"ቅድመ ክፍያ ሳይፈጸም በአቅራቢዎች እና ላኪዎች መካከል የሚደረግ ግብይት ወንጀል ነው" - ክፍል 2 | ነፃ_ሃሳብ

  Рет қаралды 5,692

AddisWalta - AW

AddisWalta - AW

Ай бұрын

Join this channel to get access to perks:
/ @addiswalta
"ቅድመ ክፍያ ሳይፈጸም በአቅራቢዎች እና ላኪዎች
መካከል የሚደረግ ግብይት ወንጀል ነው"
#Addiswalta #Ethiopia #News | ነፃ_ሃሳብ | netsa_hasab
Addis Walta Instagram: addiswalta?...
Addis walta FM 105.3 youtube : / @addiswaltafm105.3
Entertainment youtube: / @addiswaltaentertainment
Afaan Oromoo youtube: / @awafaanoromoo
Tigrigna youtube: / @awtigrigna
KZfaq Main channel: / @addiswalta
AW English : / @awenglish1
Facebook: / wmccwaltamediaandcommu...
Twitter: / walta_info
FM: Walta FM 105.3
Website: waltainfo.com
Telegram: t.me/WALTATVEth
Arabic Facebook: تلفزيون والتا بالعربي Walta TV Arabic
AW English Facebook : / 100068007437624
#WaltaTV #addiswalta

Пікірлер: 8
@selammerga1960
@selammerga1960 21 күн бұрын
ጋዜጠኛ ስሜነህ በዚህ ቃለ ምልልስ ወቅት ጥያቄ ጠይቀህ ሀላፊው መልስ እስኪሰጡ በትግስት ማዳመጥ ለምን አቃተህ ? ለምን ከ አፋቸው ነጥቀህ ለማጣጣል ትጣደፋለህ ? እኔ ቡና አቅራቢ ነኝ የሚመቸኝን የምመርጠው እኔ ነኝ ! ሁሉም አማራጭ ለምን ክፍት አልተደረገም ? የፈለገ ወደ ቡናና ሻይ ይሂድ የፈለገ ወደ ECX ይሂድ ! የኦሮሚያ ባለ ስልጣናት በሰፊው ቡናና ሻይ ውስጥ እጃቸውን ከተዋል ያለ ጥርጥር ! በ ECX ቡና እንዳይገበያይ መመርያ ከቡናና ሻይ ተሰቷል ( ከመንግስት ማለት ነው ) ያለው አማራጭ ታች ወርዶ የቡና አቅራቢዎችንና ነጋዴዎችን ሰብስቦ የሚፈልገውን አማራጭ እንዲጠቀም መፍቀድ ነው !!
@oromoohits4921
@oromoohits4921 28 күн бұрын
Shout out for lati trading
@Hkim185
@Hkim185 27 күн бұрын
