የጥቅል ጎመን ጥቅም /Amazing benefits of cabbage

  Рет қаралды 6,502

Birabiro ቢራቢሮ

Birabiro ቢራቢሮ

9 ай бұрын

የጥቅል ጎመን ጥቅም/ጥቅል ጎመን ጥቅም Is Cabbage Related To Hair And Skin?
ጥቅል ጎመን ለስላሳ ቆዳና የሚያምር ፀጉር እንዲኖረን በጣም ጠቃሚ ነው
በውስጡ 'indole-3-carbonile' የተባለ ሃይለኛ antioxidant አለው. ጉበትን ያፀዳል ማለትም detoxifies.
ይሄ ደግሞ ቆዳን ይጠቅማል ምክንያቱም መርዛማ ነገሮችን ከሰውነት ስለሚያስወግድ ነው በደም ውስጥ መርዛማ ነገሮች ሲከማቹ ቆዳ የደበዘዘና ነጠብጣቦች የበዙበት ይሆናል.
ቀጥሎ ጥቅል ጎመንን መመገብ ለፀጉርና ለቆዳ የሚሰጣቸውን 10 ጥቅሞች አቀርብላችኋለሁ
1) ፀረ እርጅና Anti-ageing agent: ጥቅል ጎመንን አዘውትሮ መመገብ ቆዳ ቶሎ እንዳያረጅ ያግዛል
በዛ ያለ የቫይታሚን ሲ ይዘት በውስጡ መኖሩ የእርጅና ሂደትን እንዲያዘገይ ያስችለዋል
ቫይታሚን ዲ ጋር አብሮ የሚሰራው ቫይታሚን ኤ ስላለውም ቆዳን ያጠራል እንዲሁም ከultraviolet ጨረር ይከላከልለታል
2 ) Skin cure: ጥቅል ጎመን አስደናቂ የሆነ ቆዳን የማዳን ባህሪ አለው ከነዚህም መካከል ሽፍታ፣ ብጉር፣ ችፌ፣ psoriasis፣ የትንኝ ንክሻ፣ የቆዳ ቁስለቶች እና arthritis ለማከም ይውላል.
3) ለእንከን የለሽና ጥርት ላለ ቆዳ: ጥቅል ጎመን ጤነኛ ቆዳ እንዲኖር ያግዛል. በብጉር ወይም በሌላ አይነት የቆዳ ችግሮች እየተሰቃያችሁ ከሆነ ጥቅል ጎመን መፍትሄ ሊሆናችሁ ይችላል
በእንፏሎት የተቀቀለን ጥቅል ጎመን ችግሩ ያለበት ቆዳ ላይ ለጥፎ ከቦታው እንዳይንሸራተት በፕላስቲክ ሸፍኖ በማሳደር በነጋታው በውሃና በሳሙና በመታጠብ የተሻለና ንፁህ ቆዳን ለመጎናፀፍ ያስችላል
4) Vitamin E ለቆዳ ቀለም: የጥቅል ጎመን ጁስ መጠጣት የቆዳ ቀለምን ያሳምራል. ጥቅል ጎመን በውስጡ potassium ይዟል ፖታሲየም ደግሞ የውስጥ አካልንና ቆዳን ያጠራል.
5) ለብጉር Sulfur-rich for acne: ሰልፈር በጥቅል ጎመን ውስጥ በብዛት ስለሚገኝ እንደ ተፈጥሯዊ የውበት ማእድን ይቆጠራል 'Nature's beauty mineral'. በማድረቅ ችሎታው ምክንያት ሽፍታና ብጉር ቶሎ ደርቀው እንዲረግፉ ትልቅ እገዛ ያበረክታል
ለጤናማ ፀጉር፣ ጥፍርና ቆዳ አስፈላጊ የሆነው የፕሮቲን ንጥረነገር
የሆነው ኬራቲን እንዲዋሃድ ይረዳል
6) የማፅዳት ባህሪ ወይም ችሎታ: የጥቅል ጎመን juice ከፍ ያለ የቫይታሚን ሲ ይዘት ስላለው እጅግ በጣም ውጤታማ በሆነ መልኩ ውስጥን ያነፃል
በተጨማሪም gingivitis ምክንያት የቆሰለና infected ድድ እንዲድን ያደርጋል
7) ለፀጉር እድገት: ጥቅል ጎመን ብዙ መጠን ያለው ቫይታሚን ኤና የፀጉር እድገትን የሚያፋጥን antioxidant ስለያዘ ፀጉር እንዲያድግ
ያደርጋል
8) ለለስላሳ ፀጉር:
ጥቅል ጎመን ፀጉርን ይመግባል ስለዚህም ለስላሳ አንፀባራቂ ፀጉር እንዲኖር ይጠቅማል ይሄን ውጤት ለማግኘት
የጥቅል ጎመን ጁስን የራስ ቅልንና የፀጉሩን ስር በመቀባት ለ1 ሰአት አቆይቶ መታጠብ
9) የፀጉር መነቃቀልን ይከላከላል: የሚነቃቀል ፀጉርን ለማከም ጥሬ የጥቅልጎመንና ኩከምበር ጁስ መጠጣት ወይም ፀጉሩን ከስር ጀምሮ መቀባት ይቻላል
ኩከምበርና ጥቅልጎመን በሲሊከንና ሰልፈር የበለፀጉ ናቸው እነዚህ ማእድናት ደግሞ የፀጉር እድገትን የሚያፋጥኑና ፀጉር እንዳይረግፍና እንዳይነቃቀል የሚከላከሉ ናቸው
10) የደረቀ ፀጉርን ያፍታታል: ጥሬ የጥቅልጎመን ጁስ ለደረቅ ፀጉር ጠቃሚ ነው ፀጉሩን ያለሰልሰዋል ብሎም አንፀባራቂ እንዲሆን ያደርገዋል. ካሮት ኩከምበርና ጥቅልጎመንን በጁስ መልክ አዘጋጅቶ መጠጣት ጤናማና የሚያምር ፀጉር እንዲኖርዎ ያስችሎታል

