Рет қаралды 377,856
#sileHiwet #Ethiopia
በመካከለኛው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት እኝህ ባልና ሚስት በደስታና በፍቅር ከሚኖሩበት ቤታቸው ውስጥ ያልተጠበቀ ነገር ተፈጠረ፡፡ በመሆኑም መልከ መልካምዋ የቤቱ እመቤት ትዝታ በመኝታ ክፍላቸው ውስጥ ህይወትዋ አልፎ ተገኘች ዘወትር ለህብረተሰቡ ደህንነት ታጥቆ የሚሰራው ፖሊስ በትዝታ ላይ እንዲህ አይነቱን ወንጀል የፈፀመውን ግለሠብ ለመለየት ስራውን ቀጠለ፡፡ በዚህም አማካኝነት በርካታ ተጠርጣሪዎች ወደ ፖሊስ ጣቢያ ብቅ ቢሉም ከመሀከላቸው ግን አንድ እውነት የደበቀ ሠው እንዳለ ግልጽ ነው፡፡ ፖሊስ በምርመራ ሒደቱ በዋናነት ተጠርጣሪ ሆነው የቀረቡት በአንደኛ ደረጃ ምርመራ ሳያደርግ የቤቱ ጥበቃ እና የቤት ሠራተኛዋ ላይ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በእለቱ ከመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የጠፋው 420,000.00 ብር መነሻ ነበር የወንጀሉም አፈፃፀም ከገንዘቡ መጥፋት ጋር ተያያዥነት ስላለው ነው ፖሊስ በነዚህ ግለሰቦች ላይ ትኩረቱን ሊያደርግ የቻለው፡፡ እንዲሁም ደግሞ ገንዘቡ በጠፋ እለት በመኖሪያ ቤት ውስጥ የነበሩት ሟች ትዝታ፣ የጥበቃ ሰራተኛውና ከቤቱ ሰራተኛ በስተቀር በሠአቱ ሌላ የመርማሪ ፖሊስን እይታ የሚስብ ተጠርጣሪ ሠው ያልነበረ መሆኑ ብቻ ሣይሆን ይህ ረብጣ ገንዘብ ተሠርቆ የቤቱ ባለቤት ትዝታ በዚህ መልኩ ህይወቷ አልፎ ስትገኝ ባለቤቷ ካሣ በቤት ውስጥ አለመኖሩ ታክሎበት ሆን ተብሎና ተጠንቶ የተፈፀመ ወንጀል እንደሆነ በማመኑ ነው የመርማሪ ፖሊስ አይን ይበልጥ በቤቱ ሠራተኛ እና የጥበቃ ሰራተኛዋ ላይ ትኩረቱን ያደረገው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሟች ትዝታ ባለቤት ካሣ ራሱ ድርጊቱን ፈፅሞታል የሚሉ ጥቆማዎች ሲመጡ ያለምክንያት አልነበረም፡፡ የትዝታ ባል ካሣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከባለቤቱ ትዝታ ጋር ከፍተኛ ግጭት የተፈጠረ ሲሆን በተደጋጋሚም በመሀከላቸው አለመግባባት በተፈጠረ ቁጥር ካሣ ዛቻና ማስፈራራት ያሠማ ነበር ታዲያ አሁን ካሣ ከመርማሪ ፖሊስ ለሚቀርብለት ጥያቄዎች እኔ አልገደልኳትም ብሎ ሲከራከር የቤት ሠራተኛዋ እና ጥበቃው ግን ወንጀሉን የፈፀመው ባልዋ ካሣ ነው ሲሉ ባለቤቷ ካሣ ደግሞ እኔ ከደሙ ንፁህ ነኝ ለሚስቴ ሞት ተጠያቂ ሁለቱ ናቸውና ለፍርድ ይቅረቡልኝ እያለ ሁለቱም እርስ በእርስ ሲወነጃጀሉ ከረሙ፡፡ የኋላ ኋላ ግን አልፎ አልፎ በዚህ መኖሪያ ቤት የቤቱን መኪና የሚያሽከረክረው አዱኛ አዲስ ጥቆማን ይዞ ፖሊስ ጣቢያ ብቅ አለ ይህ ግለሰብ ይዞት የመጣውም ጥቆማ የሟች ትዝታ ባለቤት ላይ ነበር፡፡ የሟች ትዝታ ባል ካሳ በገዛ ሚስቱ ላይ ግድያ ፈፅሟል ብሎ ፖሊስ ጣቢያ ሲቀርብ ያለምንም ምክንያት አልነበረም በመሆኑም ካሣ ሚስቱን ገሎ አዲስ ትዳር ለመመስረት ፈልጎ ነው ይህን ተግባር የፈፀመው ብሎ ጥቆማውን ሰጠ፡፡
ይህ ጥቆማ ከዚህ ግለሠብ በተጨማሪ ከጥበቃው ሠራተኛና በተለያዩ ሰዎች የተደጋገመ ሲሆን ፖሊስ ችላ ብሎ አላለፈውም፡፡
ካሣ ከትዳር አጋሩ ከሟች ትዝታ ጋር በርካታ አመታትን አሣልፎ ልጆች ከማፍራታቸው ባለፈ ንብረትንም ያካበቱ ቢሆንም ነገር ግን ከድርጅቱ ፀሐፊ ከነበረችው ወጣት ሴት ጋር ያለው ድብቅ ግንኙነት ጎልብቶ ልጅ መውለዱ በትዳሩ ላይ ከፍተኛ ችግር ተፈጥሮ ነበር፡፡ የቀድሞ ፀሐፊውና ለካሣ ልጅ የወለደችው ወጣት ከካሳ ድርጅትም ሆነ በአጠቃላይ ከህወቱ እንድትወጣ ተደርጎ ትዝታ እና ካሣ በአዲስ መንፈስ ትዳራቸውን ለመቀጠል ተስማምተው ለአመታት በሠላምና በፍቅር የኖሩ ቢሆንም እንደ ሹፌሩ እና እንደጥበቃው አዲስ መረጃ መሠረት ግን ካሳ ከዚህች ወጣት ጋር ድብቅ ግንኙነት የቀጠለ ሲሆን ትዝታን ገሎ እሷን አግብቶ ለመኖር እንደሚፈልግ አውቃለው ሲሉ ተናገሩ፡፡ ሆኖም ከተለያየ ፅንፍ ቁልፍ የሆነ መረጃ ያገኘው መርማሪ ፖሊስ የምርመራ አካሔዱን አስፍቶ ቀጠለ፡፡ ታዲያ የትዝታ ህይወት ያለፈበት ምክንያት ባልዋ ካሣ ከቀድሞ ፀሐፊው ጋር በትዳር ተጣምሮ መወሰኑ ነበር ወይስ ጥበቃውና እና የቤት ሰራተኛ የሆኑት ሁለቱ ግለሰቦች 420,000 ብር ለመወሰድ ብለው ይህን እኩይ ተግባር የፈፀሙት ለሚሉት ጥያቄዎች ለመመለስ ምርመራው የቀጠለ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የሟች ባል ካሣ ከቀድሞ ፀሐፊው ጋር ያለው ግንኙነት ከአመታት በፊት መሆኑን ካሣ ብትደጋጋሚ ለመርማሪ ፖሊስ የገለፀ ሲሆን ታዲያ ማን እውነትን ይዟል የሚለውን ለማወቅ የፖሊስ የምርመራ ሒደቱን እና ውጤቱን ይከታተሉን እያልን ጋበዝናችሁ፡፡