የሀባብ ቆዳ ጥቅሞች/የሐባብ ቆዳ ጥቅሞች ethiopian health

  Рет қаралды 2,180

Birabiro ቢራቢሮ

Birabiro ቢራቢሮ

Жыл бұрын

ይሄን ሰምታችሁ የሀባብ ቆዳን አትጥሉም/ የሐባብ ቆዳን መመገብ የሚያስገኛቸው ጥቅሞች
#ethiopian health#የሀባብ ቆዳ#የሀብሃብ ቆዳ ጥቅሞች#የሀብሃብ ቆዳ ጥቅም
ሀባብ 90%ቱ ውሃ የሆነ ጥምን ለመከላከል የሚረዳ አስደናቂ ፍሬ ነው
በቫይታሚን C, A B6 እና A ፓታሲየምና ዚንክ የበለፀገ ነው
ብዙ ሰዎች የሀባብ የውስጠኛውን ቀዩን ክፍል በልተው ልጣጩን ማለትም ነጩን ይጥሉታል
ለጤና የያዘውን ጠቀሜታ ስትሰሙ ግን የሀባብ ቆዳን አትጥሉም ምክንያቱም 95% የሃባብ ጥቅሞች ቆዳው ላይ የሚገኙ ናቸው
የሀባብ ቆዳ በቫይታሚን C, B6 እና A ፓታሲየምና ዚንክ የበለፀገ ነው
1 .የሀብሀብ ቆዳ እንደውስጡ በብዛት ውሃ የያዘ ነው በዚህ ምክንያት ኩላሊት በተገቢው መንገድ ቆሻሻን እንዲያስወግድ ያግዘዋል
በሃባብ ቆዳ ውስጥ የሚገኘው ፖታሲየምና ብዙ ውሃ የኩላሊት ጠጠር ተሰባብሮ ከኩላሊት በሽንት መልክ እንዲወገድና በኩላሊት ውስጥ የተመጣጠነ የአሲድ መጠን እንዲኖር በማድረግ ኩላሊት ጤነኛ እንዲሆን ያደርጋል
የተቆጣ ቆዳ ላይ በነጩ በኩል በማስቀመጥ የቆዳውን መቆጣትና መቅላት ማስታገስ ይቻላል
የሃባብ ቆዳን ፈጭቶ እንደማስክ ፊትን መቀባት በፀሃይ የተጎዳና የተጨማደደ ቆዳን ያስተካክላል ብጉር የሚያስከትሉት ባክቴርያዎች ቶሎ እንዳይራቡ በማድረግ ብጉርን ይከላከላል የበዛ የቆዳ ቅባታማነትን ይቀንሳል፣ እንዲሁም የቆዳን የመለጠጥ ችሎታ ያሳድጋል
ነጠብጣቦች ከቆዳ ላይ ያስወግዳል ጥብቅ ያለ የሚያበራ እንዲሆንና ቶሎ እንዳያረጅ ያስችለዋል
ቤታ ካሮቲንም ስላለው ለአይን በጣም ጠቃሚ ነው
ለፀጉር
በውስጡ የሚገኘው ሲትሩሊን በሰውነት ውስጥ ወደአጀናይን በመቀየር የደም ቧንቧዎች መጠን እንዲሰፋና በቂ ደም ወደራስቅል እንዲደርስ በማድረግ ፀጉር ጤናማ እንዲሆን ያደርጋል
ሀባብ የእርጥበት ምንጭ ነው እርጥበት ደግሞ ለጤናማና ውብ ፀጉር መሰረት ነው ፀጉር ከቄጠማ ጋር ተመሳሳይ ነው ቄጤማ /ሳር በየቀኑ ውሃ ይፈልጋል በቂ ውሃ ካላገኘ ውበቱን እንደሚያጣና እንደሚደርቅ ሁሉ ፀጉርም በቂ እርጥበት ካላገኘ አመዳም ቀለም ያለው ደረቅና በቀላሉ የሚነቃቀልና የሚሰባበር ይሆናል
ይሄን ለመከላከልና የውብ ፀጉር ባለቤት ለመሆን ሀባብና የሀባብ ቆዳን መመገብ በቂ ነው

