የሀባብ ድንቅ የጤና ጥቅሞች/ የጤና ትምህርት/ ሀብሀብ

  Рет қаралды 1,550

Birabiro ቢራቢሮ

Birabiro ቢራቢሮ

Жыл бұрын

ሀባብ ትንሽ ካሎሪና ስኳር፣ ብዙ ቫይታሚኖች፣ ማእድናትና ፀረኦክሲዳንቶችን የያዘ፣ ለመብላት ደስ የሚልና ለጤናማ አመጋገብ ስርአት አስተዋፅኦ የሚያደርግ ፍራፍሬ ነው
#የሀባብ ድንቅ የጤና ጥቅሞች#ሀባብ
ከካንሰር፣ ከልብ ህመም፣ ከሆድ ድርቀት፣ከአላስፈላጊ ውፍረትና ቦርጭ፣ ከስትሮክ፣ከኮሌስትሮል፣
ከቆዳ ድርቀት፣ ከጡንቻ ህመም ይከላከላል
ብዙ ውሃና አነስ ያለ አሰር ስላለውም የሆድ ድርቀትን ለማስወገድ፣ የምግብ ስልቀጣ እንዲቀላጠፍና ቆሻሻ በቀላሉ እንዲወገድ ይረዳል
1) በጠቃሚ ንጥረነገሮች የተሞላ ነው
ሃባብ ቫይታሚን C፤ A እና B6. አሉት በዚህ የተነሳ በሽታ የመከላከል አቅማችንን ያጠናክራል፣ ሰውነታችን አይረንን በአግባቡ መጥጦ እንዲጠቀም፣ ሰውነት ፕሮቲንን ሰባብሮ እንዲጠቀምበት ያደርጋል እንዲሁም የአይንና የቆዳ ጤናማነትን ይጠብቃል
በፖታሲየም የበለፀገ ነው ሀባብ ይሄም ከፍ ያለ የደም ግፊት እንዲስተካከል ይረዳል እንዲሁም የነርቮችን ስራ ያቀላጥፋል
በሰውነት ውስጥ የፖታሲየም ማእድን ማነስ የነርቭ ንዝረት እንዲኖር፣ መደንዘዝና የመቆንጠጥ ወይም የመነዝነዝ አይነት ስሜት ያስከትላል
የእግር ህመም የሚያስቸግራችሁ ከሆነ የፖታሲየም ማነስ ሊሆን ስለሚችል ሀባብን መመገብ አንዱ መፍትሄ ነው
2) ብዙ ላይኮፔን በውስጡ ይገኛል
ላይኮፔን በሃባብ ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኝ ፀረኦክሲዳንት ባህሪ ያለው ንጥረነገር ሲሆን ለካንሰር፤ ለልብ ህመም፤በእድሜ ምክንያት ለሚከሰት የአይን ህመም የመጋለጥን እድል ይቀንሳል እንዲሁም ህዋሶችን ከጉዳት ይጠብቃል አንዳንድ ጥናቶች እንደሚመክሩት ሃባብን አዘውትሮ መመገብ ከፍተኛ የደም ግፊት ላለባቸው ሰዎች ጠቃሚ ነው
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በላይኮፔን የዳበሩ ምግቦችን መመገብ ለስትሮክና ለልብ በሽታ የመጋጥ እድልን ይቀንሳል በውስጡ የሚገኙት ፀረአክሲዳንቶች የደም ቧንቧዎችን ተግባር ያሻሽላል
3) ሰውነት ድርቀት ወይም የፈሳሽ እጥረት እንዳይገጥመው ያደርጋል
ብዙ ሰዎች በቂ ውሃ አይጠጡም በሞቃታማ ወቅቶች ደግሞ በቂ ፈሳሽ መጠጣት ጠቃሚ ነው ምክንያቱም በእነዚህ ጊዜያት ብዙ ፈሳሽ ከሰውነታችን በላብ መልክ ይወገዳል
በቂ ውሃ መጠጣት ሰውነት እንዳይደርቅ ያደርጋል እንዲሁም መርዛማ ነገሮች ታጥበው እንዲወገዱ በማድረግ ጤናማ ቆዳ ልብና ሰውነት እንዲኖረን ያስችለናል
ሀባብ 90% ውሃ ስለሆነ የሀባብ ጭማቂን መጠጣት ሰውነት የፈሳሽ እጥረት እንዳይገጥመው ያግዛል
5) ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል
ክብደት ለመቀነስ ካሰባችሁ ሃባብን በአመጋገባችሁ ውስጥ በማካተት በቀላሉ ያሰባችሁትን ማሳካት ትችላላችሁ
በውስጡ በብዛት ውሃ ስለያዘና ትንሽ ካሎሪ ስላለው እንደ ስናክ መጠቀም ይቻላል
