No video

ሰሚራ ከእስልምና ወድ ክርስትና ለምን መጣች? ምስክርነት

  Рет қаралды 40,507

እውነት ያሳርፋል Ewnet Yasarfal

እውነት ያሳርፋል Ewnet Yasarfal

Ай бұрын

የመሐመድ አበባውን የዩትዩብ ቻናል ለማኘት ይህንን ሊንክ/ማስፈንጠሪያ ተጫኑ
• የሰሚራ ሰኢድ መሐመድ ምስክርነት ...
መልካም ዜና
የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን።
ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡-
“በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።”
መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡-
“ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥...
እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15)
ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል።
ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”
- (ኢሳይያስ 53፥10)
ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና።
{የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29)
እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው።
1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል።
2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ።
የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇
/ @dhugaanniboqachiisa
አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇
t.me/BibleAndMe
Additional: - ewnetyasarfal123@gmail.com

Пікірлер: 594
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal Ай бұрын
🎯 አብራችሁኝ በገንዘባችሁ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆናችሁ ይህንን ሊንክ ተጫኑትና አናግሩኝ።👇 t.me/BibleAndMe
@user-rq2zx1yu3x
@user-rq2zx1yu3x Ай бұрын
በርቺ እግዚአብሔር ይርደሽ
@thionlema7724
@thionlema7724 18 күн бұрын
❤❤❤❤
@thionlema7724
@thionlema7724 18 күн бұрын
እየሱስ ጌታ ነው
@user-jn4cc3wn2j
@user-jn4cc3wn2j Ай бұрын
እግዚአብሔር ይባርክሽ እኔ ኢትዮጲያ እያለሁ 1983 ዓ/ም በተዘጋ ቤቴ ገብቶ እራሱን አስተዋውቆኝ እንዲሁ በተዘጋ በር ተሰወረ። እኔ አይሁድ ነኝ እስራኤል ሀገር ነው የምኖረው ።እኔ ክርስቶስ ነኝ አለኝ ስለዚ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ ባለሁበት ሀገር ለአይሁድ ህዝብ፣ እመሰክራለሁ ።ኢየሱስ ጌታ ነው፣ ኢየሱስ ከሞት መነሳቱን እኔ ምስክር ነኝ አሜን አሜን❤❤❤❤
@user-yt5gp3bq6x
@user-yt5gp3bq6x Ай бұрын
Ye esrail amlak yirdachu ehete Sala esrail 🇮🇱 intsaliy ebakachu
@Fezersolomon
@Fezersolomon Ай бұрын
እውነትክ ነው? ተገልጦልሃል?
@melber7957
@melber7957 Ай бұрын
Waaaaaaaaaw Tadelesh! Yezemenat senk setesh!
@melber7957
@melber7957 Ай бұрын
​@@Fezersolomonendeh Yale chewata yelem❌❌ Geta lehizbu ged yelewal
@salem4086
@salem4086 Ай бұрын
My dear sister I'm so happy to be welcome to family I'm so glad you accepted Jesus you keep going keep it up God with you don't be afraid to keep it up I'm so happy for you when is safety Jesus everybody hate me I keep in praying in a forest I keep in British gospel now all my family in Christ keep praying for your family your family member Jesus will answer you prayer this is great news I'm so so so so so so so happy Yemen birthday party in Ethiopia she's so lovely lovely testimony your future is bright honey he's with you I pray for you I pray for you I wish I know your phone number please let me know can you leave your phone number
@lemlemdebele318
@lemlemdebele318 Ай бұрын
እህቴ ሰሚራ የረዳሽ እግዚአብሔር ይመስገን አባቴ ብለሽ ልትጠሪው መንገድሽ ወደሚገባው አምላክ እንኩዋን ደህና መጣሽ! እየሱስ ጌታ ነው!!!
@noahbineyam6837
@noahbineyam6837 Ай бұрын
ከአዲስ ክርስትያን እንደዚህ አይነት መረዳት እጅግ ደስ ይላል God bless you sister
@danyakadir5131
@danyakadir5131 Ай бұрын
Auzbelhmenshetan erjem shetan Kanch gar seleneber ayetayeshm Telek setan(DABELOS)NESSH
@melakumolla2053
@melakumolla2053 Ай бұрын
እኔም የገረመኝ ማስተዋልዋ እና መረዳትዋ ከላይ እንዳለው coment አውዝቢላሂ የሚያሰኝ ሳይሆን ማሻ አላህ የሚያሰኝ ነው
@eleni311
@eleni311 29 күн бұрын
​@@danyakadir5131የሙሀመድን ቅጥፈት ሰትሰማ ነው ይሄን ማለት
@noorwaga4502
@noorwaga4502 Ай бұрын
የሚገርም ምስክርነት ሰሚራ እንኳን ጌታ ረዳሽ 🙌
@RuthHayile
@RuthHayile Ай бұрын
የሚያስቀና የሕይወት ምስክርነት ሰሚራ ጌታይባርክሽ ገብቶሾል ጥንኮሬሽ ይገርማል ፀጋ ይጨመርልሽ ያውርስሽ ህልውናው ይብዛልሽ 👏👏👏👏😂😂🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤️❤️❤️❤️❤️❤️🙏
@alemheaven
@alemheaven Ай бұрын
ሀሌሉያያያያያያያያ ኦኦኦኦ የኔ ውድ ጌታ አንተ እኮ ፍቅር ነህ በፍቅር ድምፅህ ትጠራናለህ ❤❤❤አነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ ማንም ደጁን ቢከፍት ወደእርሱ እገባለሁ
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal Ай бұрын
አሜን!!
@melakumolla2053
@melakumolla2053 Ай бұрын
በጣም የሚገርም ለውጥ ነው በጣም የሚገርም መረዳት ነው ጌታ የሰጣት እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ጸጋውን ያብዛልሽ እውነት በቃ ገብቶሻል በርቺ ኢየሱስ ብቻውን አዳኝ ነው
@mimib.5296
@mimib.5296 Ай бұрын
እግዚአብሔር ስለረዳሽ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል የረገጥሽውን ሁሉ ውረሺ !!! ሁላችሁም ሙስሊም እህትና ወንድሞች ጌታ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያግኛችሁ። በአብ ቀኝ ያለው በክብር ተመልሶ የሚመጣው እኛ የምንሰግድለት እና የምናመልከው እንዲሁም የምንጠብቀው ውዳችን ***መድሀኒታችን!!! የናዝሬቱ እየሱስ ክርስቶስ የጌቶች ሁሉ ጌታ ነው።
@sisaydeneke6214
@sisaydeneke6214 Ай бұрын
ከማንም ከምንም ጋር የማይወዳደር የማናስተያየው የማናመሳስለው እውነት ኢየሱስ ስሙ ይባረክ
@eleni311
@eleni311 29 күн бұрын
እውነት ነው አሜን ሀሌሉያ 🙏❤
@MohammedAli-cd9go
@MohammedAli-cd9go Ай бұрын
እህቴ ላንቺ ላንቺ የበራው የክርስቶስ ብርሃን እየፀለይን እያነባንላቸው ላሉ ዘመዶቻችን ይብራላቸው። አሜን! ተባረኪልን!
@mame8874
@mame8874 Ай бұрын
ሰሚራዬ እንኳን ጌታ ረዳሽ አንቺ ለብዙዎች መፍትሄ ነሽ ለቤተሰቦችሽ ለጉዋደኞችሽ ሁሉ ምስክር ነሽ ጌታ መርጦሻል
@user-jh8mg7vp5v
@user-jh8mg7vp5v Ай бұрын
እንኳን ጌታ ረዳሽ ታውቂያለሽ አባቴ ሙስሊም ነበር ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ዛሬ በሱ የተነሳ ስንት ቤተሰቦቻችን ነፃ እንደወጡ በዚህ በጣም ደስ ይለኛል አሁንም ጌታን ያላገኙ ቤተሰቦቻችን እንደት እየሆኑ እንዳሉ እናውቃለን እና ጌታ ገና ቤተሰብሽ ጋር ይደርሳል ነገ ፍሬሽን ታያለሽ ዘመንሽ ያለምልም
@berihuhayele1838
@berihuhayele1838 Ай бұрын
ደስ ዝብል ምስክርነት ጎይታ ጸግኡን ሰላሙን የብዝሓልኪ
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal Ай бұрын
ትግርኛ እንደዚ ገብቶኝ አያቅም😁🥰
@tigistgirma575
@tigistgirma575 Ай бұрын
I can tell that you have peace in your life by your voice .may our God Jesus Christ always give you peace my dear sis .you have no idea how much I am happy for you .