መጀመርያ ቡናችንን የጥራት ደረጃ ካወቅን የእኛ ቡና አንደኛ ደረጃ ቡና ነዉ። ነገር-ግን አኛ ብቻ አይደለንም የራሳችንን ቡና የማንጠጣዉ አሜሪካኖችም አወሮፓዎችም ወዘተ በአጠቃላይ ዓለማት በሚባል ደረጃ የኢትዬጵያን 1ኛ ደረጃ ንፁ ቡና አይጠጡም ። ለምን ብትሉ? የኛ አንደኛ ደረጃ ቡና እንደቅመም የሚጨምሩበት እንጂ ንፁሁን ቆልተዉ አይሸጡትም። እሰከ ቅርብ ግዜ ድረሰ። ይሄን የሚቀይር ጉድ መጣባቸዉ የካናዳ ቡና Brand እንዴት መሰላቹህ እንዳልኳቹህ የኛን ቡና ንፁሁን አይቆሉትም። እንደቅመም ከብራዚልና ከቬትናም ቡና ጋራ ተደባልቆ ነዉ ለጠዕም ማጣፈጫ ትንሸዬ ነዉ የሚጨምሩበት። የሌሎቹን መራራ ቃና አሰተካክለዉበት ነዉ የሚሸጡት እንጂ 100% ንፁ የኢትዬጵንን ቡና አይሸጡም ትንሸዬ ታሪክ ልንገራቹህ ከጥቂት አሰር አመታት በፊት የአሜሪካ coffee brands እንደ Dunkin Donuts, Starbucks and McDonald's ቡና ቤቶች በካናዳ ዉሰጥ በጣም እንደአሸንዳ ፈልተዉ ነበር። ታድያ አንድ ቀን Tim Hortons የተባለ ትንሸዬ የካናዳ Brand ቡና ቤት አንድ ትልቅ የቡና ሚሰጥር ይዞ መጣ። ልብ በሉኝ McDonald's እና Starbucks የብራዚሉን Robusta....ቡና ነበር የሚጠቀሙት TIM ቡና ግን የአረቢካ ቡና ነበር የሚያፈሉትና የሚሸጡት ። ታድያ የቡና አፍቃሪዎች ተገልብጠዉ ወደ Tim Hortons ይሄዳሉ። ብዙ የአሜሪካ ብራንድ ቡና ቤቶች መንገዳገድ ጃመሩ። 98.7% የሚሆኑ የቡና ቤት ባለቤቶች ፤ቡና ቤታቸዉን ዘግተዉ ከካናዳ ወጡና ሄዱ። የቀረት ሁለቱ በጣም ትላልቆቹ ነበሩ። እነሱም መንገዳገድ ጀመሩ Starbucks ብዙ ሱቆችን መዝጋት ጀመረ McDonald's ቡናዉን በነፃ መሰጠት ጀመረ ከዝያ ሁለቱንም የአሜሪካ ቡና ብራንድ ትንፋሳቸዉን የሚሰበሰቡበት ግዜ አገኙ.. ይህም Tim Hortons ትልቅ ሰህተት ሰራ። ያለአቅማቸዉ ብዙ ቡና ቤቶችን ከፍተዉ የቡና ጥራታቸዉ እየወረደ መጣ። የዛን ግዜ McDonald's በ100% fine Arabica beans ነዉ አወል ቡና ነዉ የምናፈላዉ የሚል መፈክር አወጥተዉ እንደገና ያጧቸዉን ደንበኞች ማግኘት ጀመሩ። ግን በጣም የሚገርመዉ McDonald's ከእኛ ቡና አይገዙም ግን ገበያቸዉን መልሰዉ ያዙት ቡናቸዉ መጣፈጥ ጀምረ ብዙ ሰዉ ከድቶም ቢቀር ብዙ ሰዉ መመለሰ ቻሉ Starbucksም አረቢካ ቡና ከምሰራቅ አፍሪቃ ኢትዬጵያንንም ጨምሮ ቡናቸዉን መግዛት ጀመሩ። Starbucks የቄንጠኞች ቡና ቤት ነዉ በጣምም ዉድ ናቸዉ። እላቹሀለሁኝ Starbucksም ከሞት አፋፍ ላይ ነዉ የተነሳዉ። እንግዲህ ወደ ነጥቤ ሰመጣ ቡናችን በጠዕሙ በፍፁም ወደር የማይገኝለት ሰለሆነ። ከማንም ጋራ ተወዳደሮ ማሸነፍ እንደምንችል ልነግራቹሁ ነዉ። መጀመርያ ግን ለምን የእኛ ቡና አረቢካ ተባለ፤ እንግዲህ አረቦች ሰለሆኑ ለነጮች ያሰተዋወቁት ቡና ከአረባች የመጣ ሰለመሰላቸዉ ነበር። ሲቀጥል የኛ ቡና ምን ብናረግ ነዉ ምርቱ የሚጨምረዉ በመጀመርያ ደረጃ ለቡናዉ ዛፍ ጥላ ይፈልጋል ጥላ ከሚሰጡት ዛፎች ሰር ሆኖ ማደግ ይፈልጋል ይህ ሲሆን ብዙ አሲዳማነትና ካፊን ሰለማይኖረዉ ጣፋጭነቱን ይጨምረለታል ሲቀጥል ማዳበርያ ይፈልጋል ይህ ደግሞ የተፈጥሮ ማዳበርያ መሆን አለበት አንደኛ ደረጃ ቡና መሸጥ ከፈለግን እንደተባለዉ ቡናን በብዛት በመሸጥ ብራዚልን ካልደረሰንባት፤ በጥራት ከነሱ ለመወዳደር ጥራታችንን ከፍ ማረግ አለብን