ሌሎች ጣፋጭ ምግቦችን ለመክሰስ ከምንመገብ ሀባብን ብንበላ ለረጅም ሰአት የጥጋብ ስሜት እንዲሰማንና እንዳይርበን ስለሚያደርግ በየቀኑ ሀባብ መብላት ክብደት ለመቀነስና ከቁመታችን ጋር የተመጣጠነ ክብደት እንዲኖረን የደም ግፊታችን እንዲስተካከልና ቦርጭን ለማጥፋት ይረዳናል
7)ለካንሰር የመጋለጥ እድልን ለመቀነስ
መጠነኛ ኢንፍላሜሽን ጠቃሚ ቢሆንም የበዛ ኢንፍላሜሽን በሰውነት ውስጥ መከሰት እንደካንሰር፣ አስም፣ የልብ በሽታና አይነት 2 የስኳር በሽታ ላሉ የተለያዩ ህመሞች እንድንጋለጥ ያደርጋል
በሃባብ ውስጥ የሚገኘው ላይኮፔን ኢንፍላሜሽን እንዲቀንስ በማድረግ ካንሰር አምጪ ህዋሶች እንዳያድጉ ይከላከላል
9) ለቆዳ
የሀባብ ውሃ ቫይታሚን ኤ ቢ6 እና ሲ እንዲሁም ላይኮፔን አለው
ይሄም የቆዳ ሴሎች እንዲጠገኑ፣ ቆዳ እንዳይደርቅና እንዳይፈረፈር፣ ቆዳ ለስላሳ ጥርት ያለና የሚያምር እንዲሆን፤ ኮላጅን በብዛት እንዲመረት፣ የቆዳ የመለጠጥ ችሎታ እንዲጨምር፣ ብጉር እንዳይፈጠር፣ ቆዳ ከፀሃይ ቃጠሎ እንዲጠበቅ እንዲሁም ወደ ቆዳ የሚመጣ የደም ዝውውር እንዲጨምር ይረዳል
8) ኢንፍላሜሽንን ለመቀነስ ያግዛል ሀባብ
በሃባብ ውስጥ የሚገኘው ፀረኦክሲዳንት፣ላይኮፔንና ቫይታሚን ሲ ኢንፍላሜሽን እንዲቀንሰ ያደርጋል ኢንፍላሜሽን እብጠት፤ ያበጠው አካባቢ ህመም መኖርና መቅላት እንዲከሰት ያደርጋል ኢንፍላሜሽንን በቀላሉ ለመከላከል ደግሞ ተፈጥሯዊው መንገድ ሃባብን አዘውትሮ መመገብ ነው
11.ለአይን ጤንነት
በሃባብ ውስጥ ላይኮፔን የተባለ ፀረኦክሲዳንትና ኢንፍላሜሽንን የሚቀንስ ንጥረነገር አለ ይሄም የአይን ህዋሳት እንዳያረጁ ይከላከላል
10) የጡንቻ ህመምን ለማስታገስ
ከስፖርት በኋላ የሀባብን ጭማቂ መጠጣት ወይም ሀባብን መብላት የጡንቻ ህመምንና ስትራፖን ያስታግሳል
በውስጡ የሚገኘው ሲትሩሊን ደግሞ በሰውነት ውስጥ ናይትሪክ ኦክሳይድ እንዲመረት ይረዳል በቂ ናይትሪክ ኦክሳይድ በሰውነት ውስጥ ሲኖር ደግሞ ጥሩ የሆነ የደም ዝውውር እንዲኖር ያደርጋል
11) የሀባብ ፍሬና ቆዳ ጥቅም አላቸው
ብዙ ሰዎች የሀባቡን የውስጠኛውን ቀዩን ክፍል በልተው ቆዳውንና ፍሬውን ይጥሉታል ነገር ግን የሀባብ ፍሬና ቆዳ በጣም ብዙ ጠቃሚ ንጥረነገሮችን በውስጣቸው ይይዛሉ የሃባብ ቆዳ በጣም አነስተኛ ስኳርና ብዙ አሰር ይይዛል ከስጋው ይልቅ
እንዲሁም L-citrulline የተባለ ንጥረነገር ስላለው የደም ግፊትን ይቀንሳል ሰውነትም ቀልጣፋ እንዲሆን ያደርጋል
የሃባብ ፍሬ ሰውነታችን ጉልበት እንዲኖረው፤ የነርቮችን ስራ ለማቀላጠፍ፤ የደም ግፊትን ለማመጣጠን ትልቅ አስተዋፅኦ በሚያበረክተው ማግኒዝየም የተሞላ ነው
የሃባብ ፍሬ ደርቆ ወይም በጥሬው ሊበላ ይችላል አብሮ ከቀዪ ክፍል ጋር
ፎሌትም አለው ይህም ለካንሰርና ለድባቴ ማለትም ዲፕረሽን የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል
mono unsaturated እና poly unsaturated ፋቲ አሲዶች መገኛ ነው፤ እነዚህ አሲዶች ከልብ ድካምና ከሰትሮክ ይከላከላሉ እንዲሁም መጥፎ ኮሌስትሮል የሆነውን LDL መጠን ከደም ውስጥ እንዲቀንስ ያደርጋሉ
