የደም ግፊትን ያለመድኃኒት መቆጣጠር የሚያስችሉ ፍቱን ምግቦች| የደም ግፊት በሽታ

  Рет қаралды 674

Birabiro ቢራቢሮ

Birabiro ቢራቢሮ

Жыл бұрын

የደም ግፊትን ያለመድኃኒት መቆጣጠር የሚያስችሉ ፍቱን መንገዶች
በአለም ዙሪያ ከ1 ቢልየን የሚበልጡ ሰዎች በደም ግፊት በሽታ እንደተጠቁ የአለም የጤና ድርጅት አሳውቋል
የደም ግፊት ምልክቶች/ የደም ግፊት ምልክቶች ምን ምን ናቸው
በየትኛውም እድሜ እና ፆታ ያለ ሰው በደም ግፊት ሊጠቃ ይችላል
ዋናዎቹ ለደም ግፊት አጋላጭ ነገሮች
ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ , በቂ አካላዊ እንቅስቃሴ ያለማድረግ; ለረጅም ሰአታት ኮምፒውተርና ስልክ ላይ አፍጥጦ መቀመጥ ; የስራና የኑሮ ጫናዎች (ጭንቀቶች ናቸው
ነገር ግን 99% የሚሆነው ችግር የአመጋገብና የአኗኗር ስርአትን በማስተካከል ይቀየራል በዛሬው ቪድዮ የደም ግፊት ለመቀነስ የሚረዱ 15 የምግብ አይነቶችን ይዤላችኋለሁ ተከታተሉና ተጠቀሙበት
የደም ግፊት ምንድን ነው?
የደም ግፊት ማለት በደም ስሮች ግድግዳ ላይ በደም ምክንያት የሚፈጠር ግፊት (tension) ነው የደም ግፊት ሳይታወቅ ለብዙ አመታት ሊቆይ ይችላል ለዛም ነው “silent killer.” በመባል የሚጠራው
ከፍተኛ የደም ግፊት የደም ስሮችን በማበላሸት ለልብ ህመም፤ለስትሮክና ለኩላሊት ህመም ያጋልጣል
የደም ግፊትን በተፈጥሯዊ መንገድ ለመቆጣጠር እነዚህን ምግቦች ተጠቀሙ
የደም ግፊትን የሚቀንሱ ምግቦች /የደም ግፊትን ለመቀነስ የሚረዱ ምግቦች
1. አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች
አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች እየኖርንበት ያለው በውጥረት የተሞላ ህይወት ከሚያስከትለውን የጤና ችግር በማስወድ እጅግ በጣም ትልቅ ሚና ይጫወታል በውስጣቸው የሚገኘው ፖታሰየም የበዛ ሶዲየም ከሰውነት ውስጥ እንዲወገድ በመርዳት የደም ግፊቱ እንዲቀንስ ያደርጋሉ (ምክንያቱም የበዛ የሶዲየም መጠን በሰውነት ውስጥ መኖር የደም ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል
ኬል፤ እስፒናች፤ አሩጉላ፤ ሰላጣ Romaine lettuce ራዲሽ፤ Turnip ቅጠል (እንደቀይስር አይነት ሆኖ ነጭ ነው) ቆስጣ;ጎመን; የቀይስር ቅጠሎች (እንደጎመን ተሰርቶ
2. ቅባቱ የወጣለት ወተትና እርጎ
ቅባቱ የወጣለት ወተትና እርጎ አነስተኛ የስብ መጠንና በዛያለ ካልሲየምና ፖታሲየምይኖራቸዋል
ካልሲየምና ፖታሲየም ሶዲየም ከደም ውስጥ እንዲወገድ ስለሚረዱ የደም ግፊት መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል እርጎንና አይብን መመገብ የደም ግፊት እንዲቀንስ ያደርጋል
3 ሀብሀብ
ሲትሩሊን በመባል የሚታወቀው የአሚኖ አሲድ አይነት በውስጡ ስላለ ሀባብ የደም ግፊት እንዲቀንስ በመርዳት ትልቅ ሚና ይጫወታል
4 ብሮኮሊና የአበባ ጎመን
ብሮኮሊና የአበባ ጎመን የደም ግፊትን በሚያስተካክሉት ማግኒዝየም፣ ካልሲየም፣ፖታሲየም የተሞሉ ናቸው
5 የቀይስር ጭማቂ
ቀይስር በውስጡ ናይትሬት አለው ይሄ ጋዝ ወደናይትሪክ አሲድ በመቀየር የደም ቧንቧዎች እንዲሰፉ በማድረግ የደም ዝውውሩ ጤናማ እንዲሆን ያግዛል በተጨማሪም ካልሲየም፣አይረንና ፖታሲየም አለው እነዚህ ለልብ፣ ለምግብ መፈጨትና ለአጠቃላይ ጤንነት ይጠቅማሉ
የቀይስር ጭማቂን አዘውትሮ መጠጣት የደም ግፊት እንዲቀንስ ይረዳል
6 ነጭሽንኩርትና Herbs
