🔴የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ እና ያልተጠበቀው ውሳኔ❗️አቡነ ሉቃስ፣ አቡነ ሩፋኤል፣ አቡነ ጴጥሮስ

  Đ ĐľŃ‚ қаралды 1,423

Tsegaye kiflu

Tsegaye kiflu

Ай бұрын

#ጸጋዬ_ክፍሉ #tsegayekiflu #joinmembership
• 🛑አቡነ አብርሃም 🚩 አቡነ ሩፋኤል ... የአቡነ ሩፋኤል ጉዳይ
• 🔴የአቡነ አብርሃም ያልተጠብቀ ድርጊ... የኮሪደር ልማት
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ
ጉባኤ መግለጫ
++++++
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤
2. በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤
3. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4. የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጂ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከ አሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡
በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስመልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል።
6. የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
7. በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉባኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።
8. ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቡና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
9. በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡
10. ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀ ጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
11. የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
12. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
FAIR-USE COPYRIGHT DISCLAIMER
Copyright Disclaimer Under Section 107 of the Copyright Act 1976, allowance is made for "fair use" for purposes such as criticism, commenting, news reporting, teaching, scholarship, and research. Fair use is a use permitted by copyright statute that might otherwise be infringing. Non-profit, educational or personal use tips the balance in favor of fair use.
1) This video has no negative impact on the original works (It would actually be positive for them)
2) This video is also for informational purposes.
3) It is not transformative in nature.
4) I only used bits and pieces of videos to get the point across where necessary.
Tsegaye kiflu does not own the rights to these video clips. They have, in accordance with fair use, been repurposed with the intent of educating and inspiring others.

Пікірлер: 13
@YeMaryam-cb2mj
@YeMaryam-cb2mj Ай бұрын
በርታ ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም ፍጻሜህ እጅግ ይበዛልና እውነት በቲፎዞ ብዛት አትለካም።
@GeDo-um6oh
@GeDo-um6oh Ай бұрын
እባክህ እግዚአብሔርን ፍራ
@Tsegayekiflu
@Tsegayekiflu Ай бұрын
ለምኑ?
@user-lb2bp4ix3k
@user-lb2bp4ix3k Ай бұрын
እግዚአብሔር ፍቅር ነው። መልካም ነው። ለምን ይፈራል። አባት ይፈራልን? አርሙ እናንት ደፍተራዎችና የደፍተራ ልጆች!
@YeMaryam-cb2mj
@YeMaryam-cb2mj Ай бұрын
ያንተ እግዚአብሔር እነሱ ናቸውዴ? እንደቤተክርስቲያን ልጅነቱ የሚችለውን እያደረገ ነው ይህ ደግሞ ልኡል እግዚአብሔርን ማክበርና መውደድ እንጂ አለመፍራት አይደለም ሰው ስለሆኑ ይሳሳታሉ ግን ፈጽሞ ከነሱ የማይጠበቀውን ስህተት ማረም ተገቢ ነው ለምእመኑ ካሰብን ብቻ ይሄ ግን ምንደኞችን አያጠቃልልም
@YeMaryam-cb2mj
@YeMaryam-cb2mj Ай бұрын
በርታ ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም ፍጻሜህ እጅግ ይበዛልና እውነት በቲፎዞ ብዛት አትለካም።
@bekalumogne6635
@bekalumogne6635 Ай бұрын
@@user-lb2bp4ix3k ደፍተራ የሚለዉን ቃሉን መልሰው መላልሰው ቢያጠኑስ እንኳን ትርጓሜው ላይ ፊደሉ ላይም የሉም መሰል .. እያየን አለ ሰዉየው
@genetbekelejohn4859
@genetbekelejohn4859 Ай бұрын
Betam azenanale abun aberhan zeme belu poltec menei agebaw ? Esu ferdun yesetachul . Bebatu endekeledachu weshtamuch nachu hulachum sew aschersachu enate geni Alachua esu yeferdal ayekerem le segachu adelachu betam yaszenal ande sew tefa
@user-lb2bp4ix3k
@user-lb2bp4ix3k Ай бұрын
ክብርት ከንቲባ ከማን በሰበሰቡት ግብርና በጀት ነው የኦርቶዶክስን በማስፋፊያ ምከንያት ከለፕላን የተገነባ (የተሰራን) በመፍረሱ በምትኩ ሕንጻ የሚገነቡት? እኔ የሌላ እምነት ተከታይ ሳልሆን ለጊዜው እስከ ዛሬ ኦርቶዶክስ ነበርኩ። በብልግናቸው በተሳዳቢነታው ምክንያት ከእምነት ነጻ ሆኜ አለማመንም ማመን ነው ብዬ አለሁ።
@Tsegayekiflu
@Tsegayekiflu Ай бұрын
እግዚአብሔርን ለመካድ ያቀረብከው ምክንያት በቃህ?
@hreetabebe3979
@hreetabebe3979 Ай бұрын
አንተን ብሎ የሚዲያ ሰው! ሊቀ ጳጳስን አንተ ብሎ መጥራት የት ነው የተማርኸው? ስድ!
@Tsegayekiflu
@Tsegayekiflu Ай бұрын
ማንን ነው ያልኩትኝ? አንተስ መንፈሳዊ ሆነኽ ነው እየተሳደብከ ያለኸው?
@YeMaryam-cb2mj
@YeMaryam-cb2mj Ай бұрын
የአይጥ ምስክር ድቢጥ ንጹሀን አባቶችን እናከብራለን በልብስና በስልጣን መከበር ግን ድሮ ቀረ በቀራኒዮ የፈሰሰውን የክርስቶስን የደም ዋጋ አፈር በሚበላው ዘር ከቀየሩ ገና አቶ እንላቸዋለን
路飞被小孩吓到了#海贼王#路飞
00:41
路飞与唐舞桐
Рет қаралды 44 МЛН
THEY made a RAINBOW M&M 🤩😳 LeoNata family #shorts
00:49
LeoNata Family
Рет қаралды 30 МЛН
РусаНка
01:00
История одного вокалиста
Рет қаралды 3 МЛН
ሞኒካ ካብ ኣስመራ ፈጨጭ እዩ በይ
11:12
Awita ፍቅር
Рет қаралды 12 М.
路飞被小孩吓到了#海贼王#路飞
00:41
路飞与唐舞桐
Рет қаралды 44 МЛН