የደም ግፊት ምልክቶች ምን ምን ናቸው

  Рет қаралды 770

Birabiro ቢራቢሮ

Birabiro ቢራቢሮ

Жыл бұрын

(ደም ግፊት ምንድን ነው ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ምልክቶች ምን ምን ናቸው፣ ለደም ግፊት አጋላጭ የሆኑ ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው፣ የደም ግፊት የሚጨምሩ ምግቦች፣ የደም ግፊት መ
ከላከያ መንገዶች የደም ግፊት ምልክቶች ምን ምን ናቸው#የደም ግፊት መጠን በምን ይወሰናል.....
#የደም ግፊት ምንድን ነው
የደም ግፊት ደም በሚረጭበት ጊዜ በደም ስሮች ግድግዳ ላይ የሚፈጠረው ግፊት ያለማቋረጥ ከፍተኛ መሆን ነው
በአለም ላይ ከ1.28 ቢልየን የሚበልጡ እድሜያቸው ከ30-79 የሆኑ ሰዎች የደም ግፊት በሽታ እንዳለባቸው ይገመታል
2/3 የሚሆኑት መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው 42% የሚሆኑት ብቻ ህክምና ይከታተላሉ
ደም ግፊት በአለም ላይ ለሚፈጠረው ያለእድሜ መሞት ዋናው ምክንያት ነው
የደም ግፊት መጠን በ2 ቁጥሮች ይገለፃል.
የላይኛው systolic blood pressure የሚለካው ልብ ደም በምትረጭበት ጊዜ በደም ቧንቧዎቹ ግድግዳዎች ላይ የሚፈጠረውን ግፊት ሲሆን የታችኛው diastolic blood pressure ደግሞ
ልብ ደም ረጭታ በመሀል በሚኖረው ረፍት ነው
የደም ግፊት ምልክቶች ምን ምን ናቸው
የጤና ባለሙያዎች የደም ግፊት በሽታን አድብቶ ገዳይ
"silent killer" ብለው ይጠሩታል ምክንያቱም ብዙ ሰዎች ደም ግፊት ኖሮባቸው ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳያዩ ለብዙ አመታት ሊቆዩና ሊጎዳቸው ስለሚችል ነው
ችግሩ የሚታወቀው በደም ግፊት መጠን ምርመራ ብቻ ነው
እንደ አለም የጤና ድርጅት WHO 46% የሚሆኑት ሰዎች የደም ግፊት እንዳለባቸው እንኳን አያውቁም
ደም ግፊት መጠን ስንት ሲሆን ነው በሽታ የሚሆነው?
እንደምትኖሩበት ቦታ ትንሽ ይለያያል
በ U.S. የላይኛው 130 mmHg, የታችኛው ደግሞ 80 mmHg.
በአውሮፓ:
የላይኛው 140 mmHg, የታችኛው ደግሞ 90 mmHg.
በቤታችሁ የደም ግፊት መለኪያ መሳሪያን በመጠቀም የራሳችሁን የደም ግፊት መጠን መለካት ትችላላችሁ
የደም ግፊት በሽታ አለብዎት ብሎ ለመደምደም ቢያንስ በ2 የተለያዩ ቀናት የግፊት ምርመራ ተደርጎ በ2ቱም ቀናት የደም ግፊት መጠን
≥140/90 እና ከዚ በላይ መሆን አለበት
የደም ግፊት መጠን 140/90 mmHg or higher). የተለመደ ቢሆንም ክትትል ካልተደረገበት ግን ችግር ያስከትላል
ለደም ግፊት አጋላጭ የሆኑ ምክንያቶች
ተመራማሪዎች እንደሚያምኑት ከቅርብ ቤተሰባችሁ ደም ግፊት ያለበት ሰው መኖር ማለትም ዘረመል እናንተም ለደም ግፊት ተጋላጭ እንድትሆኑ ያደርጋል፣ ጥቁር መሆን Being Black
እድሜ ከ55 አመት በላይና ስኳር በሽታ ወይም ኩላሊት ህመም መኖር፣የልብ ችግሮች፣ የታይሮይድ ህመም፣ የእንቅልፍ ችግር፣
ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ (ጨው የበዛባቸው ምግቦች መመገብ, saturated እና trans fats ያላቸው ምግቦች መብላት;
ፍራፍሬና አትክልትን በበቂ መጠን አለመመገብ, በቂ እንቅስቃሴ አለመኖር, ሲጋራ ማጨስ አልኮል መጠጥ መጠጣት, ቅጥ ያጣ ውፍረት
በአፍ የሚዋጡ የእርግዝና መከላከያ መድሀኒቶች፣ የእንቅልፍ ችግር Obstructive sleep apnea፣
ለመዝናናት ተብለው የሚወሰዱ እፆች (including amphetamines እና ኮኬይን). የኩላሊት መድከም፣ ጭስ አልባ ትምባሆን ጨምሮ ሲጋራና የመሳሰሉትን ማጨስ
እነዚህ ለደም ግፊት በሽታ አጋላጭ ምክንያቶች ናቸው
የደም ግፊት ከፍተኛ ሲሆን ደም ግፊት ምልክቶች
ከባድ ራስምታት, የደረት ህመም; ራስ ማዞር: ለመተንፈስ መቸገር; ማቅለሽለሽ ማስመለስ ብዥ ያለ እይታ anxiety ግራ መጋባት፣ ጆሮ መጮህ፣ ነስር የተዛባ የልብ ምት