@user-vh9yj8yw2u
@user-vh9yj8yw2u Ай бұрын
እያለቀስኩ ነዉ የሰማሁት የራሴን ህይወት እያየሁ ስንፍናዬን እያየሁ ብዙ ሰዎች እየጠበቁን ይመስለኛል ነፃ መዉጣት የሚገባቸዉ እኔ ግን ለአንድም ሰዉ መስክሬ አላዉቅም ህይወቴም በጌታ እንደሆነ የሚመሰክር አይመስለኝም 😢😢😢😢😢😢😢 አባባባባባ
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal Ай бұрын
ምናልባት እየጸለይሽ ካልሆነ ጸልዪ፣ እግዚአብሔር ይረዳሻል። ያን ስታደርጊ የሚከብድሽ አለመመስከር ነው። የዳንሽበት መዳን ሲገባሽ ዝም ማለት አያስችልሽም። አይዞሽ በርቺ። መንፈስ ቅዱስ በውስጥሽ ባይኖር ይሄ ስሜት ባልተሰማሽና ባላለቀሽም ነበር። እና እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው።🥰
@user-wl7eh4po6j
@user-wl7eh4po6j Ай бұрын
ክብር ለኢየሱስ ይሁን እንኳን ጌታ እረዳሽ ኢየሱስ ጌታ ነው።🙏❤
@jo_cellular
@jo_cellular Ай бұрын
እግዚአብሔር ይባርክሽ ሰሚራ የሱስ ከድሆችና ምስኪኖች ጋር ነው ሁልጊዜ
@prada477
@prada477 Ай бұрын
“ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።”የዮሐንስ ወንጌል 14:27..... በእውነት አሀታችን ሰሚራ ተባረኪ ፀጋው ይብዛልሽ
@etefanoshabtemariam5353
@etefanoshabtemariam5353 Ай бұрын
የሚገርም ምስክርነት ነው እግ/ር ለዘላለም ዘመንሽን ይባርክ !!! ኢየሱስ ድንቅ ነው !!!
@tigimotigimo9572
@tigimotigimo9572 Ай бұрын
በጣም ደስ ይላል የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ገብቶሻል ጌታ ስለመረጠሽ ባቺላይ ብዙ ስራ ስላለው በርትተሽ ጌታን ታመኚ ጌታ ለታመኑት ታማኝነው ጌታ ይባርክሽ ሰይጣንን ስለካድሽ አለምን ስለተውሽ ሰይጣን ፈተናዎችን ወዳቺ ያመጣል አቺግን ፅኚ ባምላክሽ ተደገፌ ቃሉን በሙላት አብቢ የሰይጣንን ፈተና የምትቋቋሚው በዚነው
@user-hq1lp1gy4r
@user-hq1lp1gy4r Ай бұрын
እውነተኛ ወንጌልን ነው የተገለጠላት። በቤቱ ያፅናት ፀጋው ይብዛላት🎉🎉።
@MohammedAli-cd9go
@MohammedAli-cd9go Ай бұрын
ሰሚራ! ጌታ በደሙ ይሸፍንሽ። ለብዙዎች መዳን ምክንያት ያድርግሽ። ኢየሱስ ይመጣል! አሜን!
@user-wp9ol8fr5t
@user-wp9ol8fr5t Ай бұрын
እንኳን ወደ ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰላም ተቀላቀልሽ
@user-dg1dg6uf2w
@user-dg1dg6uf2w Ай бұрын
ስሚራ ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ እንኳንም ወደ እውነት ሕይወት መንገድ ወደ ሆነው ጌታ ኢየሱስ መጣሽ ። ተባረኪ❤❤❤
@RuthHayile
@RuthHayile Ай бұрын
ስለመሻገር ምሳሌ ግሩምነው መኞር ይሁንልኝ የክርስቶ ወንጊል ሰባኪ ተባረኪ ክብር ለኣየሱሰይሁን❤🎉🎉❤❤❤
@lemmafeye
@lemmafeye Ай бұрын
ሰሚራ ምስክርነትሽ በጣም ጡሩ ነው ። ጌታ ዘመንሽህን ይባርኬው በርች ትናንት የረዳሽ ጌታ ነጌም ይረዳሻል ክብር ከዘላአለም እስከ ዘለአለም ለእርሱ ይሁን ❤❤❤❤❤❤❤