ተፈጥሯዊ መድሃኒት በመባል የሚጠራው ነጭሽንኩርት ኮሌስትሮል እንዲቀንስ በማድረግ የመድሀኒትን ያህል ውጤታማ ነው
ነጭሽንኩርት አሊሲን የተባለ በሰልፈር የዳበረ ኮምፓውንድ አለው ሃይድሮጅን ሰልፋይድ እንዲመረት ያነቃቃል እንዲሁም ናይትሪክ ኦክሳይድን ያመጣጥናል እነዚህ ደግሞ የደም ስሮች ዘና እንዲሉና እንዲሰፉ ይረዳሉ
እንደ በሶብላ፤ሮዝመሪና ጦስኝ ያሉት herbs ተመሳሳይ ችሎታ ስላላቸው እነዚህን አዘውትሮ መጠቀም እንዲሁም አንድ ወይም ሁለት ፍንካች ነጭሽንኩርት በየቀኑ መብላት የደም ግፊት መጠን እንዲስተካከል ያደርጋሉ
7. አጃ
አጃ ከምግብ የሚገኝ የአሰር ምንጭ፤ስብ፤ቫይታሚኖችና ማእድናት መገኛ ነው ክብደት ለመቀነስ ጥሩ ነው እንዲሁም በደም ውስጥ ያለን ቅባት እንዲቀንስ ስለሚያደርግ የደም ግፊቱ ላይ ትልቅ ለውጥ ያሳያል ስለዚህ አጃን ለቁርስ አዘውትሮ መመገብ ነው
8.አቮካዶ
አቮካዶ ፀረ ደም ግፊት ባህሪ ያለው ፍሬ ነው. በአሰር ፤በጤናማ ስብ፤ፖታሲየም፣ማግኒዝየም፣ቫይታሚኖችና ማእድናት የዳበረ ስለሆነ የበዛ የጨው ክምችትን ከደም ውስጥ ያስወግዳል
በቀን ግማሽ አቮካዶ መመገብ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ይረዳል
9. ቀይስር
ቀይስር የድም ስር እንዲሰፋ በሚያደርገው በናይትሪክ ኦክሳይድ የታጨቀ ስለሆነ የደም ግፊት እንዲቀንስ ይረዳል የቀይስር ጭማቂን አዘውትሮ መጠጣት ለደም ግፊት መቀነስ ይጠቅማል
9. በቫይታሚን ሲ የዳበሩ ፍራፍሬዎች
ወይን፤ብርቱካን፤ኪዊ፤ሎሚ፤የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳሉ
በየቀኑ ቢያንስ 2 ቫይታሚን ሲ ይዘት ያላቸውን ፍራፍሬዎች መመገብ ጤናማ ያደርጋል
10. ጥቁር ቸኮሌት
ብዙዎቻችን የምንወደው ጥቁር ቸኮሌት የደም ግፊትን ውጤታማ በሆነ መልኩ የመቀነስ አቅም አለው የፍላቮኖይድ ምንጭ ነው በየቀኑ ጥቁር ቸኮሌትን ከምግብ በኋላ መመገብ አንዱ የደም ግፊትን መቀነሻ ዘዴ ነው
11. ሙዝ
ሙዝ በከፍተኛ ሁኔታ የፖታሲየም መገኛ ነው ፖታሲየም ደግሞ የበዛ ሶዲየም ከሰውነት ውስጥ እንዲወገድ በማድረግ የደም ግፊት እንዲቀንስ ይረዳል
በቀን 1-2 ሙዝ መመገብ የደም ግፊት እንዲቀንስ ይረዳል
12. Seeds
የዱባ ፍሬ፤የሱፍ ፍሬ፤ ቺያ፤ ተልባ እነዚህ ከምግብ የሚገኘው የአሰር አይነት፤ጤናማ ስብ፤ቨይታሚኖችና ማእድናት አላቸው እነዚህ ክብደታ ለመቀነስ ከማገዛቸውም በላይ የደም ግፊት እንዲቀንስ ይረዳሉ
እነዚህን አዘውትሮ በመመገብ የተጠቀሱትን ጥቅሞች ማግኘት ይቻላል
13. ምስር
ምስር የፕሮቲንና የአሰር መገኛ ነው በውስጡ ላለው ፖታሲየም ምስጋና ይግባውና የደም ግፊትን
ለመቀነስ ይረዳል
14. ሮማን
ሮማን በፀረ ኦክሲዳንት፤ ቫይታሚኖች፤ ማእድናትና አሰር የዳበረ ነው
በሁለት ቀን አንዴ 1 ብርጭቆ የሮማን ጭማቂ መጠጣት ከፍተኛ የደም ግፊት መጠንን ለመቀነስ ጠቃሚ ነው
15. የወይራ ዘይት
በውስጡ ያለው ፖሊፌኖል የደም ግፊትን በመቀነስ ውጤታማ ነው
የወይራ ዘይትን መጠቀም መጥፎው ኮሌስትሮል LDL ይቀንሳል በዚህም የደም ግፊቱ እንዲቀንስ ያደርጋል which is why olive oil is a key part of the DASH and Mediterranean diets.
17. Fatty Fish
እንደ ሳልመን፤ ማከረል፤ሂልሳና ቱና አይነት አሳዎች በኦሜጋ 3 ፋቲ አሲዶች የተሞሉ በመሆናቸው ኢንፍላሜሽን ከሰውነት ውስጥ እንዲቀንስ ይረዳሉ የደም ግፊት መጠንንም ያስተካክላል
ጥሩ የቫይታሚን ዲ መገኛ ናቸው በሳምንት ለተወሰኑ ቀናት እነዚህን የአሳ ዝርያዎች በመመገብ ወይም ሰፕልመንቶቹን በመውሰድ የደም ግፊት መጠናችሁ እንዳይጨምር ማድረግ ትችላላችሁ
Easy LLLLLLLiLL

