የደም ማነስ ምልክቶች🌻 ደም ማነስ ምልክቶች

  Рет қаралды 885

Birabiro ቢራቢሮ

Birabiro ቢራቢሮ

Жыл бұрын

ወደ 400 አይነት የሚሆኑ የደም ማነስ ( Anemia ) አሉ ከነዚህም መካከል ተመርምሮ ህክምና ካልተደረገ ለህወት ማለፍ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል በቪዲዮ የተብራሩት ምልክቶች ካለቦት ፈጥነው ምርመራ ያድርጉ በጥብቅ እመክራለሁ
• በዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኙት መረጃዎች በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ጠቃሚ ሃሳቦችን ለማካፈል ብቻ ታቅደው የቀረቡ እንጂ በምንም ዓይነት መሠረታዊ የጤና እክሎችን ለመፍታት የሕክምና ምርመራንና የሐኪም ውሳኔዎችን ለመተካት የተሰጡ አይደሉም። የጤና ምርመራንና ሕክምና የሚሹ ጤና ነክ ችግሮችን በተመለከተ ሐኪምዎን እንዲያማክሩ በብርቱ እናሳስባለን
የደም ማነስ ምልክቶች
የብረት ማነስ በሰውነት ውስጥ የሚከሰተው ሰውነት መያዝ ከሚገባው በታች የአይረን ወይም ብረት ማእድን ሲኖረው ሲሆን ይሄ ሁኔታ ደግሞ ደም ማነስ ተብሎ ይታወቃል
#የደም ማነስ ምልክቶች#ደም ማነስ ምልክቶች
በአለም ላይ የተለያዩ አይነት የደም ማነስ አይነቶች ቢኖሩም በጣም የተለመደው ግን በአይረን ወይም ብረት ማነስ ምክንያት የሚከሰተው አይነት የደም ማነስ ነው ምልክቶቹም አንዳንድ ጊዜ የተለያዩ ይሆናሉ ለምሳሌ የደም ማነሱ ደረጃ፣ በምን ያህል ፍጥነት ደም ማነሱ ተከሰተ፣ አጠቃላይ የጤና ሁኔታና የታማሚው እድሜ ምልክቶቹ የተለያዩ እንዲሆኑ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ
በአንዳንድ ሁኔታዎች ደም ማነስ ኖሮባቸው ምንም አይነት የደም ማነስ ምልክቶች ላያሳዩ ይችላሉ
ከወትሮው የተለየ ድካም ማዞርና ራስን መሳት፣ የጡንቻዎች አለመታዘዝ ወይም መድከም፣
በቀላሉ የድካም ስሜት መሰማት የተለመደ የደም ማነስ ምልክት ነው ይሄ ምልክት የሚስተዋልባቸው የብረት ማእድን ማነስ ያለባቸው ሰዎች ላይ ነው
ይሄ ድካም የሚከሰተው ሰውነት ሄሞግሎቢንን ለማምረት የሚሆን የብረት ማእድን ሲያንሰው ነው ሄሞግሎቢን በቀይ የደም ህዋስ ውስጥ የሚገኝ ፕሮቲን ሲሆን ደም ኦክስጅንን ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ተሸክሞ የሚያደርስ ነው ሰውነተ ሄሞግሎቢንን ለመስራት ብረት ያስፈልገዋል
በቂ ሄሞግሎቢን በሰውነት ውስጥ ከሌለ ጡንቻዎችና ህብረህዋሳት በጣም አነስተኛ ኦክስጂን ስለሚያገኙ የድካም ስሜት ይከተላል ልብም ሰውነት ውስጥ ኦክስጅን ያለው ደም ለማድረስ በጣም እንድትመታ ትገደዳለች
በብረት ማነስ ምክንያት ከሚከሰተው ድካም ጎን ለጎን ጥንካሬ ማጣት፣ ትኩረት ማድረግ መቸገርና በቀላሉ በቆጣት መናደድ የደም ግፊት ዝቅ ማለት፣ በቀላሉ ለመድማት መጋለጥ፣ይስተዋላል
ባልተለመደ ሁኔታ የቆዳ መገርጣት
በቀይ የደም ህዋስ ውስጥ ያለው ሄሞግሎቢን ደምን ደማቅ ቀይ ቀለም እንዲይዝ ያደርጋል የዚህ ማነስ ደግሞ ደም ፈዛዛ ቀይ ቀለም እንዲኖረው ያደርጋል በዚህም ምክንያት የቆዳ መገርጣት ይከሰታል ይሄ ሁኔታ መካለኛ ወይም ከባድና ስር የሰደደ የደም ማነስ ባለባቸው ሰዎች ላይ በብዛት ይታያል
አይናችንን የታችኛውን ሽፋን ገለጥ አድርገን በመስታወት ስናየው ደማቅ ቀይ ከመሆን ይልቅ ፈዛዛ ሮዝ ቀለም ካሳየን አንዱ ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ባላቸው ሰዎች ላይ የሚታይ ግልፅ የደም ማነስ ምልክት ነው
3. የትንፋሽ ማጠር
በብረት ማነስ ምክንያት ሄሞግሎቢን መጠን ሲያንስ ኦክስጂንም በዛው ልክ ያንሳል ስለዚህ ጡንቻዎች ስራቸውን ለመስራት ለምሳሌ እንደ በእግር መሄድ፣ደረጃ መውጣት፣ ያሉትን ለማከናወን በቂ ኦክስጂን ስለማያገኙ ቶሎ ቶሎ መተንፈስና የትንፋሽ እጥረት ይከሰታል
4. ራስ ምታት
የአይረን እጥረት ተደጋጋሚ ራስምታት ያስከትላል
5. የልብ በጣም መምታት
ጎልቶ የሚሰማ የልብ ምት ሌላው በአይረን እጥረት ምክንያት የሚመጣ የደም ማነስ ምልክት ነው
በብረት እጥረት ወቅት የሄሞግሎቢን መጠን ያንሳል በዚህ ምክንያት ደግሞ ለሁሉም የሰውነት ክፍሎች ኦክስጅን የያዘ ደም በበቂ ሁኔታ ለማዳረስ ልብ በጣም ለመምታት ትገደዳለች