2. በዛ ያለ አሰር ስላለው ኮሌስትሮልንና የስኳር መጠንን ይቆጣጠራል
ለምግብ መፈጨት ይረዳል እንዲሁም ሲትሩሊን በተባለ የአሚኖ አሲድ ይዘቱ ምክንያት ቶሎ የመጥገብ ስሜትን በማስከተል ክብደት ለመቀነስ ያስችላል
3. ኢንፍላሜሽንን ለመቀነስ ይረዳል እብጠትን የሚከላከለውን ላይኮፔን የተባለ ንጥረነገር ስለያዘ የአርተራይተስ ህመምን ስቃይ ይቀንሳል
4. የሃባብ ቆዳ ውሃ አዘልነቱና ሽንት የማሸናት ባህሪው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን በማዳን ረገድ ፍቱን ያደርገዋል
5. ነፍሰጡር ሴት ብትመገበው ቃርንና በእርግዝናው ምክንያት የሚመጣን የሰውነት እብጠት ለመቀነስ ያስችላል
በሀባብ ቆዳ ውስጥ ያለው ተፈጥሯዊ ስኳር በእርግዝና ወቅት ጠዋት ላይ የሚከሰትን ህመም morning sickness ለመቀነስ ይረዳል
6. በተጨማሪም በቂ ውሃ በሰውነት ውስጥ እንዲኖር ስለሚያደርግና
ፖታሲየም ስላለውም የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ቢመገቡት የደም ግፊታቸው እንዲቀንስና በጣም ከፍ እንዳይል ይቆጣጠራል እንዲሁም የደም ዝውውርን ያስተካክላል
የሀባብ ቆዳ ላይ የሚገኘው ፖታሲየም በደም ስሮችና ደም ቅዳ መጥበብ የተነሳ ውጥረትና ጫና እንዳይደርስባቸው በመከላከል ለልብ ድካም፣ ስትሮክና የልብ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ህመም የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል
በቆዳው ላይ የሚገኙት ሲትሩሊንና ቫይታሚን ሲ ነጭ የደም ህዋስ በብዛት እንዲመረት በማነቃቃት በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋሉ
አረንጓዴውን ክፍል ለይቶ ውስጡን ከነጩ ክፍል ጋ መብላት ሰላጣ
ላይ መጨመር ወይም ከሌሎች ፍራፍሬዎች ጋ አብሮ ፈጭቶ በጁስ
መልክ መጠጣት በተፈጥሮ ያለው ትንሽ የመምረር ጣእም ይቀንሰዋልhealth amharicየሀባብ ቆዳ ጥቅሞችየሀባብ ቆዳ ጥቅምhealth livingethiopia health tipsየሐባብ ቆዳ ጥቅሞችhealth tips in amharicfood and beauty

Пікірлер: 8
@user-zf5cs3lu1o
@user-zf5cs3lu1o 6 ай бұрын
Very useful information
@birabiro1626
@birabiro1626 6 ай бұрын
Thanks dear.
@ethiopia5722
@ethiopia5722 Жыл бұрын
እንዲህ ጠቃሚ ነገር ነው ለካ ይገርማል
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
አዎ ጠቃሚ ስለሆነ መጣል የለብንም ውዴ
@bereketasfawwossen4677
@bereketasfawwossen4677 2 ай бұрын
አመሰግናለሁ የኔ እህት ቆዳውን ፈጭተን ነው ወይስ በምን መልኩ እንጠቀም???
@birabiro1626
@birabiro1626 2 ай бұрын
1. የቆዳውን የውስጠኛውን ነጩን ክፍል ልጠን ከሌሎች ፍራፍሬዎች ጋር አድርገን ፈጭተን በጁስ ልክ መጠጣት ይቻላል 2. ነጬን የልጣጩን ክፍል ለይተን ማርማላት (Jam) ሰርተንበት መጠቀም ይቻላል 3. ፒክል ሰርተን መጠቀም (pickles) 4. ከስኳር ጋር አድርገን ከረሜላ ሰርተነውም መጠቀም ይቻላል
@bereketasfawwossen4677
@bereketasfawwossen4677 2 ай бұрын
ለቆዳችን ነጩን ነው አረንጓዴውን ፈቅፍቆ የምንጠቀመው?? ለፀጉራችንስ የቱን አረንጓዴውን ነው ወይስ ነጩን?? የኔ ቆንጆ ንገሪኝ?? መልስሽን እጠብቃለሁ ቤቴ በጣም ስለምጠቀመው?? ተባረኪ
@birabiro1626
@birabiro1626 2 ай бұрын
1. ነጩን ክፍል ሲሆን የምንጠቀመው ከፈጨነው በኋላ ለፊት ማስክ መጠቀም 2. በጁስ መፍጫ ከፈጨነው በኋላ የበረዶ መስሪያው እቃ ላይ በትናንሹ እንጨምርና ፍሪጅ ውስጥ ማቆየት ከዛ በረዶ ሲሆን በሱ ፊትን እና አንገትን ሳይጫኑ ማሸት እያዳረሱ 3. በልጣጩ የውስጠኛ ክፍል ቆዳን ማሸት ወይም መጠራረግ
DEFINITELY NOT HAPPENING ON MY WATCH! 😒
00:12
Laro Benz
Рет қаралды 60 МЛН
Nastya and SeanDoesMagic
00:16
Nastya
Рет қаралды 21 МЛН
39kgのガリガリが踊る絵文字ダンス/39kg boney emoji dance#dance #ダンス #にんげんっていいな
00:16
💀Skeleton Ninja🥷【にんげんっていいなチャンネル】
Рет қаралды 8 МЛН
A little girl was shy at her first ballet lesson #shorts
00:35
Fabiosa Animated
Рет қаралды 5 МЛН
ሩታ የእርግዝናውን መልስ ሰጠች.አብርሽ ደስተኛ ሆነ🙈❤️
21:46
የደም ግፊት ምልክቶች ምን ምን ናቸው
8:06
Birabiro ቢራቢሮ
Рет қаралды 769
DEFINITELY NOT HAPPENING ON MY WATCH! 😒
00:12
Laro Benz
Рет қаралды 60 МЛН