@Hkim185
@Hkim185 27 күн бұрын
ክፍል ሁለት ሲቀጥል የቡናችንን ጥራት ለመጠበቅ በሰዉ እጅ ቡናችንን መለቀም አለበት። በማሸን ከሆነ ሁሉንም ቡና የደረሰወንም ያልደረሰዉንም ሰለሚሸመጥጥ ጥራት ላይ ጉዳት ያመጣል የቡናም ብክነት ያመጣል ሰለዚህ ጥራቱ የተጠበቀ ቡና ለመልቀም በሰዉ እጅ መለቀም አለባቸዉ ለቃሚዎች ቀዩን የበሰለዉን ቡና ብቻ መርጠዉ ይለቅማሉ ከዛም በየሁለት ሳምንቱ በድጋሚ ይለቀማል ይህ ማለት ብዙዉን ወራቶች መለቀም ይችላሉ የቡና ፍሬ አንድላይ ፍሬ አያፈራም ወይም አይበሰልም ። ይህንን ችግር ለመታደግ የቡናዉ አበባዉን በንፋሰ ከሚዳቀል በንብ ብናዳቅለዉ ንቧ አንዲትም አበባ ሰለማትሰት ሁሉንም አበባ በአንድ ቀን ዉሰጥ ታዳቅላለች። በንብ የተዳቀለ ቡና አበባ ደግሞ ወደ 25% የምርት መጨመር ያሳያል ከዘህ ላይ ደግሞ ገበሬዉ ከንብ ማር ተጨማሪ ገቢ ያገኛል። ገበሬዉ በሔከታር ምርቱ አነሰተኛ ሰለሆነ ቡናችንን ያሰወድድብናል ለተባለዉ ደግሞ መላዉ ብዙ ነዉ አንደኛዉና የመጀመርያዉ መላ ከ30 ዓመት በላይ የሆናቸዉን ዛፎች ነቅሎ በአድሰ የቡና ችግኝ መተካት ነዉ። ገበሬዉ አንድ ሔክታር ካላዉ ሩቡን ሔክታር ነቅሎ ተከላ ይደረጋል ይህ እንገዲህ ከ3-5ዓመት ሰለሚፈጅ ያጣነዉን የቡና ገቢ Potatoes, kale, beans. Ginger. Spinach, carrots, eggplants, spinach, eggplants ከቡና ችግኝ ጋራ በመትከል መጠቀም እንችላለን እነዚህ ዝርያዎች ከቡና ጋራ ይሄዳሉ አንዱ ለአንዱ ግብሀት የሚሆን በንጥረ-ነገር ደረጃ ይቀያየራሉ ሲቀጥል በፍፁም የኬሚካል መርዛማ ማዳበርያ መጠቀም የለብንም እኛ የሚያሳሰበን መሬታችንን ጨዋማ ማረጉን ነዉ። ግን ከዚያ በላይ አደጋ አለዉ ነጮች ከኛ ቡና ወሰደዉ ብራዚል ቢተክሉ ወዘተ የኛ ቡና ኮፒ ማረግ የማይችሉት። ለምን እንደሆነ ታቃላቹህ? ለምሳሌ ጤፍን እንወሰድ አንድ ኤርትራዊ ቡናችንን ደብቆ በደርግ ዘመን እንዳወጣዉ እሱ ራሱ ጤፋችን ስርቆ ማወጣቱን አምኖ በራሱ ላይ ምሰክርና ሰጥቷል። ተሰረቀ መሰረቀ የማይችለዉ አፈራችን ነዉ ። ግን የፈለገ ሰዉ ጤፋችንን ይሰረቅ የጤፋችንን ጠዕም ኮፒ ማረግ አይችሉም። ለምን መሰላቹህ አፈራችን ዉሰጥ በቢሊዬን የሚቆጠሩ ማክሮቦች አሉ እነዚህ ማይክሮቦች በቡና ዛፍ ሥር ላይ ቤት ሰርተዉ እነሱ ለራሳቸዉ ናይትሮጂንን ከታትፈዉ ሲበሉ ሰሩ ደግሞ ከነሱ ያሰወገዱትን ናይትሮጂን ይመገባሉ ገባቹሁ ናትሮጂኑን እንዳለ አይመገቡም ሰለዚህ እነዚህ ማይክሮቦች በጣም አሰፈላጊ ናቸዉ ሰለዚህ የኬሚካል መርዘኛ ማዳበርያ ሰንጠቀም እነዚህን ባክቴሪያዎቹን እንገድላቸዋለን። አንዴ ከሞቱ ተመልሰዉ አይመጡም እነዚህ ባክቴሪያዎች ከሰፈር ሰፈር ልዩነት አላቸዉ ሰለዚህ ነዉ በየቀበሌዉ የተለያየ ጣዕም ያለዉ በና ያለን እነዚህ ባክቴሪያዎችና የአፈሩን ደህንነት ለመጠበቅ በፍፁም ኬሚካል ማዳበርያ መጠቀም የለብንም ይህ የምነግራቹህ ነገር በጣም በአጭሩ ነዉ የቡና ሹሙ በሔክታር የምናገኘዉ የቡና መጠን በጣም አነሰተኛ ነዉ ብሎናል መፍትሄዉ ለምርት ብዛት ቡናችንን መከተብ (Grafting) አለብን። ይህን በምሳሌ ለማሰረዳት የብርቱካን ችግኝ ብንተክል ብርቱካን ሰሮቹ አቅማቸዉ ንጥረ-ነገር ለመሳብ አነሰተኛ ሰለሆነ የሎሚ ችግኝ ደግሞ ሰሮቹ በጣም አቅም ያላቸዉ ናቸዉ ግን እኛ ሎሚ አንፈልግም የምንፈልገዉ ብርቱካን ነዉ። ግን የሎሚን ጠቃሚ ጎኑን ለመወሰድ እንፈልጋለን። ለዚህ የሎሚ ችግኝ ሰር የያዘዉን መርጠን የብርቱካን ቅርንጫፍ ወሰደን ሎሚወን በ grafting አንድ እናረጋቸዋለን ። ከወገብ በታች ሎሚ ከወገብ በላይ ብርተካን ማለት ነዉ እንግዲህ ጥያቂዉ ለቡናችን ማን ከወገብ በታች ችግኝ ይሁን፤ የትኛዉ የቡና ዘር ከአረቢካ ቡና ጋራ ቅርበት ኖሮት በሸታም ተቋቁሞ፤ ቅዝቃዜም ተቋቁሞ ጥሩ ምርት የሚሰጥ የሚለዉን ጥያቄ መልሱነ በሚቀጥለዉ ግዜ እነግራቹሀለሀኝ። አሁን ለምን ብራዚል አንደኛ ቬትናም ሁለተኛ አምራች ሆኑ የሚለዉን ለመመለሰ ወደ ደርግ ዘመን መሄድ አለብን ደርግና ቬትናም ኮሚኒሰቶች ሰለነበሩ ቅርበት ነበራቸዉና የቡና ምርታቸዉ በጦርነቱ ምክንያት ተቀዛቅዞ ሰለነበረ ። መንጌን እርዳታ ይጠይቁታል። መንጌም ሐይሌ ያፈራቸወ የቡና ኤክሰፕርቶች ወደ ቬትናም ላከቸዉ ። ነገር-ግን የኤክፕርት ጉዳይ ብቻ አነበረም የቬትናሞች በአለም ሁለተኛ አምራች ያረጋት የራሳቸዉ ቆራጥነት ነዉ ነገሩን የቀየረዉ። የዛሬ 30 ዓመት በፊት የቬትናም የእርሰ በእርሰ ጦርነቷ ሲያበቃና ወያኔዎች ሲገቡ አዲሳበባ አንድ ነበር። ቬትናሞች ሰላም ሰላገኙ እኛንም በኢኮኖሚ ጥለዉን ሄዱ። ይህ የሆነዉ ተሰብሰበዉ መከሩ እንዴት ቬትናምን እንዴት ከድህነት ምን አርገን እናወጣት ብለዉ ሲማከሩ። ቡና ላይ ቢሰሩ ከድህነት የመዉጫ ትኬታቸዉ መሆኑን ተረዱ። ከዝያ ቡናቸዉ ላይ በቂጢ ቁጢ ሳይሆን በብዛት ችግኙን መትከል ጀመሩ። ሲቀጥል በመሰመር መትከል የጠብታ መሰኖ መጠቀም ወዘተ ግዜዉ የደረሰበትን ቴክኖለጂ በሙሉ ተጠቅመዉ አገረቸዉን ከድህነት አወጡ እንግዲህ ቬትናዎች ቡና እንደኛ አይጠጡም ግን ኢኮነኖሚያቸዉ ምንጭ መሆኑን አወቀዉ ሰሩበትና ከዋላ መጥተዉ ዛሬ ከብራዜል ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ይቀመጣሉ። እንግዲህ ቬትናም የሚልኩት ጠዕሙ ማራራ ቡና ሰለሆነ እኛ በርተተን ከሰራን የማንደርሰባቸዉ ምክንያት አይታየኝም እንግዲህ ብዙ የምናዘምናቸወ ነገሮች አለ እሱን በክፍል ሶሰት እመለሰበታለሁኝ አንድ ላይክ ካገኘሁኝ