@aiduf1334
@aiduf1334 Ай бұрын
በጌታ በኢየሱስ ስም ዘርሽን ውረሺ በብዙ ሃይል ፀጋ ተገለጪ
@ZenebechBelachew
@ZenebechBelachew Ай бұрын
ዘመንሽ ይባርክህሽ የህቴ ልጅ ሰሚራ የምትባል አለች እሷ የዳነችልኝ ነበር የመሠለኝ ጌታ ይጠቀምብሽ
@MeseretMathiwos
@MeseretMathiwos Ай бұрын
Amen
@Bereket-mi5sg
@Bereket-mi5sg Ай бұрын
What an amazing testimony! Blessings to you semira my sister in christ Jesus 🙏 ❤️
@user-lp9sz4ct2z
@user-lp9sz4ct2z Ай бұрын
አለምን ሊያድን የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ ለተገለጠልን እውነት አንኑር ጌታ ይርዳን ተባረኩ ያባቴ ቡሩካን
@besifattekabe2544
@besifattekabe2544 Ай бұрын
እህቴ የጌታ ጸጋና ሰላም ካንቺጋ ይሁን ወንድሜ መሀመድ በርታ ጌታ ከአንተ ጋ ይሁን
@Tinay-l5h
@Tinay-l5h 8 күн бұрын
ኢየሱስ የጌታዎቹ ጌታ ነው ሃሌሉያ ኡፍፍፍ እንኳን ጌታ እረደሽ ኡፍፍፍ ጌታ ኢየሱስ ያሳርፋል እህቴ ብሩክ ነሽ
@user-bc4gl4yo4f
@user-bc4gl4yo4f Ай бұрын
ጌታ ይባርክሽ ለቤቱ ስራ የተመረጥሽ ነሽና እስከ መጨረሻ ያፅናሸ ተባረኪ
@asmarethabtemariam3286
@asmarethabtemariam3286 Ай бұрын
ሰለ ድንቅ አጠራሩ ጌታ ይመስገን!! በርቺ አህቴ የተራሽ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው :: አይትልሽም : አይተውሽም!!
@RuthHayile
@RuthHayile Ай бұрын
ቃሉን የመግለጥ ፀጋ ተስጥ ቶሾል ስትናገሪ ሰማሽ ኢየሱሰጌታ ነው👏👏👏💕💕🙏👍😍🙏
@scripture_6
@scripture_6 Ай бұрын
"እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልሽ💞🙏
@zed8788
@zed8788 Ай бұрын
ጌታ እየሱስን የምከተለው ከነሸክሜ ሰለወደደኝ ነው ::🙏🙏🙏🙏 የጠራን ጌታ ስሙ ይባረክ:: የተቸገረን ማን ይወዳል ከርሱ ውጭ?? ከርሱ ሌላ የለም ::🙏🙏🙏🙏 በጣም የማረሳው ከአመታት በፊት ስራ ቦታ ስራየ የማታ ሽፍት ነበር:/ በዛ ቀን በጣም ቆዝሜ :አዝኜ ከጌታ ቤት ርቄ ከአመታት በሃላ የተመለስኩበት ወቅት ነበር ::ቁጭ እንዳልኩ ለደቂቃወች እነቅልፍ ሸለብ አደረገኝ:: ስነቃ ማቲወስ ወንጌል 11;28 እየሰማሁት ስነቃ ገረመኝ:: ጌታ በዚህ ልክ እየደሚወደኝ የገባኝ ያ ቀን ነበር:: ለምን በግዜው መፅሀፍቅደስ ስለማላነብ ጥቅሱንም በውል አላውቀወም ::ትርጉሙም በዛ ልክ አይገባኝም ነበር ;🙏🙏🙏🙏 የገረመኝ ሰለወንጌል ያላት እውቀት አድስ አትመስልም:::🙏🙏እይዞሽ ጌታ ወላጅ አባት ነው ::🙏🙏🙏
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal Ай бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን!!🥰
@tadelchdaba1536
@tadelchdaba1536 Ай бұрын
እየሱስ ጌታ ነው እንኳን ደስ አለሽ እህቴ ይሄን ድንቅ አምላክ ስላገፕሽ።
@ChibsaSamrawit-hi8vd
@ChibsaSamrawit-hi8vd Ай бұрын
በመጀመርያ እንኳን እውነተኛ የጀነት መንገድ አገኘሽ እኳንደስ አለኝ congratulatios ! ላንች ለሆነልሽ ደስታዬ ወደር የለውም በተረፈው ሰሚራዬ ከዚህ መንፈሳዊ መረዳትሽና እድገትሽ በልዩ ልዩ ፈተና በፀጋው እየተደገፍሽ እያለፍሽ ጌታን በሙላት እስከማወቅ ጥግ በርች የመንፈስ ቅዱስ አብሮነት ካንች ጋር ይሁን አንድ ቀን በአካል ባገኝሽ ደስ ይለኛል ስልክሽ ብኖረኝ ።
@dehabberhe3293
@dehabberhe3293 Ай бұрын
የሚገርም መገለፅ ነው አህት ሰሙ የጌታ ብርሀን አብዝቶ ይብራልሸ ተባረኪ❤❤❤
@user-lc2yg9fx3g
@user-lc2yg9fx3g Ай бұрын
እኔ በውስጠ ሰለ አንች መንፈስ ወቅዱስ እንድ ይላል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ይሰጣል ዘኁልቁ 14/24 ይሰጠኛል ና በርች ጌታ ካንች ጋር አለ❤
@PetrosMemru-oc7he
@PetrosMemru-oc7he Ай бұрын
ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን እግዝአብሔር ያጽናሽ
@alemsegedgirma1165
@alemsegedgirma1165 Ай бұрын
እግዚአብሔር ይባርክሽ፤ ድንቅ የሕይወት ምስክርነት ነው። በእርግጥ እግዚአብሔር በዚች ልጅ ትልቅ አላማ አለው።
@emawayshekassahun7346
@emawayshekassahun7346 Ай бұрын
ሀሌሎያ እንዴት ያለ ድቅ ምስክርነት ነዉ ዘመንሽ ይባረክ
@misghinaokbamariam6062
@misghinaokbamariam6062 Ай бұрын
ጌታ ይባርክሽ የኔ በገታ እህት፡ በጣም አስገራሚ ምስክርነት
@user-gy8bd8vh2q
@user-gy8bd8vh2q Ай бұрын
ሠሚራ እጅግ ውድ በክርስቶስ እህቴ ቋንቋሽ እንዴት እንደሚጣፍጥ መአዛሽ እንዴት እንደሚሸት ይገርማል አንችን ያዳነ ወደዘላለማዊ መንግስቱ የጠራሽ ጌታ ይባረክ እንዴት እንደወደድኩሽ አልገልፀውም እግዜብሔር በነገር ሁሉ ይባርክሽ
@user-cf3yl3ww1t
@user-cf3yl3ww1t Ай бұрын
ሰሚራዬ እግዚአብሔር የመረጠሽ ልጅ የተረጋጋሽ በደንብ የገባሽ ጌታ ቃሉን አባባሉን በለዛ እና የማንንም ልብ እና አይምሮ በሚስብ መልኩ የሰጠሽ ድምጸ መልካም ልጅ ነሽእና ጌታ እግዚአብሄር ይባርክሽ ትልቅ አድርጎሽ እንዳንች እንደበፊቱ ተሰውሮባቸው ግራ እየገባቸው ያሉትን ወገኖቻችንን መፍትሄ ሰጪ ያድርግሽ እህቴ ተባረኪ ብሩክ ሁኚ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይሁን ሰላምና ጤና ፍቅር ከመላው ቤተሰብሽ ጋር ይስጥሽ ባይ😂🎉❤
@user-li4gw5qq4n
@user-li4gw5qq4n Ай бұрын
ይህ የጌታ እጅ ነው።ጌታ ይባርክሽ።ጌታ ፀጋውን ያብልሽ።ይህን ለሚሰሙ ላላመኑት ብርሃን ላመኑት መቀስቀሻ ማንቂያ ነው።ጌታ ይባርሽ።
@SintayehuBoku
@SintayehuBoku Ай бұрын
የተባረክሽ ጸጋ ይብዛልሽ
@asefshgebreweldi4618
@asefshgebreweldi4618 Ай бұрын
ተባረኪ ሰሚራየ ❤ጀግና እህት ወንጌላዊት
@NelomaNeloma
@NelomaNeloma Ай бұрын
ዋዉ መረዳትሽ ደስ ይላል፣ በተለይ ስለ " ሸክም የከበደባችሁ" * የረቀ ሰፈሬ * ደህንነት ትምህርት * የሞተ ሰውነቴን ቀብሬ እያልሽ የገለጽሻቸው ነገሮች እና ሌሎቹም በጣም አስገረሚ ነው ፣ ተባረኪ በጣም!
