Рет қаралды 102,240
ዘሌዋውያን 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔርም ከመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ ሲል ተናገረው፦
² ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራችው፦ ከእናንተ ማናቸውም ሰው ለእግዚአብሔር መባ ሲያቀርብ መባችሁን ከእንስሳ ወገን ከላሞች ወይም ከበጎች ታቀርባላችሁ።
³ መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።
⁴ እጁንም በሚቃጠለው መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፤ ያስተሰርይለትም ዘንድ የሠመረ ይሆንለታል።
⁵ በሬውንም በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
⁶ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ይገፍፈዋል፥ በየብልቱም ይቈርጠዋል።
⁷ የካህኑም የአሮን ልጆች በመሠዊያው ላይ እሳት ያነድዳሉ፥ በእሳቱም ላይ እንጨት ይደረድራሉ፤
⁸ የአሮንም ልጆች ካህናቱ የተቈረጡትን ብልቶች ራሱንም ስቡንም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ይረበርቡታል፤
⁹ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት የእሳት ቍርባን አድርጎ በእግዚአብሔር ዘንድ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
¹⁰ ቍርባኑም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበጎች ወይም ከፍየሎች ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርበዋል።
#aba_gebre_kidan #ርእሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረኪዳን #ጣና_ቅዱስ_ቂርቆስ #ርእሰ_ሊቃውንት #Fewus_Menfesawi #menfesawi #Aba #Africa #Ethiopia #አፍሪካ #ኢትዮጵያ #ፈውስ_መንፈሳዊ #for_you #Viral #parati #pfy #storytime #tiktok ፈውስ መንፈሳዊ ዘጣና ቅዱስ ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fewus Menfesawi / ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ / Aba Gebrekidan Girma