልን የሰማነው በልቦናችን ይፃፍልን🤲 ለአባቶቻችን እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥልን👏🕊👏🕊
@jrresadleedas8876
@jrresadleedas8876 2 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን ምን አለ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላካችኝ እደሆነ የአለም ህዝብ ቢያውቅ😢😢😢😢😢 የኛ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስምህ የከበረ የተመሰገነ ይሁን አሜን❤❤❤❤❤
@merigalemekellem5553
@merigalemekellem5553 3 жыл бұрын
Amn amn yekdus smeon bereket ydereben zend amn 🙏🙏🙌🙌
@godislove1495
@godislove1495 4 жыл бұрын
ሃይማኖታችን ህይወታችን ሰላማችን ጸጋችን በቃ ሁሉም ነሽ ተዋህዶ እምነት በደም ክርስቶስ የተመሰረተት በ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ና በ ቅዱሳን ሰማታት ጻድቃን ያማርች ተዋህዶ በቃ ተዋህዶ ዘላለም ትኑር ኣሜን።
@mangestu4336
@mangestu4336 5 жыл бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን ቃል ህይወት ያሰማልን የቅዱስ በረከት ረድኤት አይለየን አሜን
@sarawalieyesgat5602
@sarawalieyesgat5602 4 ай бұрын
አሜን ቃለ ህይወትን ያሰማልን🎉🎉🎉
@sablaayele8859
@sablaayele8859 3 жыл бұрын
Egziabeher yemesgen bewunt qale hiwoten yasemalen tsega berketachewu ayileyen Amen Egziabeher yixebeqelne Amen
@user-gi3ql9ou1f
@user-gi3ql9ou1f 5 ай бұрын
የቅዱሳን በረከት ይደርብን
@jddjffdjdjrg6569
@jddjffdjdjrg6569 Жыл бұрын
ክብር ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሜን ፫ ክብር ምስጋና ይሁን አምላክን ለወለደች ለድንግል ማርያም አሜን ፫ እኔ ጸሎት በጣም ስነፍ ነኝ ግን እንኳን ክርስቲያን ሆንክ
@user-pi8pd7bs4g
@user-pi8pd7bs4g 29 күн бұрын
አሜን አሜን አሜን
@hiwothabesha3524
@hiwothabesha3524 2 жыл бұрын
ሁላችንም አንድ ሆነን ወደ እግዚአብሔር ብንመለስ እሱ ይቅር ይለናል በሀገራችን የመጣብንን መከራ ያጠፋልናል ፅሎት ለነገሮች መልስ ይሰጣል
@gggg-vi2yx
@gggg-vi2yx 4 күн бұрын
አሜንአሜንአሜንቃልህውትየሰምዐልና
@user-zk1pr9sm5v
@user-zk1pr9sm5v Жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ያባቶቻችን በረከት ይደርብን
@simretalmaheyusamra558
@simretalmaheyusamra558 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር ይመስገን እንዴት ደስ ይላል ነብስን ያለመለማል በረቱልን በዚህ አስከፌ ዘመን እንደዛህ ቀጣሉበት
@firiyotfiritawaahidoo3921
@firiyotfiritawaahidoo3921 3 жыл бұрын
Ameen Ameen Ameen
@firiyotfiritawaahidoo3921
@firiyotfiritawaahidoo3921 3 жыл бұрын
Ameen Ameen Ameen
@molokbety6970
@molokbety6970 2 жыл бұрын
🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲💒💒💒💒💒💒💒🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏💒💒💒💕💕💕💕💕💕😭😭😭😭😭😭😭
@nakstaaaa5924
@nakstaaaa5924 2 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን
@TemesgenAmlakye
@TemesgenAmlakye 11 ай бұрын
ቃል ህይውት ያሠማልን የቅዱሣን በረከታቸው ይደረብን አሜን አሜን🥰🥰❤❤😍😍
@user-xj3ql4xz5z
@user-xj3ql4xz5z 5 жыл бұрын
አሜን፫ በረከታቸዉ ይደርብን ኦርቶዶክሥ ለዘላለም ትኑር!!!♡♡♡
@user-dy5gd5hu1d
@user-dy5gd5hu1d 5 жыл бұрын
አሜን
@user-tc5vv1rw4t
@user-tc5vv1rw4t 4 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን
@tadlucky
@tadlucky 4 жыл бұрын
የድንግል ልጅ ሆይ እባክህ የቅዱሳን በረከት ይደርብን አሜን ፫
@sabayethicell3722
@sabayethicell3722 3 жыл бұрын
የቅዱሳን በረከት ይደረብን የሰማነዉን በልቦናችን ይደርብን
@hiwetassefa3618
@hiwetassefa3618 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያስማን የአባቶቻን በረከት ይደርብ።
@user-tc9ei5dq4n
@user-tc9ei5dq4n 2 жыл бұрын
ኣሜን ተዋህዶ መሆን መመረጥ ነው እንደዝህ ኣድርጋቹሁ ስላቀረብላችሁልን እናመሰግናለን ክብር ምስጋና ለ እግዚኣብሔር ይሁን🙏🙏🙏🙏
@musammadmusammad4092
@musammadmusammad4092 3 жыл бұрын
ቅዱሥ አባታችን የቅዱሥ ሥምኦን በረኬት እረዴትሕ ይደርብን አሜን
@mesi557
@mesi557 8 ай бұрын
"እግዚአብሔር ከኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል " ቃለ ህይወት ያሠማልን🤲👏✝️
@Hana-ul9xi
@Hana-ul9xi 18 күн бұрын
የቅዱስ ስምኦን ሀብተ እረድቄቶ ይደረብብን አሜን (፫)❤❤❤❤
@user-qi6og4zt3r
@user-qi6og4zt3r 5 ай бұрын
አቤቱ የቅዱሳን የጻድቃን የሰማዕታት አምላክ ጌታዬ መድኅኒቴ ቸር መሃሪ ይቅርታህ የበዛ መአትህ የራቀ አማኑኤል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሀገራችንን ሰላም አድርግልን ልባችንን ባንተ መንገድ ምራልን አፅራረ ክርስትያንና ቤተክርስትያንን አስታግስልን አሜንን🤲🤲😭😭
@user-qh9xk4ph7k
@user-qh9xk4ph7k 5 жыл бұрын
አሜን አሜን ከዚ ብዙ ነገር መማር ይቻላል አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን
@brhanie6823
@brhanie6823 2 жыл бұрын
የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው እረድኤታቸው አይለየን አሜን፫
@babanon9062
@babanon9062 5 жыл бұрын
Amen amen amen kale hewetn yasemalen yekidusan bereketna tselotachew ayleyen amen
@noorwawww9133
@noorwawww9133 3 жыл бұрын
የቅዱስ ስምኦን በረከቱን ረዴኤቱን ይደርብን ኣሜን ኣሜን ኣሜን
@hiruuteesilaassee2560
@hiruuteesilaassee2560 2 жыл бұрын
Kale heywot yasemalen tsagahun yabizalachu tebareku AMEEN AMEEN AMEEN ✝️✝️✝️
@sallamkann3472
@sallamkann3472 3 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃል ሂወት የስማዐለን
@MiskaMaganda
@MiskaMaganda 27 күн бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን ስለሁሉም ነገር😢😢😢😢😢😢😢
@user-is9qr6ri4e
@user-is9qr6ri4e 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለሂወት ያሰማልን የአባቶቻችን ጸሎት በርከታቸው ይደርብን 🙏🙏🙏
@mulumesele3589
@mulumesele3589 4 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን የቅድስና ምልጃ ጾሎታቸው በርከታቸው ለትውልድ ሁሉም ይሁንልን አሜን ተመስገን ጌታ ሆይ ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
@abeethiopiaethiopia5800
@abeethiopiaethiopia5800 2 жыл бұрын
የቅድሳን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን በርከታቸው ይደርብን!
@slama.1235
@slama.1235 3 жыл бұрын
አሜን ቃለሂወት ያሰማልን በረከቱ ይድረሰን
@dffdfftfg4814
@dffdfftfg4814 4 жыл бұрын
የቅዱስ ስምኦን በረከት ረድኤቱ ይደርብን አሜን አሜን አሜን
@hadasberhe4812
@hadasberhe4812 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን
@beilulbrhane4315
@beilulbrhane4315 4 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን በረከት ና ረዲኤት የኣባ ስምዖን ከሁላቺን ይሁን
@fairoozfairooz3607
@fairoozfairooz3607 Жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ጎዶልያስ
@tizitaworku4498
@tizitaworku4498 4 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወትን ያሰማልን የቅዱሳን በረከታቸው ይደረብን ለምታቀረቡልን ፈጣሪ ጸጋውን ያብዛላችው
@asadeteshome1114
@asadeteshome1114 4 жыл бұрын
እንደነዝህ ያሉ አባቶች እግዚአቢሄር ያብዝልን አሜን
@royaaro9789
@royaaro9789 5 жыл бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያስማልን የቅዱስ ብርከታችን ይደርስበኝ አሜን
ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 1 / Saint Simon - Part 1
37:51
የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Рет қаралды 178 М.
Mama vs Son vs Daddy 😭🤣
00:13
DADDYSON SHOW
Рет қаралды 51 МЛН
Я обещал подарить ему самокат!
01:00
Vlad Samokatchik
Рет қаралды 9 МЛН
CHOCKY MILK.. 🤣 #shorts
00:20
Savage Vlogs
Рет қаралды 16 МЛН
ЧУТЬ НЕ УТОНУЛ #shorts
00:27
Паша Осадчий
Рет қаралды 10 МЛН
ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር ክፍል - 1 / Kidus Aba Yohannes Hatsir Part -1
47:38
የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Рет қаралды 408 М.
ስለ ንጉሥ ዳዊት ያልተሰሙ እውነታዎች | Unheard secrets about King David | @16_media16
10:36
ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ክፍል 1 / Saint Moses the Black Part - 1
54:20
የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Рет қаралды 235 М.
ቅድስት መሪና ሰማዕት ዘአንፆኪያ / Saint Marina the Antsokia
1:18:32
የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Рет қаралды 397 М.
ፍካሬ ኢየሱስ - Fkare Eyesus ||| Ethiopian Orthodox Tewahido Amharic Sermon
34:24
መዝሙረ ዳዊት - Mezmure Dawit Tube
Рет қаралды 1 МЛН
ቅድስት ሙራኤል / Kidist Murael - ሙሉ ታሪክ
1:32:15
የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Рет қаралды 231 М.
ነብዩ ዳንኤል አጭር ታሪክ
40:17
የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Рет қаралды 117 М.
Хитрая ГОРНИЧНАЯ вернула ДОМ матери 😱 #shorts
0:57
Лаборатория Разрушителя
Рет қаралды 3,3 МЛН
Comfortable 🤣 #comedy #funny
0:34
Micky Makeover
Рет қаралды 10 МЛН
За девочкой гонится бандит😳
1:00
Trailer Film
Рет қаралды 3,5 МЛН
MAGIC FINGER TRICK TUTORIAL 😱😳
0:11
Milaad K
Рет қаралды 14 МЛН
😇 or 🔥 ? #shorts
0:43
A4
Рет қаралды 6 МЛН