@abdujobir1197
@abdujobir1197 Ай бұрын
እስላም ነበርኩ በማለት አትነግዱ ባካቹ እንዲህ የምትሉ ሰዎች ስለ ሐይማኖቱና ስለ አሏህ ባግባቡ ያወቃችሁ አደሉም ይህንን ምለው ስለ አንድ ግለሠብ ባህሪያት እንጂ በሐይማኖቱ ላይ አንድም ነገር አያቀርቡም የሐይማኖት ትዛዛት አተገባበር ከሰው ሰው ይለያያል ።
@sisaydeneke6214
@sisaydeneke6214 Ай бұрын
ካልበራልህ አስቸጋሪ ነው
@mame8874
@mame8874 Ай бұрын
ሀሌ ሉያ ስምሽን የቀየረ ጌታ ስሙ ይባረክ ጴንጤ መባል እኮ ትልቅ ነገር ነው
@habtamusium8646
@habtamusium8646 Ай бұрын
ደስ የሚል ምስክርነት ! እህታችን መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ መማር ይኖርብሻል ! በርቺ
@desalenglire8641
@desalenglire8641 Ай бұрын
ተበረክ ጌታ እግዚአብሔር ይበርክሽ ዘመንሽ ይለምልም. እንኳን ጌታ ኢየሱስ እራደልሽ
@mame8874
@mame8874 Ай бұрын
ማሜ ተባረክ ምስክርነትህን ሰምቻለሁ እናንተን ያስነሳ ጌታ ይባረክ ፀጋችሁን ጠብቁ
@aklilgeorge8670
@aklilgeorge8670 Ай бұрын
ዋው ህልውናው አብሮ መሆኑ በራሱ ለጥያቄ መልስ ነው የሚገርም መረዳት ነው ገና በልጅነት ክርስትናሽ። እግዚአብሄር ሁሌ በሁሉ ነገር ካንቺ ጋር ይሁን ብዬ ባረኩሽ እህት ሰሚራ
@selasgosaye1789
@selasgosaye1789 Ай бұрын
እህቴ የዘላለም አምላክ በዘለዓለማዊ ፍቅሩ የማረከሽ ክብር ኹሉ ለሥሙ ይኹን ምን አይነት ህይወትን የምለወጥ ምስክርነት ነው በቃ ቃላት አጣሁ የእውነት ዛሬ አድስ ደስታ ሠላም ውስጤ ሞላው ለብዙዎች የበረከት ምንጭ ሁኚ ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ 1:18:20 🙏🙏🙏👉❤🤝 1:18:24
@lidunur692
@lidunur692 2 күн бұрын
God bless you my brother and sisters in Christ ❤ እኔም ከሙስሊም ነው ወደ ጌታ የመጣሁት 🙌🏻 ሐዋ. ሥራ 4:12፤ መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”
@user-fe6mo3ib2i
@user-fe6mo3ib2i 22 күн бұрын
Iam so happy hearing such wonderful blessing testimony let God bless you Samira. Be brave on proclaiming the herald of Jesus and His kingdom
@nat76
@nat76 Ай бұрын
የፈጠረን አምላክ ከሁሉም በላይ የፍጥረታት ጌታ የተመሰገነ ይሁን እህት ወንድሞቼ ክርስቶስን መምሰል ነውና ክርስቶስን እንድንመስል ይርዳን አሜን እግዚሀብሄር ይመስገን
@user-dh7qf3xd7o
@user-dh7qf3xd7o Ай бұрын
ድንቅ ምስክርነት ነው ፤ ጌታ በቤቱ ያጽናሽ ፡፡ ተባረኪ ፡፡
@saraabrha8617
@saraabrha8617 Ай бұрын
Esay enkan Egziabher redash ehtye Eyesus yadenal.
@user-st7nl5zi3n
@user-st7nl5zi3n 27 күн бұрын
ጌታ ይባርክሽ ፀጋው ይብዛልሽ አምላኬ በአንቺ ፈቃዱን ይፈጽም።ይክበርብሽም ፍፃሜሽ በድል ይሁን
@solomonkebde3651
@solomonkebde3651 Ай бұрын
Mehamed geta ybarkih be somaligna birogiram kale asitelalfuln
@AlemAsfwu
@AlemAsfwu 28 күн бұрын
ከሶማሌ እየሰማሁ ነው ደስ ይላል
@dejeneassefa1772
@dejeneassefa1772 23 күн бұрын
ድንቅ እና እውነት የሆነ ምሦክርነት ።ተባረኩ
@mekonenasfaw4805
@mekonenasfaw4805 Ай бұрын
እንኳንም ወደ አለም ብርሀን ወደ ክርሰቶሰ መጣሸ የዘለለም ህወት አገኘሸ እህቴ ከዘለለም ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሀን መጣሸ ብርች ሰምሸ በህወት መጸሐፍ ተፀፏል
@yade716
@yade716 Ай бұрын
አስደናቂ ምስክርነት! እስከ መጨረሻው ጽኒ! ስለ ጌታ መከራና ስድብ ዘላለማዊ ሽልማት ነው።
@eleni311
@eleni311 29 күн бұрын
ሰሚራዬ ሰልክሸን ሰጭኝ ፈልግሻለሁ ተባረኪ 🙏❤
@user-zh2nc8vc5o
@user-zh2nc8vc5o Ай бұрын
መንፈሳዊ ትርጉሙ ገብቶሻል እህቴ ሳሚራ ጌታ ይባርክሽ!!!!