@antenehtesfaye2487
@antenehtesfaye2487 27 күн бұрын
​@@Hkim185❤
@Hkim185
@Hkim185 26 күн бұрын
​@@antenehtesfaye2487 አንድ like ሰላገኘሁኝ ክፍል ሶሰትን አቅርቤያለሁ ሰለቡና ካዉራቹሁት ለማሰታዉሰዉ ጥያቄዎች( ነጥቦች) መልሰ እሰጣለሁ 1. ገበሬዉ የቡና ዋጋም ቢወጣም ኑሮዉ አልተሻሻለም መ, ገበሬዉ ያረጁ የቡና ተክሎቹን ቢገርዛቸዉ በትንሹ በእጥፍ ማምረት ይጨምራል። ሌላ ምንም ነገር ሳይጨምር በPruning ብቻ አንድ የቡና ዛፍ አንድ ኪሎ ያለPruning ሲሰጥ የነበረዉን ዛፍ ፤በPruning ሲደረግ በትንሹ ሁለት ኪሎ ምርት ይሰጣል 2. ምንድነዉ Pruning? መልሰ A.ግርዛት የሞተ ፤ሊሞት ያለ፤ የደረቀ፤ በበሸታ የተጠቃ ወይ ደግሞ ጉዳት የደረሰበትን ቅርጫፍ መቁረጥ ማለት ነዉ B. የቡና ዛፉ ከአንድ ሜትር ከግማሸ እንዳይበልጥ ከላይ መቁረጥና ማሳጠር ድንክዬ ማረግ C. አላሰፈላጊ ቅርንጫፎች ( sucker )በሙሉ መቁረጥ ለምሳሌ በአንድ ቅርነጮፍ ላይ ሌላ ቅርንጫፍ ከበቀለ መቁረጥ D. ግርዛት በወይን ላይ ሰለሚደረግ ከዛ የሰለጠኑ ሰዎችን ማምጣት ይጠቅማል 3.ገበሬዎች በዓመት ሶሰት ወር ብቻ ቡና ምርት በዓመት አግኝተዉ አመቱን ሙሉ መኖር አይችሉም መ, መፍትሄዉ አንድ የቡና ተክል በሁለት ሜትር ተራርቆ ሰለሚተከል በመሃሉ የቡና ጎደኞች companion plants በመትከል ናትሮጂን ለቡናዉ ተክል ይሰጣሉ Potatoes, Kale,Soybeans,Groundnuts እና Beans.nitrogen fixing companions እንደ ሹንቡራ ባቄላ ወዘተ 4. ለምን አረቢካ የሀገራችን ቡና ዉድ ሆነ? መ, መልሱ ብዙዉን ተመልሶዋል በአለም ደረጃ አረቢካን ለማምረት ብዙ አሰቸጋሪ ነዉ ፤ አንደኛ ጥላ ይፈልጋል ቀጥታ ፀሐይ አይወድም ሙቀትም ሲበዛበትም ሲያንሰበት አይወደም ። ብራዚል ዉሰጥ በቅዝቃዜ ሲመቱ ብዙ አረቢካ ቡናቸዉ ሰለሚወድም ነዉ የኛ ቡና የሚወደደዉ። ሌላዉ ደግሞ አረቢካ ቡና በበሸታ ይጠቃል Mealybugs በሸታ በ neem oil ይጠፋል Aphids ደግሞ ማር ሰለሚጥሉ ሐይለኛ ጉንዳኖች መጥተዉ ለAphids ዘብ ይቆማሉ ቡና ለቋሚዎችን በሙሉ ሰለሚበሉ ጉንዳን አለ ማለት Aphids ነዉ ታድያ ጉንዳኖቹን የሚያባርር መድሀኒት ከአታክልት የቀመመ ኢትዬጰያዊ የሆነ የፈጠራ ሰዉ ነበረ አሁን የሱ ፈጠራ ጉንዳኖቹን