ባልተለመደ ሁኔታ ፈጣን የልብ ምት ይሰማናል የደም ማነሱ ከባድ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ የልብ ችግርን ያባብሳል
6. ደረቅና የተጎዳ ቆዳና ፀጉር
የቆዳና የፀጉር መድረቅና መጎዳት አንዱ የብረት ማነስ ምልክት ነው
የብረት ማነስ በደም ውስጥ የሄሞግሎቢን መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል በዚህም ለህዋሳት መድረስ ያለበት ኦክስጅን በበቂ ሁኔታ እንዳይደርስ ይሆናል
ቆዳና ፀጉር የኦክስጅን እጥረት ሲገጥማቸው ደግሞ ደረቅና ደካማ በቀላሉ የሚሰነጠቁ ይሆናሉ
የብረት እጥረት የፀጉር መርገፍን በተለይ እስከ 45 አመት እድሜ የሆኑ ሴቶች ላይ ያስከትላል በተፈጥሮ ፀጉር ሲበጠርና ሲታጠብ በመጠኑ ይነቃቀላል ነገር ግን በጣም በብዛት የሚነቃቀል ከሆነ ከብረት ማነስ ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል
7. የአፍና የምላስ ህመምና እብጠት
የአፍ ውጭውና ውስጡ የብረት ማእድን ማነስን ያመለክታል
ያበጠ፣ የቀላ፣ ወይም ደግሞ ባልተለመደ ሁኔታ ምላስ ልሙጥ መሆንና ቅባታማ መስሎ መታየት፣ የአፍ መድረቅና ውስጡን የማቃጠል ስሜት መሰማት፣የአፍ ጥግና ጥጉ መሰንጠቅ፣ የአፍ ቁስለት፣የአፍ ህመም መሰማትና የከንፈር ማበጥ ይከሰታል
8. በእንቅልፍ ሰአት እግርን ማንፈራገጥ ወይም ማንቀሳቀስ Restless legs
ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መልኩ እግርን ማንፈራገጥ የማሳከክ ወይም የመነዝነዝ ስሜት ስለሚሰማ በብረት ምክንያት የሚከሰተው የደም ማነስ ያለባቸው ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ለዚህ ችግር 6 እጥፍ የተጋለጡ ናቸው ይላሉ ጥናቶች
9. የሚሰባበር ወይም የሰረጎደ ጥፍር /የማንኪያ አይነት ቅርፅ ያለው ጥፍር
ብዙ ጊዜ የሚታይ ምልክት ባይሆንም የሚሰባበር ወይም የሰረጎደ ጥፍር /የማንኪያ አይነት ቅርፅ ያለው ጥፍር መኖር አንዱ የብረት ማነስ ምልክት ነው
ይሄ ምልክት የሚታይባቸው ሰዎች 5% ብቻ ናቸው እንዲሁም የብረት እጥረቱ እጅግ ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ ብቻ ይከሰታል
10. የእጅና እግር መቀዝቀዝ ምክንያቱም ወደ እጅና እግር የሚደርሰው ኦክስጅን በጣም አነስተኛ ስለሆነ እንደውም አንዳንድ ሰዎች በቀላሉ ሊበርዳቸው ወይም ሊቀዘቅዛቸው ይችላል
11. ተደጋጋሚ ኢንፌክሽን አይረን ለጤናማ በሽታ የመከላከል አቅም አስፈላጊ በመሆኑና የብረት ማነስ በሰውነት ውስጥ በኢንፌክሽን ቶሎ ቶሎ ለመጠቃት ያጋልጣል ድባቴም ይታይበታል ህመምተኛው
12. ደም ማነስን ተከትሎ የሚመጣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም አነስተኛ የምግብ ፍላጎት ይኖራል ምክንያቱም የረሃብ ሆርሞን ተብሎ የሚጠራው ግሬሊን ላይ ለውጥ ስለሚፈጠር ትክክለኛ የረሃብ መልእክት ለአንጎላችን አይደርሰውም
የደም ማነስ ምልክቶች
ለምግብነት ያልተለመዱ ወይም ምግብ ያልሆኑ ነገሮችን ለመብላት መፈለግ ለምሳሌ አፈር፣ በረዶ፣ ቾክ፣ ወረቀት፣
የድባቴ መሰማት በትላልቅ ሰዎችና እርጉዝ ሴቶችም የደም ማነስ ካለባቸው ለድባቴ የመጋለጥ እድላቸው በጣም ከፍ ያለ ነው
Disclaimer: This video is not intended to provide diagnosis, treatment or medical advice. Content provided on this KZfaq channel is for informational purposes only. Please consult with a physician or other healthcare professional regarding any medical or health related diagnosis or treatment options. Information on this KZfaq channel should not be considered as a substitute for advice from a healthcare professional. The statements made about specific products throughout this video are not to diagnose, treat, cure or prevent disease.