የደም ግፊት በሽታ ክትትል ካልተደረገበት ልብ ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል;. የበዛ ግፊት በደም ስሮች ላይ መከሰት የደም ስሮቹን በማጠጠር ወደልብ የሚሄደውን ደምና ኦክስጅን ይቀንሳል
ለልብ የሚደርሰው ደም ለረጅም ደቂቃዎች ከተዘጋ የልብ ጡንቻዎች በኦክስጅን እጥረት ምክንያት ይሞታሉ ልብም ከባድ ጉዳት ስለሚደርስባት ልብ ድካም ይፈጠራል
heart failure, which occurs when the heart cannot pump enough blood and oxygen to other vital body organs; ድንገተኛ ሞት የሚያስከትል የተቆራረጠ የልብ ምት
ደም ግፊት የደም ቧንቧዎች እንዲፈነዱ ያደርጋል ደምና ኦክስጅንም ወደአንጎል እንዳይደርስ ስለሚያደርግ ለስትሮክ ያጋልጣል እንዲሁም ለኩላሊት ህመምና ስራ ማቆም ያደርሳል
የደም ግፊት የሚጨምሩ ምግቦች
ጨዋማ ምግቦችን መመገብ፣ high in saturated or trans fats
(ሶሴጅ፣በርገር፣ ኩኪሶች፣ ኬክ፣ ቺዝ፣ የፓልም ዘይት) ፣የተጠበሱ ምግቦች፣ የበዛባቸው ምግቦች መመገብ፣ ፋስት ፉድ፣ የታሸጉ ምግቦች፣ ካፌይን ያላቸው መጠጦች ለምሳሌ ቡና፣ ሻይ፣ ለስላሳ መጠጦች፣energy drinks፣ አልኮል መጠጦች
የደም ግፊት መከላከያ መንገዶች
የአኗኗርና የአመጋገብ ስርአትን በመቀየር የደም ግፊት መጠንን ማስተካከል ይቻላል
ብዙ አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ. ብዙ አለመቀመጥ. መንቀሳቀስ physically active, ለምሳሌ በእግር መጓዝ, መሮጥ, መዋኘት, ጭፈራ ወይም ጥንካሬን የሚጨምሩ እንደ ክብደት ማንሳት አይነት ስፖርቶች በሳምንት 2 ቀን መስራት፣ ክብደትን መቀነስ በጣም ወፍራም ከሆኑ፣ የታዘዘላችሁን መድሀኒት በአግባቡ መውሰድ፣ የሀኪም ክትትል አለመዝለል፣ ጨው መቀነስ፣ ማጨስ ማቆም
ሌሎች ደግሞ በተጨማሪ መድሀኒት መውሰድ ያስፈልጋቸዋል
የደም ግፊት በሽታ ካለባችሁ በሃኪም 1 ወይም2 መድሀኒት ሊታዘዝላችሁ ይችላል
ለደም ግፊት አጋላጭ የሆኑ ምክንያቶች
Primary ደም ግፊት አንድና ግልፅ የሆነ ምክንያት የለውም ግን ብዙ ምክንያቶች ተጠቃሽ ይሆናሉ ተመራማሪዎች እንደሚያምኑት ከቅርብ ቤተሰባችሁ ደም ግፊት ያለበት ሰው መኖር ማለትም ዘረመል እናንተም ለደም ግፊት ተጋላጭ እንድትሆኑ ያደርጋል፣ጥቁር መሆን Being Black፣ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ
ማለትም (ከፍተኛ የሶዲየም መጠን ያላቸው ምግቦች መመገብ/ጨው የበዛባቸው ምግቦች) እድሜ ከ55 አመት በላይና
saturated እና trans fats ያላቸው ምግቦች መብላት; ፍራፍሬና አትክልትን በበቂ መጠን አለመመገብ በቂ እንቅስቃሴ የሌለው አኗኗር፣ ቅጥ ያጣ ውፍረት፣ አልኮል መጠጦች አብዝቶ መጠቀም ናቸው
Secondary ደም ግፊት አንድ ተጠቃሽ ምክንያት ይኖረዋል ለምሳሌ
መድሀኒቶች including immuno suppressants, በአፍ የሚዋጡ የእርግዝና መከላከያ መድሀኒቶች፣ የኩላሊት ህመም፣ የእንቅልፍ ችግር Obstructive sleep apnea፣ የታይሮይድ ህመም፣primary aldosteronism (Conn's syndrome) አድሬናል እጢዎች አልዶስቴሮን የተባለውን ሆርሞን ከመጠን በላይ እንዲያመርቱ በማድረግ ኩላሊት ፖታሲየምን ከሰውነት እንዲያስወግድ ያነቃቃሉ ለመዝናናት ተብለው የሚወሰዱ እፆች (including amphetamines እና ኮኬይን). የኩላሊት መድከም፣ስኳር በሽታ መኖር፣የልብ ችግሮች፣ ጭስ አልባ ትምባሆን ጨምሮ ሲጋራና የመሳሰሉትን ማጨስ
እነዚህ ለደም ግፊት በሽታ አጋላጭ ምክንያቶች ናቸው
የደም ግፊት ለምን ያክል ጊዜ ይቆያል/አይድንም?
secondary የሚባለው አይነት ደም ግፊት ካለባችሁ ከህክምና በኋላ ወይም ግፊቱ እንዲጨምር ምክንያት የሆነው ህመም ሲታከም ደም ግፊቱ ይቀንሳል በመድሃኒት ምክንያት ከተከሰተም መድሀኒቱ ሲቀየር ችግሩ ይወገዳል
primary የሚባለው አይነት ደም ግፊት ካለባችሁ ህይወታችሁን ሙሉ አብሯችሁ ይቆያል ማለትም አይድንም
በራሳችሁ ጊዜ መድሃኒቱን ለማቆም አትሞክሩ
እርጉዝ ከሆናችሁ ወይም የማርገዝ እቅድ ካላችሁ ደም ግፊት እና እርግዝና እንዴት መያዝ እንዳለበት ከሀኪም ጋ ተማከሩ