Пікірлер: 6
@abdumohammedawol6423
@abdumohammedawol6423 9 ай бұрын
አመሰግናለሁ በቀጣይ ስለ ዱባ እና የዱባ ፍሬ ብትሰሪልን ደስ ይለኛል
@birabiro1626
@birabiro1626 9 ай бұрын
እሺ ቀጣዩ ቪድዮ ዱባና የዱባ ፍሬን የተመለከተ ይሆናል አመሰግናሁ የኔ ወንድም
@genetziguita4586
@genetziguita4586 4 ай бұрын
ምነዉ ጠፋሸ በሰላም ነዉ❤❤🎉
@birabiro1626
@birabiro1626 4 ай бұрын
ገንዬ የኔ አሳቢ ትንሽ ችግር አጋጥሞኝ ነው እመለሳለሁ ❤️❤️❤️❤️
@user-zp9ju3nk7s
@user-zp9ju3nk7s 2 ай бұрын
ጥቅል ጎመን ከለሩ ወይነ ጠጂ ማለትም ቀይስራሚ ቀለሙ ልዩነት የለውም ከአርንገጓዴው ጎመን ጥቅሙ አንድ አይነት ነው ከቻናሉ ባለቤት መልስ እጠብቃለሁ
@birabiro1626
@birabiro1626 2 ай бұрын
ልዩነት አላቸው ለምሳሌ ወይንጠጁ ጥቅልጎመን ብዙ ቫይታሚኖች አሉት ከአረንጓዴው እንዳሁም ካንሰርን የሚከላከለውን አንቶካያኒን የሚባለውን ንጥረቅመም ይይዛል አረንጓዴው የሚበልጥበትም ጥቅሞች አሉ ግን ደግሞ ሁለቱንም መመገብ የተሻለ የሁለቱንም ጥቅሞች ሰውነታችን እንዲያገኝ ያደርጋል
Iron Chin ✅ Isaih made this look too easy
00:13
Power Slap
Рет қаралды 34 МЛН
Clown takes blame for missing candy 🍬🤣 #shorts
00:49
Yoeslan
Рет қаралды 40 МЛН
Зачем он туда залез?
00:25
Vlad Samokatchik
Рет қаралды 3,3 МЛН
የጎመን ጁስ (ውህድ) 5 የጤና ጥቅም ና አዘገጃጅት/ Cabbage Juice.
8:40
ጤናዬን ሚድያ-Tenayen Media
Рет қаралды 14 М.
Iron Chin ✅ Isaih made this look too easy
00:13
Power Slap
Рет қаралды 34 МЛН