Пікірлер: 13
@lulitlula4290
@lulitlula4290 Жыл бұрын
ሼርርርርር👏👏👏❤️
@lulitlula4290
@lulitlula4290 Жыл бұрын
የምታቀርቢው ሁሉ በጣም ጠቃሚ ነው ደሞ ተጠፋፍተናል እናመሰግናለን🙏❤️
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
አመሰግናለሁ ሉላዬ
@ethiopia5722
@ethiopia5722 Жыл бұрын
Very informative
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
Thanks a lot dear
@zarasalem9565
@zarasalem9565 10 ай бұрын
❤❤❤
@genetziguita4586
@genetziguita4586 Жыл бұрын
Btam turu adrgesh Nwe yemtabrariw❤
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
አመሰግናለሁ ገኒዬ እግዚአብሄር ያክብርሽ
@akabeka2352
@akabeka2352 Жыл бұрын
የቴልግራም ወይም የዋሳፕ ኮንታክት ካለሽ ጻፊልን
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
t.me/birabiro1626 የቴሌግራም አድራሻዬ ነው ውዴ
@akabeka2352
@akabeka2352 Жыл бұрын
@@birabiro1626 ገና መክፈትሽ ነው ወይ ብሎክ ነው
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
አዎ አሁን ነው የከፈትኩት:: በፊት እጠቀምበት የነበረው አልከፍት አለኝ። ከተጠቀምኩት ቆይቼ ነበር ካሁን በኋላ በዚ ነው የምጠቀመው የኔ ውድ
@akabeka2352
@akabeka2352 Жыл бұрын
@@birabiro1626 እስቲ ወደኔ ለመደወል ሞክሪ
아이스크림으로 체감되는 요즘 물가
00:16
진영민yeongmin
Рет қаралды 61 МЛН
Little girl's dream of a giant teddy bear is about to come true #shorts
00:32
New model rc bird unboxing and testing
00:10
Ruhul Shorts
Рет қаралды 24 МЛН
A teacher captured the cutest moment at the nursery #shorts
00:33
Fabiosa Stories
Рет қаралды 12 МЛН
እርግዝና እና  የደም ማነስ | Healthy Life
9:17
News ET Social
Рет қаралды 6 М.
Robert Greene: A Process for Finding & Achieving Your Unique Purpose
3:11:18
Andrew Huberman
Рет қаралды 10 МЛН
ፋና ጤናችን - ደም ማነስ ምንድን  ነው ?
5:22
Fana Television
Рет қаралды 4,1 М.
Female Reproductive Cycle | Menstrual Cycle | Hormones
1:50:05
Dr. Najeeb Lectures
Рет қаралды 1,1 МЛН
Ethiopia | የከፍተኛ ደም ግፊት (Hypertension) ምልክቶች እና መድሃኒቶች
24:52
ፕሪሚየም - PREMIUM በ Dr. Abraham
Рет қаралды 36 М.
Diuretics | Pharmacology | Dr Najeeb
3:03:35
Dr. Najeeb Lectures
Рет қаралды 1,1 МЛН
아이스크림으로 체감되는 요즘 물가
00:16
진영민yeongmin
Рет қаралды 61 МЛН