Пікірлер: 8
@lulitlula4290
@lulitlula4290 Жыл бұрын
በጣም ገራሚ ቪዲዮ ነው ለብዙዎች ይጠቅማል እጅግ እናመሰግናለን ላይክሼርርር🙏👍❤️❤️
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
ሉላዬ ውዴ አመሰግናለሁ
@MesiGemechu
@MesiGemechu Жыл бұрын
የኔ ቆንጆ ሰላምሽ ይብዛልኝ እንኳን በሰላም መጣሽ ሰለምት ሰጭን አስፋላጊ ትምህርት ከልብ እናመሰግናለን 🙏
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
መሲዬ በጣም አመሰግናለሁ
@borena109
@borena109 Жыл бұрын
እንኳን ደሀና መጣሽ እህቴ በጣም ጥሩ መረጃ ነው ያጋራሽን እናመሰግናለን ሼር 😍
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
የኔ ቆንጆ በጣም አመሰግናለሁ
@ethiopia5722
@ethiopia5722 Жыл бұрын
Nice info as always. Keep it up sis.
@birabiro1626
@birabiro1626 Жыл бұрын
Thanks my dear
DEFINITELY NOT HAPPENING ON MY WATCH! 😒
00:12
Laro Benz
Рет қаралды 60 МЛН
ПРОВЕРИЛ АРБУЗЫ #shorts
00:34
Паша Осадчий
Рет қаралды 6 МЛН
Spot The Fake Animal For $10,000
00:40
MrBeast
Рет қаралды 149 МЛН
ለደም ግፊት ማስወገድ ያለባችሁ ምግቦች | Foods you must Avoid for Hypertension
11:40
DEFINITELY NOT HAPPENING ON MY WATCH! 😒
00:12
Laro Benz
Рет қаралды 60 МЛН