የሃባብ ቆዳ የሚሰጣቸውን የጤና ጥቅሞች በዝርዝር የሚገልፅ ቪደዮ ከዚህ በፊት የሰራሁት አለ ካርድ ላይ አደርግላችኋለሁ ማየት ከፈለጋችሁ
4. ከልብ በሽታ ይከላከላል
ላይኮፔን ሀባብ ቀይማ ቀለም እንዲኖረው የሚያደርግ ንጥረነገር ነው ላይኮፔን ኮሌስትሮልን በመቀነስ ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ህመሞች እንዳይከሰቱ ስለሚከላከል ሀባብን አዘውትሮ መመገብ ለዚህ አይነተኛ መፍትሄ ነው
5. ከባድ አስምን ቀለል ያደርጋል
ሀባብ ብዙ ቫይታሚ ሲ አለው በውስጡ ይሄ የአስምን ከባድ ስቃይ በቀን አንድ ብርጭቆ የሃባብ ጭማቂ በመጠጣት ወይም የዛን እኩል በመብላት መቀነስ ይቻላል
6. የድድ ህመም/ችግሮች ለመቀነስ
ሃባብን አዘውትሮ መብላት 25% የአለም ህዝቦችን የሚያጠቃውን የድድ በሽታ ይከላከላል ይሄ በሽታ የጥርስ መውለቅን፤ ኢንፌክሽንንና ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ህመሞችን ያስከትላል ይሄን በመከላከል ረገድ ሀባብ ትልቅ ድርሻ አለው
10. ለኩላሊትና ጉበት ጤና
የሰው ልጅ ሰውነት ከምግብና ከምንተነፍሰው አየር ለብዙ መርዛማ ንጥረ ነገሮች የተጋለጠ ነው እነዚህ መርዛማ ንጥረነገሮች በኩላሊት አማካኝነት ከሰውነት ይወገዳሉ ስለዚህ ኩላሊት ይህን ተግባር ያለችግር ማከናወን እንድትችል፣ ጫና እንዳይፈጠርበትና ጤነኛ እንድትሆን ሀብሀብ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል በሃብሃብ ውስጥ በዋነኛነት ፖታሲየምና ካልሲየም ስላለ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ከሰውነት እንዲወገዱ ይረዳል
ፕሮቲን በሰውነት ውስጥ ፕሮሰስ በሚደረግበት ጊዜ አሞኒያ ይፈጠራል
ሀባብ ጉበት አሞኒያን በቀላሉ ፕሮሰስ እንዲያደርግና እንዲያስወግድ ይረዳዋል
ጥንቃቄ
ሀባብን አብዝቶ መመገብ የበዛ ላይኮፔንና ፖታሲየም ሰውነት ውስጥ እንዲከማች ያደርጋል የላይኮፔን መብዛት (ከ30 ሚሊግራም በላይ መሆን ) ደግሞ ተቅማጥ፤ምግብ ያለመፈጨት ችግር፤ ሆድ መንፋት፤ ማቅለሽለሽና ማስመለስ እንዲከሰት ያደርጋል
በጣም ትንሽ ካሪና ስኳር ያለው ስለሆነ በየቀኑ መመገብ ትችላላችሁ ነገር ግን የስኳር ህመምተኞች ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ምክንያቱም አብዝተው ሀባብን ሲመገቡ የስኳር መጠናቸው ሊጨምር ይችላል

Пікірлер
How Many Balloons Does It Take To Fly?
00:18
MrBeast
Рет қаралды 174 МЛН
Clown takes blame for missing candy 🍬🤣 #shorts
00:49
Yoeslan
Рет қаралды 40 МЛН
የእርትብ አሰራር/ #ethiopian food
3:08
E - tube
Рет қаралды 234
የቀረፋ ሻይ የጤና ጥቅም/የቀረፋ ሻይ ጥቅም
6:00
Birabiro ቢራቢሮ
Рет қаралды 1 М.
ማን ይቅደምልን ? ? ?
6:39
Nu Enamesgen / ኑ እናመስግን
Рет қаралды 113