@fatmauae7979
@fatmauae7979 Ай бұрын
እየሱስ ጌት ነዉ🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤❤
@zerfanegash3691
@zerfanegash3691 Ай бұрын
እግዝያብሄር ፊቱን ያብራልሽ ሰላሙንም ይስጥሽ አሜን በእየሱስ ስም
@ZerihunAyele-zl8lt
@ZerihunAyele-zl8lt Ай бұрын
እንኳን ከጨለማ ወደ ብርሃን በደህና መጣሽ ❤❤❤❤
@user-rj1go6zw6e
@user-rj1go6zw6e Ай бұрын
ዋው 🎉❤❤😮ተባርከሻል❤❤😊😮😮now you are faithful servant for kingdom!! 😍😍🙌
@SmilingCherryBlossoms-ci4fz
@SmilingCherryBlossoms-ci4fz Ай бұрын
ሰሚራ ጌታ ይባርክሽ ዘመንሽ በክርስቶስ የተባረከ ይሁን።
@winoman4051
@winoman4051 3 күн бұрын
ሰሚራ❤❤❤ ፀጋው ይብዛልሽ🙏🙏 ስለተመረጥሽ እኮ ነው። ማንም ከኢየሱስ እጅ ሊያስጥልሽ አይችልም። ዮሐንስ 6:39
@adenyad
@adenyad Ай бұрын
ይህ ወንጌል ለድሆች ሸክማቸው ለከበዳቸው ለተናቁት ለተጠሉት ለምስኪኖች ነው ጌታ እየሱስ የሚለየው በዚህ ነው ከሸክም ከዚህ አለም የሚታደገን ነው!
@user-oc5zb8zt3y
@user-oc5zb8zt3y Ай бұрын
Well come to Jesus Christ. From darkness to light. This is the fact with out Jesus Christ there is no way the truth the life. John 4 16.
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal Ай бұрын
Amen!🥰
@alemudesta5793
@alemudesta5793 Ай бұрын
“እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤” - ሐዋርያት 5፥41
@neguseberi3013
@neguseberi3013 Ай бұрын
ዋው እህታችን ሳሚራ እግዚአብሔር በብዙ ይባርክሽ ክርስቶስ ዋጋ ከፈለለሽ አንቺ ደግሞ አሁን ክርስቶስ ብለሽ ቤተሰብሽን ዋጋ እያስከፈለሽ ነው ነገር ግን በሰማይ ያለሽ ዋጋ በእውነት ታላቅ እንደሆነ አምናለው ደግሞም ቤተሰብሽን አንቺ ወደ አወቅሽው እውነት እንዲመጡ በፀሎት በፆም አስቢያቸው ከአንቺ በላይም እግዚአብሔር በእርግጥ ያስባቸዋል እኛም በፀሎት አናስባቸዋለን እግዚአብሔር ቀሪው ዘመንሽን ይባርክ ደግሞም ብልህና አስተዋይ ሴት እንደሆንሽ ነው ማምነው በእውነት በአንቺ በጣም ደስ ብሎኛል ትህትናሽን እግዚአብሔር ይጨምርልሽ
@RebeccaRogu-ut6je
@RebeccaRogu-ut6je 25 күн бұрын
እኳን ለመግስቱ ወራሽአደረገሽ ተባረኪ
@Fjogfsc
@Fjogfsc 26 күн бұрын
መላ ቤተሰቦችሽን ከጨለማ ወደብርሃን እደምታመጫቸዉ ተስፋ አለኝ❤❤❤❤አደራ ስለክርስቶስ አስረዳቸዉ😢😢😢
@BalchaAbebe-ui7uq
@BalchaAbebe-ui7uq Ай бұрын
wow my child Semira this is good decision to receive Jesus as your personal savior you will get eternity life in the kingdom of God you have hop continue God is be with you He doesn't late down alone you He never separate from you I appreciate you go ahead! I love you so much be blessed God bless you all your life. By
@thionlema7724
@thionlema7724 18 күн бұрын