ብቻ የሚያባርር ከሆነ Aphids ዎቹን በሐይለኛ ዉሃ በመርጨት ከቅጠሉ ላይ ማሰወገድ ይቻላል እና neem oil በአማርኛ አላቀዉም እሱን መቀባት ነዉ በተቀረ በበሸታ የተጠቁትን ቅርንጫፎች መቁረጥ ወድያዉ ባለበት በቦታ ማቃጠል ነዉ በሸታዉ እንዳይራባ 5. መሬት የለንም እንዴት ያሉንን እንከባከብ? መ. የእበት ፍግ ባዬጋዙ የወጣለትን እንደማዳበርያ መጠቀም የቡናንም ገለባ አንደርብርብ የዛፉን ዙርያ በገለባ መሸፈን ቡና ዛፍ ዉሃም ቢወድም መጥለቅለቅን ሰለማይወድ ከመሬት ከፍ ተደርጎ መደብ ቢሰራለት ጥሩ ዉጤት እናገኛለን 6.ገበሬ ምን ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ይችላል? መ, ይህ የኔ አሳብ ነዉ ብዙ ሰዎች ቡናችንን ጠጥተዉ ሀገር ዉሰጥ ሰለሚጨሩሱት ደላር ለማግኘት አልቻልንም ሰለዚህ ሁሉ ሰዉ በየቤቱ የቡና ዛፍ ቢተክል በአምሰት አመት ዉሰጥ የራሱን ቡና በራሱ ቡና ዛፍ መሸፈን ከቻለ ቡና ችግኞች ገበሬዉ አፍልቶ ጥሬ ቡና ሳይሆን የቡና ችግኝ እየሸጠ መጠቀም ይችላል ከተሜዎችም በሙሉ ቡና ዛፍ መትከል ሲጀምሩ የችግኝ ገበያ ይጦፋል 7. ገበሬዉ ከአመረተ በኃላ የሚባክነዉ ቡናሰ መ, በትግሬዎቹ ግዜ አንድ የቡና ኤክሰቨርት ያመጡና እሰቲ ችግራችንን ንገረን ይሉታል እሺ ብሎ ገጠር ሄዶ ችግሩን ካጠና በኃላ እናንተ ምንም ችግር የለባቹሁም ቡናቹሁን በመሬት ላይ ሰታሰጡ የአፈሩን ለዛ ይዉሰዳል ሰለዚህ በአልጋ ላይ አሰጡ ብሎ አንደ ሚሊዬን ደላር??? ተቀብሎ ሄደ የሚባል አሜታ ነበር። አዎ ቡና እርጥበትም ሸታም መሳብ ሰለሚችል በአህያ ቡናችንን የምንጭን ከሆነም ሸታዉን ይሰባል ሰለዚህ አደራረቁ ላይ ትልቅ ቁጥጥር ማረግ አለብን ቡናዉ ሲለቀም የበሰለዉ ብቻ መለቀም አለበት ለዚህም ከለቃሚዎቹ ሰንረከብ በCoffee Color Sorter Machine ለቅመን ለበሰለ ቡና ከፍተኛ ዋጋ ከከፈልን ለቃሚዎቹ ቡናዉን ከመሸምጠጥ የበሰለዉን ብቻ ይለቅማሉ ማለት ነዉ የበሰለዉን ብቻ ለመልቀም ብዙ ግዜ ይወሰዳልና አንዴ ቡናዉ ከጅምሪ ጥራቱን ካልጠበቀ ሌላዉ ድካማችን ከንቱ ነዉ 8.ዋጋ ዉጣ ዉረድ ለመቋቋም መፍትሄ ምንድነዉ? መ, ብዙ መንገድ ቢኖርም ዘመናዊ ጎተራ ወሳኝነት አለዉ, ገበሬዉ ቤቱ ቡናዉን ከሚያሰቀምጥ አንድቦታ ላይ በጎተራ ቢያሰገባ እና በፈለገበት ሰዓት ቡናዉን ቢሸጥ ለሱ ግን የሚኖርበትን ገንዘብ ከራሱ ተበድሮ ይበላል። ዋጋዉ ሲወጣ ግን ሸጦ ብድሩንም ይከፍልና ትርፉን ኪሱ ያሰገባል ይህንን ጎተራ አሰራሩን ተመልከት $3000 ደላር ነዉ ዋጋዉ, በሀገራችንም በባህላዊ መንገድ ጎተራችንን ማዘመን እንችላለን ይህ ጎተራ እወን የሚሆነዉ የወረዳዉ እና የክልሉ አሰተዳደር የሁሉንም ቡና ገዝቶ በአንድ ላይ በክልሉና በወረዳዉ ሰም በመሸጥ ቀጥታ ከገበሬዉ ማሳ መላክ ይችላል ቡናን በኩታ ገጠም ፕሮሰሰ በማረግ አዲሰ አበባ ከመላክ በቀጥታ ወደ ወደብ መላክ kzfaq.info/get/bejne/r91yiZl-nLyzdok.html በቪደዬ ላይ እንደምታዩት ቡናችንን ማዘመን የምንችለዉ 2000 ውይ 50,000 ተባብረዉ አንድ ጎተራ ዉሰጥ ቡናቸዉን ቢጨምሩና ዉድያዉ ገንዘባቸዉ ተከፍሎ ቡናቸዉ ፕሮሰሰ እዛዉ ቢደረግ ቀጥታ ከሲዳማ ወደ ጅቡቲ ቢላክ ገበሬዉ ተጠቃሚ ይሆናል ብዬ እገምታለሁኝ ።ገበሬዉ ጎተራ ዉሰጥ ሲያሰገባ የአመት የሚኖርበትን ብቻ ይከፈለዋል ሰለዚህ ቡናዉ ፕሮሰሰ ሆኖ እሰከሚላክ ጠብቆ እጥፍ ትርፍ ያገኛል ይህ የሚሆነዉ 50,900 ገበሬዎች መታገሰ ሲችሉ ብቻ ነዉ ። ቡና coffee exporters ሮችም ከገበሬዉ ጋራ ሸርክና ገብተዉ ተጠቃሚ መሆን ይችችላል ለምን አንድ ገበሬ በግሉ አምሰት ጆንያ ከመላክ በሕብረት መላክ ያዋጣል የሚለዉን በቁጥር 9 እመልሰዋለሁኝ 9, Branding and Marketing ለምሳሌ ሲዳማ ዉሰጥ 50,000 ገበሬዎች እያንዳንዳቸዉ በሰማቸዉ ከሚሊኩ በአንድ ላይ በሲዳማ ቡና Branding ሰም ቢሸጡ ትልቅ ጥቅም ያገኛሉ Marketing ለመሰራት ይቀላል አይ እኛ ኩታዉ የታወቀ ቡና ነዉ መሸጥ ከተባለም ይቻላል በአንድ Brand ሰም ሰር በሲዳሞ ቡና ሰር የግለሰቡን የ50,000 ገበሬ ሰም መፃፍ ይቻላል ለምሳሌ Dove ሳሙና brand አለ ግን ብዙ ዓይነት ሳሙናዎች ያመርታል ሁሉም Dove ሰለሚሉ በምርቱ እንተማመናለን ማለት ነዉ የዉጭ ሐገር ተቀባዬችማ እያንዳንዱ ገበሬ በግሉ እንዲልኩ ነዉ የሚፈልጉት ለምን ሁሌ ጥሬ ቡና አቅራቢ ሆነን እንድንቀር ሰለሚፈልጉ ይመሰለኛል እኛ ቆልተን ፈጭተን መላክ ከፈለግን በሕብረት መላክ ያዋጣናል State of the art technology ለመጠቀም ከፈለግን በጣም ትልቅ መሆን አለብን የተሻሻሉ ማሸነሪዎች ለመግዛትና የዉጮ የሚጠቀሙበትን ቴክኖለጂ ለመጠቀም ከፈለግን አንድ ላይ ሆነን መሰራት አለብን 10, አንድ like ካገኘሁኝ ሁለተኛ አራትን አጫዉታቹሀለሁ እንዴት መንጌ ቡና ቀማሸዎች ፈረንጅ ብቻ ይሆናሉ ብሎ እንዳበራቸዉና ምን ጉድ እንደሆነ
Countries Treat the Heart of Palestine #countryballs
00:13
CountryZ
Рет қаралды 21 МЛН
Cute Barbie Gadget 🥰 #gadgets
01:00
FLIP FLOP Hacks
Рет қаралды 42 МЛН
Универ. 13 лет спустя - ВСЕ СЕРИИ ПОДРЯД
9:07:11
Комедии 2023
Рет қаралды 3,1 МЛН
Countries Treat the Heart of Palestine #countryballs
00:13
CountryZ
Рет қаралды 21 МЛН