Пікірлер: 3
@lulitlula4290
@lulitlula4290 Жыл бұрын
ቢራቢሮዬ እንኮን ደህና መጣሽ እንደሁልግዜ በጣም ጠቃሚ ነው እናመሰግናለን🙏👍❤️❤️
@genetziguita4586
@genetziguita4586 Жыл бұрын
Amsgenalew yene konjo
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
ገኒዬ ውዴ
100❤️
00:19
MY💝No War🤝
Рет қаралды 24 МЛН
DAD LEFT HIS OLD SOCKS ON THE COUCH…😱😂
00:24
JULI_PROETO
Рет қаралды 15 МЛН
Inside Out 2: Who is the strongest? Joy vs Envy vs Anger #shorts #animation
00:22
ПРОВЕРИЛ АРБУЗЫ #shorts
00:34
Паша Осадчий
Рет қаралды 6 МЛН
የአይን ግፊት በሽታ (ግላኮማ) ምንድን ነው?
5:03
Ethiopia | የከፍተኛ ደም ግፊት (Hypertension) ምልክቶች እና መድሃኒቶች
24:52
ፕሪሚየም - PREMIUM በ Dr. Abraham
Рет қаралды 36 М.
100❤️
00:19
MY💝No War🤝
Рет қаралды 24 МЛН