እየሱስ ጌታ ነው ተባረኩ
@yetimewore8587
@yetimewore8587 Ай бұрын
እህቴ እንኳን ጌታ ረዳሽ እኳን እውነቱ በራለሽ ።
@MyBalcha
@MyBalcha 21 күн бұрын
ተባረኪ ፈጣሪ ሁሉንም ይርዳቸው
@RuthHayile
@RuthHayile Ай бұрын
አሜን ጌታ ስሙ ይባረክ 💕👏👏👏👏👏🙏እንኳን እውነት ተገለጠልሽ እንኳን ደስ አለሽ እልልልልልልልልል በስማይም በመላክቶ ዘንድ እልልታነው👏👏👏👏👏🤩🤩🤩❤️❤️❤️❤️🙏
@Fikadu-sr7bq
@Fikadu-sr7bq Ай бұрын
እግዚአብሔር ይመሰገን ሁላችንም share እናድርግ ብዙዎች በዚህ ምስክርነት ይድናሉ ብይ አምናለሁ 🙏🥰🙏❤ እየሱስ ጌታ ነው🥰❤
@thionlema7724
@thionlema7724 17 күн бұрын
እኔ እከፍላለሁ ግደሏት ያለችው አክስቷ አሁን አትፍረዱባት እራሷ ወደ እየሱስ ክርስቶስ ትቀርባለች ትወደዋለች ታምነዋለች በአክስቷ በኩል እናቷ በእናቷ በኩል እህት ወንድሞቿ እያለች ትወርሳቸዋለች ሰሚራ አሜን ትወርሳቸዋለች
@dinkutasew
@dinkutasew Ай бұрын
እግዚአብሔር ሲመርጥሽ ነው ፈተናው የበዛው እንኳን ደሳለሽ ዳንሽ ዛላለማዊ ህይወት ለማግኘት ደግሞ በርቺ ይህ ሚዲያ እግዚአብሔር ይባርከው❤❤❤❤❤❤❤😂
@ergoyeyeshiwas5984
@ergoyeyeshiwas5984 Ай бұрын
ጌታ እንኳን እረዳሽ ወደሚያሳርፈዉ አምላክ ❤❤❤❤❤
@Roza-fl2wf
@Roza-fl2wf Ай бұрын
ተባረኪ እህቴ በርቺ 😍😍
@felekechgeleturoba3434
@felekechgeleturoba3434 Ай бұрын
አሜን ሰሚራ ጌታ ሰለረዳሽ ጌታ ኘመሰግናለሁ በርቺ
@aderamillo4576
@aderamillo4576 Ай бұрын
GREAT GRACING GOD BLESS YOU
@memhrandegideykahsay3906
@memhrandegideykahsay3906 Ай бұрын
2ኛ ኮሜንት ኣዘጋጅ ተባረክ። ባርከኸናልና።ሚድያህን ያስፋልህ። ከዚች ምርጥ ሙስሊም ክርስትያን ጋር ስላስተዋወቅከን በጣም ኣበረታኸን። ሰሚራ ከዘመዶችዋ ሁሉ ርቃ ብቻዋን ትገኛለች። ሞራልዋን ለመገንባትና ኣገልግሎትዋን በሚገባ እንድትተገብር ኣማኞች ሁሉ ብንረዳት ደስ ይለኛል። በበኩሌ ኣንድ በለንና ለዚች ምርጥ ኣገልጋይ ትንሽም ብትሆን ልልክ ደስተኛ ነኝ ! ሌሎች ወንድሞችም ሊኖሩ ይችላሉና ኣስተባብርልን !
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal Ай бұрын
ባስቀመጥኩት የቴሌግራም ሊንክ አናግሩኝ። ተባረኩ!!
@Tinay-l5h
@Tinay-l5h 8 күн бұрын
እንኳን በሰላም መጠሽ ወደ እውነተኛ ሕይወት መንገድ ❤️
@user-db7ti6hs1x
@user-db7ti6hs1x Ай бұрын
በጣምበርቺ ሠሚራ ፀጋዉን ያብዛልሽ
@zelekebunchamo7741
@zelekebunchamo7741 Ай бұрын
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤እንኳን ደስ አልሽ እህቴ
World’s Largest Jello Pool
01:00
Mark Rober
Рет қаралды 100 МЛН
Alex hid in the closet #shorts
00:14
Mihdens
Рет қаралды 16 МЛН
39kgのガリガリが踊る絵文字ダンス/39kg boney emoji dance#dance #ダンス #にんげんっていいな
00:16
💀Skeleton Ninja🥷【にんげんっていいなチャンネル】
Рет қаралды 8 МЛН
♦️በየኔታ ቤት ያየሁት ሕልም♦️ ባምቢ (ሐና ግደይ ከያያ ጋር
1:12:05
Quanquayenesh Media ቋንቋዬነሽ ሚዲያ
Рет қаралды 186 М.